በነጻ የተሰናበተው ሃብታሙ አያሌው ያልተፈታበት ጉዳይ ነገ በልደታ ችሎት ይታያል።

በነጻ የተሰናበተው ሃብታሙ አያሌው ያልተፈታበት ጉዳይ ነገ በልደታ ችሎት ይታያል።

የወያነ ጉጅሌ አገዛዝ በፈጠራ የአሸባሪነት ክስ አቅርቦባቸው በራሱ ችሎት እና አቃቢ ሕግ ሊፈርድባቸው ሲዘጋጅ አለም አቀፍ ጫና በመብዛቱ በነጻ እንዲፈቱ በካንጋሮው ፍርድ ቤት የተወሰነላቸው ሃብታሙ አያሌው እና አብርሃም ሰሎሞን እስካሁን እስር ቤቱ ያልፈታቸው ሲሆን ሀብታሙ አያሌውን ፍርድ ቤት ባዘዘው መሰረት ለምን እስር ቤቱ እንዳልፈታው እንዲያስረዳ ዛሬ መጥሪያ ደርሶታል፡፡ ነገ ጠዋት በ2፡30 ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡የፍርድ ቤት ትእዛዝ ባለማክበር አልተፈቱም የሚለውን የመጥሪያ ጉዳዩ በችሎት ለማየት እስር ቤቱ የሚስጠው ምክንያት እየተጠበቀ ነው ሲሉ የእስረኞች ቤተሰቦች ይናገራሉ።

ሃብታሙ አያሌው የሽዋስ አሰፋ ዳንኤል ሺበሺ እና አብርሃ ደስታ እንዲሁም አብርሃም ሰሎሞን በቀረበባቸው የፈጠራ የአሸባሪነት ክስ ከጥርጣረ ውጪ ማስረጃ የለም በመባሉ ከከፍተኛ ስቃይ እና እስር በሁላ በነጻ ተሰናብታችዋል ቢባሉም የእስር ቤቱ ሃላፊዎች አግተዋቸው ይገኛሉ።አቃቢ ሕግ ይግባኝ ሊል ነው ቢባልም እስካሁም የይግባኝ ጉዳይን በተመለከተ የወጣ መረጃ ይሁን ለተከሳሾች የደረሰ ወረቀት እንዳልተገኘ ታውቅዋል።