ብሄራዊ ባንክ ክኤሌክትሪክ ሃይል ሽያጭ የተገኘ የውጪ ምንዛሬ አልደረሰኝም አለ::(ምንሊክ ሳልሳዊ)

ብሄራዊ ባንክ ክኤሌክትሪክ ሃይል ሽያጭ የተገኘ የውጪ ምንዛሬ አልደረሰኝም አለ::(ምንሊክ ሳልሳዊ)

 

ብሄራዊ ባንክ ክኤሌክትሪክ ሃይል ሽያጭ የተገኘ የውጪ ምንዛሬ አልደረሰኝም አለ::(ምንሊክ ሳልሳዊ) #Ethiopia

በኤሌክትሪክ መቋረጥ በሃገር ወስጥ የኢንዱስትሪው መስክ ብቻ ከ40 ሚሊዮን ዶላር በላይ ኪሳራ ደርሷል::
የወያኔው አገዛዝ ለጎረቤት አገሮች ከሚሸጠው የኤሌክትሪክ ሃይል በ9 ወር የተገኘው 35 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለብሄራዊ ባንክ ገቢ አለመሆኑን ከብሄራዊ ባንክ ሰራተኞች የተገኘ መረጃ ጠቆመ::የገንዘብ ሚኒስቴር ጉዳዩን እንደማያውቀው ተናግሯል::ለጎረቤት አገሮች የተሸጠ የኤሌክትሪክ ሃይል ክፍያ በውጭ ምንዛሬ ተሰብስቦ ያለቀው በሃምሌ 2015 ሲሆን ላለፈው አንድ ወር ምም አይነት የውጪ ምንዛሬ ለብሄራዊ ባንክ ይሁም ኒውዮርክ ባንክ ላለው የኢትዮጵያ አካውንት አለመግባቱ ተረጋግጧል::

ከጎረቤት አገሮች ገንዘቡ መሰብሰቡ አጣርተናል የሚሉት የብሄራዊ ባንክ ሰራተኞች የገንዘብ ሚኒስቴርም ይህንን ጉዳይ ቢያውቅም ዝምታን መርጧል ብለዋል::የወያኔው አገዛዝ ባለስልጣናት ከኤሌክሪክ ሃይል የተገኘውን የውጪ ምንዛሬ ገቢ ወደ ባውጪ የባንክ አካውንታቸው ሲያዘዋውሩ ይህ ሁለተኛ ጊዜያቸው ሲሆን ከ35 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ዘርፈው ወስደውታል ሲሉ አጋልጠዋል::

ከዚህ ጋር በተያያዘ ዜና ይሃገር ቤቱን የሃይል ፍጆታ ሳያሟላ ለጎረቤት አገሮች ሃይል በመሸጥ በዝርፊያ ላይ የተሰማራው የወያኔ አገዛዝ በሃገር ቤት በሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እያደረሰባቸው ሲሆን ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ በመብራት መቋረጥ ብቻ ከ40 ሚሊዮን ዶላር በላይ ኪሳራ እንደደረሰባችው የባንክ ጥናቶች ጠቁመዋል::የኢትዮጵያ ሕዝብ በመብራት መቋረጥ በቂ አገልግሎት ስለማያገኝ በከፍተና ችግር ውስጥ እና በጨለማ ውስጥ መሆኑ የሚታወቅ ነው::