ሊባኖስ (ቤሩት) ከአንድ አመት በላይ ያለፕሬዘዳንት ኖራለች በዚህች ሀገር መንግስቱ እየተልፈሰፈሰ የሚገኝ ሲሆን የከተሞችን ቆሻሻ እንኳ በቅጡ መሰብሰብ አቅቶታል ነው የሚባለው ይህን ተከትሎ ከተሞቻችን በቁሻሻ ተወረሩ ያሉ ሊባኖሳዊያን ትናንትናና ሰሞኑን ከባድ አመጽ ማስነሳታቸው ነው የተነገረው አመጹ ዛሬ ጋብ ቢልም ከፖሊስም ሆነ ከተቃዋሚዎቹ ወገን የበርካታ ሰዎችን መቁሰልና መጎዳትን ማስከተሉ ነው የተነገረው እናንት ቁሻሾች በተባለው ሊባኖወሳውያኑ በዚህ […]

በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ለመከላከል ወይም ሳይከላከሉ በነፃ ለመሰናበት ውሳኔ ዛሬ ለ35ተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበሩት አራቱ በእስር የሚገኙት ጦማርያን በድጋሚ በተለዋጭ ቀጠሮ ተሸኝተዋል። በዛሬው ውሎ ችሎቱ ያልተሰየመ ሲሆን ተከሳሾች እና ጠበቆች በቢሮ ተጠርተው ዳኞች ተሟልተው ስላልተገኙ ችሎቱ ለመሰየም አለመቻሉን ዶክመንቶችን ማየትና ውሳኔውን ፅፎ ማጠናቀቅ አሁንም እንዳልቻሉ በመግለፅ ዳኛ ዘሪሁን ለጷግሜ 2 ተለዋጭ ቀጠሮ […]

የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የፍርድ ቤት ውሎ (Update) #Freezone9bloggers በዛሬው እለት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የወያኔ ካንጋሮ ፍርድ ቤት ቀርበዋል::አራቱ ጦማርያን በፍቃዱ:ናትናኤል:አቤል:እና አጥናፍ በጥቁር ሱፍ ደምቀው በፍርድ ቤቱ ተገኝንዋል::ንጽሕናቸውን በተለያየ መንገድ እየገለጹ ያሉት እና የፍርድ ቤቱን ነጻ አለመሆን በተግባር ያሳዩት ጦማርያን በራስ …

የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የፍርድ ቤት ውሎ – የካንጋሮ ፍርድ ቤቱ ድራማ – ቀጠሮ ለ36ኛ ጊዜ ጳጉሜ 2 2007 Read more »

አንድ አገር ሰላሟና ብልፅግናዋ ዘላቂና አስተማማኝ የሚሆነው የሕግ የበላይነት በተግባር ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ ዜጎች በሕግ ፊት እኩል መሆናቸውን ሲያምኑ፣ ሕግም ለሁሉም ዜጎች እኩል ጥበቃ ሲያደርግ፣ ፍትሕ ለሁሉም ተደራሽ ሲሆንና የፍትሕ ሥርዓቱ በነፃነት ሲንቀሳቀስ የሕግ የበላይነት መኖሩ ይረጋገጣል፡፡ ‹‹አንድን ንፁኅ ዜጋ …

አንድ አገር ሰላሟና ብልፅግናዋ ዘላቂና አስተማማኝ የሚሆነው የሕግ የበላይነት በተግባር ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ Read more »

በገዢው ስራዓት የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ እየተካሄደ ባለው ሰፊ የዓመቱ ግምገማ “የተቃዋሚዎች ሬድዮ መስማት” እንደዋነኛ መገምገሚያ ነጥብ ሆኖ መነሳቱን ተገለፀ።በምንጮቻችን መረጃ መሰረት- በሁሉም የስርዓቱ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ እየተካሄደ ያለውን መጠነ ሰፊ የዓመቱ ግምገማ ወታደሩ ያለማቋረጥ እየፈረሰ በመጥፋት ላይ ያለው የትጥቅ ትግል እያካሄዱ በሚገኙ ድርጅቶች የሚሰራጨውን ሬድዮ መስማት ዋናው ከሆኑ ምክንያቶች አንዱ ስለሆነ ለምን ታዳምጣላችሁ፤ እነማን ናቸው የሚያዳምጡት መታወቅ አለባቸው በማለት እየተካሄደ ባለው ስብሰባ የሰራዊቱ አዛዦች ራሳቸው […]

ኢትዬጲያዊያን ሙስሊሞች አሁን በሃገራችን ያለንበት ተጨባጭ ይህን ይመስላል አቡ ዳውድ ኡስማን ወደፊት ለመጓዝ አሁን ያለንበትን ተጨባጨ መመዘን ተገቢ ነው፡፡ የተጋረጠብንን ችግሮችም ለመጋፈጥ እና ችግሩን ጥሶ ለማለፍ ያሉትን ችግሮች ማወቁም ተገቢ ነው፡፡ ሙስሊሙ ማህበረሰብ 3 ቀላል ጥያቄዎችን ለመንግስት አቅርቧል፡፡ ይህም ጥያቄዎች …

ኢትዬጲያዊያን ሙስሊሞች አሁን በሃገራችን ያለንበት ተጨባጭ ይህን ይመስላል :: (አቡ ዳውድ ኡስማን ) Read more »

– የወያኔው ጉባኤ ጥበቃና ጸጥታ ውዝግብ አስነስቷል – የወያኔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በካድሬዎች እየተተቸ ነው – ሱማሊያ ውስጥ ሰርገኞችን የገደሉ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት ለፍርድ ቀረቡ – በደቡብ ሱዳን የመገናኚያ ብዙሀን አባላት የዜና ማእቀብ አድማ አደረጉ – በሰሜን …

የወያኔው ጉባኤ ጥበቃና ጸጥታ ውዝግብ አስነስቷል:: የወያኔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በካድሬዎች እየተተቸ ነው Read more »

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በድጋሜ የሰማያዊ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በድጋሜ የሰማያዊ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ያደረገው ሰማያዊ ፓርቲ ኢ/ር ይልቃል ጌትነትን በድጋሜ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡ ትናንት ነሀሴ 16/2007 ዓ.ም ጉባኤውን የጀመረው ፓርቲው በዛሬው ሁለተኛና የማጠቃለያ …

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በድጋሜ የሰማያዊ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ Read more »

‹‹ታግዬ ለውጥ ማምጣት እችላለሁ!›› የሚል ትውልድ አይሸነፍም! የአስተሳሰብ የበላይነት የትግል እና የድል መሰረት ነው! እሁድ ነሐሴ 17/2007 ማንኛውም የመብት ትግል የሚጀምረው በበደል ነው፡፡ አምባገነኖች በደልን የሚያደርሱት እጅግ ስልታዊ በሆነ መንገድ በመሆኑና ለዚህ በደልም ሽፋን ስለሚያደርጉለት ብዙዎች የሚበደሉት እየተበደሉ መሆናቸውን ሳይረዱ …

ታግዬ ለውጥ ማምጣት እችላለሁ!›› የሚል ትውልድ አይሸነፍም! – ድምፃችን ይሰማ Read more »

ዛሬ እንደወትሮዬ አብርሀ ደስታን ለመጠየቅ ወደ ቃሊቲ አምርቼ ነበር። ታዲያ አብርሀን ሆነ መሰሎቹን ለመጠየቅ እንዲህ በቀላሉ የሚቻል አይደለም። በጥብቅ ከሚጠበቀው ቃሊቲ ውስጥ ለመጠየቅ የሚፈቀደው ከ 6:00 – 6:30 ያለችን 30 ደቂቃ ብቻ ስትሆን እሱም በር ላይ ቆመው የአይንህ ቀለም አላማረንም …

አመክሮ ካልታሰበ አብርሃ ደስታ ጥቅምት 24 2008 የሽዋስ እና ዳንኤል ነሃሴ 30 ይፈታሉ:: Read more »

በሁለተኛው ቀን ውሎ የሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ ቀጣይ የፓርቲውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ የጉባኤው አባላት አጠቃላይ ውይይት እየተደረጉ ይገኛል፡፡ በቀጣይም የብሄራዊ ምክር ቤት፣ የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን አባላት እና የፓርቲው ሊቀመንበር ጥቆማ እና አስመራጭ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ይደረጋል፡፡ ጠቅላላ ጉባኤው ቀጣዩን የሰማያዊ ፓርቲ …

የሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ በሁለተኛው ቀን ውሎ Read more »

#Ethiopia ከኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ በሳተላይት የሚሰራጭ የራዲዮ ፕሮግራም (EPRP’s Satellite Radio transmissions to Ethiopia and Horn of Africa.) የነሐሴ 15 ቀን 2007 ዓ.ም.ዜና (August 21, 2015 News) – ወያኔ ውስጥ ውስጡን እርዳታ እየጠየቀ ነው – የወያኔ ምክር ቤት ስብሰባ …

ከኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ በሳተላይት የሚሰራጭ የራዲዮ ፕሮግራም Read more »

‹‹መጠየቅ ካለብኝ በክልል እንጂ በፌዴራል አይደለም›› አቶ ወንድሙ ቢራቱ

ለመንግሥት መግባት የነበረበትን ተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች የመንግሥት የግብር ገቢዎች በማጭበርበር በግላቸውና በዘመዶቻቸው ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ በማካበት በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩት፣

የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ ወንድሙ ቢራቱ ሰው በመግደል ወንጀል መጠርጠራቸው ለፍርድ ቤት ተገለጸ፡፡

ነሐሴ 3 ቀን 2007 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ውለው ነሐሴ 4 ቀን 2007 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው 11 ቀናት ለተጨማሪ ምርመራ ተሰጥቶባቸው የነበሩት አቶ ወንድሙ፣ በሰው መግደል ወንጀል የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኖች ያደረጉት የምርመራ መዝገብ ቀርቦ እየተጣራባቸው መሆኑ ተነግሯል፡፡ 

የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ነሐሴ 13 ቀን 2007 ዓ.ም. ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት ተጠርጣሪውን አቅርቧቸዋል፡፡ ቀደም ብሎ በተፈቀደለት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ 13 ሚሊዮን ብር የተንቀሳቀሰበት ሰነድ ከባንክ ተፈልጐ መሰባሰቡን፣ በፌዴራልና በክልል ባሏቸው ቤቶች ብርበራ መካሄዱን፣ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የሲዲ መረጃ መሰብሰቡንና የሁለት ምስክሮችን ቃለ መቀበሉን መርማሪ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ አስረድቶ፣ የሚቀረው ምርመራ እንዳለ በመግለጽ ተጨማሪ 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠይቋል፡፡

መርማሪ ቡድኑ ተጨማሪ ቀናት የጠየቀበትን ምክንያት ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው፣ ከአዲስ አበባና ከፌዴራል ፖሊስ የነፍስ ግድያ ወንጀል ምርመራ መዝገብ መጥቶለት፣ ምርመራው በደንብ መካሄዱን መገምገም ከፌዴራልና ከክልል የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ተጨማሪ የሰነድ ማስረጃዎች መሰብሰብ፣ ከገቢዎችና ጉምሩክ የተለያዩ ሰነዶችን መሰብሰብ፣ ከኦሮሚያ ገቢዎች የኢንስፔክሽን ሪፖርት መሰብሰብና ሌሎች ተጠርጣሪዎችን መያዝ እንደሚቀረው አስረድቷል፡፡ 

በተጠርጣሪው ዘጠኝ ቤቶችና በአራት ከተሞች የተደረገውን የብርበራ መረጃ መተንተን፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሰባሰቡትን የመሬትና የቤት ባለቤትነት ሰነድና  ከተለያዩ ባንኮች ገንዘብ የተቀባበሉባቸውን ደረሰኞች ማስረጃ መሰብሰብ እንደሚቀረው፣ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ በማስረዳት የተጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ቀን እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡

አቶ ወንድሙ በበኩላቸው ባቀረቡት ተቃውሞ፣ መርማሪው የፈለገውን ሰነድም ሆነ ሌላ ነገር ማግኘቱን ገልጸዋል፡፡ መርመሪዎች እሳቸውን ካሰሩ በኋላ መኖሪያ ቤታቸው በመሄድ የአምስት ዓመት ሕፃን ልጃቸው ላይ ሽጉጥ በመደቀን ያደረጉትን ማስፈራራት አምርረው ተቃውመዋል፡፡

ከታሰሩበት ዕለት ጀምሮ ማንም ቤተሰብ እንዳልጠየቃቸው፣ ምክንያቱ ደግሞ መርማሪዎቹ እንዳስፈራሯቸው መስማታቸውን ተናግረዋል፡፡ እሳቸው የክልል ተሿሚና የካቢኔ አባል መሆናቸውን በመግለጽ፣ መጠየቅ ካለባቸውም በክልል እንጂ በፌዴራል አለመሆኑን አስረድተዋል፡፡ ኮሚሽኑ በመገናኛ ብዙኃን ስማቸውን እያጠፋ መሆኑን በመግለጽ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፡፡

የኮሚሽኑ መርማሪ በበኩላቸው አቶ ወንድሙ ያቀረቡትን አቤቱታ የሰሙት በዕለቱ ለችሎቱ ሲያስረዱ መሆኑን ገልጸው፣ እሳቸው እንዳሉት ሆኖ ከተገኘ ኮሚሽኑ በድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ ዕርምጃ እንደሚወስድ አሳውቀዋል፡፡ ሥልጣኑ የክልል ነው ስለመባሉ ግን፣ የግብር ጉዳይ የፌዴራሉ ጭምር መሆኑን በመጥቀስ አስረድተዋል፡፡ የቫትንና የጉምሩክ ቀረጥን በሚመለከት የማየት ሥልጣን የፌዴራል ፍርድ ቤቶች መሆኑንም አክለዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ አቶ ወንድሙ ያቀረቡትን አቤቱታ በሚመለከት በሰጠው ትዕዛዝ ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው መከበር እንዳለበት አሳስቦ በቤተሰብ፣ በዘመዶቻቸው፣ በሃይማኖት አባትና በሕግ አማካሪያቸው የመጐብኘት መብት እንዳላቸው በመግለጽ ኮሚሽኑ ተግባራዊ እንዲያደርግ አዟል፡፡ 

በሕፃን ልጃቸው ላይ ተደረገ የተባለው እውነት ከሆነና ማስረጃ ከቀረበ ዕርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቆ፣ የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን በሕግና በአግባቡ መመርመር እንዳለበት፣ ከዚያ ውጪ የሆነ በግዳጅና በኃይል የሚገኝ መረጃን ውድቅ እንደሚያደርግ በማሳሰብ፣ መርማሪ ቡድኑ ለጠየቀው ተጨማሪ ምርመራ አሥር ቀናትን ፈቅዷል፡፡ 

 

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ከአክሰስ ቦርድ ሰብሳቢነታቸው ተነሱ

‹‹መንግሥት አክሲዮን ማኅበሩን ለማፍረስ በሚደረግ እንቅስቃሴ ላይ ጥብቅ ዕርምጃ ይወስዳል›› አቶ ኑረዲን መሐመድ፣ የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ

በድንገት ከአገር ወጥተው በተባበሩት ኤምሬት ዱባይ ከተማ ለሁለት ዓመታት ከቆዩ በኋላ ከመንግሥት ጋር ባደረጉት ድርድር ከለላ ተሰጥቷቸው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፣

አገር ውስጥ ከተመለሱ በኋላ ቀድሞ ወደነበሩበት የአክሰስ ሪል ስቴት አክሲዮን ማኅበር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የተሾሙ ቢሆንም፣ ‹‹ምንም ዓይነት ሥራ አልሠሩም›› ተብለው ከሰብሳቢነታቸው ተነሱ፡፡

የቦርድ አባላት ነሐሴ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ አቶ ኤርሚያስን ከቦርድ ሰብሳቢነታቸው ያነሷቸው፣ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ከተሾሙ ከመጋቢት 26 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ በእሳቸው ሰብሳቢነት በርካታ ስብሰባዎችን ያደረጉ ቢሆንም፣ በሥነ ሥርዓት ጉዳዮችና አሉባልታ ወሬዎች ላይ ከመነታረክ ያለፈ ምንም ዓይነት ቁምነገር አለመሥራታቸውን የቦርዱ አስቸኳይ ስብሰባ ቃለ ጉባዔ ያስረዳል፡፡ አቶ ኤርሚያስ በሕግና በሥርዓት ሊሠሩ ባለመቻላቸው፣ ቦርዱ የኩባንያውን ችግር ለመፍታት በመንግሥት ለተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ በማሳወቁ ኮሚቴው መመርያ ሰጥቶ እንደነበርም በቃለ ጉባዔው ተገልጿል፡፡ ኮሚቴው በሰጠው መመርያ ቦርዱ ስለ አክሰስ ሪል ስቴት አካሄድ ፍኖተ ካርታ እንዲያቀርብ አዞ የነበረ ቢሆንም፣ ጥቃቅንና የትም የማያደርሱ ድርጅቱን ሥጋት ላይ የሚጥሉ ነገሮች ከመነሳታቸው ባለፈ ፋይዳ ያለው ነገር ሊሠሩ ባለመቻላቸው ከቦርድ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ በሙሉ ድምፅ መወሰኑን የቦርዱ ቃለ ጉባዔ አስታውቋል፡፡ አክሰስ ሪል ስቴት በአቶ ኤርሚያስ ሲመራ ወደ ድርጅቱ ካዝና መግባት ያለባቸውን ተሰብሳቢ ሒሳቦች ከማንሳት ይልቅ ዕዳ መቀበልን እንዲያስቀድም መደረጉን ቦርዱ ገልጿል፡፡ ድርጅቱን ከውድቀት ሊያነሳ የሚችል ብዙ ተሰብሳቢ በሕጋዊ ሰነድ የተያዘ ገንዘብ ቢኖርም፣ በእሱ ጉዳይ ላይ ውይይት አለመደረጉንም ጠቁሟል፡ 

አቶ ኤርሚያስ ወደ አገር ቤት የተመለሱበት ዓላማ እንዲያሳካ በሚል ቦርዱ ብዙ ነገሮችን እያየ እንዳላየ ማለፉን ጠቁሞ፣ አሁን ግን ሥጋው መሬት ላይ እያለ የደረቀ ቋንጣ እያወረደ መሆኑን በመገንዘብ ዕርምጃውን ለመውሰድ መገደዱን ገልጿል፡፡ አቶ ኤርሚያስ ያለ ቦርዱ ተሳትፎ በራሳቸው ለተለያዩ ድርጅቶች ደብዳቤ መጻፋቸው፣ ቅጥር ማካሄዳቸውና ‹ፒንግል ሪል ስቴት› ከተባለ የቻይና ኩባንያ ጋር የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን ቦርዱ ጠቁሞ፣ ነገር ግን ኩባንያው በሕይወት ይኑር አይኑር የሚታወቅ ነገር እንደሌለ አስታውቋል፡፡ በአጠቃላይ አቶ ኤርሚያስ ከነሐሴ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ከቦርድ ሰብሳቢነታቸው ተነስተው ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት ወ/ሮ መብራት ወልደ ትንሳዔ በሰብሳቢነት እንዲመሩ በመስማማት መወሰኑን አስታውቋል፡፡ 

አቶ ኤርሚያስ መሥራችና የቦርድ ሊቀመንበር ከነበሩበት አክሰስ ሪል ስቴት፣ በአገር ውስጥና በተለያዩ አገሮች የሚኖሩ ከ2,000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች የቤት ግዢ የፈጸሙ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ቤትም ሆነ ገንዘባቸውን አለማግኘታቸውን እየገለጹ ነው፡፡ አቶ ኤርሚያስ በድንገት ከአገር ሲወጡ ቤት ገዢዎቹ የተለያዩ ተቃውሞዎችን ሲያቀርቡ ከርመው፣ በመጨረሻ መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ከአቶ ኤርሚያስ ጋር በመደራደር ለተለያዩ ግለሰቦች ቆርጠውት በነበረ ደረቅ ቼክ ምክንያት እንደማይታሰሩ ዋስትና ተሰጥቷቸው፣ በየካቲት ወር 2007 ዓ.ም. ወደ አገር ቤት ተመልሰዋል፡፡

አቶ ኤርሚያስ በወቅቱ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ከየካቲት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ሥራ እንደሚጀምሩና ማንኛውም ቤት ገዢ የፈለገውን ማለትም ቤቱን ወይም ገንዘቡን ከነወለዱ እንደሚመልሱ ቃል መግባታቸው በወቅቱ ተዘግቧል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ቤት ገዢዎች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አቶ ኤርሚያስ እንኳን ገንዘብ ሊመልሱና ስለቤት ሊያናግሯቸው ቀርቶ በአካል አይተዋቸው እንደማያውቁ እየገለጹ ነው፡፡ መንግሥት የሰጣቸውን ተስፋም ማየት ባለመቻላቸው ተስፋ እየቆረጡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በአጭር ጊዜ ተብሎ ላለፉት ስድስት ወራት ምንም ነገር አለማየታቸውን አስረድተዋል፡፡ 

የአቶ ኤርሚያስ ፍላጐት በተለያዩ መንገዶች ነገሮችን በማጓተት ድርጅቱ እንዲፈርስና ከተጠያቂነት ለመዳን ስለሆነ፣ ቃል የገባው መንግሥት በነገሩ ላይ ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡ 

በቦርዱ ጽሕፈት ቤት ለሚሠሩ 13 ሠራተኞች የሰኔና የሐምሌ ወር ደመወዝ መክፈል ሳይቻል ቀርቶ ቴክኒክ ኮሚቴውና ከቤት ገዢዎች ለተለያዩ ወጪዎች ከሰበሰበው ገንዘብ አክሲዮን ማኅበሩ ተበድሮ መክፈሉን አስረድተዋል፡፡ ይኼ የሚያሳየው ድርጅቱ ችግር ውስጥ መሆኑን እንደሆነ አስረድተው መንግሥት አስቸኳይ ውሳኔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ 

የቴክኒክ ኮሚቴው ሰብሳቢ የንግድ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ኑረዲን መሐመድ ግን በቤት ገዢዎቹም ሆነ በቦርዱ ሐሳብ አይስማሙም፡፡ እሳቸው እንደሚሉት ሰው የፈለገውን ቢያወራ ኮሚቴው መሥራት የሚችለውን እየሠራ እንደሆነና በሥራውም ውጤታማ መሆኑን ነው፡፡ 

ከየአቅጣጫው እየጮሁ የሚገኙት ከቤት ገዢዎቹ አሥር በመቶ የማይሆኑትና አቶ ኤርሚያስ ሲነኩ የሚነኩ ሰዎች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ አቶ ኤርሚያስ የሕግ ከለላ የተሰጣቸው ሥራዎች ተስተካክለው እንዲሄዱ እንጂ ከሕግ ተጠያቂነት ለማዳን አለመሆኑን የገለጹት አቶ ኑረዲን፣ በአቶ ኤርሚያስ በኩል ስላሉ ሰዎች መረጃ መጠየቅ ሲጀመር የእሳቱ ወላፈን የሚነካቸው ሰዎች ብዙ ነገር ለማድረግ እየጣሩና እየተወራጩ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ ከአንድ ወይም ሁለት ሳምንት በኋላ በተለይ አምቼ አካባቢ ያለው ፕሮጀክት ይፋ እንደሚደረግና ሥራ እንደሚጀመር የጠቆሙት ሰብሳቢው ቦርዱ፣ የቦርዱ አባላትና አስፈጻሚው የየራሳቸው አጀንዳ ስላላቸው ምንም ነገር እንዳልተሠራ የሚያስወሩት ወሬ እንደሚቆም ተናግረዋል፡፡ ሁሉም የሚሮጠው የራሱን መብት ለማስከበር መሆኑን ጠቁመው መንግሥት ግን ተረጋግቶና ሁሉንም ነገር በአግባቡ በመሥራት እያንዳንዷን ነገር ማስተማሪያ ማድረግ እንደሚፈልግ ገልጸዋል፡፡ 

አክሲዮን ማኅበሩ ከፈረሰ ተጠያቂነት ስለማይኖር በንግድ ሚኒስቴር የአክሲዮን ማኅበራት ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት የመጀመሪያ የቤት ሥራው ጥንቃቄ አድርጐ ጅምሩን ዳር ማድረስ መሆኑንም አቶ ኑረዲን አስረድተዋል፡፡ አክሲዮን ማኅበሩን ለማፍረስ የሚደረግ እንቅስቃሴ ከታየ መንግሥት ጥብቅ ዕርምጃ እንደሚወስድም አስረድተዋል፡፡ የሆነ ያልሆነ መረጃ ወጥቶ ቤት ገዢውን ተስፋ የሚያስቆርጥ ወሬ እንደሚሰማ የገለጹት አቶ ኑረዲን፣ መንግሥት አቶ ኤርሚያስ ሳይኖሩ ኃላፊነት መውሰዱን ቤት ገዢው መዘንጋት እንደሌለበት አስታውሰዋል፡፡

አቶ ኤርሚያስ ወደ አገር ቤት እንዲመጡ የተደረገው ሥራ እንዲሠሩ፣ ሚስጥሮችን እንዲያወጡና ሦስተኛ ወገኖችን እንዲታገሉ መሆኑን የገለጹት አቶ ኑረዲን፣ ቦርዱ ራሱ ሾሞ ራሱ እንዳወረዳቸው መግለጹ አግባብ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሌላ መሾምም ሆነ መነሳት ካለባቸው በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽሕፈት ቤት የፀደቀ ሰነድ መኖር እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ ይኼ ባልሆነበት ሁኔታ ስለሚካሄደው ነገር የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልጸዋል፡፡ አሁን በቦርዱም ሆነ በጥቂት ቤት ገዢዎች እየተደረገ ያለው ነገር ሥራውን የሚያስትና የሚያደናቅፍ አለመሆኑን አቶ ኑረዲን ተናግረዋል፡፡     

ቦርዱ ባሳለፈው ውሳኔና ቤት ገዥዎች እያቀረቡት ስላለው ተቃውሞ ምላሽ እንዲሰጡ አቶ ኤርሚያስን ሪፖርተር ቢሮቸአው ድረስ በመሄድና በስልክ ጭምር ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡    

 

እነ ሃብታሙ አያሌውን ለመፍታት/ከበር መልሶ ለመያዝ/ የደህንነት ቢሮ ትእዛዝ እየተጠበቀ ነው:: የቀረበባቸው ክስ ከጥርጣሬ ባለፈ በሽብርተኝነት ላይ ተሳትፎ አላደረጉም በሚል በነጻ እንዲሰናበቱ ከተደረጉት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን ለመፍታት የደህንነት ቢሮ ትእዛዝ እየተጠበቀ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በፍርድ ቤት መዳፈር ወንጀል ተለጥፎባቸው እዛው …

እነ ሃብታሙ አያሌውን ለመፍታት/ከበር መልሶ ለመያዝ/ የደህንነት ቢሮ ትእዛዝ እየተጠበቀ ነው:: Read more »

በደ/ወሎ ለጋንቦ ወረዳ የመቅደላ አንባ ዩንቨርስቲ የመሰረት ድንጋይ ወደ ቦረና በመዛወሩ የተነሳዉን ሰላማዊ ስልፍ ምክናየት በማድረግ ከጊባ ከተማ፣ጭሮ ከተማናአቅስታ ከተማ በፌደራል ፖሊስ እየታፈሱ ብዙ ወጣቶች መታሰራቸዉ ይታወቃል። በደ/ወሎ ለጋቦ ወረዳ መንግስት በፈጠረዉ በመቅደላ አባ ዩንቨርስቲ ችግር ምክናየት ሲታፈሱ የከረሙት ቁጥራቸዉ …

ከደቡብ ወሎ ዩንቨርስቲ የታፈሱ ወጣቶች ወደ ደሴ እስር ቤት ተወሰዱ:: Read more »

እኔስ ከማን ወገን ነኝ? (የትነበርክ ታደለ) ከጥቂት አመታት በፊት ኑሮዬን ለመደጎም ስል ከመደበኛው የማስተማር ሰአት ውጪ ያለውን ጊዜ ሰው ቤት እየሄድኩ ተማሪ አስጠና ነበር። በነዚህ ጊዜያት ምንም እንኳ የማገኘው ገንዘብ ከዋናው ደሞዜ አንጻር ሲታይ በእጅጉ የተሻለ ይሁን እንጂ ብዙ ለህሊናዬም …

እኔስ ከማን ወገን ነኝ? (የትነበርክ ታደለ) Read more »

ከኤርሚያስ ለገሠ 1• ደስታ እና ሀዘን ሰሞኑን ፍቺ በፍቺ ሆነናል። የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ከፊል አካል ተፈታ። ደስ አለን። የተፈቱት ካልተፈቱት ያላቸው ልዩነት ለብዙዎች ግራ ቢያጋባም!…ዛሬ ደግሞ እነ ሀብታሙ አያሌው ተፈተዋል። ይህም በግለሰብ ደረጃ ደስ የሚል ዜና ነው። ቢያንስ በቅርብ የማውቀው ሀብታሙ (” ሀብትሽ!”) ክፋ ደጉን የማታውቀው ልጁ እጁ ላይ ስታንቀላፋ፣ ወደ አልጋዋ ወስዶ ሲያስተኛት፣ ከእንቅልፏ

The post የአዲሱ ህውሀት መንግስት መጥፎ አጋጣሚ!! – (ኤርሚያስ ለገሠ) appeared first on ሳተናው (Satenaw)-Latest Ethiopian News & Breaking News.

የደቡብ ሱዳን ጦርነት በእስከአሁን ሂደት ከ 10 ሺህ በላይ ዜጎችን ህይወት መቅጠፉና በመቶ ሺህዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ስደት መንስኤ መሆኑ አይዘነጋም ይሁን እንጂ ለሀገሪቱ ሰላም ያመጣል ተብሎ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት የቅርብ ጊዜው የአዲስ አበባ ድርድር ውጤቱ የተጠበቀውን ያክል መሆን ሳይችል ቀርቷል በሰላም ስምምነቱ ሰነድ ላይ ተቃዋሚው ሪክ ማቻር ፊርማቸውን ቢያኖሩም የሀገሪቱ መንግስት ፕሬዘዳንት ሳልቫ ኪር ግን […]

የሰማያዊ ፓርቲ አንደኛ መደበኛ ጉባኤ በአዲስ አበባ ማንራሸዋ ሆቴል ተጀመረ:: የሰማያዊ ፓርቲ አንደኛ መደበኛ ጉባዬ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የተጀመረ ሲሆን የድርጅቲ ሊቀመንበር ለተሳታዊዎቹ እንኳን ደህና መጣቹ በሚል ንግግር ጉባዬውን ከፍተውታል::በጉባዬው ላይ የጠቅላላ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴው የስራ አስፈፃሚ ሪፖርት በአቶ …

የሰማያዊ ፓርቲ አንደኛ መደበኛ ጉባኤ በአዲስ አበባ ማንራሸዋ ሆቴል ተጀመረ:: Read more »

የደብል ዲጅቱ የኢኮኖሚ እድገት ፕሮፓጋንዳ እርቃኑን እየወጣ ነው:: #Ethiopia #EPRDF #DoubleDigitDevelopment #MinilikSalsawi 11% የተባለ የኢኮኖሚ እድገት ሕዝቡን ከድህነት ሊያወጣ ቀርቶ ጭራሽ የደሃ ደሃ የሚል አዲስ የቋንቋ ስያሜ ወልዷል::የኑሮ ውድነቱ እያሻቀበና ህዝቡን እያስደነገጠ ነው፡፡አጠቃላይ የምግብ ፍጆታዎች ዋጋቸው እጅግ አሻቅቧል፡፡በሚቀጥሉት ስድስት ወራት …

የደብል ዲጅቱ የኢኮኖሚ እድገት ፕሮፓጋንዳ እርቃኑን እየወጣ ነው:: (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

ዛሬ ለኢሳት የደረሰው ጥብቅ መረጃ 11ዓመታትን ወደ ኋላ በትዝታ ወሰደኝ:: ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከዋናው ጸሀፊ ቢሮ አፈትልኮ የወጣው መረጃ እንደሚያጋልጠው ለሰላም አስከባሪ 11 ሺህ የኢትዮጵያ ሰራዊት የሚከፈለው ደምወዝ ከ90 በመቶ በላይ የህወሀት ካዝና ውስጥ የሚገባ ነው:: በወር 13 ሚሊዮን ዶላር(500 ሚሊዮን ብር ገደማ) የወታደሩን ገንዘብ ህወሀቶች ይቀራመቱታል:: ይህን ጉዳይ የመንግስታቱ ድርጅት የሚያውቀው ይመስለኛል:: ለዚህም እኔ […]

የትግራይ ምእራባዊ ዞን አስተዳዳሪ የሆነው ፍስሃ በርሀ ከ44 ሚልዮን ብር በላይ ለግል ጥቅሙ በማዋሉ የተነሳ የዞኑ ነዋሪዎች ምሬታቸውን በማሰማት ላይ መሆናቸው ተገለፀ። ለደህሚት በደረሰው መረጃ መሰረት የምእራብ ትግራይ ዞን አስተዳዳሪ የሆነው ፍስሃ በርሀ ለሁመራ ከተማ መሰረተ ልማት ተብሎ በተለያየ መልኩ ከህዝብ የተዋጣው 44 ሚሊዮን ብር ስልጣኑን ተገን በማድረግ ለግል ጥቅሙ ማዋሉን ታውቆ እያለ እስከ አሁን […]

1• ደስታ እና ሀዘን ሰሞኑን ፍቺ በፍቺ ሆነናል። የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ከፊል አካል ተፈታ። ደስ አለን። የተፈቱት ካልተፈቱት ያላቸው ልዩነት ለብዙዎች ግራ ቢያጋባም!…ዛሬ ደግሞ እነ ሀብታሙ አያሌው ተፈተዋል። ይህም በግለሰብ ደረጃ ደስ የሚል ዜና ነው። ቢያንስ በቅርብ የማውቀው ሀብታሙ (” ሀብትሽ!”) ክፋ ደጉን የማታውቀው ልጁ እጁ ላይ ስታንቀላፋ፣ ወደ አልጋዋ ወስዶ ሲያስተኛት፣ ከእንቅልፏ ስትነቃ አቅፎ […]

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ከሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ ይገኙ የነበሩትና በትላንትናው እለት ነሐሴ 15 ቀን 2007 ዓ.ም የልደታው ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በነጻ ያሰናበታቸው፤ የአንድነት ፓርቲ የቀድሞ ህ/ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ ከእስር ሊለቀቁ እንዳልቻሉ ‹‹በበላይ ፍቃዱ›› ይመራ የነበረው አንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ገለፁ፡፡ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች እንደገለፁት የአቶ ሀብታሙ […]

ነኅሴ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሁለት ወጣቶች ጫካ መግባታቸውን ተከትሎ ተጨማሪ አርሶአደሮች እየተያዙ ነው። እስካሁን ባለው መረጃ ከ380 በላይ ሰዎች ተይዘው ድብደባ እየተፈጸመባቸው ሲሆን፣ ከዚህ ቁጥር ውስጥ ገሚሶቹ ሴቶች ናቸው። አብዛኞቹ ሴቶቹ የተያዙት በርካታ አርሶአደሮች አፈሳውን ለማምለጥ ጫካ መግባታቸውን ተከትሎ በባሎቻቸው ቦታ ሲሆን፣ የተወሰኑት ደግሞ ለሽፍቶች ምግብና ውሃ አቀብላችሁዋል ተብለው ነው። …

ነኅሴ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአፋር፣ በሶማሊና በሌሎች አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ አድማሱን በማስፋት ጎጃም ውስጥም ተከስትዋል።በድርቁ ጉዳት በርካታ እንሰሳት እየሞቱ መሆኑንና ሰውም ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። በተለይ ድርቁ በሶማ፣ አራራ፣ እነገ እና ሰንጠርጌ ቀበሌዎች ለበርካታ እንሰሳት ሞት ምክንያት ከመሆኑም ባሻገር ነዋሪዎችም ለከፍተኛ ችጋር ተጋልጠዋል፡፡ ድርቁ አስከፊ ደረጃ እንደደረሰ …

ነኅሴ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአንድ እስከ አራተኛ ክፍል በሚተገበረው የክላስተር ፖሊሲ በተለይ በኦሮምያ ፤ ሶማሌ እና ደቡብ ክልሎች ከአንድ እስከ አራተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች የማንበብ እና የመፃፍ ክህሎታቸው ከዜሮ ነጥብ በታች መሆኑን ከትምህርት ሚኒስትር የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡ የተማሪዎቹ የሂሳብ ማስላት ችሎታ መዳከሙን፣ በሳይንስ ትምህርት ላይ ለውጥ እንዲመጣ የተጣለው ግብም አለመሳካቱን …

ነኅሴ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለእናቶችና ህጻናት ጤንነት ታስቦ ከተለያዩ ለጋሽ ሃገራት በእርዳታ የተገኙትን አምቡላንሶች ከታሰበላቸው አገልግሎት ውጭ ለተለያዩ ፖለቲካዊ ስራ በመመደብ ሲጠቀሙባቸው እንደነበር በምዕራብ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ የሚገኙ አንድ የስራ ኃላፊ ገለጹ፡፡ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉት ኃላፊ እንደተናገሩት የወረዳ አስተዳዳሪዎች በቂ በጀት እንዲመድቡ መመሪያ ቢሰጣቸውም ችላ በማለት አገልግሎት መስጠት የነበረባቸው …

ኢሳት ዜና (ነሐሴ 15 ፣ 2007) ሰሞኑን በኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞ አውሮፕላን ውስጥ በእቃ መጫኛ ውስጥ ተደብቆ በስዊድን ጥገኝነትን የጠየቀው ኢትዮጵያ በአየር መንገድ ውስጥ በአንድ ብሄር የበላይነት የሚደርሰው በደልና ግፍ ለህዝብ ለማጋለጥ ሲል ድርጊቱን መፈጸሙን ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ አስታወቀ። የ 24 አመቱ ወጣት ይርጋሸዋ ማሽላ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ለመናገር የሚከብድ የአንድ ብሄር …

‹‹እንሰሳት በዋሉበት እየቀሩ ነው›› ነዋሪዎች በሀገሪቱ በተፈጠረው የዝናብ እጥረት ምክንያት በተለይ በአፋር፣ በሶማሊና በሌሎች አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ ጎጃም ውስጥም በመከሰቱ በርካታ እንሰሳት እየሞቱ መሆኑንና ሰውም ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለፁ፡፡ በተለይ ድርቁ በሶማ፣ አራራ፣ እነገ እና ሰንጠርጌ ቀበሌዎች ለበርካታ እንሰሳት ሞት ምክንያት ከመሆኑም ባሻገር ነዋሪዎችም ለከፍተኛ ችጋር ተጋልጠዋል ተብሏል፡፡ ድርቁ አስከፊ ደረጃ […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ በቀጣይ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ላይ የተመረጡ እና የተለመዱ ፊቶችን ስብስበው ጥያቄ ሲያቀርቡና ማብራሪያ ሲሰጡ ነበር፡፡የእኔን ቀልብ የሳበው ግን አውቀውም ይሁን ሳያውቁት ወጣቶችን እየበላ ያለ ስርዓት ባለቤት እና መሪ መሆናቸውን የገለፁበት አስተያየት ከታዳሚው ሞቅ ባለ በተደጋጋሚ ጭብጨባ መታጀቡ ነው፡፡ ባለፈው የኦባማ ጉብኝት ወቅት ዲሞክራሲ ማላት ምርጫ በስላም ማጠናቃቅ ብቻ አይደለም፡፡ ጋዜጠኞችን አክቲቪሰቶችን […]

ከታሳሪ የህሊና ሰዎች መካከል አብጦ ሊፈነዳ የተቃረበውን የፖለቲካ ድባብ ለማስተንፈስ ሲባል ወዳጄን፣ ጓዴንና የቀድሞ ባልደረባዬን አብርሀ ደስታን፣ የሽዋስ አሰፋን፣ ሐብታሙ አያሌውን፣ ዳኤል ሽበሽንና አብሃም ሰለሞንን «በነፃ» መለቀቅ በሰማሁ ጊዜ ደስታ ቢሰማኝም፤ ንጹሓኑ «በነጻ» መለቀቃቸው ከጠባቡ ጓንታናሞ ወደ ሰፊው ጓንታናሞ መዛወራቸው እንጂ አሁንም ነጻ አለመሆናቸውን፤ እንዴውም አሁን ያለንበት በነጻነት የመናገርና የመጻፍ ሁኔታ እነሱ ከመታሰራቸው በፊት ከነበረው […]

 

በነሶሊያና ሺመልስ የክሥ መዝገብ ብይን ሲጠብቁ የነበሩት አራቱ የኢንተርኔት አምደኞች ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ክሣቸው ተቋርጦ በነፃ የተሰናበቱትም በኤግዚቢትነት ተይዘው የነበሩ ንብረቶቻቸው እንደተመለሱላቸው ተናግረዋል፡፡

በኮምፕዩተሮቻቸው ውስጥ የነበሩ ልዩ ልዩ ሠነዶች ግን በመጥፋታቸው ማዘናቸውን ገልፀዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ዛሬ ነሐሴ 13/2007ዓም በ8:00 ሰዓት የጠቅላይ ፍርድ ሰበር ሰሚ ችሎት ወሳኔ ለመስጠት ሲያነጓትተው የነበረውን የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሰበር አቤቱታ ላይ ዛሬ ውሳኔውን አስተላልፏል። ፍርድ:- ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ ከዚህ ቀደም የእስር ፈርድ ቤቱ የሰጠው የ 3 አመት ፍርድ አግባብም ትክክልም ነው፣ ስለዚህ የስር ፈርድ ቤቱ ካስተላለፈው ውሳኔ ውጪ አይደለንም ፍርዱን አፅንተነዋል ፍርዱ ልክ ነው ምንም […]

በመረጃ መረብ ሰንሰለቱ አማካኝነት ወደ መንግስት መዋቅር ዘልቆ በመግባት ያገኘው የታማኝ ምንጮች መረጃ እንዳረጋገጠው በሙስሊሙ ዑማ ላይ ከፍተኛ በደልና ጭቆና የፈፀመው ህወሓት መራሹ መንግስት በአሁኑ ሰዓት የሙስሊሙ ማህበረሰብ አጠቃላይ ሁኔታ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ዘፍቆታል ። በአሁኑ ሰዓት ሙስሊሙ ማህበረሰብ የትግል ስልቱን ቀይሮ ውስጥ ለውስጥ በመደራጀት አንድነቱን እያጠናከረ እና በተናጠልና በቡድን በመሆን ስለ ቀጣይ ትግሉ እየተወያየ […]

ርዕዮት አለሙ፤ ከአዲስ አበባ ልጆች ሆነን “እከሌ (እከሊት) አክራሪ ነዉ (ናት)” ሲባል ይሰጠን የነበረዉ ትርጉም እና አሁን አክራሪነት እየሰጠ ያለዉ ትርጉም ለየቅል ይመስለኛል፡፡ ያኔ አንድ ሰዉ በአክራሪነት ሲጠራ ከብዙሃኑ በተለይ ሁኔታ ሃይማኖቱን ወይም የሚያምንበትን አንዳች ነገር አጥብቆ መያዙን እና በሚያምንበት ነገር ላይ …

አክራሪና አሸባሪዉ ኢህአዴግ ወይስ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት? – ርዕዮት አለሙ Read more »

ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በወረ ጃርሶ ወረዳ በሚገኙ በፋጂ ኢጀርሳ፣ ላንቱ ወላርጊ እና ምእራብ ኮርጎጎ ቀበሌዎች የሚኖሩ ከ300 በላይ አርሶአደሮች ከሰኔ 28 ቀን 2007 ዓም ጀምሮ ኢጀርሳ መንደር ውስጥ በሚገኝ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ታስረው እየተደበደቡ መሆኑን ቤተሰቦቻቸውና እስራቱን ለማምለጥ የተደበቁ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። …

ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው ከሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ከአንድ ዓመት በላይ በተንዛዛ የፍርድ ቤት ቀጠሮ በእስር ሲማቅቁ የነበሩት አራቱ የፖለቲካ እስረኞችን ጨምሮ ሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች፣ የልደታው ፍርድ ቤት 19ኛ የወንጀል ችሎት፣ ዛሬ ነሃሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ተከሳሾችን አሰናብቷል። በዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ የተከሰሱት የቀድሞው …

ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰንደቅ ጋዜጣ ይዞት በወጣው ዘገባ በፓትሪያርክ አቡነ ማትያስ መመሪያ የተቋቋመው አጥኚ ቡድን የመሬትና ሕንፃዎች ኪራይ ተመንን አስመልክቶ በ51 የአዲስ አበባ አድባራት ባካሔደው ጥናታዊ ሪፖርት፣ በየወሩ 100 ሚሊዮን ብር፣ በዓመት ደግሞ 1 ቢሊዮን 500 ሚሊዮን ብር በሙስና እንደሚዘረፍ ገልጿል። ቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ እና ሰፊ የመሬት …

ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንዳሉት ሰኔ 15 እና 16 የክረምቱ ዝናብ ከዘነበ በሁዋላ፣ ዝናብ ለተከታታይ ስድስት ሳምንታት አልዘነበም። ሃምሌ 29 ቀን ደግሞ ለአንድ ጊዜ ዘንቦ በመጥፋቱ ፣ ህዝቡ በከፍተኛ ሃዘን ውስጥ ገብቶ ነበር። ይሁን እንጅ ትናንት ከምሽቱ 11 ሰአት ከ30 ደቂቃ ላይ መዝነብ የጀመረው ዝናብ እስከ 12 ሰአት …

ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና የኢህአዴግ የስራ አስፈጻሚ ኮምቴ አባል አቶ ድሪባ ኩማ የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና ተግባር በከተማዋ መቀነስ ያልቻለው መመሪያዎችን በቁርጠኝነት መፈጸም የማይችል አመራር በመኖሩ ነው ሲሉ በስራቸው የሚገኙ አመራሮችን ወቅሰዋል፡፡ ከንቲባው ይህን የተናገሩት በሰኔ ወር 2007 የተጠናቀቀውን የአምስት ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸምና በቀጣይ ዓመት …

በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በሽብርተኝነት ክስ ተመሥርቶባቸው በእስር ላይ የቆዩት የቀድሞ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)፣ የሰማያዊና የአረና ፓርቲ አመራሮችና ሁለት ተከሳሾች በነፃ እንዲሰናበቱ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ነሐሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ወሰነ፡፡ የአንድነት ፓርቲ የቀድሞ …

የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ሀብታሙ አያሌውና ዳንኤል ሺበሺ፣ የአረና ፓርቲ አመራር አብርሃ ደስታ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የሺዋስ አሰፋና ሌሎች 2 ተጠርጣሪዎች በነፃ እንዲሰናበቱ ተወሰነ Read more »

ላለፉት ጊዜያት በተለያዩ እስር ቤቶች ሲንገላቱ ሲገረፉ ሲሰቃዩ ከርመው ካለወንጀላቸው ወንጀለኛ ነን ብለው ፈርመው ከማእከላዊ ማሰቃያ ወደ ቃሊቲ ማጎሪያ ከተዘዋወሩ በኋላ በካቴና ከርመው በካንጋሮው ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት የቀረበባቸው የሽብርተኝነት ክስ ከጥርጣሬ ባለፈ ተሳትፎአቸውን ማረጋገጥ አልተቻለም በማለት የለቀቃቸው መሆኑ ታውቋል::መጀመሪያም …

ካለማስረጃ የተጠረጠረ ሁሉ የሚንገላታበት ጉዳይ ሊወገድ የሚችለው በኛ ትግል ብቻ ነው:: (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

በተባበሩት መንግሰታት የሰብአዊ ድጋፍ ቢሮ ይፋ ባደረገው አዲስ ሪፖርት በኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር በያዝነው ወር 4.5ሚልዮን መድረሱን ይፋ አድርጓል፡፡ የ2015 ግማሽ አመት የሰብአዊ ድጋፍ ተፈላጊነት ከተገመገመ በኋላ ሪፖርቱ ይፋ ሲደረግ ለጋሽ አገራትና የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዩች በስፍራው መገኘታቸውን መረጃው ጨምሮ ጠቁሟል፡፡ ሪፖርቱ በተጨማሪ ለምግብና ምግብ ነክ ላልሆኑ ነገሮች የሚያስፈልገው የእርዳታ መጠን በጃንዋሪ(ጥር)ወር ተተንብዮ ከነበረው […]