‹‹ችሎቱ ታሪካዊ ስህተት እየሰራ ነው›› አቶ ሀብታሙ አያሌው በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር አቶ ሀብታሙ አያሌው ነሀሴ 14/2007 ዓ.ም ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ከተከሰሰበት የሽብር ወንጀል ነጻ ነው በማለት ከእስር እንዲፈታ የሰጠው ትዕዛዝ ተከብሮ እንዲፈታ ትዕዛዝ እንዲሰጥለት ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ ተደርጓል፡፡ ዛሬ ነሀሴ 29/2007 ዓ.ም ልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ተረኛ […]

በአሜሪካ መንግስት ኦፊሳላዊ ድረ ገጽ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ አስተባባሪነት በዓለም ላይ ለተመረጡ 20 ሴት የፖለቲካ እስረኞች ለአንድ ወር የሚቆይ ዘመቻና ማስታወሻ ሊደረግላቸው ነው፡፡ ከ20ዎቹ ሴት የፖለቲካ እስረኞች መካከል ሦስቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፣ ሁሉም የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ናቸው፡፡ ከዛሬ 20 አመት በፊት ሴቶችን ለማብቃት፣ የጾታ እኩልነትን ለማስፈን እና የልጃ ገረዶችን ሰብዓዊ መብት ለማስጠበቅ የቤጂንግ መርሃ […]

የዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ውይይቱን በቡድናዊ አካሔድ የመቆጣጠር ሙከራ ተነቅቶበታል አማሳኞች ማኅበረ ቅዱሳንን በመወንጀል መሸፈን እንደማይችሉ ሚኒስትሩ አሳስበዋቸዋል “ስለ መልካም አስተዳደር ከሚደረሰው መግባባት በመነሣት መንግሥት ርምጃ ይወስዳል” ከአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ከማኅበረ ካህናት፣ ከሰባክያነ ወንጌል፣ ከሰንበት ት/ቤቶች ተወካዮች እና የሀገረ ስብከቱ አንድነት አመራሮች ጋር በተናጠል ሲወያይ የቆየው፣ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት የማጠቃለያ ውይይት ያካሒዳል፡፡ የመርሐ ግብሩን አስተባባሪዎች …

ዓባይ ፀሃየ ለሀ ወ ሓ ት ኢ ህ ኣ ደ ግ በሊቀመንበር በድርጅት ሃላፊነት እጅግ ብዙ ኣጃቢና የህወሓት ሎሌ ፓርቲዎች ፈጥረዋል:: በመንግስት መዋቅር በፈደራል ጉዳዮች በስኳር ኢንዱስትሪዎች በጠቅላይ ምኒስቴር አማካሪነት ሰርተዋል:: 40 ዓመት ሙሉ በስልጣን በነበሩበት ቡዙ ስራዎች ፈፅመዋል:: በተለይ በሀወሓት ኢህአደግ ስርኣት ውስጥ ዘርፈብዙ የመልካም ዓስተዳደር የፍትህ የሰብኣዊ ዲሞክራሲ መብቶች መጠበቅ ተጥሰዋል:: በ5 ዙር […]

ወደ እንግሊዝ ሃገር የሚያስኬዳቸውን ቪዛ ተከልክለው ወደዚያው ሊያደርጉት የነበረው ጉዞ የተስተጓጎለባቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ፕሮፌሰር መስፍን ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ መግባታቸውን በስፍራው የሚገኙ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታወቁ:: በቅርቡ ‘አዳፍኔ’ የተሰኘ ‘አወዛጋቢ’ መጽሐፍ ለንባብ ያበቁት እኚሁ ፕሮፌሰር ዛሬ ዋሽንግተን ዱሉስ ኤርፖርት ሲደርሱ ወዳጆቻቸው ሞቅ ያለ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታውቀዋል:: ፕሮፌሰር መስፍን በአሜሪካ ቆይታቸው አዲሱ መጽሓፋቸውን በዋሽንግተን ዲሲ […]

ከሰሞኑ የተቆሰቆሰዉን ጦርነት ለመከታተልና ለማጥራት በሚል የተንቀሳቀሱ የወያኔ አንጃ ወታደሮች ቡድን ጥቃት እየደረሰባቸዉ ይገኛሉ፡ ወያኔ በአዲግራትና ከማይ ጻይ ተወርዋሪ አየር መንደርደሪያ ሰፈሮች ባሻገር በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች እያለፈና እየዘለለ የሚደርስበትን ጥቃት ለማድበስበስ በየስፍራዉ የመከላከያ ሰራዊቱ ስልጠና ላይ ነዉና የተኩስ ድምጽ ብትሰሙም እንዳትደናገጡ እያለ ከባለፈዉ መጋቢት ወር አንስቶ ወረቀት እየለጤፈና እየደሰኮረ ይገኛል። አንድ ማንነቱን ሊገልጽ ያልፈለገ የወያኔ […]

ነኅሴ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለጋሽ አገራት በተለይም የእንግሊዝ መንግስት ሪፖርቱን ቢደብቀውም፣ የአውሮፓ ህብረት ፍርድ ቤት ሪፖርቱ ይፋ እንዲሆን ባዘዘው መሰረት ይፋ ሆኗል። ሰርቫይቫል ኢን ተርናሽናል ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፤ ጥናቱን ያከናወኑት -የኢትዮጵያ ዋነኛ እርዳታ ሰጪ የሆኑት ዩናይትድ ኪንግደም፣ዲ.ዔፍ አይ ዲ የተሰኘው የም እራባውያን ለጋሾች ቡድን ፣ የአሜሪካ የረድ ኤት ድርጅት የሆነው …

ነኅሴ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአፋር ክልል፣ ዞን አንድ፣ አሳይታ ወረዳ ዋሙሌ ቀበሌ፤ በአፋምቦ ወረዳ በአላሳቦሎና ሁመዱይታ ቀበሌ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የቴምር ዛፍ በልማት ስም ተጨፍጭፏል። በዚህም በዜጎች ላይ የሰብአዊና የዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰት ተፈጽሟል ሲል ሰመጉ በ138 ኛ መግለጫው አስታውቋል። የአፋር ክልል ከእንስሳት እርባታ በተጨማሪ ሌላው ትልቅ የገቢ ምንጩ …

ነኅሴ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ከ9 ሺ በላይ አባወራ አርሶ አደሮች የሚኖሩባቸው 8 የቀበሌ ገበሬ ማህበራትን ወደ ከተማ ለማካለል የከተማው ማዘጋጃ የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ በርካታ አርሶ አደሮች ለችግር ተጋልጠዋል። ሁን ቦላሬ፣ ኦፋጋን ደባ እና ኦፋሴሬ የሚባሉ ቀ/ገ/ ማህበራት በሚዋሰኑባት አንዲት ጎጥ ብቻ 380 ቤቶች መፍረሳቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች በጠቅላላ …

ነኅሴ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በመቀሌ ከተማ የተካሄደው የገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ጉባዔ መልካም አስተዳደርና ኪራይ ሰብሳቢነትን የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ ውሳኔ አሳልፎአል መባሉ የአዲስአበባን ነዋሪዎችን በማነጋገር ላይ ይገኛል፡፡ የግንባሩ ከፍተኛ አመሮች ጭምር በከፍተኛ ሙስናና ብልሹ አሰራር በመዘፈቅ መልካም አስተዳደር እንዳይሰፍን እንቅፋት በሆኑበት በዚሁ ወቅት ፣ እነዚሁ ወገኖች ቆዳቸውን ቀይረው የመልካም አስተዳደር …

ነኅሴ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በማላዊ እስር ቤቶች ከ300 በላይ ስደተኞች የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው አሁንም በማረሚያ ቤት ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህ እስረኞች ውስጥ አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸው ታውቋል። የተፈረደባቸውን የእስር ጊዜ ያጠናቀቁትን ወደ አገራቸው እንደሚላኩ የአገሪቱ ባለስልጣናት ቢያስታውቁም እስካሁን ድረስ በእስር ቤት ውስጥ መቆየታቸውን በመጥቀስ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ድርጊቱን እየኮነኑ ነው። የስደተኞች …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ከተለያዩ የሃገራት ወደ አዉሮጳ የሚፈልሰዉ ስደተኛ እጅግ በጨመረበት በአሁኑ ወቅት ከተለያዩ የአፍሪቃ ሃገራት የተሻለ ሕይወት ፍለጋ ወደ ደቡብ አፍሪቃ የሚሰደዱ አፍሪቃዉያን ቁጥርም ጨምሯል። በሳምንቱ መጀመርያ ወደ 100 የሚጠጉ ኢትዮጵያን በአንድ የጭነት ማመላለሻ ታጭቀዉ ወደ ደቡብ አፍሪቃ በማምራት ላይ ሳሉ በዛምቢያ ፖሊስ መያዛቸዉ ተዘግበዋል።

ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ኦሞ ዞን በሃመር ወረዳ በሃመር ብሄረሰብና በዞኑ ፖሊስ መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት ተከትሎ በአካባቢው የሰፈረው የአንድ ሻለቃ ጦር አባላት በርካቶቹ ኮብልለው በመጥፋታቸው ፣ ለወታደሮቹ መጥፋት ምክንያት ናቸው የተባሉ ሰዎች ተይዘው ታስረዋል። በመከላከያ ሰራዊቱ አባላት መካካል የሚታየው አለመተማማንና ልዩነት በመስፋቱ እርስ በርስ እስከመጋጨት ደርሰዋል። ከወር በፊት …

ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ፣ ታምራት ታንቱ ባጫ የተባለ ወጣት፣ ቤቱ ለሶስተኛ ጊዜ በመንግስት አፍራሽ ግብረሃይሎች መፍረሱን ተከትሎ፣ ራሱን ያጠፋ ሲሆን፣ ባለቤቱም ራሱዋን ስታ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ውስጥ ጸሎት እየተደረገላት ነው። ወጣት ታምራት ትናንት ነሃሴ 26 የቀብሩ ስነስርአት ተፈጽሟል። ሚሚ ባቴ የተባለች የአንድ ሳምንት መጫትም በላዩዋ ላይ …

ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአማራ ክልል ከምርጫ 2007 በፊት ህብረተሰቡ መሳሪያ እንዲታጠቅ በመፍቀድ ህጋዊ ያደረገውን የመሳሪያ ፈቃድ በመንጠቅ መሳሪያዎችን ለመሰብሰብ ስልቶችን እየቀየሰ መሆኑ ምንጮች ለኢሳት አስታውቀዋል፡፡ የክልሉ ሚሊሺያ ጽህፈት ቤት ህገወጥ የጦር መሳሪያ ህጋዊ ለማድረግ ምዝገባ ካካሄደ በኋላ የመሳሪያ ፍቃድ በመስጠት ህብረተሰቡ ራሱን እንዲከላከልበት መፍቀዱን ተከትሎ፣ ከአጎራባች ክልሎች በተለይም ከትግራይ …

ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መስተዳድሩ 221 አመራሮችንና 4 ሺ 100 ሰራተኞችን ገምግሞ ጥፋተኛ ብሎአቸዋል። ሰራተኞቹ በህግ ይጠየቃሉ ተብሎአል። ኢሳት የሰራተኞችን ግምገማ በተመለከተ ከወር በፊት ባቀረበው ዘገባ፣ አብዛኞቹ ሰራተኞች እና አመራሮች ዝቅተኛ ነጥብ እንደተሰጣቸውና ሊባረሩ እንደሚችሉ ገልጾ ነበር። በዚሁ ግምገማ ምክትል ከንቲባው አቶ አባተ ስጦታውም ዝቅተኛ የግምገማ ነጥብ የተሰጣቸው በመሆኑ፣ ከሚቀነሱት …

ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስደተኞቹን ጭኖ ሲጓዝ የነበረው ከባድ መኪና በናካንዳ የድንበር የፍተሻ ጣቢያ አቅራቢያ ፓሊስ የደረሰውን ጥቆማ ተከትሎ ተይዘዋል። ሕገወጥ ስደተኞችን በማዘዋወር ሲሰሩ የነበሩ ሶስት የዛንቢያ ዜጎችም አብረው ተይዘዋል። ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከአስር እስከ ሃምሳ ዓመት ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ ይገኛሉ። ስደተኞቹ በአሁኑ ወቅት በኳቤ የደኅንነት እስር ቤት ውስጥ እንደሚገኙና …

ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ ወኪል የሆኑት አምባሳደር ሳማንታ ፓወር ፣ በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ምክንያት የታሰሩ 20 ሴቶች እንዲፈቱ ዘመቻ ይጀምራሉ። ከ20 ዎቹ ሴት እስረኞች መካከል ብሌን መስፍን፣ ሜሮን አለማየሁና ንግስት ወንድይፍራው ከኢትዮጵያ፣ ዋንግ ያኑ፣ ጋዎ ያኑና ሊዩ ዚያ ከቻይና፣ ካጂያ ኢስማዮላ ከአዘርባጃን፣ አስቴር ዮሃንስ ከኤርትራ፣ ማትሉዩባ ካሚሎቫ …

የወያነ ጉጅሌ አገዛዝ በፈጠራ የአሸባሪነት ክስ አቅርቦባቸው በራሱ ችሎት እና አቃቢ ሕግ ሊፈርድባቸው ሲዘጋጅ አለም አቀፍ ጫና በመብዛቱ በነጻ እንዲፈቱ በካንጋሮው ፍርድ ቤት የተወሰነላቸው ሃብታሙ አያሌው እና አብርሃም ሰሎሞን እስካሁን እስር ቤቱ ያልፈታቸው ሲሆን ሀብታሙ አያሌውን ፍርድ ቤት ባዘዘው መሰረት …

በነጻ የተሰናበተው ሃብታሙ አያሌው ያልተፈታበት ጉዳይ ነገ በልደታ ችሎት ይታያል። Read more »

በባህርዳር ሁለት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታሰሩ • ‹‹ሲገረፉ ተባባሪያቸውን ይናገራሉ፡፡›› ፖሊስ በባህርዳር የሰማያዊ ፓርቲ የክልል ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ የነበሩት አቶ ወርቁ ጥላሁንና የፓርቲው አባል የሆኑት አቶ ሲሳይ ታፈረ መታሰራቸውን የፓርቲው የምዕራብ ጎጃም ዞን ፀኃፊ አቶ መልካሙ ታደለ ለነገረ ኢትዮጵያ …

በባህርዳር የሰማያዊ ፓርቲ የክልል ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ የነበሩት ታሰሩ:: Read more »

᎐ተከላከሉ ከተባሉት ተከሳሾች መካከል አራቱ ሴቶች በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ጠርቶት በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ወቅት ለእስር ተዳርገው ‹‹ስብሰባ በማወክና በማነሳሳት›› የተከሰሱት እነ ሚካኤል ያሬድ ለሦስተኛ ጊዜ መከላከያ ምስክሮቻቸውን አቅርበው የነበር ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ለጥቅምት 8/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶባቸዋል፡፡ ዛሬ ነሀሴ 28/2007 ዓ.ም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ […]

  የቀድሞው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወጣት ሀብታሙ አያሌውና ሌሎች የፖለቲካ አመራሮች የልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት ከተመሰረተባቸው ክስ በነፃ ካሰናበታቸው በኋላ ነገ በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተለይ ሀብታሙ አያሌው እንደሚቀርብ ባለቤቱ ወ/ሮ ቤተልሔም ገለፀች፡፡ ቤተልሔም እንደተናገረችው ባለቤቷ በነፃ እንዲሰናበት ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከወሰነ በኋላ ባልታወቀ ሁኔታ እስርቤቱ አለቅም ማለቱንና ላልተለቀቀበት አግባብ ምንም አይነት […]

እውነትን ውጠን ራሳችንን በማረም ከታሪክ ተጠያቂነት እንዳን::(ምንሊክ ሳልሳዊ)   …… ይጻፋል::…ይነገራል::…ይደሰኮራል::…ፕሮፓጋንዳው ተጣፍጦ ይቀርባል::..ራሳችን እናርም::ምን ጎደለ?የሚል ጠፋ::ተስፋ የተሰቀለ ዳቦ ከሆነ ለውጥ ሁሉ የጭብጨባ አሽኮለሌ ከሆነ ቆየ::ምንም ፈቀቅ የለም::ኑ እንዋቀስ:: ኑ እውነትን እንዋጥ:: ኑ እንገላልጠው::ባሌለ ነገር ላይ ባልተፈጠረ ነገር ላይ ባልተወረደ ጉዳይ …

እውነትን ውጠን ራሳችንን በማረም ከታሪክ ተጠያቂነት እንዳን::(ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

በሶማሊያ ሀገር ህይወታቸው እያለፈ ያሉ የኢትዮጵያ ወታደሮች ቁጥራቸው እየጨመረ ነው እየተላኩና ህይወታቸው እያለፈ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ወታደሮች ከቀን ወደ ቀን ቁጥራቸው እየጨመረ እንደሆነ ከተለያዩ ያገራችን አካባቢዎች የደረሰን መረጃ አስታወቀ.በሶማሊያ ሃገር እየሞቱ ያሉትን የኢትዮጵያ ወታደሮች ቁጥራቸው ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የሟቾቹ ቤተሰብ በየግዜው በቴለፎን መርዶ እየደረሳቸው እንደሆነ የገለፀው መረጃው በተለይም የኦሮሚያ ክልል ህዝብ ለምንድነው […]

ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ መታሰራቸውን ተቃወሙ

የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ የነበሩትና በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ወንድሙ ቢራቱ፣ ለፌዴራልና ለክልል መንግሥታት ገቢ ማድረግ የነበረባቸውን 500 ሚሊዮን ብር ለግል ጥቅማቸው አውለዋል የሚል ጥርጣሬ በመኖሩ ኦዲት እያስደረገ መሆኑን፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ለፍርድ ቤት ገለጸ፡፡

 

መርማሪ ቡድኑ ነሐሴ 22 ቀን 2007 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት ተጠርጣሪውን ይዞ ቀርቦ እንዳስረዳው፣ ተጠርጣሪው ለግል ጥቅማቸው አውለውታል ከተባለው 500 ሚሊዮን ብር በተጨማሪ፣ በራሳቸውና በቤተሰቦቻቸው ስም የሚገኙ የቦታዎችና የቤት ሰነዶችን በማሰባሰብ ለፎረንሲክ ምርመራ መላኩን ገልጿል፡፡ ያልተያዙ ግብረ አበሮችን አድኖ መያዝ፣ የስምንት ምስክሮችን ቃል መቀበልና ሌሎች የምርመራ ሥራዎች እንደሚቀሩት በመግለጽ፣ ፍርድ ቤቱ ለተጨማሪ ምርመራ የ14 ቀናት ጊዜ እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡ 

ተጠርጣሪው አቶ ወንድሙ በበኩላቸው ባቀረቡት መቃወሚያ እንደገለጹት፣ እሳቸው የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አባል ናቸው፡፡ በሕገ መንግሥቱ የተሰጣቸው ያለመከሰስ መብት ሳይነሳ ሕገ መንግሥቱ ተጥሶ መታሰራቸው አግባብ አለመሆኑን በመግለጽ የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅላቸው ጠይቀዋል፡፡ እሳቸው የክልል ባለሥልጣን በመሆናቸው የማሰርም ሆነ የመጠየቅ መብት ያለው የክልሉ መንግሥት እንጂ የፌዴራል መንግሥት አለመሆኑን በመግለጽ ተቃውመዋል፡፡ 

ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት መያዛቸው ሕገወጥ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ በተያዙበት ወቅት 22 ሺሕ ብርና መኪናቸው የት እንዳለ አለማወቃቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡ መርማሪ ቡድኑ በሰጠው ምላሽ ተጠርጣሪው ባቀረቡት ተቃውሞ ላይ ፍርድ ቤቱ ቀደም ባለው ችሎት ብይን የሰጠበት መሆኑን አስታውሷል፡፡ 

ፍርድ ቤቱም ተጠርጣሪው ፍርድ ቤት ቀርበው በነበሩ ጊዜ ተመሳሳይ ተቃውሞ አቅርበው ትዕዛዝ የተሰጠበት መሆኑን አስታውቋል፡፡ በድጋሚ እንደማይቀበልም ገልጾላቸዋል፡፡ መርማሪ ቡድኑ ምርመራውን በፍጥነት አከናውኖ እንዲያጠናቅቅ አሳስቦ፣ ለተጨማሪ ምርመራ አሥር ቀናት ፈቅዶለታል፡፡ 

 

በስምንት ግራም ቶሪየም 100 አመት ያህል መኪና ሊያስነዳ የሚችል ማዕድን አግኝቼያለሁ. ሃኪም ንጉሴ አሰፋ. “አገር አቀፍ የባህል መድኃኒትና የህክምና ቀን” በኢትዮጵያ የምግብ መድሃኒትንና የጤና እንክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ከአለም የጤናድርጅት ጋር በመተባበር ከትላንት በስቲያን በሃርመኒ ሆቴል ባካሄደው ስብሰባ ላይ ላለፉት ሃያ አመታት በባህል የህክምና ሙያ ላይ የቆዪት ሃኪም ንጉሴ አሰፋ ላለፋት 15 አመታት በቶሪየም ማዕድን […]

የፋብሪካው ሠራተኞች ሥጋታቸውን ገልጸዋል

ታዋቂው ነጋዴ ሐጂ በዳዳ ጫሊ ጅሩ ከፍተኛ ባለድርሻ የሆኑባቸው ድሬ ኢንዱስትሪዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ሞጆ ቆዳ ፋብሪካ አክሲዮን ማኅበር፣ ቦረን ሪል ስቴትና ድሬ ኃይላንድ አክሲዮን ማኅበር አክሲዮኖችን ለሦስተኛ ወገን እንዳይሸጡና እንዳይተላለፉ ታግደው እንዲቆዩ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ነሐሴ 13 ቀን 2007 ዓ.ም.  የሰጠውን ጨምሮ ውሳኔ በተለያዩ ጊዜያት በሰጠው ትዕዛዝ በወጋገን ባንክ፣ በአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በተለያዩ ቅርንጫፍ ባንኮች የተቀመጠ ገንዘብና አክሲዮንም ካለ ታግዶ እንዲቆይ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

የታዋቂው ነጋዴ ሐጂ በዳዳ አክሲዮኖችና ገንዘብ እንዲታገዱ ምክንያት የሆነው፣ ለ50 ዓመታት የትዳር አጋራቸው መሆናቸውን የገለጹት ወ/ሮ ልኬለሽ ያዴሳ ለፍርድ ቤት ባቀረቡት የፍች ጥያቄ ምክንያት ነው፡፡

ወ/ሮ ልኬለሽ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 81 መሠረት የፍች ውሳኔ እንዲሰጣቸው ያቀረቡት፣ ሐጂ በዳዳ ትዳራቸውን አክብረው መኖር ሲገባቸው ቤታቸውን ጥለው በመውጣት ከጋብቻ ውጪ ከሌላ ሰው ጋር መኖር መጀመራቸውን በመግለጽ መሆኑን ክሱ ያስረዳል፡፡

ሐጂ በዳዳ በራሳቸው፣ በባለቤታቸውና በአራት ልጆቻቸው በተቋቋመው 112.9 ሚሊዮን ብር ዋጋ ካለው ድሬ ኢንዱስትሪዎች አክሲዮኖች ውስጥ 86,580 አክሲዮን ወይም 86.5 ሚሊዮን ብር ድርሻ ያላቸው መሆኑን ሰነዶች ያስረዳሉ፡፡

ከፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ የገዙት ሞጆ ቆዳ ፋብሪካም ከ25 በላይ ባለአክሲዮኖች ያሉት ሲሆን፣ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው ሐጂ በዳዳ መሆናቸውን ሰነዶች ያስረዳሉ፡፡

ባለቤታቸው ባቀረቡት የፍች ጥያቄ ክስ ምክንያት የባንክ ገንዘባቸውና አክሲዮኖቻቸው የታገደባቸው ሐጂ በዳዳ፣ ለፍርድ ቤቱ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ 

ሐጂ በዳዳ ለፍርድ ቤቱ በሰጡት ምላሽ ከባለቤታቸው ጋር መስማማት ባለመቻላቸው ለ50 ዓመታት የጠበቁትን ትዳራቸውን ለመተው መገደዳቸውን ገልጸዋል፡፡ ከራሳቸው ይልቅ ለቤተሰባቸውና ለአገራቸው ዕድገትና ልማት በማሰብ ሁሉን ነገር ሆነው ፋብሪካዎች ማቋቋማቸውንና ከ1,200 በላይ ሠራተኞች እንዳሏቸው አስረድተዋል፡፡ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ ልዩ ልዩ ብድር እንዳለባቸውም ገልጸዋል፡፡ ፍች ለጠየቁት ባለቤታቸው በ2,310 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተገነባ መኖሪያ ቤትና ሦስት ሚሊዮን ብር በመስጠት ትዳራቸው ሳይፈርስ ለየብቻ እንዲኖሩ በማቀድ በሰላም እየኖሩ መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡ 

በሸሪዓ ሕግ መሠረት ሌላ ሰው በማግባት ልጆች ወልደው እየኖሩ መሆኑንና ከሳሽ ባለቤታቸውን ጨምሮ ሁሉም ሰው የሚያውቅ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በመሆኑም እንዲከፋፈሉና ትዳር እንዲፈርስ የተጠየቀው አግባብ ባለመሆኑ ክሱ ተሰርዞ እንዲሰናበቱ ጠይቀዋል፡፡ ሐጂ በዳዳ ባቀረቡት ሌላ አቤቱታ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የተለያዩ ዕዳዎች እንዳለባቸው በድጋሚ ጠቅሰው፣ በገቢና በወጪ ንግድ ላይ ተሰማርተው ለአገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እያስገቡ መሆኑን በመግለጽ፣ ፍርድ ቤቱ ወደ ክርክር እንዲገቡ የሚያደርግ ከሆነ ክርክሩ በዝግ እንዲሆን ፍርድ ቤቱን ጠይቀው ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ ግን አልተቀበላቸውም፡፡ 

ሐጂ በዳዳ በበኩላቸው በወ/ሮ ልኬለሽ ያዴሳ ስም በአዋሽ ኢንተርናሽል ባንክ የተቀመጠ ገንዘብ በአራዳ ሕንፃ ሁለተኛ ፎቅ ላይ ያለ የኤሌክትሮኒክስ መደብር፣ በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ሰዴን ሶዶ ወረዳ አሌ አበባን ቀበሌ የሚገኝ ንብረትና ድሬ ኢንዱስትሪዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ግቢ ውስጥ የሚገኝ መጋዘን ውስጥ ያለ ንብረት ታግዶ እንዲቆይ ጠይቀው፣ የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ዕግድ ጥሏል፡፡ 

በድርጅቶቹ ከፍተኛ ባለድርሻ ሐጂ በዳዳና የአክሲዮን ድርሻና የባንክ ባለቤት ሒሳብ ላይ ፍርድ ቤቶች የሚጥሉት ዕድግ እንዳስፈራቸው የሞጆ ቆዳ ፋብሪካ አክሲዮን ማኅበር መሠረታዊ ሠራተኞች ማኅበር  ገልጿል፡፡ ባለሀብቱ ፋብሪካውን ከገዙት በኋላ ውጤታማ እየሆነ እንደሚገኝ የገለጸው ማኅበሩ፣ 992 ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኛ በፋብሪካው መኖሩን ገልጾ፣ በተለይ በባንክ ሒሳብ ላይ ዕግድ በመጣሉ የላብ አደሩ ደመወዝ እንዴት እንደሚከፈል ሥጋት እንደገባው አመልክቷል፡፡ ችግሩ የፋብሪካ ሠራተኞቹ ብቻ ሳይሆን ከ5,000 በላይ የሚሆኑ ቤተሰቦቻቸውም ጭምር መሆኑን ጠቁመው፣ የሚመለከተው አካል ችግሩን በቀላሉ እንዲፈቱት እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት ለጥቅምት 3 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ 

  

 

 

ከአክሊሉ ወንድአፈረው የተለያዩ ድርጅቶች የወያኔ/ ኢህአዴግን መንግስት በትጥቅ ሀይል ለማስወገድ በአስመራ ስልጣን ከያዘው ሻቢያ ጋር መቀራረብና ተባብሮ መስራትን መርጠዋል። ይህን በተመለከተ ባንድ በኩል የወያኔ/ኢህአዴግን የግፍ ስርአት ለማስወገድ ከማንም ጋር ቢሆን ማበር አስፈልጊ ነው የሚሉ ሲኖሩ ሌሎች ደግሞ የወያኔን የግፍ ስርአት …

የኢሳያስ (የሻቢያ) ስታራተጂ፤ ኢትዮጰያን ለመታደግ ወይስ እንደገና ለመግደል? Read more »

የመኢአድ ፕሬዚዳንት በነፃ ተሰናበቱ

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት ከተፈረጀው የግንቦት ሰባት ድርጅት ጋር ለመቀላቀል ሲጓዙ በቁጥጥር ሥር ውለዋል ተብለው ክስ የተመሠረተባቸው አራት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ የምስክርነት ቃል ተሰጠ፡፡

የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ የመሠረተውን የሽብር ድርጊት ወንጀል ክስ እየመረመረ ለሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት ምስክሩን ያሰማው ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ነው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የተመሠረተባቸውን ክስ እንደማይቃወሙና ድርጊቱን መፈጸማቸውን በማመናቸው፣ ዓቃቤ ሕግ በክሱ የጠቀሰውን አንድ ምስክር አሰምቷል፡፡ 

የዓቃቤ ሕግ ምስክር ሆነው የቀረቡት ግለሰብ እሳቸውም የሰማያዊ ፓርቲ አባል እንደነበሩ አስታውቀው፣ የፓርቲው የተለያዩ ክፍሎች አመራሮች የነበሩትን ብርሃኑ ተክለ ያሬድ፣ እየሩሳሌም አስፋውንና ፍቅረ ማርያም አስማማውን የሚያውቋቸው በፓርቲው ውስጥ በነበሩበት ጊዜ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ተከሳሽ ብርሃኑና እየሩሳሌም የካቲት 12 ቀን 2007 ዓ.ም. ሰላማዊ ትግሉ እንደማያዋጣ ተነጋግረው ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ለመሄድ ሲንቀሳቀሱ ምስክሩም አብረው ባህር ዳር ድረስ መሄዳቸውን ተናግረዋል፡፡ 

ባህር ዳር እንደደረሱ እሳቸው (ምስክሩ) ሐሳባቸውን በመቀየር ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውን ያስረዱ ሲሆን፣ ተከሳሽ ብርሃኑ ‹‹ለምን ትመለሳለህ? ቢያንስ ጎንደር የምናገኘው ሰው ስላለ እሱን ካገኘህ በኋላ ትመለሳለህ፤›› ቢላቸውም ሳይስማሙ ቀርተው መመለሳቸውን ገልጸዋል፡፡ ‹‹በወቅቱ ስሜታዊ ሆኜ መወሰኔ አግባብ እንዳልሆነ ስለተረዳሁ ነው፤›› በማለት ‹‹ለምን ሐሳብህን ቀየርክ?›› ለሚለው መስቀለኛ ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ምስክር ለመሆን መገደድ አለመገደዳቸውን፣ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው፣ ታስረው እንደነበርና ግንቦት ሰባት ነፃ አውጪ ወይም አሸባሪ ድርጅት መሆኑን እንዲያስረዱ በተከሳሾቹ ሲጠየቁ ዓቃቤ ሕግ ተቃውሟል፡፡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀን ድርጅት መጠየቁ አግባብ አለመሆኑን ዓቃቤ ሕግ በማስረዳቱ፣ ፍርድ ቤቱም የተከሳሾቹ ጥያቄ እንዲታለፍ በይኗል፡፡ ምስክሩ በአራተኛ ተከሳሽ ደሴ ካህሳይ ላይ የምስክርነት ቃል አልሰጡም፡፡

ፍርድ ቤቱ ብይን ለመስጠት ለመስከረም 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ 

ይህ በዚህ እንዳለ አይኤስን ለመቃወም መንግሥት ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ጠርቶት በነበረው ሰላማዊ ሠልፍ ላይ የተፈጠረውን ብጥብጥ በማደራጀትና በመምራት ተጠርጥረው ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩት የመኢአድ (የቀድሞ) ሊቀመንበር  አቶ ማሙሸት አማረ በነፃ ተለቀዋል፡፡

ዓቃቤ ሕግ የመሠረተባቸውን ክስ ሲመረምር የከረመው የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት አቶ ማሙሸትን በነፃ ያሰናበታቸው፣ ሰላማዊ ሠልፉ በተደረገበት ዕለት እሳቸው ከምርጫ ቦርድ ጋር በነበረባቸው ክርክር ፍርድ ቤት መዋላቸውን የሚያስረዳ ሰነድ በማቅረባቸው ነው፡፡ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበባቸው ምስክሮች የሰጡት የምስክርነት ቃል የተጠና መሆኑን በመቃወም ጠበቃቸው ለፍርድ ቤት በማስረዳታቸውና ምስክሮቹም የተለያየና የማይገናኝ የምስክርነት ቃል መስጠታቸው ለአቶ ማሙሸት በነፃ መሰናበት ምክንያት ሆኗል፡፡

 

ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ኦሞ ዞን በሃመር ወረዳ በሃመር ብሄረሰብና በዞኑ ፖሊስ መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት ተከትሎ በአካባቢው የሰፈረው የአንድ ሻለቃ ጦር አባላት በርካቶቹ ኮብልለው በመጥፋታቸው ፣ ለወታደሮቹ መጥፋት ምክንያት ናቸው የተባሉ ሰዎች ተይዘው ታስረዋል። በመከላከያ ሰራዊቱ አባላት መካካል የሚታየው አለመተማማንና ልዩነት በመስፋቱ እርስ በርስ እስከመጋጨት ደርሰዋል። ከወር በፊት …

ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ፣ ታምራት ታንቱ ባጫ የተባለ ወጣት፣ ቤቱ ለሶስተኛ ጊዜ በመንግስት አፍራሽ ግብረሃይሎች መፍረሱን ተከትሎ፣ ራሱን ያጠፋ ሲሆን፣ ባለቤቱም ራሱዋን ስታ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ውስጥ ጸሎት እየተደረገላት ነው። ወጣት ታምራት ትናንት ነሃሴ 26 የቀብሩ ስነስርአት ተፈጽሟል። ሚሚ ባቴ የተባለች የአንድ ሳምንት መጫትም በላዩዋ ላይ …

ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአማራ ክልል ከምርጫ 2007 በፊት ህብረተሰቡ መሳሪያ እንዲታጠቅ በመፍቀድ ህጋዊ ያደረገውን የመሳሪያ ፈቃድ በመንጠቅ መሳሪያዎችን ለመሰብሰብ ስልቶችን እየቀየሰ መሆኑ ምንጮች ለኢሳት አስታውቀዋል፡፡ የክልሉ ሚሊሺያ ጽህፈት ቤት ህገወጥ የጦር መሳሪያ ህጋዊ ለማድረግ ምዝገባ ካካሄደ በኋላ የመሳሪያ ፍቃድ በመስጠት ህብረተሰቡ ራሱን እንዲከላከልበት መፍቀዱን ተከትሎ፣ ከአጎራባች ክልሎች በተለይም ከትግራይ …

ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መስተዳድሩ 221 አመራሮችንና 4 ሺ 100 ሰራተኞችን ገምግሞ ጥፋተኛ ብሎአቸዋል። ሰራተኞቹ በህግ ይጠየቃሉ ተብሎአል። ኢሳት የሰራተኞችን ግምገማ በተመለከተ ከወር በፊት ባቀረበው ዘገባ፣ አብዛኞቹ ሰራተኞች እና አመራሮች ዝቅተኛ ነጥብ እንደተሰጣቸውና ሊባረሩ እንደሚችሉ ገልጾ ነበር። በዚሁ ግምገማ ምክትል ከንቲባው አቶ አባተ ስጦታውም ዝቅተኛ የግምገማ ነጥብ የተሰጣቸው በመሆኑ፣ ከሚቀነሱት …

ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስደተኞቹን ጭኖ ሲጓዝ የነበረው ከባድ መኪና በናካንዳ የድንበር የፍተሻ ጣቢያ አቅራቢያ ፓሊስ የደረሰውን ጥቆማ ተከትሎ ተይዘዋል። ሕገወጥ ስደተኞችን በማዘዋወር ሲሰሩ የነበሩ ሶስት የዛንቢያ ዜጎችም አብረው ተይዘዋል። ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከአስር እስከ ሃምሳ ዓመት ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ ይገኛሉ። ስደተኞቹ በአሁኑ ወቅት በኳቤ የደኅንነት እስር ቤት ውስጥ እንደሚገኙና …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ ወኪል የሆኑት አምባሳደር ሳማንታ ፓወር ፣ በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ምክንያት የታሰሩ 20 ሴቶች እንዲፈቱ ዘመቻ ይጀምራሉ። ከ20 ዎቹ ሴት እስረኞች መካከል ብሌን መስፍን፣ ሜሮን አለማየሁና ንግስት ወንድይፍራው ከኢትዮጵያ፣ ዋንግ ያኑ፣ ጋዎ ያኑና ሊዩ ዚያ ከቻይና፣ ካጂያ ኢስማዮላ ከአዘርባጃን፣ አስቴር ዮሃንስ ከኤርትራ፣ ማትሉዩባ ካሚሎቫ …

አብዛኛው ሰው በሀገሩ ኑሮ ሲጠበው፣ በሀገሩ ሰላም ሲያጣ ፣ በሀገሩ ነገሮች አልሆኑለት ሲሉ ራሱን ሊለውጥ አለያም ይደርስብኛል ሲል የሚሰጋበት ሰብአዊ መብት ረገጣ ሽሽት ወደስደት ይወጣል። አንዳንዱ እድለኛ ታስጠልለኛለች ብሎ ያላት ምድር ስቃ ትቀበለዋለች አንዳንዱን ደግሞ ህይወቱ የባሰ ቅጥአንባሩ ይጠፋውና ምነው በዚያው የሀገሬ ጅብ በበላኝ ሲል ይማረራል ለአንዳንዶች ግን ያስጠልለናል ካሉት ቦታ ሳይደርሱ በመንገድ ይቀራሉ! አንዱ […]

ባደጉት አገሮች የቴክኖሎጂ ውጤቶችና የሳይንስ ትሩፋቶች የሰው ልጅን የዕለት ተለት የኑሮ እንቅስቃሴ እየለወጡት ነው። ኡበር የተሰኘ የተንቀሳቃሽ ስልክ አፕልኬሽን የታክሲ አገልግሎት ከፍተኛ ተቀባይነት ቢያገኝም በተለምዷዊው ስርዓት አገልግሎት አቅራቢዎች ግን ከፍተኛ ትችት ሲሰነዘርበት ይደመጣል።

ሰበር መረጃ “ዛሬ ጠዋት አርበኞች ግንቦት ሰባት ባሳቻ በሰነዘረው ጥቃት ስፍር ቁጥር የሌለው የወያኔ ጋሻጃግሬዎች ሲደመሰሱ ገሚሱ ትግራይ ቦርደር ሆስፒታል እየተባለ ወደ ሚጠራዉ የህክምና ተቋም ቁስለኛ ወታደሮች ለህክምና ሲትም መዋሉን ከስፍራው ያይን ምስክር በተለይም ለ አፈትላኪ ዜና ምንጭ ዘግይቶ አድርሶናል። ይህበንዲህ እንዳለ ማይ ጻይ እየተባለ ከሚጠራዉ አካባቢ የሚነሱ ሄሊኮፍተሮች በአየር መቃወሚያ ወሰን ኢላማ ዉስጥ ገብተዋል።በተያያዘም […]

ወያኔ በመቶወቹ የሚቆጠሩ የ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙህራንን ጠራርጎ ካበረና በካደሬ ከሞላው ጀምሮ ዩኒቨርስቲው በሙስና ከመጨማለቁና የካድሬ መፈንጫ ከመሆኑ ባሻገር ወያኔ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ ኦዲት ተደርጎ የማይታወቅ ሲሆን ከሰሞኑ ደግሞ የዩኒቨርስቲው ዶርሚተሪወች ወደ ግለሰቦች መኖርያና ክራይ እየተቀየሩ ስለመሆኑ ውስጥ አወቅ ምንጮች ዘግበዋል።ይህ በንዲህ እንዳለ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አድማሱ ፀጋየና ምክትላቸው ዶ/ር ጄሉ ኦመር ከሀገር መውጣታቸውን […]

– የኢትዮጵያ ድርቅና ረሃብ አሳሳቢ ሆኗል :: – ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የሚደረገው ግድያ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል :: – ኢትዮጵያ በዋጋ ግሽበት ቀዳሚ ቦታ ይዛለች :: – አልሸባብ በሱማሊያ ውስጥ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል የጦር ካምፕን አጠቃ :: – የኢቦላ …

የኢትዮጵያ‬ ድርቅና ረሃብ … ባልታወቁ ሰዎች የሚደረገው ግድያ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል::(ፍኖተ ዴሞክራሲ) Read more »

አዳማ ከተማ በግራፊቲ ጹሁፍ ተጠለቅልቃ ማደሯን ምንጮች ከስፍራው ገለጹ::#Ethiopia #MinilikSalsawi አዳማ ከተማ በኮሚቴዎቹ ላይ የፈረደውን ኢህአዴግን በሚያሳስቡ በሚያስጠነቅቁ የግሬቪቲ ፅሁፎች ተፅፈው ማደራቸውን የቢቢኤን ምንጮች ገለፁ::በዛሬው እለት በአዳማ ከተማ ተፅፈው ካደሩት መካከል የተቀበረች ፍትህ ቀባሪዋን ትቀብራለች፣ ፍትህ ለኮሚቴው፣ ትግላችን ይቀጥልል ፣ …

አዳማ ከተማ በግራፊቲ ጹሁፍ ተጠለቅልቃ ማደሯን ምንጮች ከስፍራው ገለጹ:: Read more »

ነኅሴ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርቁ ባስከተለው ጉዳት ምክንያት የሚመገቡት ባለመኖሩ አብዛኛው ወጣቶች ወደ ጠረፍ ከተማ በመሰደድ ላይ ናቸው። በሰሜን ወሎና ዋግ ኽምራ ዞን ያሉ ነዋሪዎች በድርቁ ምክንያት እንስሳት አልቀዋል፤ መሬት የሌላቸው ወጣቶች የቀን ስራ በመስራት ቤተሰቦቻቸውን ለማገዝ ምግብ ፍለጋ ወደ ጠረፍ ከተማ እየተሰደዱ ነው። መሬት የሌላችው ወጣቶች በየአካባቢያቸው መሬት ተከራይተው …

ነኅሴ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰማያዊ ፓርቲ የአመራር አባል የሆኑት አቶ ጌትነት በሱፈቃድ በወላይታ ዞን ቦሎቶሶሬ ወረዳ አረካ ከተማ ላይ ተደብድበው መዘረፋቸውን ተናግረዋል፡፡ አቶ ጌትነት የሰማያዊን ጠቅላላ ጉባኤ ተሳትፈው ሲመለሱ ነሃሴ 20/2007 ዓ.ም አረካ ላይ ተደብድበው ስልካቸውንና የአንገት ሀብላቸውን ተቀምተዋል። የቀማቸው ሰው እጅ ከፍንጅ ቢያዝም ፖሊስ እርሳቸውን አስሮ ወንጀሉን የፈፀመውን ሰው …

ነኅሴ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማንነትና ከአስተዳደር መብት ጋር በተያያዘ ለአመታት የዘለቀው የቁጫ ህዝብ ጥያቄ፣ ምላሽ ባላገኘበት ሁኔታ፣ አሁንም የሚታሰሩ ሰዎች መኖራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ከ140 በላይ የአካባቢው የአገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ካለፉት ሁለት አመታ ጀምሮ በእስር ላይ ናቸው። ይሁን እንጅ ሰሞኑን ሌሎች የመንግስት ሰራተኞችም መታሰራቸውን ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የአካባቢው ተወላጆች ለኢሳት …

ነኅሴ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊያ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም አስከባሪ ጦር አሚሶም ስር የዘመተው የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ሰራዊት በመሃከላዊ ሶማሊያ በገልጋዱ ግዛት ውስጥ አራት ንፁሃን የሶማሊያ ዜጎችን በግፍ መግደሉንና ከሟቾቹ ውስጥ ሁለቱ መምህራን መሆናቸው ተገልጿል። ”በአካባቢያችን በኢትዮጵያ ታጣቂዎች እንደዚህ ዓይነት አስቀያሚ እርምጃዎች እየተወሰዱብን እኛ ከዚህ በላይ ልንታገስ አይገባንም።ይቅርታ ልናደርግላቸውም አይገባንም።ካለርህራሄ አራት …

ሠላማዊ ትግል ስንል? በፍቃዱ ዘ ኃይሉ / Zone 9………. ሠላማዊ ትግል ደርዘ ብዙ ትንቅንቅ ነው፡፡ አንዳንዶች ‹ሕጋዊ መንገዶችን ብቻ መጠቀም ነው› ብለው የምናሉ፤ ነገር ግን በዚህ የማይወሰንበት ጊዜአለ፡፡ ሠላማዊ ትግል ከነፍስ ማጥፋት፣ አካላዊ ጉዳት ከማድረስ እና ንብረት ከማውደም መቆጠብን ብቻ …

ሠላማዊ ትግል ስንል? በፍቃዱ ዘ ኃይሉ Read more »