በኢትዮጵያ የረሃብ መንስኤ ድርቅ ሳይሆን አምባገነናዊ መሪዎች ናቸው ተባለ
በኢትዮጵያ የሚከሰተው ተደጋጋሚ ረሃብ መንስኤ የዝናብ እጥረት ሳይሆን መሪዎች ናቸው ሲሉ ዊሊያም ኢስተርሊ የተባሉ ታዋቂ ኢኮኖሚስት ተናግረዋል። ሚስተር ኢስተርሊ “ዘ ዋል ስትሪት ጆርናል” ለተባለው ታዋቂ የአሜሪካ ጋዜጣ በፃፉት ጽሁፍ፥ “የአምባገነናዊ መሪዎቻቸውን ያህል ድርቅ ኢትዮጵያውያንን አልጎዳም” ብለዋል። ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ …