ማክሰኞ ታህሳስ 10 ቀን 2004 ዓ.ም ፡- የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በሽብርተኝነት ወንጀል በከሰሳቸው 24 የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላት፣ የመብት ተሟጋቾችና ጋዜጠኞች ላይ በኢቲቪ አኬልዳማ ዶኩመንተሪ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ሰዎችን በዋና ምስክርነት አቀረበ፡፡ ብዙዎቹ መስካሪዎች በጭንቀትና በመርበትበት ሲናገሩ፣ አንዳንዶቹም ሲያለቅሱ ነበር። ዛሬ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ አርቲስት ደበበ እሸቱ 29ነኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክር ሆኖ ከፍተኛው ፍርድ […]

ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ የሚባል በዓለም ዙሪያ ህገ-ወጥ የገንዘብ ፍሰትን የሚመረምር ድርጅት እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ከ1993ዓም እስከ 2001 ዓም ወደ 12 ቢሊዮን ዶላር ከሃገር ሸሽቷል።

በአዲስ አበባ በተደረገዉ ታላቁ ሩጫ እንደ ወትሮው ሕዝቡ በሕወሃት/ኢሕአዴግ አገዛዝ ላይ ያለዉን ብሶት ምሬት ገለጸ። በሩጫዉ የተሳተፉ ቁጥራቸው እጅግ በጣም በርካታ የሆኑ ወጣቶች በተቀናጀና በተቀነባበረ መልኩ የተለያዩ ዜማዎችን ያሰሙ የነበረ ሲሆን፣ አቶ መለስ ዜናዊ የሙአመር ጋዳፊ እድል እንደሚገጥማቸዉ በመግልጽ ለእኝሁ አምባገነን መሪ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። ጋዳፊ የተመኩበት ሰራዊታቸዉና የደህንነት አባሎቻቸዉ በጥቅምና በገንዘብ የገዟቸዉ ባሪያዎቻ ከሕዝብ ቁጣ […]

ማክሰኞ ታህሳስ 10 ቀን 2004 ዓ.ም ፡- የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በሽብርተኝነት ወንጀል በከሰሳቸው 24 የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላት፣ የመብት ተሟጋቾችና ጋዜጠኞች ላይ በኢቲቪ አኬልዳማ ዶኩመንተሪ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ሰዎችን በዋና ምስክርነት አቀረበ፡፡ ብዙዎቹ መስካሪዎች በጭንቀትና በመርበትበት ሲናገሩ፣ አንዳንዶቹም ሲያለቅሱ ነበር። ዛሬ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ አርቲስት ደበበ እሸቱ 29ነኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክር ሆኖ ከፍተኛው ፍርድ […]

ሁልጊዜ የክፉዎች፣ ገፊዎች፣ የአመጸኞችና አስጨናቂዎች መዝገበ ታሪክ እያገለባበጥን ግድፈት፣ ክፋት፣ ሴረኝነትና አረመኔነት ማተት ብቻ ሳይሆን አንዳንድ ጊዜ ደግሞ (በተለይ በአሁን ሰዓት) ዓይን የማፍረጥና እጅ የመቆረጥ ያክል ቢያመንም፣ ባንፈልገውም የሚያስፈልገን፣ ጀሮአችን ይሰማው ዘንድ ባይወድም ነፍሳችን ማወቅ የሚገባትን፣ የሚበጀንና ህልማችንን እውን የሚያደርግ፣ የሚፈለገውንም ስፍራ የሚያደርሰን እስከሆነ ድረስ እርስ በርሳችን በግላጭ መነጋገሩ፤ ከዚህም አልፎ እንደሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም ሆነ […]

[email protected] የአንድነት ፓርቲ በቅርቡ ባደረገዉ ጠቅላላ ጉባዔው ፣ ዶር ነጋሶ ጊዳዳን የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል። ይህን አስመልክቶ አጭር አስተያየት የሰጠዉ አፍቃሪ ኢሕአዴጉ አይጋ ፎረም፣ የቅንጅት ነገር እንዳበቃለት ይናገራል። “With Gebru Asrat leading ARENA and Dr Negasso leading UDJ, MEDREK may finally shed its “tseguri hemeq” inherited from Kinjit! It will also mean EPRDF will have […]

ማንም የዳስሰው አይመስለኝም፡፡ የቀይ ባህር እና ህንድ ውቅያኖስ መጋጠሚያ Gulf of aden አሰቃቂ ጉዞ እና የሱማሊያውያኑን ኢሰብአዊ ድርጊት፣የእኛም በጉዞ ላይ የዘቀጠ ማንነት.የሚካተትበት ትረካ ነው፡፡ መሳፈሪያው ቦታ እስክንደርስ እና ለመሳፈር ባህሩ ጋር ስላለው ነገር ያለውን እንዝለለው፡፡ አሁን ምናቦትን አውሱኝ እና የትራንስፖርት ሳይከፍሉ እንጓዝ……. በጀልባው ላይ ያለው የመጫን ስርዓት ፣ወደ ጀልባ መጫኛው ቦታ ያለው ጉዞ ሁሉ በጣም […]

([email protected]) «የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የዲያስፖራ ረቂቅ ፖሊሲ» በሚል ርእስ፣ በኅዳር ወር 2004 ዓ.ም ፣ በኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የተዘጋጀ 24 ገጾችን የያዘ አንድ ሰነድ አነበብኩኝ። «የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ከትዉልድ ሀገሩ ጋር ያለዉን ትሥሥር በማጠናከር በአገሩ ልማት ሰላምና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ጠንካራ ተሳታፊ ሆኖ፣ ራሱን ጠቅሞ ትዉልድ አገሩንም በመጥቀም፣ በጋራ ለማደግ የሚያስችል አመቺ ሁኔታ መፍጠርና […]

አምረን እየታገልነው ያለው ወያኔ ራሳቸውን ጀግኖችና ምርጦች አድርገው በመውሰድ የሚኩራሩ፤ “የጀግንነታቸው” ምንጭ ደግሞ ዘራቸው እንደሆነ ከልብ ያመኑ የስነልቦና ችግር ያለባቸው ሰዎች ስብስብ ነው። እነዚህ ድውያን በውስጣቸው ባለው የትንሽነት ስሜት ምክንያት በአስተሳሰብም ሆነ በሙያ የሚበለጣቸውን ሰው ማዋረድና ማሰቃየት ያስደስታቸዋል። እነዚህ ሰዎች በሃብት እንጂ በመንፈስ አላደጉምና እራስን ከሌላው ጋር እኩል አድርጎ የማየት ብቃት እና ሆደሰፊነትን ማዳበር አልቻሉም:: […]

ሰሞኑን “የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ቀን” የሚል የማስመሰያ ስያሜ የተሰጠው ድግስ በመቀሌ ከተማ ተጥሎ ሲበላና ሲጨፈር ተከርሟል። ይህ ዓመታዊ ድግስ እንደ ነገሥታት ግብር ተገዢዎች ተገዢነታቸውን፤ ምስለኔዎች ደግሞ ታማኝነታቸውን ለገዢዎቻቸው የሚያረጋግጡበት መድረክ ነው። ይህ በዓል የትግራይ ገዢ ጉጅሌ በትግራይ ላይ ብቻ ሳይሆን በአማራም፣ በኦሮሞም፣ በሲዳማም፣ በወላይታም፣ በአፋርም፣ በሶማሊም፣ በጉራጌም፣ በሃድያም፣ በአንዋኝዋክም፣ … በሁሉ የኢትዮጵያ ማኅበረሰቦች ላይ ያለውን […]

በኑረዲን – ከመርካቶ አገራችን ኢትዮጵያን በረጂም ዘመን ታሪኳ ዉስጥ አያሌ ነገስታት፤ሁለት ፕሬዚዳንቶችና አንድ ጠ/ሚኒስትር መርተዋታል። የእነዚህ መሪዎች በህዝብ መወደድና እነሱ ለህዝብ ያላቸዉ ክብር እንደየመልካቸዉ ይለያያል ሆኖም ብዙዎቹ መሪዎቻችን ኃይለኝነታቸዉ እንዳለ ሆኖ ብዙ የሚወደድ ባህሪይ ነበራቸዉ። ከሞላ ጎደል ብዙዎቹ የቀድሞ መሪዎች አገራቸዉን የሚወዱና ከራሳቸዉ ጥቅምና ዝና ይልቅ የአገራቸዉን ክብርና አንድነት የሚያስቀድሙ ነበሩ። ዛሬ ያልተጣለ ዕጣ ወጥቶላቸዉ […]

ጃኒስ ዊንተር የተባሉት ጸሀፊ ደይሊ መቨሪክ በሚባለው የደቡብ አፍሪካ ጋዜጣ ባወጡት ጽሁፍ፣ በደርባን የተካሄደው ኮፕ 17 የአካባቢ ጥበቃ ጉባኤ፣ ድንቅ የተባለ ስምምነት አድርጓል። በጸሃፊዋ አመለካከት የስምምነቱ ዋና ድል ተብሎ የተቆጠረው ደግሞ፣ የአካባቢ ጥበቃ ለማካሄድ የተፈቀደው ገንዘብ ነው። የአፍሪካ ህብረት አምባገነኖች ዋና ተደራዳሪያቸው አድረገው ከ2 አመት ገደማ በፊት የሰየሙት ዘረኛውና አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በጉባኤው ላይ ለአካባቢ […]