ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አሳይቷል በዘንድሮ የአዲስ አመት ገበያ፣ የዶሮ ዋጋ ከበፊቱ በእጥፍ የጨመረ ሲሆን በአቃቂና በሳሪስ አካባቢ ዶሮ ከ200 ብር እስከ 400 ብር የሚሸጥ ሲሆን፤ በግ ከ1100 እስከ 3500 ብር፣ በሬ ከ4500 እስከ 25ሺ ብር፣ ፍየል ከ750 እስከ 4ሺ ብር እየተሸጡ ነው፡፡ በሾላ ገበያ በግ ከ900 ብር እስከ 4500 ብር፣ …

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል ባጠናው ጥናት ከአዋሳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ የሚወጣው ኬሚካል ሃይቁንና ወንዙን በመበከሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ህይወት አደጋ ላይ ወድቋል። ከፋብሪካው የሚወጣው ውሃ በቀጥታ ወደ ጥቁር ውሃ ወንዝ የሚፈስ ሲሆን፣ ወንዙም ወደ ሃይቁ የሚፈስ በመሆኑ ተጨማሪ ስጋት ፈጥሯል። የኬሚካሉ ወደ ውሃው መግባት የአሳዎችን ስደት እንደሚያስከትል የሚገልጸው …

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመጪው መስከረም ወር 2008 መቶ በመቶ በኢህአዴግና አጋሮቹ በተያዘው ፓርላማ ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ሁለተኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ይፋ ለማድረግ በሚል በእነሠራዊት ፍቅሬ እና ሽዋፈራው ደሳለኝ አጋፋሪነት ከምሽቱ 3 ሰዓት ጅምሮ በሚሌኒየም አዳራሽ ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሚገኙበት ታላቅ የፌሽታ በዓል ተዘጋጅቷል፡፡ እነሠራዊት ፍቅሬ …

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከባህርዳር እስረኞችን ጭኖ አዲስ አበባ ወደሚገኘው ማእከላዊ እስር ቤት በመጓዝ ላይ ያለ ሚኒባስ ታክሲ ፣ ማለዳ 1 ሰአት ተኩል አካባቢ ሾላ ሰሜን ሆቴል ወይም መቀጠያ ሃበሻ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ሲደርስ ፣ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በመቆሙ በውስጡ ከነበሩት 13 እስረኞች መካከል 6ቱ ከመኪናው በመውረድ አምልጠዋል። የተቀሩት ከሚኒባስ ባለመውረዳቸው …

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በተጠለሉባቸው የስደተኞች መጠለያዎች ውስጥ የተቀሰቀሰው የኮሌራ ወረሽኝ በአጎራባች የደቡብ ሱዳንና የኢትዮጵያ ድንበሮች አካባቢ ስጋት እየፈጠረ ነው። ይህንን ተላላፊ ገዳይ በሽታ ለመግታት የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅትና ዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን በጥምረት ክትባትና የንጹህ ውሃ አገልግሎት አቅርቦት መስጠት ጀምረዋል።በአስር የስደተኞች መጠለያ …

ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ → * Ethiopian Int’l Conference in Washington DC 26 Sept 2015 * Letter of Appeal to Pope Francis I

ከትናንት ሐሙስ አንስቶ ለ 10 ቀናት የሚዘልቅ የፎቶ አውደ ርዕይ ዩናይትድ ስቴትስ- ኒው ዮርክ ከተማ ተከፍቷል። በዚህም አውደ ርዕይ ላይ የ11 ወጣት ኢትዮጵያውያን የፎቶ ስራዎች ለዕይታ ቀርበዋል።

ማስረጃዎች ለሕጋዊ ጥያቄ በሚያመቹበት ኹኔታ በአፋጣኝ ተዘጋጅተው እንዲቀርቡ ታዟል በጥምር እና በተናጠል ተጠያቂ የሚኾኑ የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች በስም ዝርዝር ይለያሉ የቤት እና የመኪና ሽልማት የተሰጣቸው አለቆች እና የስጦታው ምክንያት ተብራርቶ ይቀርባል   *          *          * የመሬት፣ የሕንጻ እና የልማት ይዞታዎች የኪራይ ውላቸው ለአንድ ዓመት ብቻ ይኾናል ከሦስተኛ ወገኖች ጋር ለመዋዋል እንዲቻል የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ በቋሚ …

የዞን 9 ጦማርያን ከታሰሩ አንድ አመት ከአምስት ወራት የተቆጠረ ሲሆን ወዳጅ ጋዜጠኞችን ጨምሮ ከጠቅላላው ዘጠኝ እስረኞች መካከል አራት ጦማርያን አሁንም በእስር ላይ በመሆናቸው ሁለተኛ እንቁጣጣሻቸውን በቅሊንጦ እስር ቤት ያከብራሉ ፡፡ ባለፉት አንድ አመት ከአምስት ወራት 36 ግዜ ፍርድ ቤት የተመላለሱ ሲሆን እስራቸው እና የፍርድ ሂደቱ በ2007 ዓ/ም ምን ይመስል እንደነበረ በመጠኑ እናያለን፡፡


የዞን 9 የእስር መስመር


መስከረም 2007  -የዓመቱ መጀመሪያ ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ በጻፈው  የቀድሞው አብዮተኛ ኑዛዜ  ተጀመረ፡፡ ጽሁፉ በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ የዞን9 ጦማር ላይ ታትሟል፡፡


ጥቅምት 2007 የህግ የበላይነት እና ጸረ ሽብርህጉ ሲገመገም የሚለው ‹‹የጸረ ሽብር ሕጉና›› የአሁኗ ኢትዮጲያ ያላቸውን ግንኙነት አንዲሁም ምን ተፅእኖ እንዳለው የሚያሳየው ልዬ ሪፓርተዥ ተዘጋጀ፡፡
ጥቅምት 11 2007 ዓ/ም በእስር ላይ ይገኙ የነበሩትን ጦማሪት ማህሌት ፋንታሁንን እና ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬን የእስር ቤት አያያዝ አስመልክቶ የቀረበውን አቤቱታ ለማየት ችሎቱ ተሰየመ፡፡ በእለቱም እስር ቤቱ የተለየ አያያዝ መኖሩን ክዶ የተከራከረ ሲሆን ፍርድ ቤቱም አንደተለመደው እንዳይደገም በሚል የማረሚያ ቃል ችሎቱን አጠናቀቀው፡፡

ከጥቅምት 12 ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ለዞን9 ጦማርያን 6 ወር የእስር ቆይታን አስመልክቶ ለቤተሰቦቻቸውን ድካም የማገዝ የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ በዞን9 ጦማርያን ወዳጆች አማካኝነት በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ፡፡

ጥቅምት 25 – የዞን9 ጦማርያን ለአስረኛ ፍርድ ቤት ቀረቡ ፡፡


ህዳር 2007  –

ህዳር 1 ቀን የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይማርያም ደሳለኝ በተለያዬ ሚዲያዎች ላይ ሲቀርቡ የሚሰጡትን አስተያየት ሕገ-መንግስታዊነትን የጣሰ መሆኑን አስመልክተው ደብዳቤ ጻፉ፡፡ ደብዳቤው የተከሳሾችን በህግ ፊት ንጹህ ሆኖ የመቆጠር መብት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየጣሱ እንደሆነ እና እንዲታረም የሚጠይቅ ነበር፡፡

ሕዳር 3  ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞቹ ለ11ኛ ፍርድ ቤት ቀረቡ ፡፡ በዚህ የፍርድ ቤት ውሎም አቃቤ ህግ በአምስት ጉዳዬች ላይ ክሱን አንዲያሻሽል ትእዛዝ ተሰጠው ፡፡ ( ሊፈጽሙ ነው የተባለውን የሽብር ወንጀል በግልጽ ማስቀመጥ፣ ቡድኑ እየተባለ የተቀመጠው ቡድን ማን እነደሆነ በግልጽ ማስቀመጥ፣ የሥራ ክፍፍልን አስመልክቶ የተጠቀሰውን በግልጽ መስቀመጥ ፣ ተላከ የተባለውን 48000 ብር አስልክቶ በግልጽ ከማን አንደተላከ ማስቀመጥ ፣ ስልጠና የተባሉት ምን እንደሆኑ በግልጽ ማስቀመጥ እና የሽብር ስልጠና ሰጪ ድርጅቱን በግልጽ ማስቀመጥ ይገኙበታል)

ሕዳር 17 – በጦማርያኑ የዋስትና መብትን አስመልክቶ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደርጎ በእስር መቆየታቸው እርግጥ ሆነ ፡፡

ሕዳር 24 – ተሻሻለ የተባለው ክስ በድጋሚ ለፍርድ ቤት ቀረበ ፡፡ ጠበቆች የተሻሻለው ክስ ላይ አስተያየታቸውን አንዲሰጡ ተነገራቸው፡፡ ተሻሻለ የተባለው ክስ ቡድኑ ግንቦት 7 ነው ከማለት ውጪ ምንም አይነት መሻሻል ሳይደረግበት ነበር ለፍርድ ቤት የቀረበው ፡፡


ታህሳስ 2007

ታህሳስ 7 – ጦማሪ ዘላለም ክብረት በእንግሊዘኛ የጻፈው የናፍቆት ደብዳቤ  ታተመ

ታህሳስ 9 – ጦማሪ አቤል ዋበላ ‹‹ሕልም እንደሆነ አይታሰርም›› የሚለው ተወዳጅ ጽሁፉ በዞን9 ጦማር ላይ ታተመ ፡፡

ታህሳስ 27 ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞቹ በድጋሚ ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ ፍርድ ቤቱ ክሱ አንዲሻሻል ታዞ ነገር ግን በተለያዩ አራት ጉዳዮች ላይ አሁንም ባለመሻሻሉ በድጋሚ አንዲሻሻል ሁለተኛ ትእዛዛ ሰጠ፡፡


ጥር 2007

ጥር 6 የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኛ ወዳጆች በድጋሚ ፍርድ ቤት ቀረቡ ፡፡ በእለቱ አቃቤ ህግ በድጋሚ አሻሻልኩት ያለውን ክስ ይዞ ቀረበ፡፡

ጥር 20 – ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግ ያቀረበውን ያልተሻሻለ ክስ እንደተሻሻለ መቁጠሩን በመግለጽ ተከሳሾች የህብረተሰቡን ደህንነት ወይም ጤና በማወክ በጸረ ሽብር ህጉ አንቀጽ 4 መከሰሳቸውን አጸና፡፡ የወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ የተጠቀሰበትን አንቀጽ በቀደመው ብይን ውድቅ በማድረጉም የተከሳሾች ጉዳይ ‹‹በጸረ ሽብር›› ሕግ ብቻ እንዲዳኝ ተወሰነ፡፡ የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ተቀጠረ፡፡

ጥር 26 – የዞን9 ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች በድጋሚ ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ ፍርድ ቤቱ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ከመስጠታቸው በፊት መሃል ዳኛው አንዲነሱላቸው አቤቱታ አቀረቡ፡፡ ችሎቱም አቤቱታውን ሰምቶ ለመወሰን ሌላ ቀጠሮ ተሰጠ፡፡

ጥር 27 – በዚህም ቀጠሮ የተገኙት ተከሳሾች ሁለቱ ዳኞች ተሟልተው የዳኛው ይቀየርልን አቤቱታን መስማት ስላልቻሉ  በማግስቱ ለጥር 28 ተቀጠሩ ፡፡

ጥር 28 – በዚሁ እለት መሃል ዳኛው ባልተገኙበት ሁለቱ ዳኞች ጉዳዩን አይተው መሃል ዳኛው በፍርድ ሂደቱ ወቅት ጣልቃ አልገቡም አንዲሁም አፋጣኝ ፍትህን አላጓደሉም በማለት ውሳኔ መስጠታቸው ተገለጸ፡፡ ይህንን ተከትሎ የመሃል ዳኛው ምንም አንኳን በጉዳዩ ላይ ዳኞች ችሎቱ ላይ አንድቀጥል ቢፈልጉም ለእኔ ግን አንዲህ እየተባል ክሱ ላይ መቆየት አግባብ ስለማይሆን ራሴን ከችሎቱ አግልያለሁ በማለት አስተያየታቸው ሰጡ ፡፡ ( ነገር ግን ችሎቱን አሁንም የሚያስችሉት እኚሁ ዳኛ ናቸው) ፡፡

በተመሳሳይ እለት ጦማሪ አቤል ዋበላ ከማረሚያ ቤት የደረሰበትን የመብት ጥሰት ( በውሻ ሰንሰለት ታስሮ መቀመጥ እና በማዕከላዊ ሳለ በደረሰበት ድብደባ እንዲጠቀም የተገደደውን የጆሮ ማዳመጫ መሳሪያውን መቀማት) አስመልክቶ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቀረበ ፡፡ ይህን አቤቱታውን በጽሁፍ አንዲያቀርብ ከፍርድ ቤት ቢነገረውም በእለቱ የነበረው ሂደት ብዙዎን በፍርድ ቤት ውስጥ እንባ አራጨ፡፡ በእለቱ የነበሩት የእስር ቤት ተጠሪ የማውቀው ጉዳይ የለም በማለት የመብት ጥሰቱን ክደዋል፡፡


የካቲት 2007

የካቲት 11 – የዳኛው መቀየር አቤቱታን ፍርድ ቤቱ ውድቅ ካደረገው በኋላ የዞን 9 ጦማርያ እና ጋዜጠኞች የካቲት 11 ቀን ለ20ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት በመገኘት የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ በእለቱን ጦማሪ በፍቃዱ ‹‹የሽብር ተግባር አልፈጸምኩም ሽብር ተፈጽሞብኛል›› ሲል፣ ጦማሪ ናትናኤል በበኩሉ ‹‹እዚህ አገር ፍትህ ቢኖር ኖሮ እኔ የቆምኩበት ቦታ ላይ መቆም የሚገባቸው ከሳሾቼ ናቸው፤ ምንም አይነት ወንጀል አልፈጸምኩም›› የሚል ቃሉን ሰጥታል፡፡ ጦማሪ አጥናፍ ‹‹ምንም አይነት ወንጀል አልፈጸምኩም›› ያለ ሲሆን ጦማሪ አቤል በበኩሉ ‹‹የኅብረተሰቡን ደህንነት ለመጉዳት አላቀድኩም ለሽብር ተግባርም አላሴርኩም ብሏል፡፡››  የሴት እስረኞችን አያያዝ አስመልክቶ አጭር ቀጠሮ የሰጠን ሲሆን አጠቃላይ የማስረጃ ማሰማት ሂደቱን ግን ከአንድ ወር ከ10 ቀን በኋላ በተከታታይ ለሶስት ቀን ቀጥሮታል፡፡

የካቲት 18 – የሴት እስረኞችን አያያዝ አስመልክቶ ችሎቱ የተሰየመ  ጉዳዬን ለማየት በድጋሚ ቀጠሮ ሰጥታል፡፡  


መጋቢት 2007

መጋቢት 21 – የሰው ምስክር ናቸው ተብለው የቀረቡ ሰዎችን ምስክርነት መስማት ተጀመረ ፡፡ ሁሉም ምስክሮች እቃዎች ሲፈተሹ ያየን ነን በማለት የተያዙ እቃዎቸን ከማየታቸው በስተቀር ያቀረቡት የተለየ የወንጀል ምስክርነት አልነበረም ፡፡ ምስክሮቹ ተከሳሾን መለየት ሲያቅታቸው የተስተዋሉ ሲሆን በመጀመሪያው ቀን 6 ሰዎች ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ የተከሳሽ ጠበቆች ባልተካደ ነገር ላይ የፍርድ ቤቱም የተከሳሾችም ጊዜ መባከን አይገባውም እቃውም የእኛ አይደለም የሚል ቃል አልሰጠንም ስለዚህ የደረጃ ምስክሮች መስማት ይቁም ቢሉም ፍርድ ቤቱ ታዛቢዎቹን መስማት መቀጠል አለበት በማለቱ የተገኙ እቃዎችን ሲዘረዝሩ ከርመዋል ( መጽኃፍት ፣ መጽሄቶች፣ አርቲክሎች ላፕ ቶፕ ስልኮች እና ሲምካርዶች የመሳሰሉት ከፍተሻ ዝርዝሩ ውስጥ የተገኙ ናቸው)

መጋቢት 22 – ተጨማሪ 8 ምስክሮች በተመሳሳይ ሁኔታ ቃላቸውን ሲሰጡ ውለዋል፡፡ ከነዚህ በላይ ምስክሮችን ማቅረብ ያልቻለው አቃቤ ህግ ተጨማሪ ጊዜ በመጠየቁ ለመጋቢት 30 ቀጠሮ ተሰጥታል፡፡

መጋቢት 30 – አቃቤ ህግ ምስክሮቼ ጠፍተውብኛል፡፡ የሲዲ ማስረጃዎችንም የያዘው ሰው በአገር ውስጥ ስለማይገኝ ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠኝ የሚል ጥያቄ አቅርቦ በመፈቀዱ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶ ችሎቱ ተበትናል ፡፡

መጋቢት 25 – ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ ይድረስ ለኢቢሲ ጋዜጠኞች የጻፈው ጽሁፍ ታትሞ ወጥቷል፡፡


ሚያዝያ 2007

ሚያዝያ 16-19  የ6ቱ ጦማርያንን እና የ3ቱን ጋዜጠኞች እስር አንደኛ አመት አስመልክቶ ለነጻነታቸው ዋጋ የሚከፍሉትን እናወድስ የሚል የሁለት ቀናት ማስታወሻ ተዘጋጀ፡፡ በማስታወሻው ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞቹ የደረሰባቸውን የመብት ጥሰት ዝርዝር እና የተያዙበትን እለት የነበረውን ድባብ ያሳየ ሲሆን ከ3 ሺህ በላይ ሰዎች በሁነቱ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል ፡፡  በዚሁ የማስታወሻ ዝግጅት ላይ የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች የላኩት የአንደኛ አመት ማስታወሻም ተስተናግዷል፡፡


ግንቦት 2007

ግንቦት 2

በዞን 9 ወዳጆች አማካኝነት የተዘጋጀው ሁለተኛው የቤተሰቦቻቸውን ሸክም መጋራት የሚለው የአንድ ሳምንት ዘመቻ ለሁለተኛ ጊዜ ተካሄዷል፡፡

ግንቦት19-21 በነዚህ ቀናት በዋለው ችሎት ላይ ከፍተኛ መወዛገብ ያሳየው አቃቤ ህግ ሲዲዎቹን እንደማስረጃ ማስመዝገብ ባለመቻሉ እና ምስክሮችንም ማቅረብ ስላልቻለ ሲዲዎቹ ከማስረጃ ላይ አንዲወገዱ እንዲሁም ተጨማሪ ምስክሮችን ለማቅረብም የተወሰነው ጊዜ በቂ ሆኖ አልተጠቀመበትም በሚል ምክንያት ተጨማሪ እድል እንዳይሰጠው ተወስኗል ፡፡

አቃቤ ህግ አንደኛ ተከሳሽ ሶልያና ሽመልስ ላይ አለኝ ያለውን የሲዲ ማስረጃ አስመልክቶ ሌሎች ተከሳሾች ማየት አለባቸው ወይስ ፍር ቤቱ በጽህፈት ቤት ማየት አለበት የሚለውን ለመወሰን ሰኔ 8 ተቀጥሯል፡፡

በተመሳሳይ ቀን ችሎት ውስጥ አቤል ዋበላ ከዳኞች ጋር በነበረው አለመስማማት የተነሳ የችሎት መድፈር ጥፋተኛ ተብሎ ለቅጣት ለግንቦት 25 ተቀጠረ፡፡

ግንቦት 23 – ሥነ-ስርዓት የሚለው የጦማሪ አቤል ዋበላ ጽሁፍ ታትሟል፡፡

ግንቦት 25 አቤል ዋበላ በችሎት መድፈር በገደብ 4 ወር ተፈርዶበታል ፡፡


ሰኔ 2007

ሰኔ 8 – ፍርድ ቤት የቀረቡት 9 ተከሳሾች  ከብይን ለሃምሌ 13 የተቀጠሩ ፡፡ በእለቱም አንደኛ ተከሳሽ ላይ የቀረበውን የሲዲ ማስረጃ በጽህፈት ቤት አይተን እንደማስረጃ ቆጥረነዋል፡፡ ለሌሎች ተከሳሾም መድረስ አይገባውም በማለት ችሎቱ ወሰነ


ሃምሌ 2007

ሃምሌ 1 ቀን 2007 ዓ/ም ባተጠበቀ ሁኔታ ሶስቱ ጋዜጠኞች እና ሁለት የዞን9 ጦማርያን ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር መፈታታቸው ዜና ተሰማ ፡፡ በእለቱ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ፣ ጋዜጠኛ አስማማው ሃይለጊዮርጊስ እና ጦማሪ ዘላለም ክብረት ሲፈቱ በማግስቱ ጠዋት ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ እና ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁን ተፈቱ፡፡

በተመሳሳይ ቀን በቀሪዎቹ 5ቱ ተከሳሾች ላይ ክሱ አንደሚቀጥል የመንግስት ወዳጅ የሆነው ሬዲዬ ፋና በድረ ገጹ አሳወቀ ፡፡

ሃምሌ 9-11 ለሶስት ቀናት የሚቆይ እስቲ አንነጋገር የማስረጃን ነገር በሚል የተዘጋጀው ዘመቻ ተካሄደ ፡፡ ይህ ዘመቻ ሃሳቡ ተከሳሾች ላይ ማስረጃ ተብለው የቀረቡ ጉዳዬችን ለአደባባይ ማብቃትና ቀሪ አራት ታሳሪዎች የሚከላከሉት ምንም ነገር እንደሌለ ለማሳወቅ የታለመ ነበር ፡፡

ሃምሌ 10 – ጦማሪ በፍቃዱ ቁዘማ፣ ከአቃቤ ሕግ ማስረጃዎች በፊት እና ጦማሪ ናትናኤል የዕለት ተዕለት ጥያቄዎቻችን ብይናቸውን አስመልክቶ የጻፋቸው ጽሁፎች ታተሙ፡፡

ሃምሌ 13 – ፍርድ ቤቱ የአንድ ምስክር ቃል ተገልብጦ አልደረሰኝም በማለት ብይኑን መስራት አለመቻሉን ገልጾ ጽሁፉ መገልበጡን ለማረጋገጥ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ ፡፡

ሃምሌ 22 – የተከሳሾች ጽሁፍ ተገልብጦ ማለቁን አረጋግጫለሁ ያለው ፍርድ ቤቱ ከጽህፈት ቤት በማስቻል በድጋሚ ለጷጉሜ 2 ቀጠሮ ሰጠ

ሃምሌ 25 – ጥቂት ስለማእከላዊ የሚል ጽሁፍ ታተመ፡፡


ሜ 2007

በአመቱ የመጨረሻ ሳምንት የመጨረሻ የእስር ሳምንታቸው ይሆናል ተብሎ ተስፋ ቢደረግም ፍርድ ቤቱ ዳኞች አልተሟሉም በሚል ሌላ ሰበብ ሁለተኛ እንቁጣጣሻቸውን በእስር እንደሚያሳልፉ ያረጋገጠውን የ31 ቀን ቀጠሮ በመስጠት ለመስከረም 27 ለአራተኛ ጊዜ በአጠቃላይ ደሞ ለ37ተኛ ጊዜ ቀጠሮ ሰጠ ፡፡ 

 

በግዙፉ የአባይ ግድብ ላይ መካሄድ ያለበት የተጽእኖ ጥናት በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ያልቀጠለው በተመረጡት አማካሪ ድርጅቶች ችግር መሆኑን የኢትዮጵያ የቴክኒክ ኮሚቴ ሰበሳቢ አስታወቁ።

ጥናቱን ያዘገየችዉ ኢትዮጵያ እንደሆነች ተደርጎ በአንዳንድ የግብጽ ወገኖች የሚሰራጨው መረጃም የተሳሳተ ነው፤ ሲሉ አቶ ጌድዎን አስፋው ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

“እንደ ረዳት ጳጳስ ነኝ” የሚሉት ሥራ አስኪያጁ፣ ሕጋዊ ህልውናዋን ለአደጋ አጋልጠውታል ምደባቸው፣ ከመንግሥት ሕግ እና ከሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን አንጻር ጥያቄ ተነሥቶበታል ለስምንት ዓመታት የሒሳብ ሪፖርት ለሚመለከተው መንግሥታዊ አካል አልቀረበም በመላው ደቡብ አፍሪቃ ያለችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በደቡብ አፍሪቃ መንግሥት አትራፊ ባልኾኑ ሕዝባዊ ድርጅቶች ዐዋጅ(NPO) ሕግ መሠረት እ.አ.አ በ26/01/1999 ሕጋዊ ፈቃድ አግኝታ፣ በቁጥር 006-083 …

ጷግሜን ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቫይስ ኒውስ የተባለው ድረገጽ የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ወቅታዊ ሁኔታ ይዞ በወጣው ዘገባ እንደገለጸው፣ የእንግሊዝ ባለስልጣናት አቶ አንዳርጋቸው ታስረው ከነበሩበት ስውር ቦታ ወደ ቃሊቲ መዛወራቸው በጎ ነገር ቢሆንም፣ በቃሊቲ በጥሩ ሁኔታ ተይዘዋል ብለው አያምኑም። የእንግሊዝ የውጭና የጋራ ብልጽግና አገራት ቃል አቀባይ ” ኢትዮጵያና ዩናይትድ ኪንግደም …

ጷግሜን ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ የተለያዩ አገራት በፈረንጆች አቆጣጠር ከ2008 እስከ 2012 ለትምህርት የመደቡትን በጀትና ወደ ውጭ አገራት በህገወጥ መንገድ የወጣውን ገንዘብ በማነጻጸር ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ ላይ እንደጠቀሰው ፣ በኢትዮጵያ በህገወጥ መንገድ የወጣው ገንዘብ፣ ለትምህርት ከወጣው ገንዘብ በ245 በመቶ ይልቃል። ድርጅቱ ቀድም ሲል ባወጣው ሪፖርት ከ2008 እስከ 2012 ባሉት …

ጷግሜን ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢሮው በጣና ሐይቅ ላይ በቱሪስት ማስጎበኘት ስራ በተሰማሩ ማህበራት አሰራር ጣልቃ በመግባቱ በተከሰሰበት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡ ባለስልጣን ቢሮው የቱሪስት ጀልባዎችን በተራ ለማሰራት ያደረገው የተራ ማስከበር ስራ ህግና ደንቡን ያልተከተለ ነው በማለት የተቃወመውን የጥዋት ብርሃን አነስተኛና መለስተኛ የግል ጀልባ ባለንብረቶች ማህበር ፣ …


የሰው ልጅ ምንጭ የተባለ ዝርያ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መገኘቱ ዛሬ፤ ጳጉሜ 05/2007 ዓ.ም ይፋ ሆኗል፡፡ የግኝታቸውንና የምርምራቸውን ሪፖርት ኢላይፍ መፅሔት ላይ ያወጡትና ጆሃንስበርግ ላይ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ሳይንቲስቶች የዝርያውን ስም “ኦሞ ናሌዲ – Homo Naledi” ሲሉ ጠርተውታል፡፡

ክሬድል ኦፍ ሂዩማንካይንድ እየተባለ በሚጠራው የዓለም ጥብቅ ውርስ አካባቢ ከደቡብ አፍሪካ ዋና ከተማ ጆሃንስበርግ ወጣ ብሎ በሚገኙ የራይዚንግ ስታር አካባቢ ተያያዥ ዋሻዎች ውስጥ ነው ቅሪተ-አካሉ የተገኙት፡፡

የጋውተንግ ጠቅላይ ግዛት የአስተዳደር ምክር ቤቱ አባል ሌቦንግ ማይሌ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “ለሣይንስና ለግኝቶች፣ ለታሪክና ለዕውቀት፤ ታላቅ ቀን ነው” ብለውታል፡፡

ዝርያው ኢትዮጵያ ውስጥ ከተገኙት ከእነ ሉሲ ዓይነቱ ዝርያ የተለየ መሆኑ ቢገለፅም ዕድሜው ስንት እንደሆነ ግን ገና አልታወቀም፡፡

የዞን 9 ጦማርያን ከታሰሩ አንድ አመት ከአምስት ወራት የተቆጠረ ሲሆን ወዳጅ ጋዜጠኞችን ጨምሮ ከጠቅላላው ዘጠኝ እስረኞች መካከል አራት ጦማርያን አሁንም በእስር ላይ በመሆናቸው ሁለተኛ እንቁጣጣሻቸውን በቅሊንጦ እስር ቤት ያከብራሉ ፡፡ ባለፉት አንድ አመት ከአምስት ወራት 36 ግዜ ፍርድ ቤት የተመላለሱ …

የዞን 9 የ2007 ዓ/ም የእስር መስመር Read more »

በዲላ ዩንቨርስቲ ውስጥ ዛሬ ጠዋት ተማሪዎች የውሃ እጦት እንዲቀረፍላቸው ዛሬ ሐሙስ ጳጉሜ 4 2007 ጠዋት ያቀረቡትን ጥያቄ ተከትሎ በተፈጠረ አለመግባባት አስተዳደሩ ከጠራቸው የልዩ ሃይል ፖሊሶች ጋር መጋጨታቸው ተሰምቷል::በተነሳው ግጭት የተወሰኑ ተማሪዎች የተጎዱ ሲሆን የልዩ ሃይል ፖሊሶች ወደ ግቢው ዘልቀው በመግባት …

በዲላ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች እና ልዩ ሃይሎች ተጋጩ Read more »

መግቢያ „ የተፈጠርነው እንደ እንስሳ ለመኖር ሳይሆን ፣ የትክክለኛውን ዕውቀትና የታታሪነትን መንገድ ለማግኘትና ለመቀዳጀት ነው ።“ ዳንቴ ዳንቴ ይህንን ያለው በ13ኛው ክፍለ-ዘመን የኢጣሊያን ህዝብ በድህነት፣ በተስቦ በሽታና በጦርነት፣ እንዲሁም ኑሮው ሁሉ ስለጨለመበት ደጉን ከክፉ መለየት ባልቻለበት ወቅትና፣ ማንኛውንም ለሰው ልጅ …

ችግሩ ወያኔን በማስወገድ ብቻ የሚፈታ አይደለም ! – ካለፈው የቀጠለ ፈቃዱ በቀለ፣ ዶ/ር Read more »

አልወድም ነበረ እርግማን ጨርሶ፣ ግን ላንተ ወዳጄ ሆዴ በጣም ጢሶ ፣ ዛሬስ ተራገምኩኝ ይሁን ብዬ ጮህኩኝ ይኸው በገሃድ፣ የወሬው ፈጣሪ ሰብቀኛው አመድ ። ዮሐንስ አድማሱ ኀብርና ምርምር /1966/ “ . . . የ13 ወራት የፀሐይ ብርሃን (13 Months of Sunshine) …

ተስማምታችሁ ተርኩልን! መነገር ያለበት ቁጥር 10 በልጅግ ዓሊ Read more »

በሃገር ውስጥ የሚመረቱ ምርቶች ለዋጋ መናር ዋነኛው ምክንያት በሕገወጥ መልኩ ከሃገር ስለሚወጡ እና የምርቶቹ በቂ አቅርቦት አለመኖር መሆኑ ተጠቆመ::ራሱ አስታጥቆ ባሰማራቸው ሕገወጥ ደላሎች እና ነጋዴዎች ራሱ እያጭበረበረ ራሱ እያስጠና ራሱ የሚነግረን የወያኔው መንግስት ጥናት እንደሚጠቁመው በርበሬ ጤፍ ቡናና የተለያዩ የኢትዮጵያ …

ጤፍ በርበሬ ቡናና የተለያዩ ምርቶች ወደ ጎረቤት ሃገሮች በሕገወጥ መንገድ እየወጡ ነው:: Read more »

  Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ባለፉት 20 አመታት ሁላችን አንድ የታዘብነው ጉዳይ አለ::ስለኢትዮጵያዊነት ጠንካራ አቋም ያላቸው ስለሃገር የፖለቲካ ይሁን የኢኮኖሚ አንድነት የማህበረሰብ ትሥሥር ታላቅ አመኔታ ያላቸው ሰዎች ሲሰደዱ ሲወገዱ ሲሸበቡ አይተናል በአጠቃላይ አይፈለጉም:: የመንግስታዊ ፖለቲካ ጡዘት ውስጥ ሳይገቡ ስልጣን …

ሕወሓት እና አለቅላቂዎቹ ስለኢትዮጵያዊነት ሲነሳ ያቅለሸልሻቸዋል:ኢትዮጵያዊነት በህዝብ ልብ ውስጥ ላይወርድ የነገሰ ነው:: (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

  Amdom Gebreslasie የፌስቡክ ተቃዋሚዎች ኣብዮታዊ እርምጃ ይወሰድባቸዋል…! ______________ የትግራይ ፌስቡክ ተጠቃሚዎች ኣብዮታዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው መሆኑ በኣባይ ወልዱ የሚመራው የህወሓት ኣንጃ ኣሳወቀ። ኣንጃው ይህ ኣብዮታዊ እርምጃ እንደሚ ወስድ ያሳወቀው “12ተኛ ጉባኤ እንዴት ኣለፈ…?” የሚል ኣጀንዳ በየመንግስት መስርያ ቤቶች፣ ከመቐለ ከተማ …

የትግራይ ፌስቡክ ተጠቃሚዎች ኣብዮታዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው መሆኑ በኣባይ ወልዱ የሚመራው የህወሓት ኣንጃ ኣሳወቀ። Read more »

አምዶም ገብረስላሴ ኣንጃው ይህ ኣብዮታዊ እርምጃ እንደሚ ወስድ ያሳወቀው “12ተኛ ጉባኤ እንዴት ኣለፈ…?” የሚል ኣጀንዳ በየመንግስት መስርያ ቤቶች፣ ከመቐለ ከተማ ኑዋሪዎች፣ የክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ካድሬዎችና ኑዋሪዎች ውይይት እየተካሄደ ነው። በመቐለ ማዘጋጃ ቤት ማክሰኞ 3/ 13/ 2007 ዓ/ም በኣቶ ተስፋኣለም ተወልደብርሃን …

የትግራይ ፌስቡክ ተጠቃሚዎች ኣብዮታዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው መሆኑ በኣባይ ወልዱ የሚመራው የህወሓት ኣንጃ ኣሳወቀ Read more »

የታደለ አገልጋይ የበላዩን ከስሕተት ይጠብቃል፡፡ ‹አማካሪ የሌለው ንጉሥ ያለ አንድ ዓመት አይነግሥ› እንዲሉ፡፡ አክዓብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከክርስቶስ ልደት በፊት(871-852 ቅልክ) የነበረ ንጉሥ ነው፡፡ የሚስቱን የኤልዛቤልን ቃል ሰምቶ ነቢያተ እሥራኤልን ሊያጠፋ ተነሣ፡፡ ብዙዎች በሰይፉ ጠፉ፣ ብዙዎችም አገር ጥለው ተሰደዱ፡፡ በአክአብ ቤተ መንግሥት ውስጥ ግን አብድዩ የተባለ ልብ ያለው ባለሟል ነበር፡፡ ንጉሡን ከጥፋቱ ማዳን ቢያቅተው በንጉሡ ስሕተት ባለመስማማቱ 100 ነቢያትን በሁለት ዋሻ ውስጥ ደብቆ የቤተ መንግሥቱን ምግብ እየመገበ ከአክዓብ ጥፋት አድኗቸው ነበር፡፡ በዚያ ዘመን ነቢያት የእሥራኤል የዕውቀትና የእምነት መሪዎች ናቸው፡፡ የእሥራኤል ባህል፣ ታሪክ፣ ትውፊትና ዕውቀት የሚተላለፈው በነቢያት ትውፊት ነበርና፡፡ ነቢያቱን ማጥፋትም ሀገሪቱን ያለ ታሪክ፣ ዕውቀት፣ ባህል፣ ሥርዓትና ቅርስ ማስቀረት ነበር፡፡ ለዚህ ነው አብድዩ የንጉሡን ዐዋጅ ማስቀየር ቢያቅተው ነቢያቱን ደብቆ እየመገበ ሀገሪቱን ከከባድ ጥፋት የታደጋት፡፡ 

ይህንን ሥራውን ማንም እንዲያውቅለትም፣ እንዲያውቅበት አላደረገም፡፡ ዓላማው ዕውቅና ጥቅም ማግኘት ሳይሆን ሀገር ማትረፍ ነውና፡፡ የንጉሡን የጥፋት ዐዋጅ ማስቀረት አልችልም ብሎ ዝም አላለም፤ ነገር ግን በዐቅሙ የሚችለውን በማድረጉ በእውነትም እሥራኤል የዕውቀት፣ የታሪክና የባህል ጥፋት እንዳይገጥማት አደረገ፡፡ ያን ክፉ ዘመንም አሻገራት፡፡  
 
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የበላዮቻቸውን ጥፋት ከማስቀጠል ይልቅ በራሳቸው ዐቅም የሚችሉትን መልካምነት የፈጸሙትን ብቻ ሳይሆን፣ ‹ትእዛዝ ከበላይ እግር ወደ ላይ› ከማለት አልፈው አለቆቻቸውን ከጥፋት የታደጉ የበታች አገልጋዮችንም ታሪክ እናገኛለን፡፡ የሶርያው ንጉሥ የቤን ሐዳድ 2ኛ የጦር አዛዥ ንዕማን ወደ ሰማርያ መጥቶ ነቢዩ ኤልሳዕን ባገኘው ጊዜ ከለምጽ ሕመሙ ይድን ዘንድ በዮርዳኖስ ወንዝ እንዲጠመቅ መክሮት ነበር፡፡ ንዕማን በዚህ ደስተኛ አልሆነም፡፡ ተቆጥቶም ወደ ሀገሩ ሊጓዝ ተነሣ፡፡ አንደኛው ባለሟሉ ግን ለጦር አዛዥ የሚገባ ምክርን መከረው ‹‹ጌታዬ ምን ቸገረህ፣ ውረድና ተጠመቅ፤ ከተፈወስክ እሰዬው፤ ክልሆነ ግን ከሰማርያ ጋር የምንዋጋበት ምክንያት እናገኛለን››፡፡ የጦር አዛዡ ንዕማን በዚህ የወታደሩ ሐሳብ ተስማማ፡፡ ዮርዳኖስ ወርዶም ተጠመቀ፡፡ ዳነም፡፡ አገልጋዩም አዛዡን ከጥፋት አዳነው፡፡ ንዕማንም ሊፈጽመው በነበረው ስሕተት ተጸጸተ፡፡
 
በታሪክ ውስጥ ግን እንደ አብድዩና የንዕማን ወታደር የበላዮቻቸውን ስሕተት የማይደግሙ ወይም አለቆቻቸውን ከስሕተት የሚታደጉ የበታቾች ብቻ አይደሉም የነበሩት፡፡ ያሉትም፡፡ አለቆቻቸው ያላሰቡትን ጥፋት በመሥራት አለቆቻቸውን ያስደሰቱ መስሏቸው ሀገር ያጠፉም አሉ፡፡ ‹ከለማበት የተጋባበት› እንዲሉ፡፡ ‹ጌታዬ እንዲህ ባደርግለት ይደሰታል› ብለው በማሰብ ከልክ እያለፉ፣ የሌለ እየጻፉ፣ ያልታዘዘ እየፈጸሙ ግፍ ሲሠሩ የኖሩ፡፡ ያዘው ሲባሉ ጣለው፤ እሠረው ሲባሉ ግደለው፤ አምጣው ሲባሉ ስቀለው፤ ተቀበለው ሲባሉ ቀማው የተባሉ እየመሰላቸው ሕግ ሲያልፉ፣ ገደብ ሲጥሱ የኖሩ አሽከሮችም ነበሩ፡፡ አሉም፡፡   
 
በሀገራችን ከነነዌ ጾም በኋላ የሚመጣው ኀሙስ ‹የዕብድ ኀሙስ› ይባላል፡፡ ቀኑ አለቆቻቸውን ለማስደሰት ሲሉ በግፍ ላይ ግፍ፣ በክፋት ላይ ክፋት፣ በመከራ ላይ መከራ፣ በቅጣት ላይ ቅጣት፣ በእንግልት ላይ እንግልት በሕዝብ ላይ ለሚጨምሩ አሽከሮች መታሰቢያ ነው፡፡ እንደ አብድዩና የንዕማን ወታደር ‹እስኪ ነገሩን እንየው› ከማለት ይልቅ ጭካኔ፣ ግፍ፣ ቅጣትና በደል አለቆቻችንን ይበልጥ ያስደስትልናል ብለው ለሚያስቡ አሽከሮች መታሰቢያ፡፡
 
በሸዋው ንጉሥ አስፋ ወሰን ዘመን ንጉሡ ለዘመቻ እየተጓዙ በደብረ ብርሃን አልፈው አንጎለላ ደረሱ፡፡ ይህን ጊዜ ጎሜ ጎሹ የተባለ አሽከር አስፋ ወሰንን በምን ላስደስታቸው ይልና በራሱ ጊዜ ዐዋጅ ያውጃል (‹መቼም ንጉሡ ሥራ በዝቶባቸው ረስተውት ነው እንጂ ይህን ሳያውጁ አይቀሩም‹ ብሎም ይሆናል)፡፡ ‹‹በዚህ ሀገር ያለውን ሰው ሁሉ አንድ ሳታስተርፍ በለው ብለውሃል› የሚል ዐዋጅ፡፡ ሠራዊቱም የንጉሥ ዐዋጅ መሰለውና አእምሮው ትቶ ጉልበቱን በማሠራት ፈረሱን እየጋለበ ከበሬሳ እስከ አያብር፣ ካንድ ዐርብ እስከ መገዘዝ የነበረውን ሀገር ሁሉ በነነዌ ፋሲካ ዕለት ኀሙስ ዘምቶበት ዋለ፡፡ ሕዝብ አለቀ፣ ተሰደደ፣ በሀገርም ላይ መከራ ወረደ፡፡ ንጉሡም የሆነውን ሲሰሙ አዝነው ጎሜ ጎሹን ‹‹ማን አዞህ ዐወጅክ?› ቢሉት ‹‹ጌታዬ መቼም የዘመትነው ለዚህ ነው ብዬ ነው›› አለ ይባላል፡፡ ቃላዊ መረጃዎች እንደሚነግሩን አስፋ ወሰን ጎሜ ጎሹን ቀጥተውና አሥረው ከዘመቻ ወደ አንኮበር ላኩት፡፡
ሕዝቡም ‹‹ወይ ጎሜ ጎሹ ወይ ጎሜ ጎሹ
በድፍን ሀገር ዕዳ ነስናሹ› ብሎ ገጠመበት፡፡ ቀኑም ‹የዕብድ ኀሙስ ተባለ›› ይላሉ ጸሐፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ በጻፉት የዳግማዊ ምኒሊክ ታሪክ ላይ፡፡
 
የቻለ እንደ ንዕማን ወታደር አለቃውን ከስሕተት ይታደጋል፣ ከጥፋት ያድናል፤ ያልቻለም እንደ አብድዩ የበላዩን ስሕተት ማረም ቢያቅተው እርሱን ስሕተቱ ይዞት እንዳይጠፋ ራሱን ከስሕተቱ ያድናል፣ ከጥፋቱም ይጠብቃል፡፡ ለሌሎችም የመዳኛ ምክንያት ይሆናል፡፡ እንደ ጎሜ ጎሹ ‹አለቃየ ይህን ባጠፋለት ደስ ይለዋል› ብሎ የሚያስብ አሽከር ግን ‹በድፍን ሀገር ዕዳ ይነሰንሳል›፡፡ ጎሜ ጎሹዎች ትንሽ ቀዳዳ ካገኙ አስፍተው ስለሚጓዙባት አለቆቻችን ምንም አይሉንም ብለው ያስባሉ፤ እንዲያውም አብልጠው በማሰባቸው እንደሚሸለሙ ያምናሉ፡፡ ጎሜ ጎሹዎች የአለቆቻቸውን በር በመዝጋት፣ እንደ አለቆቻቸው ሆነው በመወሰን፣ ቁጣውን ወደ ጥፊ፣ ጥፊውን ወደ ግርፊያ፣ ግርፊያውን ወደ ግድያ በማሳደግ የተሻለ አፈጻጸም ለማሳየት ይተጋሉ፡፡ 
 
አብድዩና የንዕማን ወታደር የበዙላት ሀገር ዶፍ ዝናብን በጣራ፣ ካፊያን በጥላ እንደሚከለል ሰው፣ ከላይ የሚመጣውን ጥመት አቃንተው፣ የሚወርደውን ጥፋት አርመው፣ ቁጣውን በትዕግሥት፣ መዓቱን በምሕረት ስለሚለውጡት ድፍን ሀገር ዕዳ ሳይሆን ፋታ ያገኛል፡፡ ጎሜ ጎሹዎች ሲበዙ ግን በበሆር ላይ ቆረቆር፣ በዕንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ፣ በዕዝል ላይ እንጥልጥል፣ በራቁት ላይ ብርድ፣ በጥማት ላይ ንቃቃት ይሆናል፡፡ ሕዝቡ እንዳለው ጎሜ ጎሹዎች ‹በድፍን ሀገር ዕዳ ይነሰንሳሉ›፡፡ እነርሱ ለዕለቱ የሚያገኙትን ሹመት ሽልማት፣ ጉርሻና ድርሻ እንጂ አለፍ ዘለቅ አድርገው የችግሩን ውጤት አያስቡትምና ጎሜ ጎሹዎች የሚያመጡትን ዕዳ ሀገር ስትከፍለው ትኖራለች፡፡    
 
በቀጣዩ ዓመት ኢትዮጵያችን ጎሜ ጎሹዎች ሳይሆን አብድዩዎችና የንዕማን ወታደሮች የሚበዙባት ሀገር ትሁን፡፡

የዜናው ሊንክ፡- (ዜናውን እስኪያገኙ ወደታች ስክሮል ማድረግ አይዘንጉ)፡- http://www.bbc.com/news/live/world-africa-34104060…

ቢቢሲ በድረገጹ አዲሱን የድምጻችን ይሰማ የትግል መለያ ምልክት( struggle logo )አስመልክቶ ዘገባ አቀረበ:: #Ethiopia #EthioMuslims #‎StruggleLogo‬ ታዋቂው የእንግሊዝ የዜና ማሰራጫ ቢቢሲ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የሃይማኖት ነጻነታቸውን ለማረጋገጥ እና የታሰሩ ወኪሎቻቸው እንዲፈቱ እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግስት የሚያደርስባቸውን ግፍ በመቃወም በሚያደርጉት ትግል አስመልክቶ መሪ …

ቢቢሲ በድረገጹ አዲሱን የድምጻችን ይሰማ የትግል መለያ ምልክት( struggle logo)አስመልክቶ ዘገባ አቀረበ:: Read more »

Hailemaraim visits graduating troops
የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት መከላከያ ሰራዊት ለአባይ ግድብ መስሪያ ገንዘብ እንዲያዋጡ ለቀረበላቸው ጥሪ። እንዳልተቀበሉት ምንጮቻችን ከመከላከያ ውስጥ ገለፁ፣በምንጮቻችን መረጃ መሰረት።- የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እንደ አዲስ ለአባይ ግድብ መስሪያ የሚሆን በሚል ገንዘብ እንዲያዋጡ በአመራሮቻቸው ለቀረበላቸው ጥሪ። አንቀበልም ማለታቸውን የገለፀው መረጃው። ለቀረበው ጥሪ ሳይቀበሉት የቀሩበት ምክንያትም “ ባለፉት ጊዚያት በተደጋጋሚ የከፈልነውን ገንዘብ ቦንድ ይሰጣቸኋል ተብለን እስከ አሁን ድረስ […]

ተሸራርፈው እና ተገልብጠው ጎልተው እንዳይወጡ መደረጋቸውን ዳይሬክቶሬቱ ገምግሟል “የመልካም አስተዳደር ድምፃችን አልተሰማም፤ ውክልናችንም አንሷል” (ሰንበት ት/ቤቶች) ምክክሩ፣ በሀገረ ስብከቱ የሰባቱ ክፍላተ ከተማ እና በሌሎችም አህጉረ ስብከት ይቀጥላል (ሰንደቅ፤ ፲፩ኛ ዓመት ፭፻፳፪፤ ረቡዕ፣ ጳጉሜን ፬ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት 170 አድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ሰባክያነ ወንጌል፣ ካህናት፣ የሰንበት …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

– ወያኔ‬ ትግራይን የቱሪስት ማአከል የማድረግ ጥረት አልተሳካለትም:: – የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ቸል ብለውናል በማለት የወያኔ ባለስልጣኖች ክስ ማሰማት ጀመሩ ::   ‎- ፓስተርን ነኝ ባዩ ወንጀለኛው ታምራት ላይኔ ከወያኔ ጋር እየሰራ ነው ተባለ ::   ‎- ሻእቢያ ወያኔን ወታደራዊ …

ወያኔ‬ ትግራይን የቱሪስት ማአከል የማድረግ ጥረት አልተሳካለትም:: ታምራት ላይኔ ከወያኔ ጋር እየሰራ ነው Read more »

የማህበራዊ ቦይኮት ዘመቻችንን የመረጃ መሰብሰቢያ ፎርሙን በመሙላት እንጀምራለን! የቦይኮቱ ዓይነት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል! ረቡእ ጳጉሜ 4/2007 ኢትዮጲያውያን ሙስሊሞች የመንግስትን ወሰን የለሽ በእምነታችን ጣልቃ መግባትን ተከትሎ እያካሄድነው ባለነው የመብት ማስከበር ሰላማዊ ትግል አንጸባራቂ ድሎች እንደተገኙ ሁሉ በተቃራኒው ደግሞ በተደጋጋሚ ከሌሎች በሚደርሱብን …

የማህበራዊ ቦይኮት ዘመቻችንን የመረጃ መሰብሰቢያ ፎርሙን በመሙላት እንጀምራለን! የቦይኮቱ ዓይነት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል! Read more »

  ብሄራዊ ባንክ ክኤሌክትሪክ ሃይል ሽያጭ የተገኘ የውጪ ምንዛሬ አልደረሰኝም አለ::(ምንሊክ ሳልሳዊ) #Ethiopia በኤሌክትሪክ መቋረጥ በሃገር ወስጥ የኢንዱስትሪው መስክ ብቻ ከ40 ሚሊዮን ዶላር በላይ ኪሳራ ደርሷል:: የወያኔው አገዛዝ ለጎረቤት አገሮች ከሚሸጠው የኤሌክትሪክ ሃይል በ9 ወር የተገኘው 35 ሚሊዮን ዶላር በላይ …

ብሄራዊ ባንክ ክኤሌክትሪክ ሃይል ሽያጭ የተገኘ የውጪ ምንዛሬ አልደረሰኝም አለ::(ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

ኤርትራ የኢትዮጵያ ወረራ ያሰጋኛል አለች

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ጳጉሜን 3 ቀን 2007 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ ኢትዮጵያ ኤርትራን ለመውረር እያስፈራራች መሆኗን አስታውቋል፡፡ ምንም እንኳ የመረጃው ምንጭ ማን እንደሆነ የኤርትራ መንግሥት ባይናገርም፣

ኢትዮጵያ ኤርትራን ለመውረር ከአሜሪካ ይሁንታ ማግኘቷንና ኢትዮጵያም በይፋ መግለጿን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ምንም እንኳ ከወራት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ኤርትራን በተመለከተ በፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ፣ የኤርትራ መንግሥት ኢትዮጵያንና ሌሎች የጎረቤት አገሮችን ለማተራመስ የያዘውን ስትራቴጂ የማይተው ከሆነ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ተገዶ ዕርምጃ እንደሚወስደና የኢትዮጵያን ሕዝብ እንደሚያሳውቅ መናገራቸው አይዘነጋም፡፡ በወቅቱ የኤርትራ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ምንም ሳይል አሁን የኢትዮጵያ ወረራ ያሰጋኛል ማለቱ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ በምሥሉ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ ዩኑስ በኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ቀን አከባበር ሥነ ሥርዓት በቅርቡ በተካሄደበት ወቅት የሚታዩ ሲሆን፣ ዝርዝር ዘገባው ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ ወይም በ ፖለትካ ገጽ ላይ ይመልከቱ፡፡ 

 

ጦማሪያኑ ለአራተኛ ጊዜ ለብይን መቀጠራቸውን ተቃወሙ

‹‹አንድ ዳኛ ምንም ማድረግ አይችልም›› ዳኛ ዘሪሁን ደሳለኝ

‹‹ከዳኞች ጋር ምንም ችግር የለብንም ከማን ጋር እንደተጣላን ገብቶናል›› በእስር ላይ ያሉ ጦማሪያን

በተጠረጠሩበት የሽብር ተግባር ወንጀል ክስ ከተመሠረተባቸው በኋላ የከሳሽ ዓቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ ቀርቦባቸው ለብይን የተቀጠሩት አራት ጦማሪያን፣ ለአራተኛ ጊዜ ጳጉሜን 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱን ተቃወሙ፡፡ 

ተከሳሾቹ ጦማሪያን ናትናኤል ፈለቀ፣ አቤል ዋበላ፣ አጥናፍ ብርሃኔና በፍቃዱ ኃይሉ ጳጉሜን 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ብይን እንደሚሰጥ የጠበቁ ቢሆንም፣ ጉዳያቸው በሦስት ዳኞች የሚታይ ከመሆኑ አንፃር በዕለቱ አንድ ዳኛ አቶ ዘሪሁን ደሳለኝ ብቻ የተገኙ በመሆናቸው ብይኑ ሳይሰጥ ቀርቷል፡፡ ብይኑ ተሠርቶ የተጠናቀቀ ቢሆንም፣ ዳኞች ባለመሟላታቸውና በመዝገቡ ላይ ባለመፈረማቸው ብይኑ ሊነገር እንደማይችል ዳኛ ዘሪሁን ገልጸዋል፡፡ 

በዳኞች አለመሟላት ለሁለተኛ ጊዜ መቀጠሩ ያበሳጫቸው ተከሳሾቹ፣ ‹‹እኛ ከዳኞች ጋር ምንም ችግር የለብንም፡፡ ከማን ጋር እንደተጣላን ገብቶናል፡፡ የምንፈልገው ቁርጥ ያለው እንዲነገረን ነው፡፡ ወይ በነፃ እንሰናበት ወይም ተከላከሉ እንባል፡፡ ብይን ለመስጠት በሚቀጠሩት ቀናት መካከል ያለው ጊዜ ለእኛ ሕመም ነው፤›› በማለት ቅሬታቸውን ተናግረዋል፡፡ 

የጦማሪያኑ ጠበቃ አቶ አመሀ መኰንን ‹‹ዳኞች እንዲሟሉ መተባበር ያለብን ነገር ካለ እንተባበር ወይም ለፍርድ ቤቱ አስተዳደር እናመልክት፤›› የሚል ሐሳብ ለዳኛ ዘሪሁን አቅርበዋል፡፡ ዳኛው በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹የሚቻል ከሆነ ሞክሩ፤›› ብለዋል፡፡ እሳቸውም ብይኑ ቢሰጥ እንደሚመርጡ፣ ተጠርጣሪዎቹን ዓይናቸውን ባያዩ ደስ እንደሚላቸውና (በተደጋጋሚ በመመላለሳቸው) በግላቸው እንደሚከብዳቸው ተናግረዋል፡፡ 

ያልተሟሉት ዳኞች በተለያዩ ምክንያቶች መቅረታቸውን በመጠቆም፣ እንደተሟሉ እስከ መስከረም 10 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ ለማረሚያ ቤቱ ተነግሮ ብይኑ ሊሰጥ እንደሚችል በጽሕፈት ቤት አስታውቀዋል፡፡

 

በቁጥጥር ሥር የዋሉት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ነው

የጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ጋሕነን) ተብሎ በሚጠራው የሽብር ቡድን ውስጥ አባል ከሆኑትና በካናዳ፣ በእንግሊዝ፣ በኤርትራና በተለያዩ አገሮች ከሚገኙ አባላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ የጋምቤላን ክልልን ለመገንጠል ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋል የተባሉ ሦስት ተጠርጣሪዎች ጳጉሜን 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ተከሰሱ፡፡

የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ተረኛ ችሎት ክስ የመሠረተባቸው ተጠርጣሪዎች ኦሞት አጉዋ ኦክዋይ፣ አሽኔ አስቲን ቲቶይክና ጀማል ዑመር ሆጃሌ የሚባሉ ናቸው፡፡ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ከስድስት ወራት በፊት የሽብር ቡድን የተባለው ጋሕነን ኬንያ ናይሮቢ በሚያካሂደው ስብሰባ ላይ ለመካፈል ሲሄዱ፣ መጋቢት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መሆኑን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

አንደኛው ተከሳሽ ኦሞት አጉዋ ኦክዋይ ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ ‹‹የጋምቤላን ክልል ከፌዴሬሽኑ መገንጠል›› የሚል ፖለቲካዊ ግብ በማስቀመጥ፣ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለማፈራረስ የአገር ውስጥ አስተባባሪ በመሆን ሲንቀሳቀስ እንደነበር በክሱ ተገልጿል፡፡ የሽብር ቡድኑ ከፍተኛ አመራር ከሆነውና በደቡብ ሱዳን ከሚገኘው ኡቺች ከሚባለው ግለሰብ ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ ኤርትራ ውስጥ ወታደራዊ ሥልጠና የወሰዱ አባላትን ወደ ጋምቤላ እንዲልክለት በማድረግ፣ የሽብር ቡድኑን ተልዕኮ እንዲያስፈጽሙ በጋምቤላ ልዩ የፖሊስ አባላት ውስጥ እንዲቀጠሩ ማድረጉንም አክሏል፡፡

ተከሳሹ በጋምቤላ ከተማ ውስጥም የቡድኑን አባላት በመሰብሰብና አመራር በመስጠት፣ እንግሊዝ ለንደን ውስጥ ከሚኖረውና ከፍተኛ አመራር ከሆነው ኝኬው አቡላ ከሚባል ግለሰብ ጋር በኢሜል በመገናኘት የአባላቱ ቁጥር እንዲጨምር መጠየቁን ክሱ ያስረዳል፡፡ ኝኬው አቦላ በውጭ አገር የሚገኙ ጋዜጠኞች አኝዋክ ዞን ሄደው መረጃ እንዳይሰበስቡ የኢትዮጵያ መንግሥት የከለከለ መሆኑን ለኦሞት ገልጾለት ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ አምስት ሰዎች፣ ከጋምቤላ አኝዋክ ዞን የቡድኑ አባላት፣ ከደቡብ ኦሞ አሥር ሰዎችን መልምሎ ኬንያ በሚደረገው የቡድኑ ስብሰባ ላይ እንዲሳተፉ እንዲያደረግ ባዘዘው መሠረት፣ መልዕክት በማስተላለፍና በማደራጀት ተግባር ላይ መሳተፉን ክሱ ያብራራል፡፡ ለሽብር ተግባር ማስፈጸሚያ 3,000 የእንግሊዝ ፓውንድ የተላከለት መሆኑንም አክሏል፡፡

ሁለተኛው ተከሳሽ አሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት ውስጥ በሚኖረው የሽብር ቡድኑ ከፍተኛ አመራር በሆነውና በቅጽል ስሙ ኡጆ በሚባለው ግለሰብ አማካይነት በ2006 ዓ.ም. የሽብር ቡድኑ አባል ሆኖ መመልመሉን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡ ከዚያም እንግሊዝ አገር ከሚኖረው የሽብር ቡድኑ አባል ኝኬው አቡላ ጋር በኢሜል በመገናኘት፣ ‹‹የጋምቤላን ክልል ከሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች በመገንጠል ራሱን የቻለ ሉአላዊነት አገር መመሥረት›› በሚለው ሐሳቡ ተስማምቶ፣ በማጃንግ ዞን የሚኖሩ የማጃንግ ብሔርና ደገኞች መካከል በተፈጠረው አለመግባባት፣ የማጃንግ ብሔሮች ተጐድተው እያለ፣ መንግሥት ዕርምጃ የወሰደው በማጃንግ ከፍተኛ አመራሮችና በጋምቤላ ክልል የልዩ ኃይል ፖሊስ ላይ ብቻ እንደሆነ በመግለጽ፣ ሐሰተኛ መረጃ ለሽብር ቡድኑ ያቀብል እንደነበር በክሱ ተብራርቷል፡፡ 

ተከሳሹ የአገር ውስጥ ከፍተኛ አመራር ከሆነው አንደኛ ተከሳሽ ኦሞት ጋር በስልክ ግንኙነት በማድረግ ቀኑ በትክክል ባልታወቀበት የካቲት ወር 2007 ዓ.ም. አራት ኪሎ አካባቢ በመገናኘት፣ ኑዌሮች ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመመሳጠር የሰብዓዊና የዴሞክራሲ መብት ጥሰት እያደረሱ መሆኑን፣ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ለማዳረስ የጋሕነን ከፍተኛ አመራሮች በኬንያ ናይሮቢ በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ እንዲገኝ መመካከራቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡ መንግሥት በጋምቤላ ነባር ብሔረሰቦች፣ በተለይም በማጃንግ ላይ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን እየፈጸመ መሆኑንና በክልሉ የመሬት ወረራ እያደረገ መሆኑን ለማስገንዘብ ‹‹Deforstation, Dis-Possission and Displacement of Gambella in General and Major People in Particular›› የሚል ጥናታዊ ጽሑፍ በስብሰባው ላይ እንዲያቀርብ ተሰጥቶት እንደነበር ክሱ ያብራራል፡፡ 

ሦስተኛው ተከሳሽ ደግሞ በጥቅምት ወር 2006 ዓ.ም. ‹‹የአካባቢ ግንኙነትና ጥበቃ›› በሚል ሽፋን በኬንያ ናይሮቢ የሽብር ቡድኑ በሚያደርገው ስብሰባ ላይ በመገኘት፣ መንግሥት የአካባቢው ተወላጆችን ከመሬታቸው በማፈናቀል ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ለቡድኑ አመራሮች መረጃ በመስጠት 8,800 ብር መቀበሉን የተመሠረተበት ክስ ይገልጻል፡፡ በስብሰባው ላይ እንደሚገኝ ለአንደኛ ተከሳሽ ማረጋገጫ በመስጠቱና በመገኘቱ 6,039 ብር መቀበሉንም አክሏል፡፡

በአጠቃላይ ሁሉም ተጠርጣሪ ተከሳሾች የሽብር ቡድኑ በኬንያ ናይሮቢ በሚያደርገው ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ለመሄድ መጋቢት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውለው፣ ላለፉት ስድስት ወራት ምርመራ ሲደረግባቸው ሰንብተው ጳጉሜን 2 ቀን 2007 ዓ.ም. በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ በአመራርነት፣ በማናቸውም መልኩ መሳተፍና ድጋፍ መስጠት ወንጀል እንደ ቅደም ተከተላቸው ክስ ተመሥርቶባቸዋል፡፡        

 

መንግሥት ሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለመጀመር ታሳቢ ካደረጋቸው መሥፈርቶች መካከል አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በነጠላ አኃዝ ውስጥ ይሆናል የሚል ቢሆንም፣ በሐምሌ ወር የጀመረው ባለሁለት አኃዝ የዋጋ ግሽበት በነሐሴ ወርም 11.6 በመቶ ማደጉ ተገለጸ፡፡

ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለሥልጣን ነሐሴ 28 ቀን 2007 ዓ.ም. ያወጣው የነሐሴ ወር አገር አቀፍ የሸማቾች ዋጋ መመዘኛ ኢንዴክስ እንደሚያሳየው፣ የነሐሴ ወር አገር አቀፍ ጠቅላላ የችርቻሮ ዋጋ ኢንዴክስ ከ2006 ዓ.ም. ነሐሴ ወር ጋር ሲነፃፀር 11.6 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

 ለዚህ ጭማሪ ምክንያት የሆኑት የምግብና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች 14.7 ከመቶ፣ መጠጥ፣ ሲጋራና ትምባሆ 7.8 በመቶ፣ ልብስና መጫሚያ 8.9 በመቶ፣ የቤት ኪራይ፣ የቤት መሣሪያ ዕቃዎች፣ ውኃና ኢነርጂ 11.1 በመቶ ዋጋቸው በመጨመሩ እንደሆነ ኢንዴክሱ ያስረዳል፡፡

በተጨማሪም የቤት ዕቃዎች፣ የቤት ማስጌጫዎች፣ የቤት ቁሳቁስና የቤት ሠራተኛ ደመወዝ 7.0 ከመቶ፣ ሕክምና 4.1 ከመቶ፣ ኮሙዩኒኬሽን (መገናኛ) 2.7 ከመቶ፣ ሬስቶራንትና ሆቴሎች 7.7 በመቶና ሌሎች ዕቃዎችና አገልግሎቶች 4.3 ከመቶ ጭማሪ በማሳየታቸው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ 11.6 በመቶ ሊሆን መቻሉን ባለሥልጣኑ ያስረዳል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ ለታየው የ11.6 በመቶ የዋጋ ዕድገት ምክንያት ከሆኑት መካከል ዋነኛው አብዛኞቹ የምግብ ዓይነቶች ጭማሪ በማሳየታቸው መሆኑን፣ የባለሥልጣኑ የነሐሴ ወር የዋጋ መመዘኛ ኢንዴክስ ሪፖርት ይገልጻል፡፡

ከእነዚህም መካከል ሥጋ 10.7 በመቶ፣ ወተት፣ አይብና እንቁላል በ15.9 በመቶ፣ አትክልት፣ ጥራጥሬ፣ ድንችና ሌሎች የሥራ ሥር ምግቦች 26.7 በመቶ፣ ስኳር፣ ማርና ቸኮሌት 2.4 በመቶ፣ እንዲሁም ሌሎች ምግቦች 61.4 ከመቶ ዕድገት በየኢንዴክሶቻቸው ላይ ማስመዝገባቸውን ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡ 

በሌላ በኩል ዳቦና እህል 0.1 በመቶና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች 12.4 ከመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡

የነሐሴ ወር 2007 ዓ.ም. የአገር አቀፍ ጠቅላላ ችርቻሮ ዋጋ መመዘኛ ኢንዴክስ ከ2006 ዓ.ም. ነሐሴ ወር ሲነፃፀር በ11.6 በመቶ ጭማሪ ለማሳየቱ አስተዋጽኦ ካደረጉት መካከል አዲስ አበባ 15.5 በመቶ፣ አፋር 18.5 በመቶ፣ አማራ 10.0 በመቶ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ 9.0 በመቶ፣ ድሬዳዋ 3.9 በመቶ፣ ጋምቤላ 6.8 በመቶ፣ ደቡብ ክልል 6.8 በመቶ፣ ሶማሌ 8.3 በመቶና ትግራይ 6.0 በመቶ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

መንግሥት ሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ግቦችን ሲያቅድ መነሻ ካደረጋቸው ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች መካከል አንዱ የዋጋ ግሽበት በነጠላ አኃዝ ሥር መሆኑን ነበር፡፡ በእርግጥም የዋጋ ግሽበት ላለፉት ሁለት ዓመታት ባለሁለት አኃዝ ዕድገት ጭማሪ አድርጎ አያውቅም፡፡ ይሁን እንጂ በ2007 ዓ.ም. ሐምሌ ወር የዋጋ ግሽበቱ ወደ 11.9 በመቶ ከፍ ብሎ ነበር፡፡ ከስታትስቲክስ ባለሥልጣን መረጃ ማየት እንደሚቻለው፣ የነሐሴ ወር የዋጋ ግሽበት መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል፡፡

 

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ለብዙ ኢትዮጵያዊያን፤ የኤርትራ ከኢትዮጵያ መገንጠልና የአገነጣጠሏ ሁኔታ፤ የውስጥ አካላችንን ያኔም፣ አሁንም እያንጠረጠረው ነው። በርግጥ በየኪሳችን ያለ የየግል ንብረት ስለተነጠቀብን አይደለም። በኤርትራ መገንጠል የቀረብን የግል ጥቅም ስለነበረም አይደለም። የሀገር ጉዳይ፤ ከንብረት፣ ከአባትና እናት፣ ከኑሮ የበለጠ ክብር የምንሠጠው ነው። በወቅቱ የቅርብ ጓደኛዬ …

የኤርትራ ጉዳይ – አንዱዓለም ተፈራ Read more »

ሰንደቅ ጋዜጣ ላይ የፌዴራል ጉዳዬች ሚኒስትሩ ዶክተር ሽፈራው ከኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚነት ተነሱ የሚል ዜና አነበብኩ፡፡ አዋሳ ከሚገኝ አንድ የጤና ኮሌጅ ዲንነት ወንጌላዊ ተልዕኮዋቸውን በሚገባ ወደሚወጡበት የመለስ ዜናዊ እጅ ስራ ወደሆነው ፌዴራል ጉዳዬች ሚኒስተር በቀጥታ ተዘዋውረው የመጡት ዶ/ር ሽፈራው ወንጌላዊ ተልዕኮዋቸውን …

የፌዴራል ጉዳዬች ሚኒስትሩ ዶክተር ሽፈራው ከኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚነት ተነሱ Read more »

ጷግሜን ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስልጣን ላይ ያለውን የኢህአዴግ አገዛዝ በሃይል ለማስወገድ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ” አገር አድን ሰራዊት” ማቋቋማቸውን ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች እየቀረቡ ነው። የአፋር ድርጅት የጋራ ንቅናቄ፣ የትግራይ ህዝብ የጋራ ንቅናቄ፣ የአማራ ዲሞክራሲ ሃይሎች ንቅናቄ እና አርበኞች ገንቦት 7 ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ በጋራ የአገር አድን ንቅናቄ የሚባል ድርጅት መመስረታቸውን ጳጉሜ 3 …

ጷግሜን ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቃቢ ህግ ምስክሮችን ያሰማው በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ችሎት ላይ ሲሆን፣ በተከሳሾች ወርቅዬ ምስጋናው፣ አማረ መስፍን፣ ቢሆኝ አለናና አትርሳው አስቻለው ላይ 6 ምስክሮች ቀርበው መስክረዋል። ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው አቃቢ ህግ ያቀረባቸው 13 ምስክሮች ማን ላይ እንደሚመሰክሩ ግልጽ አድርጎ ባለማቅረቡ ጠበቆች ተቃውሞ አስምተዋል። አንደኛው ምስክር በ12ኛው ተከሳሽ አትርሳው …

ጷግሜን ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ለልዩ ልዩ ባለሙያዎች ባቀረበው የቀጣይ አምስት አመታት የትምህርት ዕቅድ ውይይት ላይ፣ ባለፉት አመታት የትምህርትን ስራ በትምህርት ባለሙያዎች ሳይሆን ለጉዳዩ ዕውቅና በሌላቸው የፖለቲካ ሰዎች እንዲመራ መደረጉና የዘመቻ ስራ ላይ ማተኮሩ የትምህርቱ ጥራት ለመውደቁ ዋና መንስዔ መሆኑን የስብሰባው ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡ በውይይቱ ላይ …

ጷግሜን ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰኞ ዕለት በሶማሊያ ጌዶ ግዛት የቀድሞ አስተዳዳሪ የነበሩት ሞሃመድ አብዲ ከሊል ከባድ መሳሪያ ከታጠቁ አጃቢዎቻቸው ጋር በመሆን ጋርባሃሬ ከተማ ሲገቡ አካባቢው የጦርነት ድባብ ውስጥ መውደቁን የከተማዋ ነዋሪዎች እማኝነታቸውን ሰጡ። የገርባሃሬ ነዋሪዎች በኢትዮጵያ ሰራዊት የሚደገፈው አዲሱ የጁባላንድ አስተዳዳሪ አህመድ ማዶቤ በከተማዋ በኃላፊነት መሾሙ እየታወቀ የሞሃመድ ከሊል ወደ ከተማዋ …

  • ‹‹አቃቤ ህግ አዛዥ ናዛዥ ሆኗል›› ጠበቃው … • ‹‹አርበኛው ግንባር የሚገኘው ሻዕቢያ ነው›› ምስክር …. በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር :- የፌደራል አቃቤ ህግ ዛሬ ጳግሜ 3/2007 ዓ.ም በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ …

አዛዥ ናዛዥ አቃቤ ህግ በእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮነን መዝገብ 6 ምስክሮችን አሰማ :: Read more »

የፖለቲካ አስተዳደሩ ካልተወገደ ድህነትን እና የኑሮ ውድነትን መቅረፍ አይቻልም:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎EthiopianEconomy‬ ‪#‎EthiopianOppositionParties‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የኑሮ ውድነትና የፖለቲካ አስተዳደር እጦት ተወራራሽ ናቸው:: በሃገሪቱ የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ ከ2008 መግቢያ ጀምሮ በተለያዩ ምግብ ነክ በሆኑ እና ምንብ ነክ ባልሆኑ …

የፖለቲካ አስተዳደሩ ካልተወገደ ድህነትን እና የኑሮ ውድነትን መቅረፍ አይቻልም:: (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

  ኤርትራ ‹‹የኢትዮጲ ያ አይነ ውሃ አላማረኝም ›› ማለቷ ተሰማ! (አሌክስ አብርሃም) የኤርትራ የኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ትናንት መግለጫ አውጥቶ ነበር ….እናም በመግለጫው ኤርትራ ‹‹በኢትዮጲያ እየተደረገባት ያለው ዛቻና ወታደራዊ ትንኮሳ እየጨመረ ነው …ማስፈራሪያውም በርክቷል ›› መባሉን ዘ ገልፍ ቱዴይ ዘግቦታል ፡፡ የኤርትራው …

ኤርትራ ‹‹የኢትዮጲያ አይነ ውሃ አላማረኝም ›› ማለቷ ተሰማ! (አሌክስ አብርሃም) Read more »