Yared E Yimura :  “ኢትዮጵያዉያንን ማከም ሄዴክ ነዉ። መድሃኒት መዉሰድ አይወዱም። ቢጀምሩም አይጨርሱም። የረጅም ጊዜ ክትትል የሚፈልግን ህመም በአግባቡ አይከታተሉም። ደግሞ የ አብዛኛዎቹ ኬዝ የስኳር ህመም ነዉ። ምንድነዉ የምትመገቡት? ብዬ ስጠይቃቸዉ ሁሉም እንጀራ ይሉኛል። እና እንጀራ ከምን እንደሚሰራ ለማወቅ በከተማዉ …

በሰሜን አሜሪካ እንጀራ ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያመጡ ከሚችሉ ንጥረ ነገሮች እንደሚዘጋጅ መረጃዎች ይጠቁማሉ:: Read more »

ዛሬ ነሃሴ 14/2007 ዓ.ም የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የተከሰሱትን 2ኛ ተከሳሽ ሀምታሙ አያሌው፣ 3ኛ ተከሳሽ ዳኤል ሽበሽ፣ 4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታና 5ኛ ተከሳሽ የሸዋስ አሰፋ እንዲሁም 7ኛ ተከሳሽ አብሃም ሰለሞን በነፃ እንዲለቀቁ ወስኗል፡፡ በአንፃሩ አንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ከአሁን ቀደም ተከሶበት በነበረውና ከ15 አመት በላይ እንደሚያሳስር የሚታወቀው የፀረ ሽብር ህጉ አንቀፅ አራት ‹‹ማሴር፣ […]

የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት የህወሓት አገዛዝ የደህንነት ቢሮ ጮርቃ ህፃናትን በሰላይነት እያሰለጠነ እንደሚገኝ ታወቀ፡፡ የህወሓት ብሄራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ በርካታ ህፃናትን ከየአካባቢው መልምሎ አዲስ አበባ ውስጥ የስለላ ትምህርት በስውር እያስተማረ ይገኛል፡፡ ብሄራዊ መረጃና ደህንነት ህፃናቱን አገዛዙን ብቻ በታማኝነት እንዲያገለግሉ የሚያመቻች የስለላና ሌሎች ተያያዥ ትምህርቶችን ለረጅም ጊዜ በተከታታይ በመስጠት አስተሳሰባቸውን በመግራት አእምሯቸውን በሚፈለገው መልኩ ለመቅረፅ […]

የተመሠረተበትን 35ኛ ዓመት በታላቅ ፌሽታ ለማክበር ደፋ ቀና በማለት ላይ የሚገኘው የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን ንቅናቄው ሰሞኑን በሚያካሂደው ጉባዔ ላይ እንደማይመረጡ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ህወሃትም በተመሳሳይ ሁኔታ የሟቹን የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍንን ያሰናብታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የብአዴን ምንጮች እንደሚሉት ኢህአዴግ ባስቀመጠው የመተካካት ስርዓት መሠረት […]

ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ድንበር አቋርጣችኋል የተባሉ ኢትዮጵያዊያን ማላዊ ውስጥ በእሥር ላይ ይገኛሉ። እነዚህ 232 ኢትዮጵያዊያን የሚገኙበት ሁኔታም እጅግ አስከፊና ጤንነትንም የሚጎዳ መሆኑን እዚያው ኗሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል። ከእነዚህም አንዷ ዋና ከተማይቱ ሊሎንግዌ ውስጥ ከሃያ ዓመታት በላይ የኖሩት ወ/ሮ …

ማላዊ ውስጥ 232 ኢትዮጵያዊያን ታስረዋል Read more »

ነኅሴ ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተመሠረተበትን 35ኛ ዓመት በታላቅ ፌሽታ ለማክበር ደፋ ቀና በማለት ላይ የሚገኘው የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን ንቅናቄው ሰሞኑን በሚያካሂደው ጉባዔ ላይ እንደማይመረጡ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ህወሃትም በተመሳሳይ ሁኔታ የሟቹን የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍንን ያሰናብታል ተብሎ …

ነኅሴ ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ፣ ኢሰመጉ የአሁኑ ሰመጉ ባወጣው 137ኛ ልዩ መግለጫ፣ ከምርጫ 2007 ጋር በተያያዘ 6 ሰዎች መገደላቸውንና 83 የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች መታሰራቸውን በስም ዘርዝሮ አቅርቧል። በደብረማርቆስ ከተማ ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓም የተገደለው ወጣት ሳሙኤል አወቀ፣ በፖለቲካ አመለካከቱ ምክንያት የተገደለ መሆኑን የቅርብ ቤተሰቦቹ …

ነኅሴ ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር ባወጣው ሪፖርት በኢትዮጵያ ውስጥ የመኸርና የክረምት ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ ባለመጣሉና በመዘግየቱ ምክንያት በተፈጠረው ድርቅ ሰለባ ለሆኑ ከ4 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ግምቱ ከ386 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይም ከ7 ቢሊዮን 700 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ አፋጣኝ የሆነ የሕይወት አድን የምግብና ሌሎች …

ኢሳት ዜና (ነሐሴ 12 ፣ 2007) በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን የዞኑ አስተዳደር ህገ ወጥ ግንባታ ናቸው ያላቸውን መኖሪያ ቤቶች ለማፍረስ መሞከሩን ተከተሎ ነዋሪዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው በርካታ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸውና መደብደባቸው ተገለጠ። በሳምንቱ መገባደጃ በዞኑ በምትገኘው የቦሎሶሶሬ ወረዳ በተቀሰቀሰ በዚሁ ግጭት ከ20 በላይ ነዋሪዎች በላይ ነዋሪዎችና ህገ-ወጥ ናቸው የተባሉትን ግንባታዎች ለማፍረስ የተሰማሩ ከ10 በላይ አፍራሽ …

(ስሉሥ ወልደሂወት) “ማንም የቆመ የሚመስለው ቢኖር እንዳይወድቅ ይጠነቀቅ”! መጽሓፍ ቅዱስ የሰው ልጅ ፍላጎት ሁሌ የሚያድግና የማይሟላ በመሆኑ የለውጥ ጥያቄን ለመመለስ ሁሌም ሰለተሻለ አማራጭ፣ ስለተሻለ ዘዴ ወይም ስትራቴጂ ማሰቡና መነጋገሩ ተገቢና ጤናማ መሆኑ የማይታበል እውነት ነው፡፡ በዲሞክራሲያዊ ማህበረሰብ ዘንድ የተቀደሰና ከነቀፋና ትችት የፀዳ የፖሊሲ አቋም ወይም የፖሊሲ አፈፃፀም የማይኖር መሆኑም እንደዚሁ። ዜጐች በግልም ይሁን በተደራጀ መልኩ በነፃነትና ከማንኛውም ተጽእኖ በጸዳ መልኩ የፖሊሲ አማራጮችን መተቸችና የመልካም አስተዳደር ግድፈቶችን ነቅሶ ማውጣት የሚችሉበት ሁኔታ ከተፈጠረ ያ ማህበረሰብ የታደለ ነው ማለት ይቻላል፡፡ የፖለቲካ መሪዎች በዓቅም ውስንነት፣ በግንዛቤ እጥረት፣ የግል ፍለጎት በማሰቀደም ወይም በቅንነት እጦት ምክንያት የሕዝቦችን ጥቅም አደጋ ውስጥ ሊከቱ የሚችሉበት እድል ሰፊ ነው። በመሆኑም የፖሊሲ አማራጮችንና የአፈፃፀም ግድፈቶችን ከመተቸት ባላፈ ፖሊሲውን ለማስፈፀም ሃላፊነት የወሰዱ የፖሊቲካ ድርጅቶች አመራር፣ ውስጣዊ ድርጅታዊ ህይወትና የአመራሩ የግል ማንነት ሳይቀር አብጠርጥሮ ማወቅና መተቸት በሰለጠነው ዓለም የተለመደና ውጤታማ የሆነ የዲሞክራሲ ባህል ነው፡፡ ከሰሞኑ አቶ ዳዊት ገብረ እግዚአብሔር የተባሉ ዜጋ በተለየ ሁኔታ በህወሓትና ህወሓት በሚመራው የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የልማትና መልካም አስተዳደር ፖሊዎችና አፈጻጸም ላይ የሰላ ትችት በመሰንዘር ላይ ይገኛሉ፡፡ የአቶ ዳዊት ትችት ከግል ገጠመኝና ትዝብት በመነሳት በአጠቃላይ በስርዓቱ፣ ስርዓቱ በቆመባቸው ምሰሶችና የማስፈፀምያ ፖሊሲዎች ስትራቴጂዎች እንደዚሁም የድርጅቱና የድርጅቱ አመራር ዓቅምና ህዝባዊነት ላይ ጥያቄ አስነስቷል፡፡ ቀደም ብዬ እንዳልኩት ከፖሊሲ የተሻለ ፖሊሲ፣ ከተሻለው ፖሊሲ እጅግ የተሻለ ፖሊሲ መኖሩ የማይቀር ስለሆነ፤ አቶ ዳዊት ስለተሻለ አመራር፣ […]

በሕዝብ ሃብት መቀለድ ተይዟል::ሰበታ አከባቢ ያልተጠናው የባቡር ሃዲድ እየፈረሰ ነው:: ሰበታ አካባቢ ያለ የባቡር ሃዲድ መስመር በወያኔ ባለስልጣናት ትእዛዝ እየፈረሰ ነው በምስሉ እንደሚታየው አሁን ከተገነቡት መሀል አንዱ ሲሆን ምክንያትቱ ሳይታወቅ ሁኔታ በ24 ሰአት አንዲፈረሰ ትዕዛዝ ተሰጥቷል በተለያዩ የአዲስ አበባ አከባቢዎች በርካታ የሆኑ የባቡር መስመሮች የሚፈርሱ እንዳሉ የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል::ይህ ያልተጠና እና በሕዝብ ሃብት ላይ እየተቀለደ […]

ዛሬ በዞን 9 ጦማሪያን የፍርድ ቤት ውሎ የገረመኝ ዛሬ ረፋድ ላይ፤ ናቲ፣ አጥናፍ፣ በፍቄና አቤል በፊት ለፊት በር ችሎት ከገቡ በኋላ፣ እኛም ችሎቱን እንታደማለን ብለን ስንጠብቅ፤ ለጠበቃቸው ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱ ተነገረ፡፡ ጦማሪያኑንም በጓሮ በር በማስወጣት ‹‹አንበሳ ቤት›› እንዲቀመጡ ተደረገ፡፡ በፊት ለፊት አስገብቶ በጓሮ በር ማስወጣት ምን ይባላል? ለምንስ ይሆን? በስፍራው የተገኙ የእስረኛ ቤተሰቦች፣ ዘመዶች፣ ጓደኞች፣ […]

የቀድሞው የብሥራተ ገብርኤል፣ የመካኒሳ ሚካኤል እና የገርጂ ጊዮርጊስ አለቆች ተጠቅሰዋል ከግለሰቦች ጋር የሕገ ወጥ ጥቅም ተጋሪ በመኾን አድባራቱን ለዕዳ የዳረጉ አለቆች ይገኙበታል የመኪና እና የኮንዶሚኒየም ቤት ቁልፍ ሽልማት በፓትርያርኩ ሳይፈቀድ እንዳይሰጥ ተወስኗል ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደ ጥንተ ክብሯ የሚመልስ የፀረ ሙስና እንቅስቃሴ ይደረጋል ተብሏል በጥናታዊ ሪፖርቱ፣ ‹‹አስገራሚ እና ለምዝበራ የተመቸ›› በተባለ አሠራር፣ የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል …

በኢትዮጵያ ከሚገኙት ከ30 ከሚበልጡት የመንግሥት እና በብዛት ከተከፈቱት የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ዘንድሮ ከ90 ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎች ተመርቀዋል። ዩኒቨርሲቲዎቸች እና የኮሌጆች ምሩቃን የቀሰሙትን እውቀት እና በሥልጠና ያገኙትን ሙያዊ ክሂሎት የተሻለ ኑሮ እድል ከፋች አድርገው ተመልክተውታል። ይሁንና፣ ገሀዱ እንደጠበቁት ሆና ሳያገኙት …

ምሩቃን እና የሥራ ዕድል Read more »

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መንጌ ወረዳ የመንግስት ሃይሎች አርብ እለት በሰነዘሩት ጥቃት 12 ሰዎች ተገደሉ። ከሟቾቹ ውስጥ 5ቱ ህይወታቸው ያለፈው እስር ቤት ከተወሰዱ በኋላ በምግብ ተመርዘው እንደሆነ የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ አስታወቀ። የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ (ቤሕነን) ሊቀመመንበር አቶ አብዱልዋህድ መሃዲ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት አርብ ነሐሴ 8 ቀን 2007 የመንጌ ወረዳ ነዋሪዎች በስርዓቱ ላይ […]

በኬንያ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር የዋሉት 100 ኢትዮጵያዊያን ትናንት አመሻሽ ላይ ነው፡፡በወጣትነት የእድሜ ክልል የሚገኙት ታሳሪዎቹ በተፋፈነ ሁኔታ በአንድ ትልቅ መኪና ተሳፍረው ወደ ናይሮቢ በመገስገስ ላይ እንዳሉ በፖሊሶች በተደረገ ፍተሻ መያዛቸው ታውቋል፡፡ታሳሪዎቹ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናት አቅደው የነበሩ መሆናቸውም ተነግሯል፡፡ እንደ ዴይሊ ኔሽን ዘገባ ከሆነም ስደተኞቹ በሞያሌ በኩል በድብቅ በማለፍ ወደ መሩ ካውንቲ ማምራታቸውን መረጃ የነበራቸው የኬንያ ፖሊሶች በቀላሉ በቁጥጥር ስር ሊያውሏቸው […]

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአለፈው ምርጫ ጋር ተያይዞ ፣ የአካባቢው ህዝብ የስርዓቱ ደጋፊ አይደለም፣ በምርጫውም ለመሳተፍም ሆነ ከመንግስት ጎን ለመቆም ፍላጎት አላሳየም በሚል የበቀል እርምጃ እንደተወሰደባቸው የአካባቢው ተወላጆች፣ የልዩ ሃይል አባላት በወሰዱት የጭካኔ እርምጃ እስካሁን በመንጌ ወረዳ 11 ሰዎች መገደላቸውን ገልጸው፣ ግጭቱ ወደ ዳቡስ አካባቢም የተዛመተ በመሆኑ የሟቾቹ ቁጥር ከፍተኛ …

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ወሎ ለጋምባ ወረዳ ከዩኒቨርስቲ ግንባታ ጋር በተያያዘ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወጣቶች ተይዘው መታሰራቸውን የደረሰን ዜና አመልክቷል። ከታሰሩት መካከል 6 ያክሉ የመንግስት ሰራተኞች ናቸው። ዩኒቨርስቲው ይገነባበታል ተብሎ እቅድ ተይዞ በነበረበት በቱሉ አወሊያ አንድ ፖሊስ ተደብድቦ አቀስታ ሆስፒታል ገብቷል። በአካባቢው የሰፈረው የፌደራል ፖሊስ ወጣቶችን …

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት የመኢአድ ፓርቲ የአመራር አባላት በእስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው የአይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል። ወጣት ተስፋየ ታሪኩ፣ ቀድም ብሎ በእስር ቤት ውስጥ እየተደበደቡ መሆኑን ለፍርድ ቤት ማመልከቱን ተከትሎ ፣ ፖሊሶች ዘቅዝቀው በጠመንጃው ሳንጃ በሽፋኑ ጀርባውን ደብድበውታል፣ እጁና እግሮቹም ተጎድተዋል። ተስፋየን …

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ ሬዲዮ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ አስመልክቶ በሰራው ዘገባ ፣ የአገሪቱ ሰራተኞች በአለም ላይ እጅግ ዝቅተኛ የሆነ ክፍያ ከሚያገኙ አገሮች ቀዳሚ መሆናቸውን ጠቅሶ፣ የውጭ አገር ኩባንያዎች ሰራተኞቹን እንደ ባሪያ እንደያዙዋቸው ገልጿል። ከ11 ሚሊዮን በላይ ስራ አጥ ባለበት የሰራተኛውን የመጨረሻ የክፍያ ወለል ማስተካከል ፈታኝ መሆኑን የገለጸው ቢቢሲ፣ ወጣቱ በ50 …

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ወታደሮች በሶማሊያ ሂራን ክልል ውስጥ ከአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ጦር፣ አሚሶም ተልኮ ውጪ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የአሚሶም ምድብ አራት የጦር አዛዥ የሆኑት አብዱራህማን አብዲ ዲምቢሊ ቅሬታቸውን አሰሙ። ጅቡቲያዊው የጦር አዛዥ ኮማንደር አብዱረህማን ፣ ካለ ህብረቱ ጦር ትእዛዝ በሂራን ግዛት የኢትዮጵያ ወታደሮች አልሸባብን ደምስሰው አካባቢውን ከተቆጣጠሩት በኋላ …

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመላ ሃገሪቱ በ2001 ዓ.ም የተቋቋመው የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ የታሰበለትን ሃገራዊ ፋይዳ በተገቢው ሁኔታ ለማድረስ እንዳልቻለ የአማራ ክልል የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ የሽዋስ ተናገሩ፡፡ ዳይሬክተሩ በክልሉ በልዩ ልዩ ቦታዎች በተካሄደው ውይይት ለተሳታፊዎች እንደገለጹት በአመለካከትና ክህሎት ዙሪያ ሰፊ ክፍተት አለ ብለዋል። መዛኝ …

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሚኒስትሩ ሚካኤል ማኩዊ የምስራቅ አፍሪካ በየነ መንግስታት ኅብረት ኢጋድ ዋና አደራዳሪ የሆኑትስዩም መስፍን በተደራዳሪዎች ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ ይሞክራሉ ሲሉ ወቀሳቸውን አሰምተዋል። ሚካኤል ማኩዊ ” የኢጋድ አደራዳሪዎች ደቡብ ሱዳንን የሙከራ ምድር ለማድረግ ይሞክራሉ።አንዳንዶቹ በጭራሽ ዓለማቀፋዊ ተቀባይነት የሌላቸው ናቸው።የግድ መፈረም አለባችሁ ብሎ ለተደራዳሪዎች አስገዳጅ ውል ማቅረብ፣ ካልፈረማችሁ እኛ …

የት እንዳሉ ሳይታወቁ ቀርተው የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በአባታቸው መጎበኘታቸው ተሰማ:: የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመን ላይ ተይዘው ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈው ከተሰጡ በኋላ አፍቃሪ የመንግስት ድረገጾች በፎቶ ሾፕ አንዳርጋቸው የአዳማን መንገድ ሲጎበኝ በሶሻል ሚድያዎች ለጥፈው ሲዋሹ ነበር:: ከዚህም በተጨማሪ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም አቶ አንዳርጋቸውን ልማቱን እያስጎበኘነው ነው ሲሉ በአሜሪካ ድምጽ ራድዮ […]

ኢሳት ዜና (ነሐሴ 12 ፣ 2007) በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መንጌ ወረዳ የመንግስት ሃይሎች አርብ እለት በሰነዘሩት ጥቃት 12 ሰዎች ተገደሉ። ከሟቾቹ ውስጥ 5ቱ ህይወታቸው ያለፈው እስር ቤት ከተወሰዱ በኋላ በምግብ ተመርዘው እንደሆነ የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ አስታወቀ። የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ (ቤሕነን) ሊቀመመንበር አቶ አብዱልዋህድ መሃዲ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት አርብ ነሐሴ 8 ቀን …

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያን ህዝብ ንብረትና አንጡራ ሀብት በመመዝበር በአለም አቀፍ ደረጃ አሉ በሚባሉ ታላላቅ የንግድ ተቋማትና ባንኮች ላይ ባለድርሻ እየሆኑ ይገኛሉ ለጊዜዉ ስማቸዉን መጥቀስ አስፈላጊ የልሆኑ ከፍተኛ ባለስልጣናት በደቡብ አፍሪካ ዚምባብዌ ኡጋንዳ ቦትሱዋና ዉስጥ ትላላቅ ህንጻዎችን፣ እና የእንግዳ መቀበያ ሆቴሎችን ( gust houses ) ፣ መሬቶችና ሌሎችታላላቅ የንግድ ተቋማት ላይ እግራቸዉን እየተከሉ ይገኛሉ። […]

የመላው ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ) የውጭ ግንኙነት ሀላፊ አብርሃም ጌጡ ሰኔ 12 /2007 ልደታ ፓሊስ መምሪያ ታሰረ ብዙም ሳይቆይ ወደ 5ኛ ፓሊስ ጣቢያ ተዛወረ ልደታ ፍርድ ቤት ሚያዝያ 13/2007 ዓም የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ወጣቶችን አደራጅተህ ሚያዝያ 14/2007 ዓም መንግስት የጠራውን ሠልፍ እንዲረበሽ አድርገሃል የሚል ክስ ቀረበበት ጊዜ ቀጠሮ ላይ እያለ ሳይቋጭ […]

_በፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና በምክትላቸው በአርበኛ መዓዛው ጌጡ የተመራው የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራር በኤርትራ በረሃ በተለያዩ የጦር ካምፖች የሚገኙትን የነጻነት ታጋዮችን ጎበኘ። አቶ ነዓምን ዘለቀና አቶ ኤፍሬም ማዴቦም ተገኝተዋል። ታጋዮቹ ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡ ከአመራሮቹም ጋር ተወያይተዋል። _ባለፈው ዓርብ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መንጌ ወረዳ ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የሚመራው መንግስት ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ 17 ኢትዮጵያውያን ተገደሉ። ስርዓቱ በቃን […]

በሚሌ ወረዳ የሀርሲስ ቀበሌ ነዋሪዎች በድርቅ መጎዳታቸውን የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ግርማይ ጋብሩ በአፋር ክልል ታዘዋውሮ ዘግቧል። Listen

አንደኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ ‹‹ሀገሬ በፋሽስት አምባገነኖች ተይዛ ዜጎች በጨቋኝ ስርዓት ውስጥ ስላሉ ሀገሬንና ህዝቤን ነጻ ለማውጣት ወጣትነቴን ሰውቼ ለመታገል ግንቦት ሰባት ከሚባል ነጻ አውጭ ድርጅት ጋር ለመቀላቀል ወስኜ ወደዚያው አቅንቻለሁ፡፡ ስለዚህ ድርጊቱን ፈጽሜያለሁ፣ የግንቦት ሰባት አባል ነኝ፡፡ ወንጀለኛ ግን አይደለሁም›› ሲል ቃሉን ለፍርድ ቤቱ ሰጥቷል፡፡ ሁለተኛ ተከሳሽ እየሩሳሌም ተስፋው በበኩሏ፣ ‹‹ድርጊቱን ፈጽሜያለሁ፤ ነገር ግን […]

ወደ 150 ሚሊዮን የሚጠጋ ብር በሻንጣ ጠርቆ ለንደን የገባ የሀገራችን ዘራፊ የወያኔ ባልደረባ በእንግሊዝ ፖሊሶች ክትትል እጅ ከፈጅ ተያዘ።ከፍርድ ቤት ጋር በተያያዘ ለጊዜው ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቁ ምንጮች እንደገለጹት ፣ አንድ የህወሃት አባል 5 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ የሚገመት ጥሬ ገንዘብና ወርቅ በሻንጣው ይዞ ወደ ለንደን ሲገባ ጋትዊክ አየር ማረፊያ ላይ በፖሊሶች ተይዟል። ግለሰቡ ፍርድ ቤት ቀርቦአል። […]

ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከፍርድ ቤት ጋር በተያያዘ ለጊዜው ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቁ ምንጮች እንደገለጹት ፣ አንድ የህወሃት አባል 5 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ የሚገመት ጥሬ ገንዘብና ወርቅ በሻንጣው ይዞ ወደ ለንደን ሲገባ ጋትዊክ አየር ማረፊያ ላይ በፖሊሶች ተይዟል። ግለሰቡ ፍርድ ቤት ቀርቦአል። ዳኛው ” ይህን ያክል ገንዘብ እንዴት በሻንጣ ልትይዝ ቻልክ …

ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሳምንት በደቡብ ወሎ ለጋምባ ወረዳ ከዩኒቨርስቲ ግንባታ መቋረጥ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ለውጥ የተጀመረው ተቃውሞ በተለያዩ መንገዶች እየቀጠለ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በተለያዩ አጎራባች ወረደዎችና ቀበሌዎች ህዝቡ መኪና መንገዶችን በድንጋይ በመዝጋትና መኪና እንዳይተላለፍ በማድረግ እንዲሁም በጋራ በመሰባስብና ድምጻቸውን በማሰማት ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ የነበቱ ሲሆን፣ ዛሬም ዩኒቨርስቲው በሚገነባበት …

ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማውና ደሴ ካህሳይ ልደታ ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ፣ የተጠቀሰውን ድርጊት መፈጸማቸውን ነገር ግን ወንጀለኞች አለመሆናቸውን ተናግረዋል። በወጣቶቹ ላይ የቀረበው ክስ ግንቦት 7 የተባለውን አሸባሪ ቡድን ለመቀላቀል ሲሄዱ ማካይድራ በተባለው የድንበር ከተማ ላይ ተይዘዋል የሚል ነው። ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው …

ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፍርድ ቤት በቅርቡ ከፍተኛ ቅጣት የጣለባቸው የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ የጠየቁ 20 ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸዋል። ህዝበ ሙስሊሙ በመንግስት ላይ እንዲነሳ ቀስቅሰዋል በሚል በ14ኛ ወንከል ችሎት የተከሰሱት ከድር መሃመድ፣ ነዚፍ ተማም፣ ካሊድ መሃመድ፣ ፉአድ አብዱልቃድር፣ ኢብራሂም ካሚል፣ አብዱ ጁባር፣ ሁሴን አህመድ፣ ሃሚድ …

ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወኪላችን በላከው ሪፖርት በከተማ ውስጥ ባለፉት 3 ቀናት ከፍተኛ ሆነ የነዳጅ እጥረት በመከሰቱ ፣ አሽከርካሪዎች ነዳጅ ለማግኘት ሲቸገሩ ታይቷል። በርካታ ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ቀኑን ሙሉ በየማደያዎች ተሰልፈው የታዩ ሲሆን፣ ይህንን ተከትሎ የታየው የዋጋ ጭማሪ ህዝቡን ለምሬት ዳርጎታል። በባህርዳርም እንዲሁ በቅርቡ ተመሳሳይ የነዳጅ እጥረት መከሰቱ መዘገቡ ይታወሳል።

ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ባለው ድርድር፣ ፕ/ት ሳልቫኪርና ተቀናቃኛቸው ሪክ ማቻር ተገኝተዋል። የድርድሩ የመጨረሻው ቀን ዛሬ ሲሆን፣ ሁለቱ ተፋላሚ ሃይሎች ፊርማቸውን የማያኖሩ ከሆነ ማእቀብ ይጠብቃቸዋል ተብሎአል። የተለያዩ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ድርድሩን በተመለከተ የሚጋጩ መረጃዎችን እየለቀቁ ነው። የዩጋንዳው መሪ ዩዎሪ ሙሰቬኒ ድርድሩ ሳይጠናቅ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

የደቡብ ሱዳን የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር የኢጋድ ዋነኛ አደራዳሪ የሆኑትን ኢትዮጵያዊውን አምባሳደር ስዩም መስፍንን ከሰሱ፡፡ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ ማይክል ማኩኢ በአምባሳደር ስዩም መስፍን ላይ ጠንከር ያለ ወቀሳ ከመሰንዘር በተጨማሪም የኢጋድን የድርድር አካሄድ ወቅሰዋል፡፡ ከስምምነት ላይ የግዴታ መድረስ አለባችሁ ሲል ኢጋድ በደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ሀይላት ላይ ያስቀመጠውን ማሳሰቢያ የድርድር አካሄድ አይደለም ያሉት ሚኒስትሩ ኢጋድም ሆነ አምባሳደር ስዩም መስፍን ‘መመሪያ […]

ወያኔ ሐርነት ትግራይ የሚመራዉ መንግስት ወታደራዊ ፍርድ ቤት በሁለት የሰራዊቱ ከፍተኛ አባላት ላይ እርምጃ ወሰደ. በተልይም ለአርበኞች ግንቦት 7 መረጃ አቀብላችኍል የተባሉት እነዚህ ሁለት ወታደሮች በሰሜኑ እዝ ዉስጥ የተካተቱና የ 24 ተኛ ክፍ ለ ጦርን በመረጃ ፍሰት ምክንያት በማስጠቃት እና የሜካናይዝዱን እንዲሁም የእግረኛዉን አስተላለፍ የማጥቃትና የአቀማመጥ ወታደራዊ ዲዛኖችን ወይም ጥብቅ የምህንድስና የጦር ስልችን ለጠላት አሳልፋችሁ […]

በጠቅላይ ሚኒስተራችን የትውልድ ቦታ በሆነችው በቦሎሶ ሶሬ በከተማ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ምክንያት ነዋሪዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጩ በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ሥር በምትገኘው የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ከከተማ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ, ሕገወጥ ግንባታዎችን ለማፍረስ የአረካ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በመሞከሩ ነዋሪዎች ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸው ታወቀ የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የትውልድ ቦታ በሆነው የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዋና ከተማ […]

ታዳጊዋ ህጻን ጽንሱን በጊዜ ማቋረጥ ወይስ መውለድ ነበረባት ? በማከላዊ አሜሪካ( ፓራጓይ) ውስጥ ነዋሪ የሆነችው ሰሟ ለጊዜው ያልተጠቀሰው የ 10 አመቷ ጨቅላ ባለፈው ሚያዚያ ወር ከፍተኛ የሆድ ቁርጠት ሰሜት ሲሰማት ችግሯን ለወላጅ እናቷ ትናገራለች። ወላጅ እናቷም በአቅራቢያቸው ከሚገኝ አንድ ሆስፒታል ይወስዷታል። ዶክተሮቹም ለራሳቸውም ሆነ ለእናቷ እና ለጨቅላ ለጃቸው አንድ የለጠበቁት መርዶ ያረዷቸዋል። እርሱም ያቺ ለአቅመ […]

የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ የተቃዋሚ ድርጅቶችን ትደግፋላችሁ በሚል ወያኔ ህዝብን እያሸበረ ነው የመቅደላ ዩኒቨርስቲ ከግንባታው በፊት ለእርስ በርስ ግጭት መንስኤ ሆኖ የሰው ህይወት መቅጠፉ ተሰማ። የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች በስብሰባ ተጠምደዋል በደቡብ ወሎ የወያኔ የፀጥታ ሃይሎች በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ነው ተባለ። ሁለት የአይማኖት መሪዎች የትጥቅ ትግሉን እንደሚቀላቀሉ አስታወቁ በሽብር ወንጀል ተከሶ ቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኘው አበበ ካሴ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመበት […]

ሰበር ዜና ቢቢኤን ሰኞ በዛሬው እለት አዲስ አበባ በግሬቪቲ የተቃውሞ ፅሁፎችና ወረቀቶች ተጥለቅልቃ አደረች። በህዝበ ሙስሊሙ ኮሚቴዎች ላይ ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ ከ7 እስከ 22 መፈረዱን ተከትሎ የቁጣ መልእክት ያዘሉ መልእክቶች በአዲስ አበባ በስፋት ተፅፈው ማደራቸውን የቢቢኤን ምንጮች ገልፀዋል። በቀይ ቀለም እንዲሁም በቀይ በቢጫ፣ ነጭ ወረቀቶች ከተፃፉት መልእክቶች መካከል ይብቃ!!! አንባገነን ስርአት ከትከሻችን ይውረድ! ዋ!ዋ! ዋ! […]

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ ከ70 በላይ አማርኛ ተናጋሪ ገበሬዎች፣ ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎ ከመኖሪያ ቀዬአቸው መፈናቀላቸውን የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) በሪፖርቱ አመለከተ፡፡ የአንድ ሰው ሕይወት መጥፋቱንም አረጋግጫለሁ፤ ብሏል፡፡ ሰመጉ ጉዳዩን ሲመረምር መክረሙን ጠቁሞ፣ “ብሔር ተኮር ማፈናቀልና እንግልት በአስቸኳይ ይቁም” በሚል ርዕስ ይፋ ባደረገው 136ኛ ሪፖርቱ የወረዳው የጸጥታ ሓላፊዎችና ባለሥልጣናት የብሔር ግጭቱን […]

– የፖለቲካ እስረኞች ምሕረት እንዲደረግላቸው ጠይቋል

– የዳያስፖራ ልማት ባንክ ይቋቋም ተብሏል

መንግሥት የዳያስፖራ ፖሊሲን ይፋ ካደረገ ከሁለት ዓመት በኋላ በአገር አቀፍ ደረጃ በያመቱ እንዲካሄድ በወሰነው መሠረት፣ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰናዳው የዳያስፖራ ቀን በርካታ ቅሬታዎች ከዳያስፖራው ለመንግሥት ኃላፊዎች ቀረቡ፡፡ 

በተለያዩ አገሮች እንደሚኖሩ ከሚገመቱት ሁለት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መካከል አምስት ሺሕ ያህሉ ለአምስት ቀናት በሚሊኒየም አዳራሽ ሲካሄድ ቆይቶ እሑድ ነሐሴ 10 ቀን 2007 ዓ.ም. በሚጠናቀቀው የዳያስፖራ ቀን በዓል ላይ መሳተፋቸውን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በዚህ መሠረት ነሐሴ 7 ቀን 2007 ዓ.ም. በተደረገ ውይይት ወቅት የዳያስፖራ አባላቱ በመንግሥት በኩል የሚገጥሙዋቸውን ችግሮች በመዘርዘር ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡ 

መንግሥት እንዲያስተካክል ከተጠየቀባቸው ጉዳዮች መካከል የዳያስፖራው ማኅበረሰብ በቢሮክራሲ ውጣ ውረድና በመረጃ እጦት የሚደርስበት እንግልት ይጠቀሳል፡፡ በተለይ ነዋሪነታቸው በእንግሊዝ የነበረውና ወደ አገር ቤት ከመጡ ሁለት ዓመታት ያስቆጠሩት አቶ ሀብቴ ፈረደ፣ ከቱርክ በወኪልነት በባቡር መስመር ግንባታ ላይ ለማሳተፍ ያመጡት ኩባንያ በቢሮክራሲ ሳቢያ ፋይናንሱን ወደ ኬንያና ወደ ኡጋንዳ ለመውሰድ መገደዱን ተናግረዋል፡፡ ሜጀር ግሩፕ የተባለውን የቱርክ ኩባንያ አፈላልገው ማምጣታቸውን የገለጹት አቶ ሀብቴ፣ ኩባንያው 375 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውንና ከአዋሽ-ወልዲያ እስከ ሃራ ገበያ የሚዘረጋውን የባቡር መስመር ለመገንባት ጨረታውን አሸንፎ እንደነበር ይናገራሉ፡፡ 

ይህ ኩባንያ ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልገውን 1.7 ቢሊዮን ዶላር ለማምጣት የአንድ ዓመት ጊዜ ተሰጥቶት እንደነበር አስታውሰው፣ ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ምንጮች 1.9 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ችሎ እንደነበርም ጠቅሰዋል፡፡ ይሁን እንጂ ኩባንያው ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ከማምጣቱ አንድ ወር ቀደም ብሎ፣ ፕሮጀክቱ ያፒ መርከዚ ለተባለ ለሌላ የቱርክ ኩባንያ ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡ ጉዳዩን በማስመልከት የኢትዮጵያ ባቡር ኮርፖሬሽንን ሲጠይቁ፣ ሌሎች ያልተነኩ ፕሮጀክቶች ስላሉ እነዚያ ላይ ትሳተፋላችሁ እስከዚያ ጠብቁ የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ 

አቶ ሀብቴ እንደሚሉት፣ መንግሥት ከዚህ በኋላ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሌሎች አዳዲስ የባቡር ፕሮጀክቶችን ያስጀምራል የሚል ዕምነት ያጣው የቱርኩ ኩባንያ፣ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ሊያድርግ ያመጣውን ገንዘብ ወደ ኬንያና ኡጋንዳ ወስዷል፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው ግን የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ባቡር ኮርፖሬሽን ተገቢውን ምላሽ ሊሰጡ ባለመቻላቸው እንደሆነ አክለዋል፡፡ ውይይት እንዲደረግ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም አንድ ጊዜ ሚኒስቴሩ ሌላ ጊዜ ኮርፖሬሽኑን ይመለከተዋል በሚል ተደጋጋሚ ምክንያት ኩባንያው ሳይሳተፍ መቅረቱን ገልጸዋል፡፡ በመድረኩ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዶች ላይ አስረጅ ሆነው የቀረቡትና ጥያቄው በቀጥታ የተሰነዘረላቸው የገንዘብና ኢኪኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታው አቶ አህመድ ሺዴ ምላሽ ሳይሰጡበት አልፈውታል፡፡ 

ከአቶ ሀብቴ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በኩል የሚታደሰውን የትውልደ ኢትዮጵያዊነት መታወቂያ አገልግሎት ለማግኘት የሚገጥማቸውን ውጣ ውረድ የገለጹም ነበሩ፡፡ ከኤምባሲ ሠራተኞች ተገቢውን መረጃና ማብራሪያ የሚሰጣቸው በማጣት ብቻ በእያንዳንዱ የሰነድ ልውውጥ እስከ 40 ዶላር እየከፈሉ እንደሚቸገሩ አባላቱ አስታውቀዋል፡፡ በውጭ አገር ፍች ከፈጸሙ በኋላ የጋራ ንብረታቸውን ጠቅልለው በመምጣት ባዶ ለሚያስቀሯቸው  ባሎቻቸው ፈቃድ እየተሰጠ ችግር ላይ እንደወደቁ የተናገሩ ሴቶችም እያለቀሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምንና አቶ አህመድን መፍትሔ እንዲሰጧቸው ተማጽነዋል፡፡ 

በአሜሪካ ለ30 ዓመታት መኖራቸውን ለሪፖርተር የገለጹት ወይዘሮ ሰብለ ነቢየልዑል፣ ወደ ኢትዮጵያ ጠቅልለው በመምጣት በቆዳና በውበት ክብካቤ ላይ የሚሠራ ‹‹ዚኒያ ኤስቴቲክስ ኤንድ አንታይ ኤጂንግ ክሊኒክ›› የተባለው የጤና ተቋም ሥራ በጀመሩ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ያለማስጠንቀቂያ እንዲዘጋባቸው መደረጉን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ላቀረበላቸው ቅድመ ሁኔታ የአንድ ዓመት ጊዜ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም፣ ከስምንት ወራት በላይ ሊሰጣቸው እንደማይችል ገልጾ ክሊኒካቸው ሊዘጋ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡ ክሊኒኩ ፈቃድ ያወጣው አሜሪካ በሚገኙት የወይዘሮ ሰብለ አጋር በሆኑት ዶ/ር ስም በመሆኑ እየተመላለሱ እንዲሠሩ፣ ወይም የአንድ ዓመት ጊዜ ተሰጥቷቸው በአሜሪካ የሚያስፈልጉ ጣጣዎችን ጨራርሰው እስኪመጡ ክሊኒካቸው ከሚዘጋ፣ እስከዚያው ድረስ ተመጣጣኝ በሆኑ የሕክምና ባለሙያዎች ሥራውን ለማስኬድ እንዲፈቀድላቸው ያቀረቡት ጥያቄም ውድቅ እንደተደረገባቸው አስረድተዋል፡፡ እስካሁን አሥር ሚሊዮን ብር ከግል ሀብታቸው ኢንቨስት ማድረጋቸውንም ገልጸዋል፡፡ 

ከክሊኒኩ ባሻገር አቬላሜድ ቢዝነስ ቴክኖሎጂ የተሰኘ የመረጃና የትንተና ተቋም ለመመሥረት ሲንቀሳቀሱ ቢቆዩም፣ በገጠማቸው ውጣ ውረድ ሳቢያ እውን ሊያደርጉት እንዳልቻሉ የሚናገሩት ወይዘሮ ሰብለ፣ እስከቻሉት ጊዜ ድረስ ሞክረው የማይቻል ከሆነ ግን ወደ ኬንያ ሊወስዱት ወይም ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሊያቀኑ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ በአሜሪካ ሳይቀር ጥቂቶች ብቻ የሚገለገሉበት የዚህ ዓይነቱ ክሊኒክ ተፈላጊነቱ ከፍተኛ በመሆኑ፣ ጥያቄ እየቀረባለቸው እንደሚገኝም አስረድተዋል፡፡ 

በመድረኩ ለባለሥልጣናቱ ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል የፖለቲካ እስረኞችና በሃይማኖት ምክንያት የታሰሩ ካሉ እንዲፈቱ የሚለው ይገኝበታል፡፡ መንግሥት በፖለቲካና በሃይማኖት ምክንያት ያሰራቸው ሰዎች እንዳሉ እንሰማለን ያሉት ጥያቄ አቅራቢዎች፣ ምሕረት እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡ ከዚህ ባሻገርም ለዳያስፖራው ጥያቄዎች መፍትሔ ሊሆኑ ይችላሉ ከተባሉት መካከል የዳያስፖራ ልማት ባንክ እንዲቋቋም፣ ገለልተኛ የዳያስፖራ ኮሚሽን እንዲመሠረት፣ የዳያስፖራው አባላት በአክሲዮን መደራጀት የሚችሉበት ዕድል እንዲሰጥ የሚጠይቁት ይጠቀሳሉ፡፡ ዶ/ር ቴድሮስና አቶ አህመድ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችና ማስተካከያ ይደረግባቸዋል ስላሏቸው የመልካም አስተዳደር፣ የመንግሥት አገልግሎትና መሰል ጉዳዮች ላይ ማሻሸያ እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡ በፖለቲካና በሃይማኖት ጉዳይ ታሰሩ ስለተባሉት ሰዎች ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በቀጥታ ምላሽ ሳይሰጡበት አልፈዋል፡፡

ተደጋግመው ለባለሥልጣናቱ ከቀረቡት ችግሮች ባሻገር የዳያስፖራው መድረክ ለዶ/ር ቴድሮስ አፍቅሮት የታየበትም ነበር፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እንደ አንድ ታዋቂ አርቲስት ከፍተኛ ጭብጨባና ፉጨት ተስተጋብቶላቸዋል፡፡ ፎቶ አብረዋቸው እንዲነሱ የሚጠይቋቸውና ፊርማቸውን እንዲያኖሩላቸው የሚወተውቱም በርካቶች ነበሩ፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ ሎሬት ሰዓሊና ገጣሚ ገብረክስቶስ ደስታ ከደረሰው ስደት ተኮር ግጥም በመዋስ የመግቢያ ንግግራቸውን አሰምተዋል፡፡ አንጋፋው ድምፃዊ ዓሊ ቢራን በማጀብም አንጎራጉረዋል፡፡  

በሌላ በኩል ለአሥረኛ ጊዜ በተካሄደው ዓመታዊ የዳያስፖራ ኢንቨስተሮች ሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ፣ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ቢዝነስ ፎረም አምባሳደር ግርማ ብሩን ጨምሮ ሁለት ኢንቨስተሮችን ሸልሟል፡፡ ሐሙስ ነሐሴ 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ምሽቱን በሸራተን አዲስ በተካሄደ ሥነ ሥርዓት አምባሳደር ግርማ ብሩ ለዳያስፖራ ኢንቨስትመንትና የንግድ መስኮች ላበረከቱት ድጋፍ ‹‹የዓመቱ የቢዝነስ ሻምፒዮና›› ተብሎ የተሰመውን አምና በአሜሪካ የተጀመረውን የተቋሙን ሽልማት ከዶ/ር ቴድሮስ እጅ ተቀብለዋል፡፡ ዶ/ር አከዘ ጣዕመና አቶ ታምራት በቀለ በጤና ዘርፍ ባደረጉት ኢንቨስትመንትና አስተዋጽኦ ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ 

ዘንድሮ የልዩ አስተዋጽኦ ተሸላሚ እንደሚሆኑ ይፋ የተደረጉት በኢትዮጵያ የሕምክና አገልግሎት ዘርፍ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ ሁለት ባለሀብቶች ናቸው፡፡ ከቢዝነስ ፎረሙ በተገኘው መረጃ መሠረት በአሜሪካ ሲማሩና ሲሠሩ ቆይተው ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ኢንቨስት በማድረግ ትልልቅ የሕክምና ተቋማትን የሚያንቀሳቅሱት አቶ ታምራት በቀለና ዶክተር አከዛ ጣዕመ ናቸው፡፡

 አቶ ታምራት የኢንተርናሽናል ክሊኒካል ላብራቶሪስ እህት ኩባንያ ለሆነው ሜድፋርም ሆልዲንገስ አፍሪካ መሥራችና ዋና ሥራ አስፋጻሚ ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ. በ2004 ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ የላቦራቶሪውን ተቋም በአዲስ አበባ መሥርተዋል፡፡ በአፍሪካ ዓለም አቀፍ መሥፈርቶች የጤና ክብካቤ ዕውቅና በማግኘት የሚሠራ ተቋም ለመሆን የበቃ ላቦራቶሪ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በኢትዮጵያ ብቸኛው ፈቃድ ያገኘ ተቋም በመሆን የሚንቀሳቀሰው ይህ ላቦራቶሪ፣ ባለፉት አሥራ አንድ ዓመታት 900 ሺሕ ደንበኞችን ማፍራት መቻሉም የኩባንያው ዝክረ ታሪክ ይዘረዝራል፡፡ ባለትዳርና የአምስት ልጆች አባት የሆኑት አቶ ታምራት ኑሯቸው በአዲስ አበባ ካደረጉ ሰንብተዋል፡፡ 

ዶ/ር አከዛ በበኩላቸው የቅዱስ ያሬድ ጠቅላላ ሆስፒታልንና በቅርቡም አሜሪካን ሜዲካል ሴንተርን ከሸሪኮቻቸው ጋር በመመሥረት፣ በሜዲካል ዳይሬክተርነት እየሠሩ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በግል ሆስፒታሎች ማኅበር ፕሬዚዳንትነት ማገልገላቸውም ይታወቃል፡፡ የሦስት ልጆች አባት የሆኑት ዶ/ር አከዛና አጋሮቻቸው የመሠረቷቸው የሕክምና ተቋማት፣ በአዲስ አበባና በአጎራባች አካባቢዎች ለሚኖሩ አንድ መቶ ሺሕ ታካሚዎች አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በአሁኑ ወቅትም ግማሽ ቢሊዮን ብር በሚጠጋ ካፒታል የሜዲካል ቱሪዝም ይፈጥራል ያሉትን ዘመናዊ ሆስፒታል ለመገንባት እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ ባለፈው ዓመት አቶ አዲስ ዓለማየሁና አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ በአሜሪካ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ተሸላሚ እንደነበሩ ይታወሳል፡፡ 

 

 

 

ፖሊስ ዋና ተጠርጣሪ ያላቸውን አራት ሰዎች ከሷል

በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ሥር በምትገኘው የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ከከተማ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ፣ ሕገወጥ ግንባታዎችን ለማፍረስ የአረካ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በመሞከሩ ነዋሪዎች ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸው ታወቀ፡፡ 

የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የትውልድ ቦታ በሆነው የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዋና ከተማ አረካ ዙሪያ የሚገኙ ስድስት ቀበሌዎችን በከተማው ሥር ለማካለል፣ በሕገወጥ መንገድ ተገንብተዋል በተባሉ ከ940 በላይ ቤቶች ላይ ማዘጋጃ ቤት እንዲፈርሱ ሐሙስ ነሐሴ 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀለም መቀባት ጀምሮ ነበር፡፡ 

ነገር ግን ባለይዞታዎች የተገነቡትን ቤቶች በቀጥታ በከተማ ማካለሉ ውስጥ ማስገባት እየተቻለ ሊፈርስብን አይገባም በማለት በመቃወማቸው፣ በተጠቀሰው ዕለት ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ ግጭት መነሳቱን ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ 

ፖሊስ የተወሰኑ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ቢያውልም፣ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ በድጋሚ ከረር ያለ ግጭት ተከስቷል፡፡ 

በተለይም በሁለተኛው ግጭት ባለይዞታዎቹ ድንጋይ መወርወር በመጀመራቸው፣ ፖሊስም በድብደባ አፀፋ መመለሱ ተገልጿል፡፡ ከ20 በላይ ሲቪሎችና አሥር የሚሆኑ የአፍራሽ ግብረ ኃይል አባላት መጎዳታቸው ታውቋል፡፡

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኢዮብ ዋቴ የተነሳውን ግጭትም ሆነ የደረሱ ጉዳቶችን አረጋግጠው፣ የብጥብጡ ዋና ተጠያቂዎች በሕገወጥ መንገድ ቤት የገነቡ ሰዎችና የእነሱ ተባባሪ ደላሎች ናቸው በማለት ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ግጭት ለማነሳሳት ዋነኛ የተባሉ አራት ሰዎች ክስ ተመሥርቶባቸው የጊዜ ቀጠሮ እንደተጠየቀባቸውም አቶ ኢዮብ ገልጸዋል፡፡

የቤቶቹን ሕገወጥነት አስመልክቶ ዋና አስተዳዳሪው፣ ‹‹ሕገወጦቹ ከደላሎች ጋር በመሆን ስድስቱ ቀበሌዎች ወደ ከተማ እንደሚካለሉ እያወቁ በሕገወጥ መንገድ ቤቶቹን ገንብተዋል፤›› ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ቤቶቹን መገንባት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ በተደጋጋሚ ግለሰቦች ምንም ዓይነት ግንባታ እንዳያደርጉ የወረዳው አስተዳደር ማስጠንቀቁን አቶ ኢዮብ አስታውሰዋል፡፡ 

እሳቸው የታሰሩት ሰዎች አራት ብቻ ናቸው ቢሉም፣ ምንጮች ግን የታሳሪዎች ቁጥር እስከ 40 እንደሚደርስ ይናገራሉ፡፡ 

ነገር ግን አቶ ኢዮብ ብዛት ያላቸው ሰዎች መቁሰላቸውን አልሸሸጉም፡፡ በፖሊስ በኩልም ሁለት ፖሊሶች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸውም አክለው ገልጸዋል፡፡ 

የከተማ ማስፋፋት ፕሮግራሙን አስመልክተው በሶዶና በቦዲቲ ከተሞችም ተመሳሳይ የማካለል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን፣ ችግሩ ግን የተፈጠረው አረካ ላይ ብቻ እንደሆነ አቶ ኢዮብ አስረድተዋል፡፡ 

በዋነኛነት ግጭቱ በተፈጠረበት የአረካ ማስፋፊያ ፕሮግራም በከተማው ዙሪያ የሚገኙ ስድስት የቀበሌ ገበሬ ማኅበሮችን ለማካለል ታቅዶለታል፡፡ ነገር ግን ግጭቱ የተቀሰቀሰው ዱቦ፣ አቹራ፣ ዶላና ኡቶ በተባሉት አራቱ ቀበሌዎች መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡