የፌዴራል ጉዳዬች ሚኒስትሩ ዶክተር ሽፈራው ከኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚነት ተነሱ
ሰንደቅ ጋዜጣ ላይ የፌዴራል ጉዳዬች ሚኒስትሩ ዶክተር ሽፈራው ከኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚነት ተነሱ የሚል ዜና አነበብኩ፡፡ አዋሳ ከሚገኝ አንድ የጤና ኮሌጅ ዲንነት ወንጌላዊ ተልዕኮዋቸውን በሚገባ ወደሚወጡበት የመለስ ዜናዊ እጅ ስራ ወደሆነው ፌዴራል ጉዳዬች ሚኒስተር በቀጥታ ተዘዋውረው የመጡት ዶ/ር ሽፈራው ወንጌላዊ ተልዕኮዋቸውን በመንግስት ሰልጣን ሽፋን በሚገባ ተወጥተዋል፡፡
ለዚህ የወንጌል ስራቸው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ የምስጋናና ለተልዕኮዋቸው መልካም ምኞት መግለጫ ደብዳቤ ልከውላቸው ነበር(ደብዳቤውን ከስር አያይዤዋለሁ)፡፡ ከሶስት ቀናት በፊት በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ የፌዴራል ጉዳዬች ሚኒስትር ከአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ከማኅበረ ካህናት፣ ከሰባክያነ ወንጌል፣ ከሰንበት ት/ቤቶች ተወካዮች እና የሀገረ ስብከቱ አንድነት አመራሮች ጋር ያደረገውን ውይይት ዶ/ር ሽፈራው መምራቱ ሀራ ተዋህዶ ከተባለ ድረ ገፅ ላይ አንብቤያለው፡፡
ዛሬ ላይ ከኢህአዲግ ስራ አስፈፃሚነት የተባረሩት የወንጌል ተልዕኮዋቸውን በሚገባ እንዲወጡ ነፃነት እንዲያገኙ ነው ? ወይስ ሙስሊሞች ላይ እንዲተገበሩት የተሰጣቸው ወንጌላዊ ተልዕኮን በተገቢው መልኩ አላሳካህም ተብለው በግምገማ ተባረው ? Ye Emmu Lij