የሐዋሳ ጉዳይ አጠቃላይ ሪፖርታዥ
- የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳድር ከሐዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ምእመናን ጋራ ተወያዩ
- ርእሰ መስተዳድሩ የገዳሙን አገልግሎት እና ጸጥታ የሚያውኩ “ድንጋይ ወርዋሪዎችን” አስጠንቅቀዋል
- “ከአሁን በኋላ የማዳምጠው የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤልን ብቻ ነው፤ እሰር ካሉኝ አስራለሁ፤ ማናችሁም ከእርሳቸው ውሳኔ ውጭ መሆን አትችሉም፡፡”(አቶ ሺፈራው ሽጉጤ)
- “ቤተ ክርስቲያን የአንድ ክልል አይደለችም፤ ዘረኝነትን ትቃወማለች፤ በዘረኝነት ልትታወክ አይገባም፡፡”(ብፁዕ አቡነ ገብርኤል)
- የርእሰ መስተዳድሩ አቀራርቦ የማወያየት ጥረት ፓትርያርኩን እና ጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ክፉኛ አስነቅፏቸዋል
(ደጀ ሰላም፤ ፌብሩዋሪ 19/2011፤ የካቲት 12/2003 ዓ.ም):- ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ ከማቅረብ ይልቅ “ጠጠር መወርወር” በሚመርጡ ሁከተኞች ላይ አስተዳደራቸው ርምጃ እንደሚወስድ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አስጠነቀቁ፡፡ “ፍላጎታችን ተስማምታችሁ አምልኮታችሁን እንድትፈጽሙ ነው፤ ማንኛውንም ተቃውሞ ተዋረዱን ጠብቆ በሰላማዊ መንገድ ማቅረብ ይቻላል፤ የአድማ ስብሰባ አይፈቀድም፤ ጠጠር እወረውራለሁ የሚል ካለ ጠባችን ከእርሱ ጋራ ነው፤ ለእርሱ የተዘጋጀ ስፍራ አለ – አቦስቶ! እዚያ ወስደን እናሳርፈዋለን!!” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ ሀገረ ስብከቱን በተመለከተ በመስተዳድሩ ዘንድ ተቀባይነት የሚኖረው እና ተፈጻሚነት የሚያገኘው የሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ውሳኔ ብቻ በመሆኑ ማናቸውም ወገኖች ከብፁዕነታቸው ውሳኔ ውጭ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ለተሰብሳቢዎቹ በአጽንዖት ተናግረዋል፡፡
(Read More ወደሚቀጥለው ገጽ ይዞራል . . . . .)
