የጠ/ሚ መለስ ንግግርና የህዝብ አስተያየት

በትናንትናዉ ዕለት ስምንተኛ ጠቅላላ ጉባኤዉን ያካሄደዉ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ኢህአዴግ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በመጪዉ ዓመታት ፓርቲያቸዉ ያቀዳቸዉን የልማት ተግባራት አስመልክተዉ ሰፊ ንግግር አድርገዋል።