የህገ-ወጡ መጅሊስ አመራሮች በሶላት ሰአት በመካ እየተዝናኑ፤የህዝብን ገንዘብ እየመዘበሩ መሆናቸውን ተገለጸ
የህገ-ወጡ መጅሊስ አመራሮች በሶላት ሰአት በመካ እየተዝናኑ፤የህዝብን ገንዘብ እየመዘበሩ መሆናቸውን የቢቢኤን ምንጮች በቪዲዪ በመቅረጽ አጋለጡ ተቃውሞም ገጥሟችዋልለሃጅ የሄዱ ሙስሊሞች በመስተግዶ በችግር እየተሰቃዩ ባሉበት ይህን ማድረጋቸው እንዳሳዘናቸው ሙስሊሙም በየደረሱበት ሊቃወማቸው እንደሚገባ ተገለጸ
ቢቢኤን፤- ነሃሴ 29/2007
የህገ-ወጡ መጅሊስ ምዝበራ ከትላንት እስከ ዛሬ ልዩ ፕሮግራም
http://goo.gl/awbGex
የህገ-ወጡ የመጅሊስ አመራሮች ፕሬዝዳንቱ ሙሃመድ አሚኒን ጨምሮ አህባሹ ኡመር የህዝብን ገንዘብ ከሃጃጆች በመመዝበር፤ ሃጃጆችን እያንገላቱ እነሱ ግን እየተዝናኑ እና እቃዎችን እየሸመቱ መሆናቸውን የቢቢኤን ምንጮች አጋልጠዋል፡፡በሀገር ቤት ኢስላምን ለማጥፋት፤አህባሽን ለማስፋፋት በተለይም ደግሞ ሳኡዲአረቢያን ጭምር የዋህብያ መፈጠሪያ እያሉ የሚያጥላሉ የህገወጥ መጅሊስ አባላት በሳኡዲአረቢያ ጎደና ላይ ሲዘዋወር ማየት አስገራሚ ነው ያሉት ምንጮቻችን በአሁኑ ጊዜ ሃጃጆችን እያንገላቱ እነሱ በህዝብ ገንዘብ ውድ ወደ ሆኑ ሱቆች በመግባት ልብስ ሲያሰፉ እና ሲዝናኑ በቪዲዪ በመቅረጽ የቢቢኤን ምንጮች አጋልጠዋል፡፡
ለሶላት አዛን እየተባለ ባለበት ሰአት እነሱ ግን በጎዳናዎች ላይ ይዘዋወሩ እንደነበር የታወቀ ሲሆን ኢትዪጲያዊያን ሙስሊሞችም የወያኔ ተላላኪ ናችሁ በማለት እንደተናገሯቸው ገልጽዋል፡፡ በሳኡዲ የሚገኙ ኢትዪጲያዊያን ሙስሊሞች የህገ-ወጥ የመጅሊስ አመራሮች በሀገር ቤት ኢስላምን ለማጥፋት የሚሰሩ እንዲሁም ሃጃጆችን ብር የመዘበሩ በመሆናቸው ህዝቡ በየደረሱበት እየተከተለ እነሱን ተቃውሞውን መግለጽ እንዳለበት ገልጽዋል፡፡