‹‹እኛን የማገድ ሥልጣን የላቸውም›› ዶ/ር ታዲዎስ ቦጋለ በብርቱካን ፈንታ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ለድርጅቱ ውስጣዊ ብጥብጥ መንስዔዎች ናቸው ያላቸውን 14 አባላቱን በፍርድ ቤት እንዲታገዱ ማድረጉን ትናንት በጽሕፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታወቀ፡፡

– ጅንአድ ከውጭ አገር ዕቃዎችን በገፍ ሊያስገባ ነው በውድነህ ዘነበ የንግድ ሚኒስቴር በገበያ ውስጥ የተፈጠረውን የሸቀጦች አቅርቦት ችግርን መፍታት ያስችላል ያለውን አዲስ ጥናት በሚቀጥለው ሳምንት ያጠናቅቃል፡፡

  በታምሩ ጽጌ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ሊቀመንበር ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ወደ ፓርቲያቸው ተመልሰው የዕለት ከዕለት ሥራቸውን ለማከናወን አሁን ብቃት እንደሌላቸው ለፓርቲው መግለጻቸውን፣ በቅርቡ ኢንጂነር ግዛቸው የተኩትና የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

በታምሩ ጽጌ ለም ሆቴል አካባቢና ከቀድሞው ኢምፔሪያል ሆቴል አለፍ ብሎ ባሉ የኖክ ነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች ላይ በተመሳሳይ ሰዓት የፈነዱ ፈንጂዎችን ማጥመዳቸው የተረጋገጠባቸውና ወንጀለኛ ሆነው በመገኘታቸው በከፍተኛው ፍርድ ቤት በሞት፣ በዕድሜ ልክና በዓመታት እንዲቀጡ የተወሰነባቸው አምስት ግለሰቦች ላይ ቅጣቱ እንዲፀና የፌዴራል …

በነዳጅ ማደያ ላይ ፈንጂ በመጣላቸው በሞት የተቀጡ ግለሰቦች ውሳኔ ፀና Read more »

በውድነህ ዘነበ ባሳለፍነው ሳምንት ቅዳሜ ዕለት በራሳቸው አነሳሽነት መርካቶ ላይ የተሰበሰቡ 800 የሚጠጉ መካከለኛ ነጋዴዎች መንግሥት ‹‹የአገሪቱን የንግድ እንቅስቃሴ ሥርዓት ለማስያዝ›› በሚል እየወሰደ ያለው አዲሱ ዕርምጃ ክፉኛ ችግር ውስጥ እየተከተታቸው መሆኑን ገለጹ፡፡

በሊቢያ የህዝብ አመፅ ይቃጣል ተብሎ ሳይታሰብ ፤ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ፣ተጀምሮ እንደቀጠለ ነው። ይሁንና በግብፅ የታየውን ቁጥብነት ያላንጸባረቁት የአገሪቱ የጦር አኤሮፕላኖችና ሄሊኮፕተሮች፣ ለተቃውሞ አደባባይ በወጣው ህዝባቸው ላይ መተኮሳቸው ከተዘገበ ወዲህ በዓለም ዙሪያ ፤

በሊቢያ ሰልፈኞች ላይ መንግስት የወሰደው እርምጃ በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ውግዘትን አስከትሏል። የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በሰው ልጅ ላይ የተፈጸመ ወንጀል ሊሆን ይችላል እያለ ነው። ቱርክ ለሊቢያ ባለስልጣናት ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ሰዳለች።

ሰሜን አፍሪቃንና የአረብ አገሮችን በየተራ በማዳረስ ላይ ያለው ኅዝባዊ ቁጣ፤ ከአራት አስርታት በላይ ያችን አገር በጠንካራ መዳፍ ተጭነው የገዙትን ፕሬዝዳንት ጋዳፊን ወንበር መነቅነቅ ይዟል። የጦር ኃይላቸውና ቅጥር ነብሰ ገዳዮች ለተቃውሞ በወጣው ሰልፈኛ ላይ እየተኮሱ መሆናቸው የተዘገበባት ሊቢያ መፍረክረክ የያዘች ትመስላለች። …

የሊቢያው ኅዝባዊ አመፅ ፈጣንና ያልተጠበቁ ውጤቶቹ። Read more »

ቤን አሊን፥ ከቱኒዝ፥ ሙባረክን ከካይሮ አሽቀንጥሮ የጣለዉ አዲሱ ሕዝባዊ አመፅ የአረቡን አለም እየናጠ በአዲስ ጎዳና እየዘወረዉም ነዉ። የፕሬዝዳንት ጆርጅ ደብሊዉ ቡሽና የጠቅላይ ሚንስትር ቶኒ ብሌሯ ዲሞክራሲያዊት ኢራቅም ከአዲሱ ሕዝባዊ ነዉጥ አላመለጠችም

“የአሁኑ የኢትዮጵያ መሪዎችና መልቲነት” በሚለው ጽሁፍ በአጠቃላይ መልቲዎች ምን ዐይነት ፀባይ እንደሚያራምዱ ለማሳያት ተመክሯል። በዚህ ፅሁፍ ደግሞ በፖለቲካ አመራር ላይ ያሉ መልቲዎች ምን አይነት ጸባይ አንደሚያሳዩና እነሱን እንዴት መዋጋት እንደሚቻል ለማሳየት እንሞክራለን። ከዚህ በፊት ለማሳየት እንደተሞከረው መልቲዎች እጅግ ቀዝቃዛ ስሜት …

መልቲዎችን እንዴት ማቸነፍ ይቻላል? በደጉ ማረው Read more »

በቱኒዚያ የተጀመረው የዓረብ አገሮች አብዮት ፕሬዚዳንት አል አቢዲን ቤን አሊን ለ23 ዓመት ከተቆናጠጡበት የሥልጣን ወንበራቸው አስነስቷቸዋል፡፡ አብዮቱ በግብፅ ቀጥሎ በታህሪር አደባባይ ለ18 ቀናት በተካሄደው ተቃውሞ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክን ለ30 ዓመታት ከተደላደሉበት የሥልጣን ወንበር አሰናብቷቸዋል፡፡ ይህ የዓረብ አገሮች አብዮት እንደ ወረርሽኝ …

መሪዎች ከዓረብ አገሮች አብዮት ምን ይማራሉ? Read more »

በዓረብ አገሮች የሠራተኞችን ጉዳይ የሚከታተል ተቋም ባለመኖሩ ችግሩ ተባብሷል በታምሩ ጽጌ ከኢትዮጵያ ወደ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኩዌት፣ ዱባይና የመን በሕገወጥ መንገድ የሚላኩ ኢትዮጵያውያን እየደረሰባቸው ያለውን ስቃይ፣ እንግልት፣ አካል መጉደልና ሞት ለመታደግ መንግሥት ከጎናቸው እንዲቆምና

– የኖርዌይ ልዕልትና የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ይመጣሉ በዳዊት ታዬ የኮንፈረንስ ቱሪዝም ፍሰት እያደገና አሁን ባለው ደረጃ ከአቅም በላይ እየሆነ በመምጣቱ፣ የኮንፈረንስ ቱሪዝምን ብቻ የሚመለከት መሥሪያ ቤት እንደሚቋቋም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አስታወቁ፡፡

በኃያል ዓለማየሁ በኢትዮጵያ ከተመሠረተ 50 ዓመታት ገደማ ያስቆጠረውን ሬስ ኢንጂነሪንግ ኩባንያ ሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ከወራት ድርድር በኋላ ሙሉ በሙሉ እንደገዛውና ከዚህ ወር ጀምሮም እንደተረከበው ታወቀ፡፡

በአስራት ሥዩም ባለፈው ሐምሌ ወር በኢትዮጵያ ንግድና ዘርፉ ማኅበራት ምክር ቤትና በቀድሞው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መካከል ስምምነት የተደረሰበት የጋራ የምክክር መድረክ የፊታችን ማክሰኞ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊካሄድ ነው፡፡

በምስራቅ አፍሪቃዊቱ ሀገር ዩጋንዳ ትናንት ምክር ቤታዊ እና ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ተካሄደ። በፕሬዚደንታዊው ምርጫ ሰባት የተቃዋሚ ወገን ዕጩዎች ዩጋንዳን ላለፉት ሀያ አምስት ዓመት በመሩት የስድሳ ስድስት ዓመቱ ፕሬዚደንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ አንጻር ተወዳድረዋል።

የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳድር ከሐዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ምእመናን ጋራ ተወያዩ ርእሰ መስተዳድሩ የገዳሙን አገልግሎት እና ጸጥታ የሚያውኩ  “ድንጋይ ወርዋሪዎችን” አስጠንቅቀዋል “ከአሁን በኋላ የማዳምጠው የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ አቡነ  ገብርኤልን ብቻ ነው፤ እሰር ካሉኝ አስራለሁ፤ ማናችሁም ከእርሳቸው ውሳኔ ውጭ መሆን …

የሐዋሳ ጉዳይ አጠቃላይ ሪፖርታዥ Read more »

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንዳስረዳው ባለፈው ሣምንት ስድስት በከባዱ የታጠቁ ፖሊሶች በትራፊክ በተጨናነቀችው መሃል አዲሳባ ውስጥ ከመኪናቸው ዱብ ዱብ ይላሉ። ወዲያው እያዋከቡና እያጣደፉ ወደ ማዕከላዊ ፖሊስ ለምርመራ ይወስዱታል። በምርመራ ማዕከሉ በታሠረባቸው ሁለት ሰዓታት ማንነታቸውን ካልገለፁት ምክትል የፖሊስ ኮሚሽነር ፊት ቀርቦ ማስጠንቀቂያ …

የሰሜን አፍሪካ ሕዝባዊ እንቅስቃሴና ኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛ Read more »

የአዋሳ ከተማ አስተዳደር በህገ ወጥ መንገድ የአርሶ አደር መሬት ገዝተው መኖሪ ቤትና የተለያዩ ግንባታዎችን ያከናወኑ ናቸው ባላቸው ሰዎች ላይ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ገልጿል። ከ1985 ጀምሮ በተለይ ዳቶ በተሰኘው አከባቢ መኖሪያ ቤት ሰርተው እየኖሩ እንደሆኑ የሚገልጹት ነዋሪዎች መንግስት ያለምንም አማራጭ ሊያፈናቅለን …

40 ሺህ የአዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ቤታችሁን ልቀቁ ተባሉ Read more »

በቦስተን ዩኒቨርሲቲ የፍሬዴሪክ ፓርዲ የጥናት ማዕከል ለህትመት በበቃውና የኢትዮጵያን ምርጥ ቡና የንግድ ምልክት ባለቤትነት ያረጋገጠውን ጥረት በምሳሌነት የተመለከተን አንድ ጥናት መነሻ በማድረግ የተጀመረ ውይይት ነው። አንድ የምርት ውጤት ቁሳዊ ይዞታው ከሚያስገኛቸው ቀጥተኛ ጠቀሜታዎች ባሻገር ሊገኙ የሚችሉትንና intangible values በመባል የሚታወቁትን፤ …

ውይይት፥ «ቡና የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት፥ ባህልና ልማት!» ክፍል ሁለት፤ Read more »

(መሀመድ ሰልማን) ወደ ዛላንበሳ የአዲግራቱ ወያላ “ዛላንበሳ! ዛላንበሳ! አሀደ ሰብ ዛላንበሳ!” እያለ ጮኾ ተጣራ፡፡ ስጠጋው ጊዜ “እተው እተው…ቀልጥፍ” አለኝ፡፡ ተሳፈርኩኝ፡፡ ከአዲግራት ወደ ዛላንበሳ ለመሄድ የ10 ብር ታክሲ መያዝ በቂ ነው፡፡ ሚኒባሱ እኔ ከተቀመጥኩበት የኋላ ወንበር ስር ኩልል ያለ ድምፅ የሚያወጣ …

ከአዲግራት እስከ ዛላንበሳ፤ ቁርጥራጭ ማስታወሻዎች (ክፍል ሁለት፤ የመጨረሻ) Read more »

“በሰሜን አፍሪቃ እና መካከለኛው ምሥራቅ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አብዮት ከሰሃራ በታች ወደ አሉ የአፍሪቃ አገሮች ይዳረሳል ወይስ አይዳረስም?” በሚል አፍሪካዊያን በየቦታው ክርክሮች ይዘዋል። ቤን ዓሊ ከቱኒዝያ እንደተባረረ ከፊል ግብፃዊያን ግብፅን ከቱኒዝያ የሚለዩዋት ነገሮች ላይ አጽንዖት እየሰጡ “ግብፅ ቱኒዝያ አይደለችምና እዚያ የሆነው …

የኢትዮጵያ ወጣቶች ከቱኒዝያና ግብፅ እኩያዎቻቸው ሊማሯቸው የሚገቡ ቁምነገሮች Read more »

Ethiopia Zare ረቡዕ የካቲት 9 ቀን 2003 ዓ.ም. Feb 17, 2011)፦ በኦጋዴን አካባቢ የሚደረገው የአማጽያን እንቅስቃሴ ከሚጠበቀው በላይ መንግስትን እንዳስጨነቀው በቅርቡ ይፋ የሆነው የአሜሪካ ሚስጥራዊ ሪፖርት አጋለጠ። በአዲስ አበባ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ዶናልድ ያማሞቶ በኖቬምበር 2007 በሚስጢር ያስተላለፉትን ዲፕሎማቲክ መልእክት ከትላንት በስቲያ (ፌብረርዋሪ …

የመለስ መንግስት በኦብነግ እንቅስቃሴ እንደተሸበረ ዊኪሊክስ አጋለጠ Read more »

ከአገራችን ባህል አኳያ በዳይና ተበዳይ ይቅር መባባል ይቅርታን መቀበል መስጠት የተለመደ ጥንታዊ ባህላችን ነዉ። ተበዳይ ለዘለቄታ አብሮ ለመኖር ቂም በቀልን ትቶ በዳይን ይቅር ብሎ በሽምግልና ችግርንም መፍታት ለአገር ልማት በጋራ ለመኖር እና ለመስራት ታላቅ መፍትሄ መሆኑ የሚታወቅ ነዉ።

ህዝባዊ አመጽ በግብፅና ቱኒዚያ ከተቀጣጠለበት ጊዜ አንስቶ ሁኔታዎች በቻይናም ሊገነፍሉ የደረሱ ይመስላል። አንድ ቻይናዊ ፖለቲከኛ ነገሮች በኛም ሀገር በቋፍ ላይ ነው ያሉት ሲሉ ገልፀዋል። በእርግጥ በግብፅና ቱኒዚያ የተከናወነው አይነት ህዝባዊ አመፅ በቻይናም ቢቀጣጠል ምን ይከሰት ይሆን?

(መሀመድ ሰልማን) አዲግራት ነው ያለሁት፡፡ 35 ኪሎ ሜትሮችን ወደ ሰሜን ፈቀቅ ብል ኤርትራ ገባሁ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱ በማይገባኝ መልኩ ጥሎብኝ አሥመራን እናፍቃታለሁ፡፡ አይቻት ግን አላውቅም፡፡ “የማያውቁት አገር እንዴት ይናፍቃል?!” አትበሉኝ፡፡ ተረቱ የማይሰራበት ጊዜ ካለስ? ናፍቆቴን በከፊል ለማስታገስ ወደ ድንበር መጠጋት …

ከአዲግራት እስከ ዛላንበሳ፤ ቁርጥራጭ ማስታወሻዎች (ክፍል አንድ) Read more »