ብሄራዊ ባንክ ክኤሌክትሪክ ሃይል ሽያጭ የተገኘ የውጪ ምንዛሬ አልደረሰኝም አለ::(ምንሊክ ሳልሳዊ) #Ethiopia በኤሌክትሪክ መቋረጥ በሃገር ወስጥ የኢንዱስትሪው መስክ ብቻ ከ40 ሚሊዮን ዶላር በላይ ኪሳራ ደርሷል:: የወያኔው አገዛዝ ለጎረቤት አገሮች ከሚሸጠው የኤሌክትሪክ ሃይል በ9 ወር የተገኘው 35 ሚሊዮን ዶላር በላይ …

ብሄራዊ ባንክ ክኤሌክትሪክ ሃይል ሽያጭ የተገኘ የውጪ ምንዛሬ አልደረሰኝም አለ::(ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

ኤርትራ የኢትዮጵያ ወረራ ያሰጋኛል አለች

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ጳጉሜን 3 ቀን 2007 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ ኢትዮጵያ ኤርትራን ለመውረር እያስፈራራች መሆኗን አስታውቋል፡፡ ምንም እንኳ የመረጃው ምንጭ ማን እንደሆነ የኤርትራ መንግሥት ባይናገርም፣

ኢትዮጵያ ኤርትራን ለመውረር ከአሜሪካ ይሁንታ ማግኘቷንና ኢትዮጵያም በይፋ መግለጿን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ምንም እንኳ ከወራት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ኤርትራን በተመለከተ በፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ፣ የኤርትራ መንግሥት ኢትዮጵያንና ሌሎች የጎረቤት አገሮችን ለማተራመስ የያዘውን ስትራቴጂ የማይተው ከሆነ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ተገዶ ዕርምጃ እንደሚወስደና የኢትዮጵያን ሕዝብ እንደሚያሳውቅ መናገራቸው አይዘነጋም፡፡ በወቅቱ የኤርትራ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ምንም ሳይል አሁን የኢትዮጵያ ወረራ ያሰጋኛል ማለቱ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ በምሥሉ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ ዩኑስ በኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ቀን አከባበር ሥነ ሥርዓት በቅርቡ በተካሄደበት ወቅት የሚታዩ ሲሆን፣ ዝርዝር ዘገባው ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ ወይም በ ፖለትካ ገጽ ላይ ይመልከቱ፡፡ 

 

ጦማሪያኑ ለአራተኛ ጊዜ ለብይን መቀጠራቸውን ተቃወሙ

‹‹አንድ ዳኛ ምንም ማድረግ አይችልም›› ዳኛ ዘሪሁን ደሳለኝ

‹‹ከዳኞች ጋር ምንም ችግር የለብንም ከማን ጋር እንደተጣላን ገብቶናል›› በእስር ላይ ያሉ ጦማሪያን

በተጠረጠሩበት የሽብር ተግባር ወንጀል ክስ ከተመሠረተባቸው በኋላ የከሳሽ ዓቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ ቀርቦባቸው ለብይን የተቀጠሩት አራት ጦማሪያን፣ ለአራተኛ ጊዜ ጳጉሜን 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱን ተቃወሙ፡፡ 

ተከሳሾቹ ጦማሪያን ናትናኤል ፈለቀ፣ አቤል ዋበላ፣ አጥናፍ ብርሃኔና በፍቃዱ ኃይሉ ጳጉሜን 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ብይን እንደሚሰጥ የጠበቁ ቢሆንም፣ ጉዳያቸው በሦስት ዳኞች የሚታይ ከመሆኑ አንፃር በዕለቱ አንድ ዳኛ አቶ ዘሪሁን ደሳለኝ ብቻ የተገኙ በመሆናቸው ብይኑ ሳይሰጥ ቀርቷል፡፡ ብይኑ ተሠርቶ የተጠናቀቀ ቢሆንም፣ ዳኞች ባለመሟላታቸውና በመዝገቡ ላይ ባለመፈረማቸው ብይኑ ሊነገር እንደማይችል ዳኛ ዘሪሁን ገልጸዋል፡፡ 

በዳኞች አለመሟላት ለሁለተኛ ጊዜ መቀጠሩ ያበሳጫቸው ተከሳሾቹ፣ ‹‹እኛ ከዳኞች ጋር ምንም ችግር የለብንም፡፡ ከማን ጋር እንደተጣላን ገብቶናል፡፡ የምንፈልገው ቁርጥ ያለው እንዲነገረን ነው፡፡ ወይ በነፃ እንሰናበት ወይም ተከላከሉ እንባል፡፡ ብይን ለመስጠት በሚቀጠሩት ቀናት መካከል ያለው ጊዜ ለእኛ ሕመም ነው፤›› በማለት ቅሬታቸውን ተናግረዋል፡፡ 

የጦማሪያኑ ጠበቃ አቶ አመሀ መኰንን ‹‹ዳኞች እንዲሟሉ መተባበር ያለብን ነገር ካለ እንተባበር ወይም ለፍርድ ቤቱ አስተዳደር እናመልክት፤›› የሚል ሐሳብ ለዳኛ ዘሪሁን አቅርበዋል፡፡ ዳኛው በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹የሚቻል ከሆነ ሞክሩ፤›› ብለዋል፡፡ እሳቸውም ብይኑ ቢሰጥ እንደሚመርጡ፣ ተጠርጣሪዎቹን ዓይናቸውን ባያዩ ደስ እንደሚላቸውና (በተደጋጋሚ በመመላለሳቸው) በግላቸው እንደሚከብዳቸው ተናግረዋል፡፡ 

ያልተሟሉት ዳኞች በተለያዩ ምክንያቶች መቅረታቸውን በመጠቆም፣ እንደተሟሉ እስከ መስከረም 10 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ ለማረሚያ ቤቱ ተነግሮ ብይኑ ሊሰጥ እንደሚችል በጽሕፈት ቤት አስታውቀዋል፡፡

 

በቁጥጥር ሥር የዋሉት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ነው

የጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ጋሕነን) ተብሎ በሚጠራው የሽብር ቡድን ውስጥ አባል ከሆኑትና በካናዳ፣ በእንግሊዝ፣ በኤርትራና በተለያዩ አገሮች ከሚገኙ አባላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ የጋምቤላን ክልልን ለመገንጠል ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋል የተባሉ ሦስት ተጠርጣሪዎች ጳጉሜን 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ተከሰሱ፡፡

የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ተረኛ ችሎት ክስ የመሠረተባቸው ተጠርጣሪዎች ኦሞት አጉዋ ኦክዋይ፣ አሽኔ አስቲን ቲቶይክና ጀማል ዑመር ሆጃሌ የሚባሉ ናቸው፡፡ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ከስድስት ወራት በፊት የሽብር ቡድን የተባለው ጋሕነን ኬንያ ናይሮቢ በሚያካሂደው ስብሰባ ላይ ለመካፈል ሲሄዱ፣ መጋቢት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መሆኑን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

አንደኛው ተከሳሽ ኦሞት አጉዋ ኦክዋይ ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ ‹‹የጋምቤላን ክልል ከፌዴሬሽኑ መገንጠል›› የሚል ፖለቲካዊ ግብ በማስቀመጥ፣ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለማፈራረስ የአገር ውስጥ አስተባባሪ በመሆን ሲንቀሳቀስ እንደነበር በክሱ ተገልጿል፡፡ የሽብር ቡድኑ ከፍተኛ አመራር ከሆነውና በደቡብ ሱዳን ከሚገኘው ኡቺች ከሚባለው ግለሰብ ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ ኤርትራ ውስጥ ወታደራዊ ሥልጠና የወሰዱ አባላትን ወደ ጋምቤላ እንዲልክለት በማድረግ፣ የሽብር ቡድኑን ተልዕኮ እንዲያስፈጽሙ በጋምቤላ ልዩ የፖሊስ አባላት ውስጥ እንዲቀጠሩ ማድረጉንም አክሏል፡፡

ተከሳሹ በጋምቤላ ከተማ ውስጥም የቡድኑን አባላት በመሰብሰብና አመራር በመስጠት፣ እንግሊዝ ለንደን ውስጥ ከሚኖረውና ከፍተኛ አመራር ከሆነው ኝኬው አቡላ ከሚባል ግለሰብ ጋር በኢሜል በመገናኘት የአባላቱ ቁጥር እንዲጨምር መጠየቁን ክሱ ያስረዳል፡፡ ኝኬው አቦላ በውጭ አገር የሚገኙ ጋዜጠኞች አኝዋክ ዞን ሄደው መረጃ እንዳይሰበስቡ የኢትዮጵያ መንግሥት የከለከለ መሆኑን ለኦሞት ገልጾለት ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ አምስት ሰዎች፣ ከጋምቤላ አኝዋክ ዞን የቡድኑ አባላት፣ ከደቡብ ኦሞ አሥር ሰዎችን መልምሎ ኬንያ በሚደረገው የቡድኑ ስብሰባ ላይ እንዲሳተፉ እንዲያደረግ ባዘዘው መሠረት፣ መልዕክት በማስተላለፍና በማደራጀት ተግባር ላይ መሳተፉን ክሱ ያብራራል፡፡ ለሽብር ተግባር ማስፈጸሚያ 3,000 የእንግሊዝ ፓውንድ የተላከለት መሆኑንም አክሏል፡፡

ሁለተኛው ተከሳሽ አሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት ውስጥ በሚኖረው የሽብር ቡድኑ ከፍተኛ አመራር በሆነውና በቅጽል ስሙ ኡጆ በሚባለው ግለሰብ አማካይነት በ2006 ዓ.ም. የሽብር ቡድኑ አባል ሆኖ መመልመሉን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡ ከዚያም እንግሊዝ አገር ከሚኖረው የሽብር ቡድኑ አባል ኝኬው አቡላ ጋር በኢሜል በመገናኘት፣ ‹‹የጋምቤላን ክልል ከሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች በመገንጠል ራሱን የቻለ ሉአላዊነት አገር መመሥረት›› በሚለው ሐሳቡ ተስማምቶ፣ በማጃንግ ዞን የሚኖሩ የማጃንግ ብሔርና ደገኞች መካከል በተፈጠረው አለመግባባት፣ የማጃንግ ብሔሮች ተጐድተው እያለ፣ መንግሥት ዕርምጃ የወሰደው በማጃንግ ከፍተኛ አመራሮችና በጋምቤላ ክልል የልዩ ኃይል ፖሊስ ላይ ብቻ እንደሆነ በመግለጽ፣ ሐሰተኛ መረጃ ለሽብር ቡድኑ ያቀብል እንደነበር በክሱ ተብራርቷል፡፡ 

ተከሳሹ የአገር ውስጥ ከፍተኛ አመራር ከሆነው አንደኛ ተከሳሽ ኦሞት ጋር በስልክ ግንኙነት በማድረግ ቀኑ በትክክል ባልታወቀበት የካቲት ወር 2007 ዓ.ም. አራት ኪሎ አካባቢ በመገናኘት፣ ኑዌሮች ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመመሳጠር የሰብዓዊና የዴሞክራሲ መብት ጥሰት እያደረሱ መሆኑን፣ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ለማዳረስ የጋሕነን ከፍተኛ አመራሮች በኬንያ ናይሮቢ በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ እንዲገኝ መመካከራቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡ መንግሥት በጋምቤላ ነባር ብሔረሰቦች፣ በተለይም በማጃንግ ላይ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን እየፈጸመ መሆኑንና በክልሉ የመሬት ወረራ እያደረገ መሆኑን ለማስገንዘብ ‹‹Deforstation, Dis-Possission and Displacement of Gambella in General and Major People in Particular›› የሚል ጥናታዊ ጽሑፍ በስብሰባው ላይ እንዲያቀርብ ተሰጥቶት እንደነበር ክሱ ያብራራል፡፡ 

ሦስተኛው ተከሳሽ ደግሞ በጥቅምት ወር 2006 ዓ.ም. ‹‹የአካባቢ ግንኙነትና ጥበቃ›› በሚል ሽፋን በኬንያ ናይሮቢ የሽብር ቡድኑ በሚያደርገው ስብሰባ ላይ በመገኘት፣ መንግሥት የአካባቢው ተወላጆችን ከመሬታቸው በማፈናቀል ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ለቡድኑ አመራሮች መረጃ በመስጠት 8,800 ብር መቀበሉን የተመሠረተበት ክስ ይገልጻል፡፡ በስብሰባው ላይ እንደሚገኝ ለአንደኛ ተከሳሽ ማረጋገጫ በመስጠቱና በመገኘቱ 6,039 ብር መቀበሉንም አክሏል፡፡

በአጠቃላይ ሁሉም ተጠርጣሪ ተከሳሾች የሽብር ቡድኑ በኬንያ ናይሮቢ በሚያደርገው ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ለመሄድ መጋቢት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውለው፣ ላለፉት ስድስት ወራት ምርመራ ሲደረግባቸው ሰንብተው ጳጉሜን 2 ቀን 2007 ዓ.ም. በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ በአመራርነት፣ በማናቸውም መልኩ መሳተፍና ድጋፍ መስጠት ወንጀል እንደ ቅደም ተከተላቸው ክስ ተመሥርቶባቸዋል፡፡        

 

መንግሥት ሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለመጀመር ታሳቢ ካደረጋቸው መሥፈርቶች መካከል አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በነጠላ አኃዝ ውስጥ ይሆናል የሚል ቢሆንም፣ በሐምሌ ወር የጀመረው ባለሁለት አኃዝ የዋጋ ግሽበት በነሐሴ ወርም 11.6 በመቶ ማደጉ ተገለጸ፡፡

ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለሥልጣን ነሐሴ 28 ቀን 2007 ዓ.ም. ያወጣው የነሐሴ ወር አገር አቀፍ የሸማቾች ዋጋ መመዘኛ ኢንዴክስ እንደሚያሳየው፣ የነሐሴ ወር አገር አቀፍ ጠቅላላ የችርቻሮ ዋጋ ኢንዴክስ ከ2006 ዓ.ም. ነሐሴ ወር ጋር ሲነፃፀር 11.6 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

 ለዚህ ጭማሪ ምክንያት የሆኑት የምግብና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች 14.7 ከመቶ፣ መጠጥ፣ ሲጋራና ትምባሆ 7.8 በመቶ፣ ልብስና መጫሚያ 8.9 በመቶ፣ የቤት ኪራይ፣ የቤት መሣሪያ ዕቃዎች፣ ውኃና ኢነርጂ 11.1 በመቶ ዋጋቸው በመጨመሩ እንደሆነ ኢንዴክሱ ያስረዳል፡፡

በተጨማሪም የቤት ዕቃዎች፣ የቤት ማስጌጫዎች፣ የቤት ቁሳቁስና የቤት ሠራተኛ ደመወዝ 7.0 ከመቶ፣ ሕክምና 4.1 ከመቶ፣ ኮሙዩኒኬሽን (መገናኛ) 2.7 ከመቶ፣ ሬስቶራንትና ሆቴሎች 7.7 በመቶና ሌሎች ዕቃዎችና አገልግሎቶች 4.3 ከመቶ ጭማሪ በማሳየታቸው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ 11.6 በመቶ ሊሆን መቻሉን ባለሥልጣኑ ያስረዳል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ ለታየው የ11.6 በመቶ የዋጋ ዕድገት ምክንያት ከሆኑት መካከል ዋነኛው አብዛኞቹ የምግብ ዓይነቶች ጭማሪ በማሳየታቸው መሆኑን፣ የባለሥልጣኑ የነሐሴ ወር የዋጋ መመዘኛ ኢንዴክስ ሪፖርት ይገልጻል፡፡

ከእነዚህም መካከል ሥጋ 10.7 በመቶ፣ ወተት፣ አይብና እንቁላል በ15.9 በመቶ፣ አትክልት፣ ጥራጥሬ፣ ድንችና ሌሎች የሥራ ሥር ምግቦች 26.7 በመቶ፣ ስኳር፣ ማርና ቸኮሌት 2.4 በመቶ፣ እንዲሁም ሌሎች ምግቦች 61.4 ከመቶ ዕድገት በየኢንዴክሶቻቸው ላይ ማስመዝገባቸውን ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡ 

በሌላ በኩል ዳቦና እህል 0.1 በመቶና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች 12.4 ከመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡

የነሐሴ ወር 2007 ዓ.ም. የአገር አቀፍ ጠቅላላ ችርቻሮ ዋጋ መመዘኛ ኢንዴክስ ከ2006 ዓ.ም. ነሐሴ ወር ሲነፃፀር በ11.6 በመቶ ጭማሪ ለማሳየቱ አስተዋጽኦ ካደረጉት መካከል አዲስ አበባ 15.5 በመቶ፣ አፋር 18.5 በመቶ፣ አማራ 10.0 በመቶ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ 9.0 በመቶ፣ ድሬዳዋ 3.9 በመቶ፣ ጋምቤላ 6.8 በመቶ፣ ደቡብ ክልል 6.8 በመቶ፣ ሶማሌ 8.3 በመቶና ትግራይ 6.0 በመቶ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

መንግሥት ሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ግቦችን ሲያቅድ መነሻ ካደረጋቸው ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች መካከል አንዱ የዋጋ ግሽበት በነጠላ አኃዝ ሥር መሆኑን ነበር፡፡ በእርግጥም የዋጋ ግሽበት ላለፉት ሁለት ዓመታት ባለሁለት አኃዝ ዕድገት ጭማሪ አድርጎ አያውቅም፡፡ ይሁን እንጂ በ2007 ዓ.ም. ሐምሌ ወር የዋጋ ግሽበቱ ወደ 11.9 በመቶ ከፍ ብሎ ነበር፡፡ ከስታትስቲክስ ባለሥልጣን መረጃ ማየት እንደሚቻለው፣ የነሐሴ ወር የዋጋ ግሽበት መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል፡፡

 

ሰንደቅ ጋዜጣ ላይ የፌዴራል ጉዳዬች ሚኒስትሩ ዶክተር ሽፈራው ከኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚነት ተነሱ የሚል ዜና አነበብኩ፡፡ አዋሳ ከሚገኝ አንድ የጤና ኮሌጅ ዲንነት ወንጌላዊ ተልዕኮዋቸውን በሚገባ ወደሚወጡበት የመለስ ዜናዊ እጅ ስራ ወደሆነው ፌዴራል ጉዳዬች ሚኒስተር በቀጥታ ተዘዋውረው የመጡት ዶ/ር ሽፈራው ወንጌላዊ ተልዕኮዋቸውን …

የፌዴራል ጉዳዬች ሚኒስትሩ ዶክተር ሽፈራው ከኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚነት ተነሱ Read more »

  • ‹‹አቃቤ ህግ አዛዥ ናዛዥ ሆኗል›› ጠበቃው … • ‹‹አርበኛው ግንባር የሚገኘው ሻዕቢያ ነው›› ምስክር …. በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር :- የፌደራል አቃቤ ህግ ዛሬ ጳግሜ 3/2007 ዓ.ም በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ …

አዛዥ ናዛዥ አቃቤ ህግ በእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮነን መዝገብ 6 ምስክሮችን አሰማ :: Read more »

የፖለቲካ አስተዳደሩ ካልተወገደ ድህነትን እና የኑሮ ውድነትን መቅረፍ አይቻልም:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎EthiopianEconomy‬ ‪#‎EthiopianOppositionParties‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የኑሮ ውድነትና የፖለቲካ አስተዳደር እጦት ተወራራሽ ናቸው:: በሃገሪቱ የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ ከ2008 መግቢያ ጀምሮ በተለያዩ ምግብ ነክ በሆኑ እና ምንብ ነክ ባልሆኑ …

የፖለቲካ አስተዳደሩ ካልተወገደ ድህነትን እና የኑሮ ውድነትን መቅረፍ አይቻልም:: (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

  ኤርትራ ‹‹የኢትዮጲ ያ አይነ ውሃ አላማረኝም ›› ማለቷ ተሰማ! (አሌክስ አብርሃም) የኤርትራ የኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ትናንት መግለጫ አውጥቶ ነበር ….እናም በመግለጫው ኤርትራ ‹‹በኢትዮጲያ እየተደረገባት ያለው ዛቻና ወታደራዊ ትንኮሳ እየጨመረ ነው …ማስፈራሪያውም በርክቷል ›› መባሉን ዘ ገልፍ ቱዴይ ዘግቦታል ፡፡ የኤርትራው …

ኤርትራ ‹‹የኢትዮጲያ አይነ ውሃ አላማረኝም ›› ማለቷ ተሰማ! (አሌክስ አብርሃም) Read more »

ታማኝ መጋዣን አጥብቀህ ጫነው –ሀይላማርያም ደሳለኝ በያዝከው ቀጥል ተባለ ። ለምን ? #Ethiopia የወያኔ ውስጣዊ ችግር ተባብሷል፤ … የቻይና ቀውስ አንደምታ፤ …. ግልገል ጊቤ ሶስት ችግር ፈጣሪ ነው ተባለ የሳውዲ እስር ቤቶች ኢትዮጵያውያንን በገፍና በግፍ ማሰር ቀጠሉ’፤ [youtube http://www.youtube.com/watch?v=TvF7jSH0or8]

የትግላችን መለያ አርማ በአካል እና በጽሑፍ በሁለት መልኩ የሚገለጽ ይሆናል! ድምጻችን ይሰማ! አርማዎቹ ጠቋሚ ጣት እና አንድ ቁጥር ናቸው! ማክሰኞ ጳጉሜ 3/2007 ለዛሬ የትግላችንን መለያ ምልክት ይፋ እንደምናደርግ መግለጻችን ይታወሳል፡፡ በዚሁ መሰረት የሰላማዊ ትግላችን አርማ በአካል እንቅስቃሴ ሲገለጽ የጠቋሚ ጣት …

የትግላችን መለያ አርማ በአካል እና በጽሑፍ በሁለት መልኩ የሚገለጽ ይሆናል! ድምጻችን ይሰማ! Read more »

በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦች ክልል በወላይታ ዞን የወላይታ ሶዶ ከተማ አካባቢ አርሶአደሮች ያለ አግባብ ከይዞታችን ተፈናቅለናል ሲሉ ማማረራቸውን አንድ የዓይን ምስክር ተናገሩ ። ከተማይቱን ለማስፋፋት በተያዘው እቅድ በሺህዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች መኖሪያ ቤቶች እየፈረሱ እና አርሶአደሮቹም ከይዞታቸው እየተፈናቀሉ እንደሆነ ለዶቼቬለ አስረድተዋል። …

የወላይታ ሶዶ አርሶአደሮች ሮሮ እና የከንቲባው ምላሽ Read more »

የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምፅ አድማጮች እና ተመልካቾች አብራችሁን ትቆዩ ዘንድ የአክብሮት ግብዣችንን እነሆ ,,,, #Ethiopia መረጃ ሙሉ ያደርጋል ስለዝህ የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምፅ አድማጮች እና ተመልካቾች ለእለቱ የመራረጥናቸውን ሳምንታዊ ዜናዎች ጣእም ካላቸው ዜማዎች ጋር እንዲሁም ስለሚያገባን እንጦምራለን በሚል መርህ ትኩስ መረጃዎችን በማቅረብ …

የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምፅ አድማጮች እና ተመልካቾች አብራችሁን ትቆዩ ዘንድ የአክብሮት ግብዣችንን እነሆ ,,,, Read more »

ኖርዌጂያዊው የሒልተን ሆቴል ዋና ሥራ አስኪያጅ ነሐሴ 28 ቀን 2007 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ በቂርቆስ ፖሊስ መምርያ ታስረው ከቆዩ ከሰዓታት በኋላ ቃላቸውን ሰጥተው በዋስ ተለቀቁ፡፡ ሚስተር ሀኮን ጋርደር ላርሰን በሆቴሉ በሥራ ላይ እያሉ የፍርድ ቤት የእስር ትዕዛዝ በያዙ ፖሊሶች የተወሰዱት፣ ላለፉት …

የሒልተን ሆቴል ዋና ሥራ አስኪያጅ በቂርቆስ ፖሊስ መምርያ ታስረው ቃላቸውን ሰጥተው በዋስ ተለቀቁ፡፡ Read more »

የዞን9 ጦማርያን ጉዳይ ዳኞች አልተሟሉም በሚል ሰበብ ለ37ተኛ ጊዜ ተቀጥሯል። #Ethiopia #Freezone9bloggers #KangarooCourt በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ለዛሬ በተደጋጋሚ የተላለፈው የብይን ጥበቃ በድጋሚ ዳኞች አልተሟሉም በሚል ሰበብ ለ37ተኛ ጊዜ ተቀጥሯል። በዳኞች አለመሟላት የተነሳ ችሎቱን ማስቻል አልችልም ብለው በቢሮ ተከሳሾችን እና …

የዞን9 ጦማርያን ጉዳይ ዳኞች አልተሟሉም በሚል ሰበብ ለ37ተኛ ጊዜ ተቀጥሯል። Read more »

አዲሱ የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት ስብሰባ ነሃሴ 16ና 17/2007 ዓ.ም በተደረገው የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ አስመራጭ የነበረው ኮሚቴ የብሔራዊ ምክር ቤትን፣ የኢዲትና ምርመራ ኮሚሽን አባላትን ውጤት ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህም መሰረት በጠቅላላ ጉባኤው ምርጫ ከ1ኛ-50ኛ የተመረጡ አባላት እንደ ውጤታቸው 37ቱ ቋሚ …

አዲሱ የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት ጱግሜ 1/2007 ዓ.ም በይፋ ስራውን ጀምሯል፡፡ Read more »

አሜሪካ መንግስት ኦፊሳላዊ ድረ ገጽ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ አስተባባሪነት በዓለም ላይ ለተመረጡ 20 ሴት የፖለቲካ እስረኞች መካከል ሶስት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ዘመቻና ማስታወሻ እየተደረላቸው ነው፡፡ ከዛሬ 20 አመት በፊት ሴቶችን ለማብቃት፣ የጾታ እኩልነትን ለማስፈን እና የልጃ ገረዶችን ሰብዓዊ …

ሶስቱ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ሴት የፖለቲካ እስረኞች በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘመቻ እየተደረላቸው ነው Read more »

በዚህ ሳምንት ሕዝባዊ ስራዎች ይኖሩናል!‪ === ሰኞ ጳጉሜ 2/2007 === ‪ የስራ ካላንደራችንን ላልደረሳቸው ሁሉ በማዳረስ እንረባረብ! -====== ድምፃችን ይሰማ :- 1/ ነገ ማክሰኞ ጳጉሜ 2/2007 የትግላችን መለያ ይፋ ይሆናል! ለአራት አመታት ያክል በሰላማዊነት እና ሕጋዊነት የቆየው ትግላችን ሊገለጽበት እና …

ድምፃችን ይሰማ : በዚህ ሳምንት ሕዝባዊ ስራዎች ይኖሩናል!‪ የትግላችን መለያ ይፋ ይሆናል! የማህበራዊ ቦይኮት የትብብር መንፈግ ዘመቻችንን እንጀምራለን! Read more »

ብዙ ጊዜ ስለተቃራኒ ፆታ ፍቅር መጻፍ ብዙመ አልወድም ወይም አይመቸኝም ይህ ተከታዩን በቂሊንጦ እስር ቤት ከሰሞኑ የተፈፀመው የቀለበት ስነስርዓት ስሠማ ግን የሆነ የተለየ ነገር ሆኖ ስላገኘሁት ትንሽ ፈለግኩኝ፡፡ Ermias Tokuma Alemayehu ጉዳዩ እንዲህ ነው በተደጋጋሚ ከዚህ ቀደም እዚህ ፌስቡክ ላይ …

የህወሀት እስርና እንግልት ያልበገረው ፍቅር ቂሊንጦ የተካሄደው የቀለበት ስነስርዓት Read more »

አዳፍኔ ፍርሃትና መክሸፍ

ሰሞናኛ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ አሸብረው የተሸበሩ የዘረኛ ቡድን ካድሬ የሆኑ የሕወሓት ጫጩቶች የማህበራዊ ሚዲያ ጫጫታ ነው::ምሁር በሽታቸው የሆነ ሕወሓቶች ጫጫታቸው ያተኮረው በፕሮፌሰር መስፍን ላይ መሆኑ ምን ያህል በበታችነት ዛሬም እንደሚያላዝኑ ያሳየ ነው::ፕሮፌሰር መስፍን አዳፍኔ የተባለውን የእኩይ ፖለቲከኞችን ሴራ ፍንትው አድርገው …

የሕወሓትን ጓዳ ከነጫጩቶቿ ያንቀጠቀጠው የፕሮፌሰር መስፍን አዳፍኔ ፍርሃትና መክሸፍ (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

የግንባሩን መሪዎች መርጧልም።እስካሁን ባለዉ ልምድ መሠረት የግንባሩ ዉሳኔዎችና መሪዎች ማለት የኢትዮጵያ ፖሊሲ ወይም መርሕና መሪዎች ናቸዉ። ጉባኤዉንና ዉሳኔዎቹን ለዚሕ ሳምንት ዉይይታችን ርዕስ ያደረግነዉም ዉሳኔ፤ ምርጫዉ መላዉ ኢትዮጵያን ሥለ ሚነካ ነዉ።

በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ የሚደርሰው ግፍ አንደቀጠለ ነው። … በጋምቤላ የወያኔ ታጣቂዎች ዘረፋ ሲቀጥል በደደር ቆቦ ኣንድ የወያኔ ባለስልጣን ተገደለ። … Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) …. የጦርነት ቀጠና በሆነው በምስራቅ ኢትዮጵያ ሰፍሮ የሚገኘው እና ጄነራል ኣብርሃ የሚመራው የደቡብ ምስራቅ እዝ ክፍለጦር …

በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ የሚደርሰው ግፍ አንደቀጠለ ነው። በጋምቤላ የወያኔ ታጣቂዎች ዘረፋ ሲቀጥል በደደር ቆቦ ኣንድ የወያኔ ባለስልጣን ተገደለ። (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

Empower women, don’t imprison them! #FreeThe20. ህወሓት/ኢህአዴግ የሴቶች፣ ራሳቸውን ያወቁ ሴቶች፣ ለሀገራቸው ያገባናል ለሚሉ ሴቶች፣ አድርባይ ላልሆኑ ሴቶች፣ እንደ ጣይቱ ሞትን ለማይፈሩ ሴቶች ፀር ነው፡፡ ተወዳዳሪ የማይገኝለት፡፡ ከቻይና በስተቀር፡፡ ይኸ ስርዓት አንድ ሰሞን ‹‹አፈርማቲቭ አክሽን›› ሆኖ ነበር ቋንቋው ሁሉ፡፡ ሴቶችን …

ህወሓት ለሀገራቸው ያገባናል ለሚሉ ሴቶች፣ አድርባይ ላልሆኑ ሴቶች፣ እንደ ጣይቱ ሞትን ለማይፈሩ ሴቶች ፀር ነው፡፡ Read more »

ገቢዎችና ጉምሩክ ነን ባዮች ከፓሊስ ጋር በመጣመር መርካቶ አካባቢ ላይ፤ ሸማቹን ህብረተሰብ መንገድ ላይ እያስቆሙ የያስከውን እቃ የገዛህበት የቫት ደረሰኝ አምጣ ወይም አሳየን እያሉ በጠራራ ፀሐይ እየዘረፉት ነው! – Sara MoAwol

ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ላይ ፍኖተ ሰላም አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ የአንዲት እርጉዝ ሴት እና ሌሎች 5 ሰዎች ህይወት አልፏል። – ሃኒ ሰሎሞን (ፌስቡክ) 16095

የህገ-ወጡ መጅሊስ አመራሮች በሶላት ሰአት በመካ እየተዝናኑ፤የህዝብን ገንዘብ እየመዘበሩ መሆናቸውን የቢቢኤን ምንጮች በቪዲዪ በመቅረጽ አጋለጡ ተቃውሞም ገጥሟችዋልለሃጅ የሄዱ ሙስሊሞች በመስተግዶ በችግር እየተሰቃዩ ባሉበት ይህን ማድረጋቸው እንዳሳዘናቸው ሙስሊሙም በየደረሱበት ሊቃወማቸው እንደሚገባ ተገለጸ ቢቢኤን፤- ነሃሴ 29/2007 የህገ-ወጡ መጅሊስ ምዝበራ ከትላንት እስከ ዛሬ …

የህገ-ወጡ መጅሊስ አመራሮች በሶላት ሰአት በመካ እየተዝናኑ፤የህዝብን ገንዘብ እየመዘበሩ መሆናቸውን ተገለጸ Read more »

ኢትዮጵያ እና ሱዳንን በሚያዋስኑ የመተማ እና ገላባት ከተሞች የመተማ ነዋሪዎችን ቁጣ ተከትሎ ውጥረት መንገሱን የአከባቢው ነዋሪዎች ለምንሊክ ሳልሳዊ ጠቁመዋል ፡፡ነዋሪዎቹ እንዳስታወቁት ባለፈው ሳምንት የአስረአንድ ኢትዮጵያውያን መታረድ የፈጠረው ሕዝባዊ ቁጣ አከባቢውን ውጥረት ውስጥ በመከትቱ ድንበሩ የተዘጋ ሲሆን የከተሞቹ የንግድ እንቅስቃሴ ጭር …

በኢትዮጵያ ሱዳን ድንበር መተማ ገላባት ውጥረት ነግሷል ፡፡ Read more »

የትግራይ ነፃነት ግንባር /ህወኃት/ ገና ከፅንስሱ ሲነሳ ለሙን የሰሜን ወሎን፣ ምዕራባዊ ጎንደርን እና ምዕራባዊ ጎጃምን በማካተት ታላቁን የትግራይ ሪፐብሊክ መመስረት ግብ አድርጎ መመስረቱና ለዚህም አላማው ስኬት የቻለውን ሁሉ በማድረግ ላይ እንድሚገኝ የሚታወቅ ነገር ነው። በተለይም በወልቃይት፣ ፀገዴና አርማጭሆ ያካሄደው መስፋፍት በአካባቢው ነዋሪ ህዝብ ላይ ትውልድ ይቅር የማይለው ግፍ ፈጽሟል፡ አሁንም የመስፋፋት ህልሙን እውን ለማድረግና ቀሪ […]

የአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች ህወሓት “ክልል አንድ” እያለ በሚጠራው በጎንደር-ወልቃይት ደጃች ሜዳ ወረዳ አቤራ ቀበሌ ስልኪ ዳግባ በተባለው ቦታ ነሃሴ 23 2007 ዓ.ም በህወሓት መከላከያ ኃይል ላይ ድንገተኛ የተኩስ ውርጅብኝ በመክፈት ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ወታደሮችን ገድለውና አቁስለው ድል ተቀዳጅተዋል፡፡ በአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞችና በህወሓት የመከላከያ ሰራዊት መካከል የተካሄደው ድንገተኛ የሆነ ከባድ ፍልሚያ እኩለ […]

‹‹ችሎቱ ታሪካዊ ስህተት እየሰራ ነው›› አቶ ሀብታሙ አያሌው በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር አቶ ሀብታሙ አያሌው ነሀሴ 14/2007 ዓ.ም ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ከተከሰሰበት የሽብር ወንጀል ነጻ ነው በማለት ከእስር እንዲፈታ የሰጠው ትዕዛዝ ተከብሮ እንዲፈታ ትዕዛዝ እንዲሰጥለት ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ ተደርጓል፡፡ ዛሬ ነሀሴ 29/2007 ዓ.ም ልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ተረኛ […]

በአሜሪካ መንግስት ኦፊሳላዊ ድረ ገጽ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ አስተባባሪነት በዓለም ላይ ለተመረጡ 20 ሴት የፖለቲካ እስረኞች ለአንድ ወር የሚቆይ ዘመቻና ማስታወሻ ሊደረግላቸው ነው፡፡ ከ20ዎቹ ሴት የፖለቲካ እስረኞች መካከል ሦስቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፣ ሁሉም የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ናቸው፡፡ ከዛሬ 20 አመት በፊት ሴቶችን ለማብቃት፣ የጾታ እኩልነትን ለማስፈን እና የልጃ ገረዶችን ሰብዓዊ መብት ለማስጠበቅ የቤጂንግ መርሃ […]

ዓባይ ፀሃየ ለሀ ወ ሓ ት ኢ ህ ኣ ደ ግ በሊቀመንበር በድርጅት ሃላፊነት እጅግ ብዙ ኣጃቢና የህወሓት ሎሌ ፓርቲዎች ፈጥረዋል:: በመንግስት መዋቅር በፈደራል ጉዳዮች በስኳር ኢንዱስትሪዎች በጠቅላይ ምኒስቴር አማካሪነት ሰርተዋል:: 40 ዓመት ሙሉ በስልጣን በነበሩበት ቡዙ ስራዎች ፈፅመዋል:: በተለይ በሀወሓት ኢህአደግ ስርኣት ውስጥ ዘርፈብዙ የመልካም ዓስተዳደር የፍትህ የሰብኣዊ ዲሞክራሲ መብቶች መጠበቅ ተጥሰዋል:: በ5 ዙር […]

ወደ እንግሊዝ ሃገር የሚያስኬዳቸውን ቪዛ ተከልክለው ወደዚያው ሊያደርጉት የነበረው ጉዞ የተስተጓጎለባቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ፕሮፌሰር መስፍን ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ መግባታቸውን በስፍራው የሚገኙ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታወቁ:: በቅርቡ ‘አዳፍኔ’ የተሰኘ ‘አወዛጋቢ’ መጽሐፍ ለንባብ ያበቁት እኚሁ ፕሮፌሰር ዛሬ ዋሽንግተን ዱሉስ ኤርፖርት ሲደርሱ ወዳጆቻቸው ሞቅ ያለ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታውቀዋል:: ፕሮፌሰር መስፍን በአሜሪካ ቆይታቸው አዲሱ መጽሓፋቸውን በዋሽንግተን ዲሲ […]

ከሰሞኑ የተቆሰቆሰዉን ጦርነት ለመከታተልና ለማጥራት በሚል የተንቀሳቀሱ የወያኔ አንጃ ወታደሮች ቡድን ጥቃት እየደረሰባቸዉ ይገኛሉ፡ ወያኔ በአዲግራትና ከማይ ጻይ ተወርዋሪ አየር መንደርደሪያ ሰፈሮች ባሻገር በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች እያለፈና እየዘለለ የሚደርስበትን ጥቃት ለማድበስበስ በየስፍራዉ የመከላከያ ሰራዊቱ ስልጠና ላይ ነዉና የተኩስ ድምጽ ብትሰሙም እንዳትደናገጡ እያለ ከባለፈዉ መጋቢት ወር አንስቶ ወረቀት እየለጤፈና እየደሰኮረ ይገኛል። አንድ ማንነቱን ሊገልጽ ያልፈለገ የወያኔ […]

የወያነ ጉጅሌ አገዛዝ በፈጠራ የአሸባሪነት ክስ አቅርቦባቸው በራሱ ችሎት እና አቃቢ ሕግ ሊፈርድባቸው ሲዘጋጅ አለም አቀፍ ጫና በመብዛቱ በነጻ እንዲፈቱ በካንጋሮው ፍርድ ቤት የተወሰነላቸው ሃብታሙ አያሌው እና አብርሃም ሰሎሞን እስካሁን እስር ቤቱ ያልፈታቸው ሲሆን ሀብታሙ አያሌውን ፍርድ ቤት ባዘዘው መሰረት …

በነጻ የተሰናበተው ሃብታሙ አያሌው ያልተፈታበት ጉዳይ ነገ በልደታ ችሎት ይታያል። Read more »

በባህርዳር ሁለት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታሰሩ • ‹‹ሲገረፉ ተባባሪያቸውን ይናገራሉ፡፡›› ፖሊስ በባህርዳር የሰማያዊ ፓርቲ የክልል ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ የነበሩት አቶ ወርቁ ጥላሁንና የፓርቲው አባል የሆኑት አቶ ሲሳይ ታፈረ መታሰራቸውን የፓርቲው የምዕራብ ጎጃም ዞን ፀኃፊ አቶ መልካሙ ታደለ ለነገረ ኢትዮጵያ …

በባህርዳር የሰማያዊ ፓርቲ የክልል ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ የነበሩት ታሰሩ:: Read more »

᎐ተከላከሉ ከተባሉት ተከሳሾች መካከል አራቱ ሴቶች በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ጠርቶት በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ወቅት ለእስር ተዳርገው ‹‹ስብሰባ በማወክና በማነሳሳት›› የተከሰሱት እነ ሚካኤል ያሬድ ለሦስተኛ ጊዜ መከላከያ ምስክሮቻቸውን አቅርበው የነበር ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ለጥቅምት 8/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶባቸዋል፡፡ ዛሬ ነሀሴ 28/2007 ዓ.ም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ […]

  የቀድሞው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወጣት ሀብታሙ አያሌውና ሌሎች የፖለቲካ አመራሮች የልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት ከተመሰረተባቸው ክስ በነፃ ካሰናበታቸው በኋላ ነገ በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተለይ ሀብታሙ አያሌው እንደሚቀርብ ባለቤቱ ወ/ሮ ቤተልሔም ገለፀች፡፡ ቤተልሔም እንደተናገረችው ባለቤቷ በነፃ እንዲሰናበት ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከወሰነ በኋላ ባልታወቀ ሁኔታ እስርቤቱ አለቅም ማለቱንና ላልተለቀቀበት አግባብ ምንም አይነት […]

እውነትን ውጠን ራሳችንን በማረም ከታሪክ ተጠያቂነት እንዳን::(ምንሊክ ሳልሳዊ)   …… ይጻፋል::…ይነገራል::…ይደሰኮራል::…ፕሮፓጋንዳው ተጣፍጦ ይቀርባል::..ራሳችን እናርም::ምን ጎደለ?የሚል ጠፋ::ተስፋ የተሰቀለ ዳቦ ከሆነ ለውጥ ሁሉ የጭብጨባ አሽኮለሌ ከሆነ ቆየ::ምንም ፈቀቅ የለም::ኑ እንዋቀስ:: ኑ እውነትን እንዋጥ:: ኑ እንገላልጠው::ባሌለ ነገር ላይ ባልተፈጠረ ነገር ላይ ባልተወረደ ጉዳይ …

እውነትን ውጠን ራሳችንን በማረም ከታሪክ ተጠያቂነት እንዳን::(ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

በሶማሊያ ሀገር ህይወታቸው እያለፈ ያሉ የኢትዮጵያ ወታደሮች ቁጥራቸው እየጨመረ ነው እየተላኩና ህይወታቸው እያለፈ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ወታደሮች ከቀን ወደ ቀን ቁጥራቸው እየጨመረ እንደሆነ ከተለያዩ ያገራችን አካባቢዎች የደረሰን መረጃ አስታወቀ.በሶማሊያ ሃገር እየሞቱ ያሉትን የኢትዮጵያ ወታደሮች ቁጥራቸው ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የሟቾቹ ቤተሰብ በየግዜው በቴለፎን መርዶ እየደረሳቸው እንደሆነ የገለፀው መረጃው በተለይም የኦሮሚያ ክልል ህዝብ ለምንድነው […]

ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ መታሰራቸውን ተቃወሙ

የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ የነበሩትና በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ወንድሙ ቢራቱ፣ ለፌዴራልና ለክልል መንግሥታት ገቢ ማድረግ የነበረባቸውን 500 ሚሊዮን ብር ለግል ጥቅማቸው አውለዋል የሚል ጥርጣሬ በመኖሩ ኦዲት እያስደረገ መሆኑን፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ለፍርድ ቤት ገለጸ፡፡

 

መርማሪ ቡድኑ ነሐሴ 22 ቀን 2007 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት ተጠርጣሪውን ይዞ ቀርቦ እንዳስረዳው፣ ተጠርጣሪው ለግል ጥቅማቸው አውለውታል ከተባለው 500 ሚሊዮን ብር በተጨማሪ፣ በራሳቸውና በቤተሰቦቻቸው ስም የሚገኙ የቦታዎችና የቤት ሰነዶችን በማሰባሰብ ለፎረንሲክ ምርመራ መላኩን ገልጿል፡፡ ያልተያዙ ግብረ አበሮችን አድኖ መያዝ፣ የስምንት ምስክሮችን ቃል መቀበልና ሌሎች የምርመራ ሥራዎች እንደሚቀሩት በመግለጽ፣ ፍርድ ቤቱ ለተጨማሪ ምርመራ የ14 ቀናት ጊዜ እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡ 

ተጠርጣሪው አቶ ወንድሙ በበኩላቸው ባቀረቡት መቃወሚያ እንደገለጹት፣ እሳቸው የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አባል ናቸው፡፡ በሕገ መንግሥቱ የተሰጣቸው ያለመከሰስ መብት ሳይነሳ ሕገ መንግሥቱ ተጥሶ መታሰራቸው አግባብ አለመሆኑን በመግለጽ የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅላቸው ጠይቀዋል፡፡ እሳቸው የክልል ባለሥልጣን በመሆናቸው የማሰርም ሆነ የመጠየቅ መብት ያለው የክልሉ መንግሥት እንጂ የፌዴራል መንግሥት አለመሆኑን በመግለጽ ተቃውመዋል፡፡ 

ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት መያዛቸው ሕገወጥ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ በተያዙበት ወቅት 22 ሺሕ ብርና መኪናቸው የት እንዳለ አለማወቃቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡ መርማሪ ቡድኑ በሰጠው ምላሽ ተጠርጣሪው ባቀረቡት ተቃውሞ ላይ ፍርድ ቤቱ ቀደም ባለው ችሎት ብይን የሰጠበት መሆኑን አስታውሷል፡፡ 

ፍርድ ቤቱም ተጠርጣሪው ፍርድ ቤት ቀርበው በነበሩ ጊዜ ተመሳሳይ ተቃውሞ አቅርበው ትዕዛዝ የተሰጠበት መሆኑን አስታውቋል፡፡ በድጋሚ እንደማይቀበልም ገልጾላቸዋል፡፡ መርማሪ ቡድኑ ምርመራውን በፍጥነት አከናውኖ እንዲያጠናቅቅ አሳስቦ፣ ለተጨማሪ ምርመራ አሥር ቀናት ፈቅዶለታል፡፡ 

 

በስምንት ግራም ቶሪየም 100 አመት ያህል መኪና ሊያስነዳ የሚችል ማዕድን አግኝቼያለሁ. ሃኪም ንጉሴ አሰፋ. “አገር አቀፍ የባህል መድኃኒትና የህክምና ቀን” በኢትዮጵያ የምግብ መድሃኒትንና የጤና እንክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ከአለም የጤናድርጅት ጋር በመተባበር ከትላንት በስቲያን በሃርመኒ ሆቴል ባካሄደው ስብሰባ ላይ ላለፉት ሃያ አመታት በባህል የህክምና ሙያ ላይ የቆዪት ሃኪም ንጉሴ አሰፋ ላለፋት 15 አመታት በቶሪየም ማዕድን […]

የፋብሪካው ሠራተኞች ሥጋታቸውን ገልጸዋል

ታዋቂው ነጋዴ ሐጂ በዳዳ ጫሊ ጅሩ ከፍተኛ ባለድርሻ የሆኑባቸው ድሬ ኢንዱስትሪዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ሞጆ ቆዳ ፋብሪካ አክሲዮን ማኅበር፣ ቦረን ሪል ስቴትና ድሬ ኃይላንድ አክሲዮን ማኅበር አክሲዮኖችን ለሦስተኛ ወገን እንዳይሸጡና እንዳይተላለፉ ታግደው እንዲቆዩ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ነሐሴ 13 ቀን 2007 ዓ.ም.  የሰጠውን ጨምሮ ውሳኔ በተለያዩ ጊዜያት በሰጠው ትዕዛዝ በወጋገን ባንክ፣ በአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በተለያዩ ቅርንጫፍ ባንኮች የተቀመጠ ገንዘብና አክሲዮንም ካለ ታግዶ እንዲቆይ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

የታዋቂው ነጋዴ ሐጂ በዳዳ አክሲዮኖችና ገንዘብ እንዲታገዱ ምክንያት የሆነው፣ ለ50 ዓመታት የትዳር አጋራቸው መሆናቸውን የገለጹት ወ/ሮ ልኬለሽ ያዴሳ ለፍርድ ቤት ባቀረቡት የፍች ጥያቄ ምክንያት ነው፡፡

ወ/ሮ ልኬለሽ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 81 መሠረት የፍች ውሳኔ እንዲሰጣቸው ያቀረቡት፣ ሐጂ በዳዳ ትዳራቸውን አክብረው መኖር ሲገባቸው ቤታቸውን ጥለው በመውጣት ከጋብቻ ውጪ ከሌላ ሰው ጋር መኖር መጀመራቸውን በመግለጽ መሆኑን ክሱ ያስረዳል፡፡

ሐጂ በዳዳ በራሳቸው፣ በባለቤታቸውና በአራት ልጆቻቸው በተቋቋመው 112.9 ሚሊዮን ብር ዋጋ ካለው ድሬ ኢንዱስትሪዎች አክሲዮኖች ውስጥ 86,580 አክሲዮን ወይም 86.5 ሚሊዮን ብር ድርሻ ያላቸው መሆኑን ሰነዶች ያስረዳሉ፡፡

ከፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ የገዙት ሞጆ ቆዳ ፋብሪካም ከ25 በላይ ባለአክሲዮኖች ያሉት ሲሆን፣ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው ሐጂ በዳዳ መሆናቸውን ሰነዶች ያስረዳሉ፡፡

ባለቤታቸው ባቀረቡት የፍች ጥያቄ ክስ ምክንያት የባንክ ገንዘባቸውና አክሲዮኖቻቸው የታገደባቸው ሐጂ በዳዳ፣ ለፍርድ ቤቱ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ 

ሐጂ በዳዳ ለፍርድ ቤቱ በሰጡት ምላሽ ከባለቤታቸው ጋር መስማማት ባለመቻላቸው ለ50 ዓመታት የጠበቁትን ትዳራቸውን ለመተው መገደዳቸውን ገልጸዋል፡፡ ከራሳቸው ይልቅ ለቤተሰባቸውና ለአገራቸው ዕድገትና ልማት በማሰብ ሁሉን ነገር ሆነው ፋብሪካዎች ማቋቋማቸውንና ከ1,200 በላይ ሠራተኞች እንዳሏቸው አስረድተዋል፡፡ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ ልዩ ልዩ ብድር እንዳለባቸውም ገልጸዋል፡፡ ፍች ለጠየቁት ባለቤታቸው በ2,310 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተገነባ መኖሪያ ቤትና ሦስት ሚሊዮን ብር በመስጠት ትዳራቸው ሳይፈርስ ለየብቻ እንዲኖሩ በማቀድ በሰላም እየኖሩ መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡ 

በሸሪዓ ሕግ መሠረት ሌላ ሰው በማግባት ልጆች ወልደው እየኖሩ መሆኑንና ከሳሽ ባለቤታቸውን ጨምሮ ሁሉም ሰው የሚያውቅ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በመሆኑም እንዲከፋፈሉና ትዳር እንዲፈርስ የተጠየቀው አግባብ ባለመሆኑ ክሱ ተሰርዞ እንዲሰናበቱ ጠይቀዋል፡፡ ሐጂ በዳዳ ባቀረቡት ሌላ አቤቱታ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የተለያዩ ዕዳዎች እንዳለባቸው በድጋሚ ጠቅሰው፣ በገቢና በወጪ ንግድ ላይ ተሰማርተው ለአገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እያስገቡ መሆኑን በመግለጽ፣ ፍርድ ቤቱ ወደ ክርክር እንዲገቡ የሚያደርግ ከሆነ ክርክሩ በዝግ እንዲሆን ፍርድ ቤቱን ጠይቀው ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ ግን አልተቀበላቸውም፡፡ 

ሐጂ በዳዳ በበኩላቸው በወ/ሮ ልኬለሽ ያዴሳ ስም በአዋሽ ኢንተርናሽል ባንክ የተቀመጠ ገንዘብ በአራዳ ሕንፃ ሁለተኛ ፎቅ ላይ ያለ የኤሌክትሮኒክስ መደብር፣ በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ሰዴን ሶዶ ወረዳ አሌ አበባን ቀበሌ የሚገኝ ንብረትና ድሬ ኢንዱስትሪዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ግቢ ውስጥ የሚገኝ መጋዘን ውስጥ ያለ ንብረት ታግዶ እንዲቆይ ጠይቀው፣ የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ዕግድ ጥሏል፡፡ 

በድርጅቶቹ ከፍተኛ ባለድርሻ ሐጂ በዳዳና የአክሲዮን ድርሻና የባንክ ባለቤት ሒሳብ ላይ ፍርድ ቤቶች የሚጥሉት ዕድግ እንዳስፈራቸው የሞጆ ቆዳ ፋብሪካ አክሲዮን ማኅበር መሠረታዊ ሠራተኞች ማኅበር  ገልጿል፡፡ ባለሀብቱ ፋብሪካውን ከገዙት በኋላ ውጤታማ እየሆነ እንደሚገኝ የገለጸው ማኅበሩ፣ 992 ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኛ በፋብሪካው መኖሩን ገልጾ፣ በተለይ በባንክ ሒሳብ ላይ ዕግድ በመጣሉ የላብ አደሩ ደመወዝ እንዴት እንደሚከፈል ሥጋት እንደገባው አመልክቷል፡፡ ችግሩ የፋብሪካ ሠራተኞቹ ብቻ ሳይሆን ከ5,000 በላይ የሚሆኑ ቤተሰቦቻቸውም ጭምር መሆኑን ጠቁመው፣ የሚመለከተው አካል ችግሩን በቀላሉ እንዲፈቱት እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት ለጥቅምት 3 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ 

  

 

 

ከአክሊሉ ወንድአፈረው የተለያዩ ድርጅቶች የወያኔ/ ኢህአዴግን መንግስት በትጥቅ ሀይል ለማስወገድ በአስመራ ስልጣን ከያዘው ሻቢያ ጋር መቀራረብና ተባብሮ መስራትን መርጠዋል። ይህን በተመለከተ ባንድ በኩል የወያኔ/ኢህአዴግን የግፍ ስርአት ለማስወገድ ከማንም ጋር ቢሆን ማበር አስፈልጊ ነው የሚሉ ሲኖሩ ሌሎች ደግሞ የወያኔን የግፍ ስርአት …

የኢሳያስ (የሻቢያ) ስታራተጂ፤ ኢትዮጰያን ለመታደግ ወይስ እንደገና ለመግደል? Read more »

የመኢአድ ፕሬዚዳንት በነፃ ተሰናበቱ

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት ከተፈረጀው የግንቦት ሰባት ድርጅት ጋር ለመቀላቀል ሲጓዙ በቁጥጥር ሥር ውለዋል ተብለው ክስ የተመሠረተባቸው አራት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ የምስክርነት ቃል ተሰጠ፡፡

የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ የመሠረተውን የሽብር ድርጊት ወንጀል ክስ እየመረመረ ለሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት ምስክሩን ያሰማው ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ነው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የተመሠረተባቸውን ክስ እንደማይቃወሙና ድርጊቱን መፈጸማቸውን በማመናቸው፣ ዓቃቤ ሕግ በክሱ የጠቀሰውን አንድ ምስክር አሰምቷል፡፡ 

የዓቃቤ ሕግ ምስክር ሆነው የቀረቡት ግለሰብ እሳቸውም የሰማያዊ ፓርቲ አባል እንደነበሩ አስታውቀው፣ የፓርቲው የተለያዩ ክፍሎች አመራሮች የነበሩትን ብርሃኑ ተክለ ያሬድ፣ እየሩሳሌም አስፋውንና ፍቅረ ማርያም አስማማውን የሚያውቋቸው በፓርቲው ውስጥ በነበሩበት ጊዜ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ተከሳሽ ብርሃኑና እየሩሳሌም የካቲት 12 ቀን 2007 ዓ.ም. ሰላማዊ ትግሉ እንደማያዋጣ ተነጋግረው ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ለመሄድ ሲንቀሳቀሱ ምስክሩም አብረው ባህር ዳር ድረስ መሄዳቸውን ተናግረዋል፡፡ 

ባህር ዳር እንደደረሱ እሳቸው (ምስክሩ) ሐሳባቸውን በመቀየር ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውን ያስረዱ ሲሆን፣ ተከሳሽ ብርሃኑ ‹‹ለምን ትመለሳለህ? ቢያንስ ጎንደር የምናገኘው ሰው ስላለ እሱን ካገኘህ በኋላ ትመለሳለህ፤›› ቢላቸውም ሳይስማሙ ቀርተው መመለሳቸውን ገልጸዋል፡፡ ‹‹በወቅቱ ስሜታዊ ሆኜ መወሰኔ አግባብ እንዳልሆነ ስለተረዳሁ ነው፤›› በማለት ‹‹ለምን ሐሳብህን ቀየርክ?›› ለሚለው መስቀለኛ ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ምስክር ለመሆን መገደድ አለመገደዳቸውን፣ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው፣ ታስረው እንደነበርና ግንቦት ሰባት ነፃ አውጪ ወይም አሸባሪ ድርጅት መሆኑን እንዲያስረዱ በተከሳሾቹ ሲጠየቁ ዓቃቤ ሕግ ተቃውሟል፡፡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀን ድርጅት መጠየቁ አግባብ አለመሆኑን ዓቃቤ ሕግ በማስረዳቱ፣ ፍርድ ቤቱም የተከሳሾቹ ጥያቄ እንዲታለፍ በይኗል፡፡ ምስክሩ በአራተኛ ተከሳሽ ደሴ ካህሳይ ላይ የምስክርነት ቃል አልሰጡም፡፡

ፍርድ ቤቱ ብይን ለመስጠት ለመስከረም 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ 

ይህ በዚህ እንዳለ አይኤስን ለመቃወም መንግሥት ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ጠርቶት በነበረው ሰላማዊ ሠልፍ ላይ የተፈጠረውን ብጥብጥ በማደራጀትና በመምራት ተጠርጥረው ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩት የመኢአድ (የቀድሞ) ሊቀመንበር  አቶ ማሙሸት አማረ በነፃ ተለቀዋል፡፡

ዓቃቤ ሕግ የመሠረተባቸውን ክስ ሲመረምር የከረመው የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት አቶ ማሙሸትን በነፃ ያሰናበታቸው፣ ሰላማዊ ሠልፉ በተደረገበት ዕለት እሳቸው ከምርጫ ቦርድ ጋር በነበረባቸው ክርክር ፍርድ ቤት መዋላቸውን የሚያስረዳ ሰነድ በማቅረባቸው ነው፡፡ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበባቸው ምስክሮች የሰጡት የምስክርነት ቃል የተጠና መሆኑን በመቃወም ጠበቃቸው ለፍርድ ቤት በማስረዳታቸውና ምስክሮቹም የተለያየና የማይገናኝ የምስክርነት ቃል መስጠታቸው ለአቶ ማሙሸት በነፃ መሰናበት ምክንያት ሆኗል፡፡

 

አብዛኛው ሰው በሀገሩ ኑሮ ሲጠበው፣ በሀገሩ ሰላም ሲያጣ ፣ በሀገሩ ነገሮች አልሆኑለት ሲሉ ራሱን ሊለውጥ አለያም ይደርስብኛል ሲል የሚሰጋበት ሰብአዊ መብት ረገጣ ሽሽት ወደስደት ይወጣል። አንዳንዱ እድለኛ ታስጠልለኛለች ብሎ ያላት ምድር ስቃ ትቀበለዋለች አንዳንዱን ደግሞ ህይወቱ የባሰ ቅጥአንባሩ ይጠፋውና ምነው በዚያው የሀገሬ ጅብ በበላኝ ሲል ይማረራል ለአንዳንዶች ግን ያስጠልለናል ካሉት ቦታ ሳይደርሱ በመንገድ ይቀራሉ! አንዱ […]