የኢሳያስ (የሻቢያ) ስታራተጂ፤ ኢትዮጰያን ለመታደግ ወይስ እንደገና ለመግደል?
ከአክሊሉ ወንድአፈረው
የተለያዩ ድርጅቶች የወያኔ/ ኢህአዴግን መንግስት በትጥቅ ሀይል ለማስወገድ በአስመራ ስልጣን ከያዘው ሻቢያ ጋር መቀራረብና ተባብሮ መስራትን መርጠዋል። ይህን በተመለከተ ባንድ በኩል የወያኔ/ኢህአዴግን የግፍ ስርአት ለማስወገድ ከማንም ጋር ቢሆን ማበር አስፈልጊ ነው የሚሉ ሲኖሩ ሌሎች ደግሞ የወያኔን የግፍ ስርአት ማስወገድ አስፈላጊ ሲሆን ሻቢያ ኢትዮጵያን በተመለከተ የሚከተለው ፖሊሲ በብሄራዊ ጥቅማችን ላይ እና በመጻኢው ነጻነታችን ላይ እጅግ ታላቅ አደጋን ስለሚያሰከትል ድንገት ብቅ ያለው ተቋርቋሪነት ከምን የመነጨ እንደሆነ ጠንቅቆ መረዳትና ታላቅ ስህተት ከመፈጸም መታቀብ ያሻል ይላሉ:: በዚህ ጽሁፌ የሻቢያ “ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪነት” በተግባር ሲታይ ምን ማለት እንደሆነ ለማሳየት በጥቂት ውሱን ጉዳዮች ላይ በማተኮር ያለኝን አመለካከት አካፍላለሁ። ጽሁፉን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ