በንግግር ሃሳቤን የመግለጽ ችሎታዬ በጣም ደካማ ስለሆነ አንዳንዴ እንደማንኛውም ሃገር ወዳድ የሚሰማኝን በወረቀት መሞነጫጨር እወዳለሁ። ሁሌ ለንባብ ባላበቃውም አልፎ ኣልፎ ሃሳቤን ለማውቃቸው አካፍዬ ልምድ ለመቀያየር፤ እርስ በርስ ለመማማር የተሻለ መንገድ ሆኖ አግኝቼዋለሁኝ። ታዲያ የዛሬ ዓምት ግድም እንደ አቅሜ ሃላፊነትን በመውሰድ …

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን በራሱ መንገድ ይጠብቃታል እኛም እንተባበረው !! ብስራት ኢብሳ (ከሆላንድ) Read more »

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 25/2010፤ ጥቅምት 15/2003 ዓ.ም):- የሐዋሳ ምእመናን የደረሰውን  በደልና ጥፋት የሚያሳይ ባለ 73 ገጽ የጽሑፍ ማስረጃ እና 6 የድምጽ እና የምስል (Audio and Video) ችግሩን ለማጣራት ወደ ቦታው ላቀናው ልዑክ አቀረቡ። አቤቱታ አቅራቢዎቹ ያቀረቡት ማስረጃ በደምሳሳው ሲታይ በሀ/ስብከቱ …

የሐዋሳ ምእመናን የደረሰውን በደል በማስረጃ አቀረቡ፤ አጣሪው ተልዕኮውን ፈጽሞ ተመልሷል Read more »

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 24/2010፤ ጥቅምት 14/2003 ዓ.ም):- “በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 ድንጋጌ መሠረት ከጥቅምት 12 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ” በመካሔድ ላይ የሚገኘው የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሊቀ መንበርነትና በብፁዕ አቡነ ሉቃስ ፀሐፊነት የተወከለው 9 አባላት ያሉት …

የቅ/ሲኖዶስ አጀንዳዎች Read more »

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 24/2010፤ ጥቅምት 14/2003 ዓ.ም):- የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ዋና ኃላፊ ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል “ደጀ ሰላም የተሰኘው ‘ድህረ ገጽ’ (ድረ ገጽ ለማለት መሆኑ ነው) … በማንነቴና በሃይማኖቴ ላይ ከባድ የግድያ ወንጀል” ስለፈፀመ “የሀገሪቱን ሕገ መንግሥት በመጠቀም …

ሰበር ዜና፦ አባ ሰረቀ ብርሃን ደጀ ሰላምን እና ማ/ቅዱሳንን ሊከሱ ነው Read more »

የኢትዮጵያ መንግሥት በለጋሾች የሚያገኘውን እርዳታ ተቃዋሚዎችን ለማፈን ይጠቀምበታል የሚል ክስ መስማት ከጀመሩበት ካለፈው ዓመት መጀመሪያ አንስቶ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፍ የልማት ኤጀንሲ (ዩኤስኤአይዲ) ተጨማሪ ተቆጣጠሪዎችን ከኬንያ አስመጥቶ የእርዳታውን ክፍፍል ይከታተል እንደነበረ በኢትዮጵያ የተልዕኮው ኃላፊ ቶማስ ስታል ገልፀዋል፡፡ ማእከሉ ዩናይትድ ስቴትስ የሆነው …

የHRWን ክሥ ትኩረት እንደሚሰጠው USAID አስታወቀ Read more »

አበራ ለማ ይድረስ ለሥነኪን ተጠባቢው አለማየሁ ታዬ – ታለህበት ይህች ሂሣዊ ንባብ አከል ማስታወሻዬ ትድረስህ። እንደ ተጋባዥ የሥነ ግጥም የኔታ ሁኜ፣ አንተ ደግሞ የ”ፍካታ የሥነ-ጽሑፍ ክበብ” ታሊባን* ሁነህ የዛሬ አሥራ ምናምን ዓመታት በፊት እንደተዋወቅን ከላክልኝ መልዕክት ተረድቻለሁ። የዘሩት በቅሎ፣ አሽቶ፣ …

ቆነጃጅት፣ ወይንና ቅኔ Read more »

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 24/2010፤ ጥቅምት 14/2003 ዓ.ም):- የሐዋሳውን ችግር ለመፍታት ቃል በተገባው መሠረት አጣሪ ኮሚቴው ሐዋሳ ከተማ ከገባ በኋላ ምእመናኑን ማነጋገሩን ትናንት ቅዳሜ ጀምሯል። የሊቀ ጳጳሱ ደጋፊዎች እና አቤቱታ አቅራቢዎች የየበኩላቸውን አቤቱታ ለአጣሪው ለማሰማት ሲሞክሩ መጯጯሆች ይሰሙ ነበር። ሁለቱም ቡድን በቅርብ …

አጣሪ ኮሚቴው በሐዋሳ Read more »

አቡነ ሳሙኤልን ከአ.አበባ ለማስነሣት የአ.አ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችና ፀሐፊዎች ፈረሙት ተብሎ ለአጀንዳነት የቀረበው ደብዳቤ ውድቅ ተደርጓል፤ (ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 24/2010፤ ጥቅምት 14/2003 ዓ.ም):- ቅ/ሲኖዶስ ትናንት ቅዳሜ ሁለተኛ ቀን ጉባዔውን ቀጥሎ ዘጠኝ አባላት ባሉት አጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴ ተዘጋጅቶ የቀረበለት የአጀንዳ ዝርዝር …

የቅ/ሲኖዶስ ሁለተኛ ቀን ውሎ Read more »

(በዳዊት ታዬ) ባለፈው ማክሰኞ ጥቅምት 9 ቀን 2003 ዓ.ም. በፓርላማ የመንግሥትን አቋም ያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፣ አገሪቱ የገጠማት የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ከሥርጭት ኋላቀርነት የመነጨ መሆኑን አስረድተዋል፡፡  

– ገንዘቡን ለማሰባሰብ የምርጫው ‹‹ኔትወርክ›› ሥራ ይጀምራል (በውድነህ ዘነበ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሁለት ዓመት የሥልጣን ቆይታ በኋላ የቀድሞውን የከተማውን ጊዜያዊ አስተዳደር ዱካ በመከተል፣ ከነዋሪው ሕዝብ 600 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ሀብት በማሰባሰብ የልማት ሥራዎችን ማካሄድ የሚያስችለውን አዲስ ዕቅድ ይፋ አደረገ፡፡

– ከ26,400 ተፈታኞች 6,600 ብቻ ናቸው ያለፉት (በታምሩ ጽጌ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ ኢንዱስትሪውን በሙያ ብቃት ምዘና ተግባራት ላይ በባለቤትነት እንዲሳተፍ አቅም መፍጠር ባለመቻሉ፣ ከባድ አደጋ እንደተጋረጠበት አስታወቀ፡፡ የቴክኒክና ሙያ ተማሪዎች ብቃት እንዲሁ ለአደጋ መጋለጡ …

የቴክኒክና ሙያ ተማሪዎች ብቃት አደጋ ውስጥ ነው Read more »

– አልሚዎች ቅሬታ አላቸው (በውድነህ ዘነበ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ባደረገው ስብሰባ፣ ለሪል ስቴት ልማት የወሰዱትን ቦታ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ የተጠቀሙ ባለሀብቶች ጉዳይ በጥልቀት ተመርምሮ ማስተማርያ በሚሆን መንገድ እንዲቀጡ ወሰነ፡፡

– ከቀረጥ ነፃ የገቡ መኪኖች በጉምሩክ ተይዘዋል (በኃይሌ ሙሉ) በአገር አቀፍ ደረጃ በተፈቀደው ብድር መሠረት የቻይና ስሪት የሆኑ ሲኖትራክ መኪኖችን ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ የተፈቀደላቸው ተቋራጮችና የትግራይ ቤቶች ልማት ኤጀንሲ የተፈራረሙት ውል የጉምሩክን ሕግ የሚጥስ ሆኖ ተገኘ፡፡

(በምሕረት ሞገስ) ካለፈው ዓመት ማብቂያ አንስቶ በአትክልት ዋጋ ላይ የተከሰተውን የዋጋ ንረት ተከትሎ ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ በአትክልት ተራ አላግባብ ዋጋ በመጨመር ላይ የተገኙ ሱቆች ላይ አስተዳደራዊ ዕርምጃ የመውሰድ ሥራ መጀመሩን አስተዳደሩ ለሪፖርተር ገለጸ፡፡

(በውድነህ ዘነበ) ላለፉት አሥርት ዓመታት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንግዶቿን ስትጋብዝ የቆየችበት የግብዣ አዳራሽ፣ የመሬት አስተዳደርና ግንባታ ፈቃድ ባለሥልጣን ቢሮ አድርጐ እንዲጠቀምበት ተሰጠው፡፡ አዳራሹ ለቢሮዎች በመሸንሸኑ የአዲስ አበባ አስተዳደር ሠራተኞች ቅሬታ አድሮባቸዋል፡፡

– ከ10 ሰዓት በኋላ እንዲሠሩ አማራጭ በአስተዳደሩ ቀርቦላቸዋል (በብርቱካን ፈንታ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቀደም ሲል በነበሩት ሁለት የአስተዳደር ወቅቶች ቦታና ፈቃድ እንዲሁም ብድር ተሰጥቷቸው ተደራጅተው ይሠሩ የነበሩ የአነስተኛና ጥቃቅን ነጋዴዎች ሕጋዊ አይደሉም በሚል ቦታቸውን ተነጠቁ፡፡

(በታምሩ ጽጌ) የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ በተጠረጠሩበት የ100 ሺሕ ብር የሙስና ወንጀል ክስ መስርቶባቸው የነበሩት የፌዴራል ፖሊስ ሕዝብ ግንኙነትና ጉዳዮች ኃላፊ ኮማንደር ደምሳሽ ኃይሉን፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ጥቅምት 12 ቀን 2003 ዓ.ም. …

የፌዴራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ከተከሰሱበት የሙስና ወንጀል በነፃ ተሰናበቱ Read more »

ምዕራፍ ብርሃኔ | ሪፖርተር በክረምት የትምህርት ክፍለ ጊዜ ለአራት ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በሐምሌ ወር 2002 ዓ.ም. የተመረቁ ተማሪዎች፣ ጊዜያዊ ዲግሪያቸውን ለመውሰድ ሲጠይቁ፣ ‹‹አልተመረቃችሁም›› በመባላቸው ቅሬታ እያሰሙ ነው፡፡ እንዳልተመረቁ የተነገራቸው ተማሪዎቹ የእንግሊዝኛን ቋንቋ ዓብይ፣ የኦሮሚኛን ቋንቋን ደግሞ …

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመረቁ ተማሪዎች ‹‹አልተመረቃችሁም›› ተባሉ Read more »

ደግ መመኘት መልካም ነገር ነው። የምፈልገውን ነገር ጠንቅቀን ማወቃችን እጅግ አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው። መድረሻችንን ማወቅ ያለብን ለጉዞ ከመነሳታችን በፊት ነው። አዎ! ግልጽ የሆነ ራዕይ ያለን መሆኑ ወሳኝ ነገር ነው። ይሁን እንጂ ራዕይ ወሳኝ ነገር ቢሆንም እንኳን ብቻውን ግን የትም …

ብሩህ ራዕያችንን በተግባራዊ እንቅስቃሴ እንደግፍ! Read more »

ዋና ፅ/ቤቱ ለንደን የሚገኘው ሂዩማን ራይትስ ዋች የተባለው ዓለምአቀፍ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ረቡዕ ጥቅምት 9 ቀን 2010 ዓ.ም. ባወጣው ሪፖርቱ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ከውጭ ለጋሾች የሚያገኙትን እርዳታ ከገዥው ፓርቲ ጋር ለማይስማሙት በመንፈግ በመደበኛነት እንደመሣሪያ ይጠቀምበታል ብሏል፡፡ የድርጅቱ መርማሪና ጉዳይ …

የመለስ መንግስት በ”አፈና” ተወቀሰ – VOA Read more »

ሲሣይ አጌና (ከአዲስ አበባ) ”ክቡር ጠ/ሚኒስትሩን እኛ አገር ብዙ ብዙ ልንላቸው እንችላለን። በሌላ ሀገር ያላቸው ክብር ግን እንደ አሸናፊ አትሌት ነው። በጂ 8 በለው፣ በጂ 20 ስብሰባ ላይ ሲገኙ ትልቅ ክብር ነው ያላቸው” – አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 22/2010፤ ጥቅምት 12/2003 ዓ.ም):- የሐዋሳውን ችግር ለመፍታት ቃል በተገባው መሠረት አጣሪ ኮሚቴው ዛሬ ሐዋሳ ከተማ ገብቷል። በ12 የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች እንዲሁም በሚኒ ባሶች እና የቤት መኪናዎች ተጭኖ የመጣው ቁጥሩ ከ700 በላይ የሚሆን የሐዋሳ እና አካባቢው ሕዝበ ክርስቲያን …

አጣሪ ኮሚቴው ወደ ሐዋሳ ተጉዟል Read more »

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 22/2010፤ ጥቅምት 12/2003 ዓ.ም):- የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በዛሬ ውሎው አጀንዳዎችን በመቅረጽ እና ዋና ዋና መነጋገሪያ ነጥቦች ሲያወጣ ውሏል። በቅዱስ ፓትርያርኩ በጽሑፍ በተዘጋጀ ንግግር የተጀመረው ይህ ጉባኤ ቅዱስነታቸው በሥራ አስፈጻሚ ጉባኤው እና በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ላይ ያላቸውን ቅሬታ …

የቅዱስ ሲኖዶስ የዛሬ ውሎ Read more »

(VOA) — የኢትዮዽያ መንግስት የቤቶችና የከተማ ልማት ሚንስትር የግል የግንባታ ኩባንያዎችን ለማጠናከር በሚል 70 ከመቶ ብድር በመስጠት ገልባጭ መኪኖችን ከቀረጥ ነፃ እንድያስገቡ ፈቅዷል። ይህም የተደረገው ኩባንያዎቹ የመንግስት የጋራ ቤቶችን (ኮንዶሚኒየም) እንዲሰሩ በሚል እንደሆነም ተገልጿል። በዚህ መሃል መንግስት የጋራ ቤቶች ግንባታ …

በመንግስት ብድር ለህንጻ ተቋራጮች የተገዙ የገልባጭ መኪናዎች ታገዱ – VOA Read more »

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 22/2010፤ ጥቅምት 12/2003 ዓ.ም):- ዛሬ የሚጀመረው የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ በብዙ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ መልካም ውሳኔዎች ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። ስለጉዳዩ የሚያጠኑ ደጀ ሰላማውያን እንደሚናገሩት ከሆነ፦ በአምናው ጉባዔ ላይ ወሳኝ መነጋገሪያ የነበረው የ“ሕገ ቤተ ክርስቲያን” ጉዳይ፤ ስለ “ቀኖና …

ቅዱስ ሲኖዶስ ስለምን ጉዳይ ይነጋገራል? Read more »

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 22/2010፤ ጥቅምት 12/2003 ዓ.ም):- የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ ዛሬ ሲጀመር አበው በፍቅር እና በሰላም ተወያይተው መልካም ውሳኔ ለመወሰን እንዲችሉ የሚያግባባ የሀገር ሽማግሌዎች ቡድን ጥረት ሲያካሂድ መቆየቱ ታውቋል። በአባቶች መካከል ያለው ልዩነት እንዲቀረፍ፣ ሰላምና እርቅ እንዲወርድ ሲሞክር የቆዩት ሽማግሌዎች …

የሀገር ሽማግሌዎች አባቶችን ለማስማማት ሲሞክሩ ቆይተዋል Read more »

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 22/2010፤ ጥቅምት 12/2003 ዓ.ም):- የቅ/ሲኖዶስ ጉባዔ ትናንት በጸሎተ ምሕላ ተጀምሯል። ቁጥራቸው ከ38 የማያንስ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በዚሁ የመክፈቻ የጸሎት ሥነ ሥርዓት ላይ ትምህርት የሰጡት ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ስለ ቅ/ሲኖዶስ የማይገሰስ መንፈሳዊ ሥልጣን በሰፊው አስተምረዋል። “ቅዱስ ሲኖዶስ …

የቅ/ሲኖዶስ መክፈቻ ጸሎተ ምሕላ እና የብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ትምህርት Read more »

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 22/2010፤ ጥቅምት 12/2003 ዓ.ም):- የቅ/ሲኖዶስ ጉባዔ ትናንት ሐሙስ በጸሎተ ምሕላ ከመጀመሩ አስቀድሞ ከአዋሳ የመጡ ከ700 ያላነሱ ሰዎች ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ከትሞ ውሏል። በ12 የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች እንዲሁም በሚኒ ባሶች እና የቤት መኪናዎች ተጭኖ የመጣው የሐዋሳው ሕዝበ …

የሐዋሳ ምእመናን ለ4ኛ ጊዜ ለአቤቱታ ወደ አዲስ አበባ መጡ Read more »

የኢትዮጵያ ሴቶች በጀግንነት፤ በቆራጥ ተጋድሎ፤ በብርቱ ሰራተኛነት፤ በችግር ጊዜ መላ በመምታትና የቤተሰቡን መሰረታዊ ህይወት በመምራት፣ የረጅም ዘመን ልምድና ታሪክ አልቸው። በዚህ ጉዳይ ቅዱስ መጽሃፍ ኢትዮጵያዊቷ ሲፖራ የባለቤቷን የታላቁን የእስራኤል መሪና ነብይ የሙሴን ህይወት ከሞት እንዴት ልታተርፍ እንደቻለች ያስረዳናል። የሆነውም እንዲህ …

ከታሪክ አሻራ ከሲፖራ እስከ ብርቱካን ሚደቅሳ – ከሄኖክ ታፈሰ Read more »

ታዋቂው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድን “ሂውማን ራይትስ ዋች” ማክሰኞ እለት ባወጣው ሪፖርት በኢትዮጵያውያን ስም ከምእራባውያን አገራት የሚሰበሰበው እርዳታ ለጭቆና እየዋለ ነው ሲል በዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ ላይ ከፍተኛ ወቀሳን ሰንዝሯል። አንድ መቶ አምስት ገጾች ያሉት እና “እድገት ያለነጻነት፡ እርዳታ በኢትዮጵያ …

ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ እርዳታን ለጭቆና እያዋለ ነው ሲል ሂውማን ራይትስ ዋች አወገዘ Read more »

በአውሮጳ ህብረት የወያኔ አምባሳደር የሆነው ብርሃኔ ገብረ ክርስቶስ ባለፈው ቅዳሜ ጥቅምት 6 ቀን 2003 አም የኢትዮጵያን አድስ አመት ለማክበር በሚል ሽፋን በቤልጅዬም እና አካባቢዋ የሚኖሩትን ኢትዮጵያዊያን በልዩ የግብዣ ጥሪ በመጋበዝ ኤ ሲፒ ሀውስ acp house በተባለው የአፍሮ ካረቢያን ህንጻ አዳራሽ …

በብራስልስ የሚገኘው የዘረኛው ወያኔ ኤምባሲ ወደ አንድ መቶ ለሚጠጉ ሆድ አደሮች ግብር ማብላቱ ታወቀ Read more »

ዘረኛው አምባገነን መለስ ዜናዊ በግንቦት 15 2002 የምርጫ ተውኔት አካሄዶ 99.6 በመቶ ማሸነፉን ካወጀ በኋላ፤ ባላፈው ወር አዲስ ካቢኔ እንዳዋቀረ ይታወሳል። ባለፉት ሃያ አመታት ቁልፍ የስልጣን መቀመጫዎችን በትግራይ ተወላጆች እጅ አኑሮ የቆየው ዘረኛ ስርአት፤ የሌላ ብሔር ሰዎችን ለይስሙላ ለሃላፊነት ቦታዎች …

በአዲሱ የወያኔ ካቢኔ እውነተኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ነው ተባለ Read more »

በወያኔ ቁንጪዎች አፈና ምክንያት ወደኢትዮጵያ የሚያደርገውን የሳተላይት ስርጭት ለጊዜው እንደተቋረጠበት የሚታወቀወ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን ኢሳት ፤ በውጪ አገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በኢንተርነት በሚያሰራጨው የስትሪሚንግ ቴለቪዥን አገልግሎት ባለፈው ቅዳሜ ባሰራጨው ዜና በግል ድርጅት ስም በጫት ንግድ ከተሰማሩት 7 ድርጅቶች አንዱ የወያኔው ቁንጮ …

የዘረኛው እና ፋሽስቱ መለስ ዜናዊ ባለቤት አዘብ መስፍን በጫት ንግድ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እንደምታገበስብስ ታወቀ Read more »

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ፓርቲ (ወይም ኦፌዴን) የስራ አስፈጻሚ አባል እና የሶሾ-ኢኮኖሚክ ደፓርትመንት ሃላፊ የነበሩት ዶ/ር ታመነ ለታ ለስደት መዳረጋቸውን “ኦሮሞ ፓርላመንታሪያንስ” የተባለ ድረ-ገጽ ዘግቧል። ከድረ-ገጹ ጋር ቃለመጠይቅ ያደረጉት ዶ/ር ታመነ ለምን እንደተሰደዱ ሲገልጹ፦ ምንም እንኳ የህጋዊ ፓርቲ አባል ቢሆኑም …

የኦፌዴን ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ አባል ለስደት መዳረጋቸው ታወቀ Read more »

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ታሪካዊው የቅዱስ ዮሴፍ መቃብር አርፈው የሚገኙ በሺሆች የሚቆጠሩ አጽሞች ተቆፍረው እየወጡ እና በጅምላ መቃብሮች ውስጥ እየተቀበሩ መሆኑን ዘገባዎች አመልክተዋል። አዲስ ፎርቹን የተባለው የእንግሊዝኛ ጋዜጣ እንደዘገበው፥ ባለፈው አመት የተመሰረተው እና የአዲስ አበባ ቋሚ የቀብር ቦታ ልማትና አስተዳደር …

በቅዱስ ዮሴፍ መቃብር ያረፉ አጽሞች መረበሽ አንዳንድ ኢትዮጵያውያንን አስቆጥቷል Read more »

በትውልድ ኢትዮጵያዊ እና በዜግነት ሳውዲ የሆነው ቢሊየነር ሼክ ሙሃመድ አላሙዲ ከፊሊፒንስ አገር የቀን ሰራተኞች ማስመጣቱን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ድርጅት – ኢሳት – ዘግቧል። ኢሳት የአዲስ አበባ ዘጋቢውን ጠቅሶ እንደዘገበው ሰራተኞቹ በመዲናይቱ በሚገኘው እና አራዳ ጊዮርጊስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ስራ ጀምረዋል። …

ሼክ ሙሃመድ አላሙዲ የቀን ሰራተኞችን ከውጭ አገራት ወደ ኢትዮጵያ እያስመጣ መሆኑ ተዘገበ Read more »

በወያኔ ቁጥጥር ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተቀማጭ ገንዘብ ቀውስ ጫፍ ላይ እንደሚገኝ ለአገዛዙ ቅርብ የሆነው ሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ አመልክቷል። ባንኩ በተቀማጭ ከያዘው 57 ቢሊዮን ብር ውስጥ ዘጠና በመቶ በላይ የሚሆነውን በብድር መስጠቱ እና ከዛም ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የተበደሩት …

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተቀማጭ ገንዘብ ቀውስ ጫፍ ላይ መሆኑ ታወቀ Read more »

እንደ እርዳታ ድርጅቶች ግምት በአለም ዙርያ 250.000 ያህል ህጻናት በዉትድርና ተሰማርተዉ ይገኛሉ። ባለፉት ሃያ አመታት በዩጋንዳ ብቻ 30.000 ህጻናት በዉትድርና ተግባር እንዲሰማሩ ታፍነዉ ተወስደዋል አልያም የወሲብ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።