ቅዱስ ሲኖዶስ ስለምን ጉዳይ ይነጋገራል?


(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 22/2010፤ ጥቅምት 12/2003 ዓ.ም):- ዛሬ የሚጀመረው የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ በብዙ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ መልካም ውሳኔዎች ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። ስለጉዳዩ የሚያጠኑ ደጀ ሰላማውያን እንደሚናገሩት ከሆነ፦
  1. በአምናው ጉባዔ ላይ ወሳኝ መነጋገሪያ የነበረው የ“ሕገ ቤተ ክርስቲያን” ጉዳይ፤
  2. ስለ “ቀኖና ቤተ ክርስቲያን” ማለትም ከቦሌው ሐውልት ጀምሮ በየጊዜ ስለሚጣሱ ቀኖናዎች ጉዳይ፤
  3. ከዚህ በፊት በቅ/ሲኖዶሱ ተሰይሞ ፓትርያርኩ ከሥራ ስላገዱት “የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ’ በድጋሚ ሥራ መጀመር ጉዳይ፤
  4. በቅርቡ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የተለያዩ እርከኖች ላይ ስለተሾሙት ባለ ሥልጣኖች ጉዳይ፤
  5. በፓትርያርኩ አቅራቢነት ይነሣል የሚባለው “የአዳዲስ ጳጳሳት ሹመት” ጉዳይ፤
  6. አሁንም በቅ/ፓትርያርኩ ለውይይት ይቀርባል የሚባለው ለፓትርያርኩ “እንደራሴ የመሾም” ጉዳይ፤
እነዚህ እና እነዚህን የመሳሰሉ ጉዳዮች ለውይይት ይቀርባሉ ተብሎ ይገመታል። ደጀ ሰላም ስለነዚህ አጀንዳዎች ማንነትና ምንነት የምታጠናቅረውን ዘገባ እንደደረሰልን ለማቅረብ እንሞክራለን። ተከታተሉን።