መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ከሆኑት መካካል ኡስታዝ ያሲን ኑሩ፣ ሳቢር ይርጉ፣ አቡበከር ዓለሙ እና ገጣሚው ሙኒር ሁሴን ከእስር መለቀቃቸውን አስመልክቶ ድምፃችን ይሰማ ባወጣው መግለጫ፣ ሁሉም እስረኞች ካለምንም ቅድመ ሁኔታዎች እስካልተፈቱ ድረስ ትግላቸው እንደሚቀጥሉ በአጽንኦት ገልጿል። ድምፃችን ይሰማ ፣ ” ተፈቺዎቹም ይሁኑ ታሳሪዎቹ ጀግኖቻችን ሃይማኖታችን በተደፈረበት፣ …

መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በለቡ መዝናኛ ውስጥ ከሴት ጓደኛዋ ጋር በመዝናናት ላይ የነበረችው ሰሎሜ ጉልላት የተባለችው የ20 ዓመት ወጣት ”አንቺ ሰው የማታናግሪው ለምንድ ነው?” በሚል ተልካሻ ምክንያት መሳሪያ የታጠቀው የፌደራል ፓሊስ አባል ተኩሶ ገድሏታል። ታጣቂው በወቅቱ እራሱንም ለማጥፋት ጭንቅላቱ አካባቢ ላይ ያቆሰለ ሲሆን፣ ሳይሞት በሕይወት መትረፉንና በሕክምና ላይ እንዳለ ለማወቅ …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ኛ የወንጀል ምድብ ችሎት በብርሃኑ ተክለ ያሬድ መዝገብ በተከሰሱ አራት የሰማያዊ አመራር አባላት ላይ ብይን ለመስጠት ዛሬ ቢሰየምም ለውሳኔው ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ።

እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ለህዳር 21 ተቀጠሩ ‹‹የሽብር ተከሳሽ በመሆናችን ህክምና ተከልክለናል›› ተከሳሾቹ በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን አቋርጠው ኤርትራ የሚገኘውን ግንቦት ሰባት የተባለ በተወካዮች ም/ቤት ሽብርተኛ የተባለ ድርጅትን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ በድጋሜ ለብይን …

ድንበርን አቋርጠው ሽብርተኛ ድርጅትን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል የተከሰሱ ለህዳር 21 ተቀጠሩ:: Read more »

Minilik Salsawi – መጀመሪያ ማወቅ ያለብን የማያቋርጠው ትግላችን ፍሬ እያፈራ መሆኑን እና ጥንካሬን እያላበሰን መሆኑን አንዘንጋ::በአዲስ አመት 2008 መምጫ ላይ የወያኔው ጉጅሌ መንግስት በሰጠው መግለጫ (በምሕረት?)ፈታሄቸው ያላቸው ኢትዮጵያውያን እስረኞች የተፈተቱት ሕዝቦች ግፍን ላለመቀበል በጋራ ባደረጉት ትግል ጫና እንጂ በወያኔ አምባገነናዊ …

የተፈቱ እስረኞች በማያቋርጥ የትግል ውጤት ሂደት እንጂ በወያኔ የዋህነት አይደለም:: Read more »

ሰሎሜ ጉልላት የተባለችው የ20 ዓመት ወጣት ከጓደኛዋ ጋር በመሆን በለቡ ኮንዶሚኒየም ቤቶች አካባቢ በሚገኝ የጓደኛቸው መዝናኛ ውስጥ በመዝናናት ላይ እያሉ ነው ከተጠርጣሪው ገዳይ ጋር የተገናኙት፡፡ ለጊዜው ስሟን መናገር ካልፈለገችው ጓደኛዋ መረዳት እንደተቻለው፣ የፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሰው ግለሰብ ከዚህ ቀደም ሰሎሜን …

ወጣት ሶሎሜን የገደላት ፖሊስ ጭንቅላቱን በጥይት መትቶ ራሱን ለማጥፋት ሞክሮ ተርፏል:: Read more »

በፍኖተ-ዴሞክራሲ ሬዲዮ ለቀረበው ውንጀላ የተሰጠ አጸፋዊ መልስ ሠሞኑን የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ንብረት የሆነው «ፍኖተ-ዴሞክራሲ» በመባል የሚታወቀው የሳተላይት ሬዲዮ ጣቢያ በዐማራው ነገድ ተወላጆች ላይ የጅምላ ክስ አቅርቧል። ክሱ «በአማራ ሕዝብ ስም ሌሎችን መዝለፍ የሚወገዝ ነው» በሚል ርዕስ ያዘጋጀውንመግለጫ ነሐሴ ፳፪ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም. በሬዲዮ አስተላልፏል[1]፤ በጽሑፍ ደግሞ በተባባሪ ድረ-ገፆች «አሲምባ[2]» እና «ደብተራው[3]»አሠራጭቷል። ከሁሉም የሚያሣዝነው […]

ኢትዮጵያ ውስጥ እያደገ የመጣው የሰብዓዊ ዕርዳታ ፍላጎት ከሚሰጠው ምላሽ ጋር ሊጣጣም እንዳልቻለ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ – ኦቻ የአዲስ አበባ ፅሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም       ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 “ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የእራሱን ጥላ የሚፈራው ለምንድን ነው?“ በሚል ርዕስ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡ በዚያ ትችት ላይ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ደጋፊዎች የወያኔው አመራሮች በግንቦት ስለሚካሄደው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ በፍርሀት ቆፈን ውስጥ …

ኢትዮጵያ የተሻሉ አማራጮችን አጥታ ነውን ? Read more »

አሜሪካ ከመጣች 20 አመት አለፋት። ታዋቂ ድምፃዊ ናት። ከአመታት በፊት ተወልዳ ካደገችበት ጐንደር ይኖሩ የነበሩ ወላጅ እናቷን ወደዚህ ታስመጣለች። ምስኪን እናት አገሩ አልተመቻቸውም። ድምፃዊቷ በከፈተችው (ዝጉብኝ) መሸታ ቤት ዋልጌ ሃበሾች የሚያሳዩዋቸው ድርጊቶች እንባ ያስፈስሣቸው ያዘ። ሙዚቃው ሲረብሻቸው ይነጋል። ድምፃዊቷ ልጃቸው …

የፀፀት ደወል Read more »

(ሪፖርተር፤ ነአምን አሸናፊ፤ መስከረም ፪ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.) የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፖፕ እና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ካልዕ፣ በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ላይ ለመታደም እና የአራት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ፣ መስከረም ፲፭ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. ከቤተ ክርስቲያኒቱ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋር በመኾን አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡ ፓትርያርክ አቡነ ቴዎድሮስ አራት ቀናት …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

“በምህረት” እንዲፈቱ ከተወሰነላቸው ኡስታዞቻችን እና ወንድሞቻችን መካከል አራቱ ተፈቱ! አቡ ዳውድ ኡማን በሃሰት በሽብር ወንጀል የተፈረደባቸው በኡስታዝ አቡበከር አህመድ መዝገብ ከሚገኙት ኮሚቴዎቻችን እና ወንድሞቻችን መካከል ስድስት የሚሆኑትን አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ በይቅርታ መንግስት እንደፈቱ መወሰኑን መዘገቡ የሚታወስ ሲሆን እስከዛሬ ድረስ …

“በምህረት” እንዲፈቱ ከተወሰነላቸው በኡስታዝ አቡበከር አህመድ መዝገብ በሃሰት የተፈረደባቸው መካከል አራቱ ተፈቱ! Read more »

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌዴራል የሥነምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን የባለስልጣናትን ሐብት ምዝገባ ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ እንደተሳነው የኮምሽኑ ምንጮች አጋለጡ፡፡ ለጠ/ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆኑትን የኮምሽኑ ኮምሽነር ዓሊ ሱሌይማን ትዕዛዝ ተቀብለው ብቻ የሚያስሩና የሚፈቱ በመሆናቸው በአዋጁ መሰረት ለህዝብ ይፋ መደረግ የነበረበት የባለለስጣናት የሐብት ምዝገባ በወቅቱ ለማከናወን ድፍረት ማጣታቸው ታውቆአል፡፡ የሐብት ምዝገባ ሥራን በኢንፎርሜሽን …

የኢትዮጵያ፤ የሱዳንና የግብፅ የጋራ ኮሚቴ ባለፈዉ መጋቢት ጥናቱን እንዲያደርጉ የመረጣቸዉ ሁለቱ ኩባንዮች የጥናት ዉጤታቸዉን ባለፈዉ ነሐሴ ማብቂያ ለኮሚቴዉ ማቅረብ ነበረባቸዉ

”ከሚያዚያ ወር ጀምሮ የ7ዓመት ግምገማ እያደረግን ቆይተናል። በዚህም ሞላ በፖለቲካ አመራር ድርጅቱን አዳክሞታል የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰናል። ሰራዊቱ የአመራር ለውጥ በሚፈልግበት ጊዜ ላይ በተካሄደው በዚሁ ግምገማ ሞላ ከፍተኛ ተቀውሞ ከድርጅቱ አመራሮችና አባላት ደርሶበታል። ” ”ይዞ የወጣው ታጋይ ቁጥሩ ተጋኗል። ያም ቢሆን ለስራ ተብለው(የኪነት ቡድኑ ለበዓል) የተታለለ ነው። በተቻለን መጠን አብዛኛውን መልሰናል። የተዋጋው ከእኛው ጋር ነው። […]

መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፋይናንሻል ታይምስ እንደዘገበው ባለፈው ታህሳስ ወር 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዳላር ከግል ባንኮች የተበደረው መንግስት፣ ተጨማሪ በድር ለመውሰድ እንቅስቃሴ ጀምሯል። በሚቀጥለው ሳምንት የመንግስት ባለስልጣኖች ከአበዳሪ ተቋማት መሪዎች ጋር ለንደን ውስጥ ይገናኛሉ። ላዛርድ የተባለ የመንግስት የገንዘብ አማካሪ ድርጅት ባለስልጣኖቹን ከጀርመኑ ዶች ባንክና ከአሜሪካው ጄፒ ሞርጋን ሃላፊዎች ጋር እንደሚያገናኛው የዘገበው …

መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቀድሞው የህወሃት አባልና በሁዋላም የአፋር ፓርቲ መስርተው የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆነው ለ20 አመታት በስልጣን ላይ የነበሩት አቶ እስማኤል አሊ ሴሮ ከስልጣናቸው ከተነሱ በሁዋላ፣ የአብዴፓ ሊቀመንበር ሆነው በተመረጡት በአቶ ጠሃ ሙሃመድ ቡድንና በአቶ አሊ ሴሮ ቡድን መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል። የውዝግቡ መነሻ አቶ ጠፋ የክልሉ ፕሬዚዳንት ሊሆኑ …

መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በንግድ ስራ የምትደዳረዋ ካሚል ሙሃመድ ታውኒ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አላት በሚል በኬንያ ልዩ ፖሊስ ተይዛ ለሶማሊና ለኢትዮጵያ መንግስታት ተላልፋ መሰጠቷን ተከትሎ ሰቆቃ እንደተፈጸመባት ተናግራለች። ቃሏን ለፍርድ ቤት ስታሰማ እንባዋ ያቋርጣት እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል። ወ/ት ትዌኒ የህክምናዋን ወጪ ለመሸፈን የኬንያ መንግስት የገንዘብ ካሳ እንዲሰጣት ፍርድ ቤትን ጠይቃለች። ፍርድ …

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በማዕከላዊ ሶማሊያ ሂራን ግዛት ራሶ መንደር አቅራቢያ የ20 ና የ25 ዓመት ወጣት የሆኑት ወንድማማቾች ሶማልያዊያንና አንድ ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ በአልሸባብ ታጣቂዎች በግፍ ተገለው ተገኝተዋል። ሁለቱ ወንድማማቾች ባለፈው ሳምንት ነበር በቡቃበል ከተማ ውስጥ በድንገት የኢትዮጵያ ወታደሮችና የሶማሊያ መንግስት ሰራዊቶች አካባቢውን ለቀው ሲወጡ በአልሸባብ ሚሊሻዎች ታግተው የተያዙት። የአካባቢው …



አንድ ጆሮና ጊዜ የገጠሙለት ሰው ነበር አሉ፡፡ ሰውዬው የተማረው ትምህርት የለውም፡፡ ሁለት ችሎታ ግን ነበረው፡፡ ሲባል የሰማው እውነትም ይሁን ስሕተት ልቅም አድርጎ ይይዝና ሌላ ቦታ ሄዶ የተማረው ያህል ያንደቀድቀዋል፡፡ ሁለተኛው ችሎታው ደግሞ አፈ ጮሌ ስለሆነ ነገር በምላሱ ይቆላል፡፡ ያንንም ይኼንንም እያቆላመጠ ከተማሩትና ከተመራመሩት በላይ ከብሮና ታፍሮ ይኖራል፡፡ አንድ ቀን የማያውቀውን ቀለም ሲያዜም የሰሙት ሊቅ አፍረው አቀረቀሩ፡፡ እርሱ ግን ከዕውቀት የደነገለ ነበርና አልገባውም፡፡ በኋላ ቀረብ ብሎ ‹ደኅና ነዎት የኔታ› አላቸው፡፡ እርሳቸውም ‹ደኅና ነህ›› ብለው ዝም አሉት፡፡ እርሱም ያላወቁት ስለመሰለው ‹አላወቁኝም መሰል መሪጌታ እኮ ነኝ› አላቸው፡፡ሊቁም ‹ዐዉቄሃለሁ› አሉት፡፡ እንዳቀረቀሩ፡፡ ‹ታድያ ምነው ካወቁኝ ከነ ማዕረጌ ሳይጠሩኝ ቀሩሳ› አላቸው፡፡ ‹አንተን አከብራለሁ ብዬ ሞያውን እንዳልሰድበው ፈርቼ ነው›› አሉት ይባላል፡፡
 
እኔም ‹እርቲስቶቻችን› የሚለው ቃል በትእምርተ ጥቅስ ያደረግኩት ሊቁ የፈሩትን ፈርቼ ነው፡፡ እንዳልተውባቸው ደግሞ ምን ብዬ እንደምጠራቸው ግራ ገብቶኝ፡፡ የአዲስ ዓመት ዋዜማውን መርሐ ግብር በዕለቱ ለማየት ስላልቻልኩ ቪዲዮውን ነው የተመለከትኩት፡፡ ሊነግሩን የፈለጉት ስለ እድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ፣ ስለ ሀገራችን ዕድገት፣ ስላለፈው ስኬታችን ቢሆንም እንኳን የቀረበው ዝግጅት ግን አደገች የምትባለውን ኢትዮጵያን የማይመጥን፣ ጥበብ ዞር ብላ ያላየቺው፣ ከንግግር ከፍ፣ ከፉከራ ዝቅ ያለ፤ ከፕሮፓጋንዳ ወረድ፣ ከዲስኩር ራቅ፣ ከድንፋታ ጠጋ ያለ ወለፈንዲ ሆኖ ነው የታየኝ፡፡ 
 
በሀገራችንኮ የልቅሶ ሥነ ሥርዓት እንኳን ወግ አለው፤ ጥበብ አለው፤ ትርዒት አለው፤ ፍሰት አለው፤ ድባብ አለው፤ ፈጠራ አለው፤ ርቀት አለው፣ ምጥቀት አለው፤ ደረጃ አለው፡፡ ይኼኮ ወግ የለው፣ ጥበብ የለው፣ ትርዒት የለው፣ ፍሰት የለው፣ ፈጠራ የለው፣ ደረጃ የለው፡፡ ድፍረት ብቻ፡፡ መሪዎቻችን ግን ለምንድን ነው የጥበብ አማካሪ የማይኖራቸው? ለምንድን ነው ጥበብን ከሚሰድቡ ሰዎች ጋር አብረው የሚቆሙት? ለምን ‹አርቲስቶቹን› እናከብራለን ብለው ሞያውን ይሰድቡታል? ይህቺ ሀገርኮ ሰማየ ሰማያት ደርሰው የመጡ፣ ድንጋዩን አቅልጠው ጥበብ የሚያፈልቁ፣ አራት ጸሐፊ አስቀምጠው አንድ አንድ ምዕራፍ እየነገሩ መጽሐፍ የሚያስጽፉ፤ መሰንቆ እንደ ሰው፣ ክራር እንደ ወፍ፣ በገና እንደ መልአክ የሚያናግሩ፤ ስንትና ስንት ጠቢባን ነበሩባት፡፡ ከሐይቅ ዳር የሸንበቆ ውዝዋዜ ተነሥተው ኅሊና የሚመስጥ አቋቋም የቀመሩ፣ እያዜሙ ሲሄዱ እንኳን ገበሬውን በሬዎቹን የሚያስደምሙ ጠቢባን ነበሩባት፡፡ እንዴት በጥበብ ሀገር በኢትዮጵያ ጠቢብ ነኝ የሚል ሰው ‹ከዕውቀት ርቆ፣ ንጽሕ ጠብቆ› በድፍረት ይኖራል? ይኼኮ ሀገርን መድፈር ነው?  
አገሪቱ አድግበታልሁ፣ እመነደግበታለሁ፣ እለወጥበታለሁ፣ አሰላለፌን አስተካክልበታለሁ ብላ የደከመችበት የአምስት ዓመት ዕቅድ እንዴት በስሕተትና በድፍረት በተሞላ መድረክ እንዲታወጅ ይፈቀዳል? ይህንን ዕቅድ ባስታወስን ቁጥር ያንን ትልቅ ስሕተት እንድናስታውስ ለምን ተፈረደብን? ጥበብ ሳይሆን ድፍረት ትዝ እንዲለን ለምን ተገደድን? 
 
ጥበብ ምንም ዓይነት ይዘት ይኑረው የጥበብን ደረጃ ማሟላት ግን አለበት፡፡ ልማታዊም ሆነ አብዮታዊ፣ ዲሞክራሲያዊም ሆነ አምባገነናዊ፣ ይዘቱ ይለያይ እንጂ የጥበብ ደረጃው ግን አንድ ነው፡፡ ጥበብም የሚያሰኘው የጥበቡ ደረጃ እንጂ የያዘው ይዘት አይደለም፡፡ እንዴት ምግብ ቤቶቻችን ለምግብ አሠራርና አቀራረብ የሚጨነቁትን ያህል ለሀገራዊ መድረክ የሚጨነቅ ይጥፋ? እንዴት የበያይነቱ ምግብ ያህል ጥበብ በሀገራዊ መድረክ ላይ እንጣ?
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹ሀገራችን የራስዋ የሆነ ልዩ የዘመን አቆጣጠር አላት› ብለው ነገሩን፡፡ እውነት ነው ጠቅላይ ሚኒስትራችን የሀገር ባህል ልብስ ለብሰው በነገሩን የሀገራችን ልዩ የዘመን ቆጠራ እንስማማለን፡፡ ‹አርቲስቶቹ›› ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሳስተዋል፤ ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ የዘመን አቆጣጠር የላትም›› አሉን፡፡ ‹‹አዲስ ዘመንም የሚብተው እንደ አውሮፓውያን በእኩለ ሌሊት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችን የዘመን አቆጣጠራችን የተለየ ነው ያሉት ተሳስተው ነው›› አሉን፡፡ ኧረ እባክዎን ይጠይቁልን? ለምን ‹‹አርቲስቶቹ›› ጠቅላይ ሚኒስትሩን መቃወም ከፈለጉ የፖለቲካ ድርጅት መሥርተው በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው ተቃዋሚ ፓርቲ አያቋቁሙም? ደግሞስ ለሌሎች ያልተፈቀደ እንዴት ለእነርሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የቀጥታ የዓመት በዓል ሥርጭት እንዲቃወሙ ተፈቀደላቸው? እንደ አሜሪካ የምርጫ ክርክር በቀጥታ ሥርጭት ተቃዋሚና መንግሥት በአንድ መድረክ የሚቀርቡ ከሆነማ እውነትም ሀገሬ ተለውጣለች?
 
የዛሬ ዓምስት ዓመት እንዲሁ ያለ ስሕተት ‹አርቲስቶቹ› ሲሠሩ ዐውቀው በድፍረት ሳይሆን ሳያውቁ በስሕተት ነው ተብሎ ታለፈ፡፡ ዘንድሮ እንዳይደገምም ብዙዎች በሚችሉት ሁሉ አስቀድመው አሳሰቡ፡፡ ሰሚም መስሚያም ጠፋና ስሕተቱ በባሰ ሁኔታ ተደገመ፡፡ ሰውና ሰይጣን የተለያዩትኮ ከስሕተት በመታረምና ባለመታረም ነው፡፡ ወደ ሥልጣኔው መሄድ ሲገባን ወደ ስ…   
ጠቅላይ ሚኒስትር ሆይ፤ አሁን ማንን እንመን? እርስዎን እንመን ወይስ ‹አርቲስቶቻችንን››?
  

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “ስለሚያገባን እንጦምራለን” በሚል መሪ ቃል ከዛሬ አራት ዓመት በፊት የተቋቋመው የዞን ፱ ዐምደ መረብ ጸሃፍት የሕገመንግስቱ የመጻፍ ነጻነት በሚፃረረው መልኩ እንደ ሌሎቹ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በአሸባሪነት ተከሰው ካለ ፍትሕ በእስር ቤት የሚገኙት ጦማሪያኑና የቡድኑ አባላት ለፕሬስ ነፃነት ላደረጉት አስተዋፆ ዓለማቀፉን የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ተሸላሚ አድርጓቸዋል። የጋዜጠኞች መብት …

CPJ Zone 9 Bloggers Ethiopia - CPJ will honor Zone 9 bloggers with 2015 International Press Freedom Awards.

የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የሲፒጂ አለማቀፍ የፕሬስ ነጻነት የ2015 ሽልማት ተሸላሚ ሊሆኑ ነው:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪- CPJ will honor Zone 9 bloggers with 2015 International Press Freedom Awards. Minilik Salsawi – “ስለሚያገባን እንጦምራለን!” በማለት ለሕዝብ የዲሞክራሲን እና የሕግ ጽንሰ ሃሳብን በዳበረ መልኩ …

የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የሲፒጂ አለማቀፍ የፕሬስ ነጻነት የ2015 ሽልማት ተሸላሚ ሊሆኑ ነው:: Read more »

መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የታዋቂዋ አርቲስት የቀብር ስነስርዓት በ ቅድስ ስላሴ ካቴደራል ወዳጅ ዘመዶቿና አድናቂዎቿ በተገኙበት ተፈጽሟል። አርቲስት ሰብለ ተፈራ በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ወሎ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አይቤክስ ሆቴል አካባቢ በግንቦት ወር 1968 ዓም. የተወለደች ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በንፋስ ስልክ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቃለች። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷንም በዛው …

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታጋይ መኮንን ተስፋዬ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት ድርጅቱ ከሚያዚያ እስከ ነሃሴ በነበሩት ወራት ከታች እስከ ላይ የ7 ዓመታት ግምገማ አድርጓል። የሞላ አመራር “ትህዴንን ወደ ድል አላበቃውም ይቀየር” የሚል ጥያቄ በመላ ሰራዊት አባላት መነሳቱን የተነገሩት ምክትል አዛዡ፣ ሞላ አስጎደም አገርህን አድን ከሚለው አዲስ ጥምረት መመስረት ጋር …

መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ትህዴን፣ የቀድሞው የድርጅቱ መሪ ሞላ አስገዶም የተወሰኑ ተከታዮቹን በመያዝ በሱዳን በኩል አድርጎ ኢትዮጵያ መግባቱን ተከትሎ በሰጠው መግለጫ ” የተወሰኑ በትግሉ የቆዩና ግላዊ ጥቅማቸው የተነካባቸው ግለሰቦች ትግሉን ባሻቸው መንገድ ሊጠመዝዙት ስላልቻሉና በአብዛናው ታጋይ በመድረክ ተይዘው መፈናፈና ስላጡ ተስፋ ቆርጠው ከትግሉ ጎራ ሸስተዋል” ብሎአል። ንቅናቄው …

ግንቦቶቹ የደምህት አመራርና ወታደሮች ከድተው ለወያኔ እጅ መስጠታቸውን የኤርትራው ትግል እየተጠናከረ ስለሆነ ነው እያሉ ይቀልዱብናል። መቸም የጨነቀው ብዙ ሊል ይችላል ግን ግንቦቶቹ አንድ ነገር እባካችሁ ተረዱ፤ መጀመሪያ የራሳችሁን ግንቦት 7 የሚባለውን ቤታችሁን አጠናክሩ። ለራሳችሁ ጥንካሬና በእግራችሁ ለመቆም ስሩ። ሊቀመንበራችሁም አስመራ …

የግንቦት 7 ስትራቴጂ፤ «ጭብጥ ቆሎ ይዘህ ወደ አሻሮ ተጠጋ» Read more »

የባለፈው ሣምንት በኤርትራ የጋራ ንቅናቄ ከመሠረቱት አራት በትጥቅ ትግል የተሠማሩ ንቅናቄዎች የአንደኛው የትግራይ ሕዝብ የጋራ ንቅናቄ መሪ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተገልጿል፡፡

የግብፅ ፖፕ ቴዎድሮስ ዳግማዊ ለመስቀል በዓል አዲስ አበባ ይገባሉ

የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፖፕና ፓትርያርክ ቴዎድሮስ ዳግማዊ በመስቀል በዓል አከባበር ላይ ለመታደምና የአራት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ፣ መስከረም 15 ቀን 2008 ዓ.ም. አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡

የኮፕቲክ ፓትርያርክ ቴዎድሮስ አራት ቀናት በሚወስደው ቆይታቸው መስከረም 16 ቀን 2008 ዓ.ም. የሚከበረውን የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ከመታደማቸው በተጨማሪ፣ ወደ አክሱምና ላሊበላ አቅንተው ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ሥፍራዎችን እንደሚጎበኙም ታውቋል፡፡ 

ከዚህ በተጨማሪም በሚኖራቸው ቆይታ በአዲስ አበባ የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላትን፣ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ከታዋቂ ግለሰቦች ጋር እንደሚነጋገሩ ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ከፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመና ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ፣ እስካሁን ግን የተረጋገጠ ነገር አለመኖሩን አክለው አብራርተዋል፡፡  

ፓትሪያርኩ የአዲስ አበባ ጉዟቸውን አስመልክቶ ከሳምንት በፊት ከግብፅ የውኃ ሀብት ሚኒስትር ሆሳም አል ሞጋሃዚ ጋር መነጋገራቸው የተዘገበ ሲሆን፣ በውይይታቸውም ወቅት ግብፅ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ ያላትን ጥያቄዎች አንስተው ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናትና ከአቡነ ማትያስ ጋር ውይይት እንዲያደርጉ ሚኒስትሩ መጠየቃቸውና የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ተዘግቧል፡፡ 

ፖፕ ቴዎድሮስ በበኩላቸው ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ሁለቱ ቤተ ክርስቲያናት ባላቸው ታሪካዊ ግንኙነት የተነሳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በዚህ ረገድ እየተባበሯቸው እንደሆነና አስተዋጽአቸውም ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋል በማለት ስታር አፍሪካ የተሰኘ ድረ ገጽ ላይ የወጣ ዘገባ ያትታል፡፡

የኢትዮጵያ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ባለፈው ጥር ወር ግብፅን ለስድስት ቀናት በይፋ በጎበኙበትና በካይሮ ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግሥት ከፕሬዚዳንት አልሲሲ ጋር በተወያዩበት ወቅት፣ ፕሬዚዳንቱ የዓባይ ወንዝ ለኢትዮጵያውያን የልማት ምንጭ ቢሆንም ለግብፅ ግን ልማት ብቻ ሳይሆን የደም ሥር መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል፡፡ 

አቡነ ማትያስም በበኩላቸው በጠንካራ ትስስር ላይ የተመሠረተው የሁለቱ አገሮች ግንኙነት፣ ከዓባይ የሚመነጭ ውኃ የማያቋርጥ የጋራ ሀብት በመሆኑ በፍትሐዊነትና በእኩልነት ተጠቃሚ የሚኮንበት ይሆናል ማለታቸውም አይዘነጋም፡፡ 

ፖፕ ቴዎድሮስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. በ1952 ማንሱራ በተሰኘ የግብፅ ከተማ የተወለዱ ሲሆን፣ በ1975 ከኤሌክሳንዳርያ ዩኒቨርሲቲ በፋርማሲ የመጀመሪያ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡ ለጥቂት ዓመታት በመንግሥት ቁጥጥር ሥር የሚገኝ መድኃኒት ፋብሪካን ከአስተዳደሩ በኋላ፣ ቅዱስ ፒስሆግ የተባለ ገዳም በመግባት የሥነ መለኮት ትምህርት በማጥናት እ.ኤ.አ. በ1989 ተመርቀዋል፡፡ 

የአቡነ ሺኖዳ ሕልፈተ ሕይወትን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት 118ኛው የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በመሆን ከሦስት ዓመት ወዲህ በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡   

 

 

Minilik Salsawi :- የደምሕት ታጋይ ሞላ አስገዶምን ተከትሎ ብዙ የኮካዎች ውሮሸባ የቀወሱ ሃሳቦች የስም ማጥፋቶች የተበሳጩ ኪሳራዎች የደቀቁ የተልፈሰፈሱ ዲያስፖራዎች የእርስ በእርስ ግልምጫዎች እና ዘለፋዎች አሳፋሪ ዘመቻዎች እና ፍረጃዎች ወዘተ ያላነበብነው ነገር የለም::እውነት ከማይዋጥላቸው ድንጉጥ ያልበሰሉ ፖለቲከኞች ጀምሮ ኪሳራ የተከናነቡ …

መንግስታዊ ውዥንብር – የአረና ሰዎች ሽርጉድ – የመንደርተኝነት አጀንዳ ድምዳሜው (ምንሊክ ሳልሳዊ‬) Read more »

  የአርቲስት ሰብለ ተፈራ የቀብር ስነሥርዓት ብዙ ሺህ አድናቂዎቿ እና ወዳጅ ዘመዶቿ በተገኙበት ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ተፈጸመ::ባለቤቷ የሚያሽከረክረው መኪና ከቆመ መኪና ጋር ተላትሞ የአርቲስቷ ሕይወት በአዲሱ ዓመት ያለፈ ሲሆን ባለቤቷ ሞገስ ተስፋዬ ላለፉት 3 ቀናት እስር …

የአርቲስት ሰብለ ተፈራ የቀብር ስነሥርዓት ተፈጸመ ::ባለቤቷ ሞገስ ተስፋዬ በ15 ሺ ብር ዋስ ተለቀቀ:: Read more »

ከመግለጫው በስተጀርባ ጌታቸው ሺፈራው የትህዴን ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ሞላ አስግዶም ከኤርትራ መውጣታቸውን ተከትሎ በህወሓት/ኢህአዴግ እና በተቃዋሚዎች በኩል ያልተጠበቁ ስሜቶች ተስተናግደዋል፡፡ ከተቃዋሚዎች በላይ ግን ራሱ ስርዓቱና ደጋፊዎች በክስተቱ ስሜታዊ ሆነው፡፡ ለዚህም በስርዓቱ ደጋፊ ሚዲያዎችና በደህንነት ተቋሙ እየተላለፉ ያሉትን መረጃዎች ማየት በቂ …

የሻዕቢያ ተላላኪ ሲላቸው የነበሩትን ሰው በአንዴው የራሱ ተላላኪ አድርጓቸዋል፡፡ ከመግለጫው በስተጀርባ ጌታቸው ሺፈራው Read more »

    በአለማየሁ አንበሴ የፍቅር አዲስ – “ምስክር” ታዋቂዋ ድምፃዊት ፍቅር አዲስ ነቃጥበብ፤እንደ ብዙዎቹ ድምጻውያን ሁሉ ለብዙ ዓመታት ድምጽዋን ሳንሰማ ቆይተናል፡፡ 2007 ዓ.ም ሊሰናበት ጥቂት ቀናት ሲቀሩትና አዲሱ ዓመት ለመጥባት እየተሽኮረመመ ሲጠባበቅ እሷ በመሃል 8ኛ የዘፈን አልበሟን ይዛ ከተፍ አለች፡፡  …

ፍቅር አዲስ ነቃጥበብ ስምንተኛ አልበሟን አውጥታለች Read more »

አቶ ሞላ አስገዶም ትግሉን ባሻቸው መንገድ ሊጠመዝዙት ስላልቻሉ ከትግሉ ጎራ ሸሽተዋል። – (አስመራ የሚገኘው ትህዴን) #Ethiopia #MinilikSalsawi አስመራ የሚገኘው ትህዴን መግለጫ አወጣ – “የሸሹት የግል ጥቅማቸው የቀረባቸው ናቸው” – ከትህዴን የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ድርጅታችን ትህዴን በየካቲት 1993 ዓ/ም ብረት አንስቶ …

አቶ ሞላ አስገዶም ትግሉን ባሻቸው መንገድ ሊጠመዝዙት ስላልቻሉ ከትግሉ ጎራ ሸሽተዋል። (አስመራ የሚገኘው ትህዴን) Read more »

ድርጅቱ ችግሩን ቀርፌያለሁ ይላል

የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የክፍያ ሥርዓት ችግር እንደገጠመው ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ድርጅት በበኩሉ ችግር ተፈጥሮ እንደነበር አምኖ በአሁኑ ወቅት መቀረፉን ገልጿል፡፡ 

የኤሌክትሪክ አገልግሎት ድርጅቱ ማዕከላዊ የክፍያ ሥርዓት (ቢሊንግ ሲስተም) ከሁለት ወራት በፊት በገጠመው ችግር ሳቢያ፣ የደንበኞችን ወርኃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያ ለሁሉ ለተባለው የተቀናጀ የአገልግሎት መክፈያ ማዕከል መላክ እንዳልተቻለ ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ 

ደንበኞች ወደ ክፍያ ለሁሉ በሚሄዱበት ጊዜም ትክክለኛ መረጃ እንደማይነገራቸውና በሌላ ጊዜ እንዲመጡ ብቻ እንደሚገልጹላቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ 

ጉዳዩን በተመለከተ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የክፍያ ለሁሉ የሥራ ኃላፊዎች የተፈጠረው ችግር እነሱን እንደማይመለከት ይገልጻሉ፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሚሰጠን የደንበኞች ወርኃዊ ፍጆታ መረጃ መሠረት ደንበኞችን ማስከፈል ነው ሥራችን፡፡ መረጃ ካልደረሰን ማስከፈል አንችልም፤›› ብለዋል፡፡ 

በመሆኑም ጉዳዩ የበለጠ የሚመለከተው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በዚሁ መሠረት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ድርጅት የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ገብረ እግዚአብሔር ታፈረ ተጠይቀው ችግሩ ተፈጥሮ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ 

የማዕከላዊ የክፍያ ሥርዓት ሰርቨር የመረጃ ካርድ በመቃጠሉ ምክንያት ችግሩ እንደተፈጠረ የተናገሩት የውጭ ግንኙነት ኃላፊው፣ ካርዱ በአገር ውስጥ ስለማይገኝና ከውጭ ተገዝቶ እስኪገባ ድረስ የሐምሌ ወር የኤሌክትሪክ ፍጆታን ደንበኞች ማለትም ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚዎች ከሆኑ ድርጅቶች በስተቀር መክፈል አለመቻላቸውን አስረድተዋል፡፡ 

በአሁኑ ወቅት ግን ችግሩ የተቀረፈ በመሆኑ የሐምሌ ወር የክፍያ ቢል መውጣቱንና ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ ደንበኞች የነሐሴ ወር ፍጆታቸውን መክፈል እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡ 

የቀድሞው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽንን ለሁለት በመክፈል በ64.7 ቢሊዮን ብር የተፈቀደ ካፒታልና በ16.2 ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል የተቋቋመው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማኔጅመንት ፓወር ግሪድ ኮርፖሬሽን ለተባለ የህንድ ኩባንያ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ 

ኩባንያው ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎትን በመስጠት ደንበኞችን ማርካት ዋነኛ ኃላፊነቱ ሲሆን፣ መንግሥት ለሁለት ዓመት 16.7 ሚሊዮን ዶላር በመክፈል የሰጠው የማኔጅመንት ኮንትራት ነሐሴ 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ተጠናቋል፡፡ 

 

በያሬድ ቁምቢና ውብዓለም ተስፋዬ የአዲስ አመት ዋዜማ ጳጉሜ 5 ቱሉ ዲምቱ አቃቂ ደብረ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመገኘት ‹የመዳን ቀን ዛሬ ነው› እና‹ የጅራፍ ንቅሳት› የተሰኙ ሁለት የራሷን ግጥሞች አቅርባለች፡፡ ገና በስራዋ ስትታይ ድንቅ የትወና ብቃትና ፈጠራዋ የብዙዎችን ቀልብ መሳብ የቻለች ብርቅዬ ድንቅ አርቲስት ነበረች …ሰብለ ተፈራ፡፡ ፍጹም ባልተጠበቀ እና ድንገተኛ […]

አባቶቻችንን የተማርንባቸውን መድረሳዎች ለመስራት እና እዚህ ለማድረስ ከፍተኛ መስዋእትነት እንደ ከፈሉ ታሪካቸውን ሲነግሩን እና ያለፉትን ስርአቶች ጋር ተናንቀው እዚህ እንዳደረሱት የማይካድ ሃቅ ነው ፡፡ በሀገራችን መስጅዶችና መድረሳዎች ባለፉት ስርአት ደም ፈሶባቸዋል አጥንት ተክስክሶባቸዋል፡፡ መስጅዶችና ኢስላማዊ ትምህርት ቤቶችን እዚህ ለማድረስ በርካታ …

የትግላችን መነሻ ምንድን ነው ? በአሁኑ ሰአት በየ አካባቢያችን ምን እየተከናወነ ነው ? (አብዱረሂም አህመድ:BBN) Read more »

አርቲስት እንድሪስ አህመድ ከ45 አመታት በፊት ነበር በብሄራዊ ቴዓትር ስራ የጀመሩት። ወሎ ክፍለ ሃገር ቢወለዱም ዳንስ የተማሩት በቅጽል ስሙ ውቤ በርሃ ተብሎ በሚታወቀው ደጃች ውቤ ሰፈር ነበር። አርቲስ እንድሪስ አህመድ ቡጊና ትዊስት ከደነሱበት ብሄራዊ ቴዓትር በጡረታ ቢሰናበቱም አሁን በፊልም ትወና ላይ ተሰማርተዋል።

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

በኤርትራ ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረው የትህዴን ጦር በመሪው ሞላ አስገዶም እየተመራ ወደ ኢትዮጵያ ገባ:: #Ethiopia ወያኔ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ከ700 በላይ እንደሚሆኑ የተገመተው የደህሚት ጦር ከነ ሙሉ ትጥቁ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ በሁመራ እና በመተማ አድርጎ ሰላማዊ በሆነ መንገድ መምጣቱን የፋና …

በኤርትራ ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረው የትህዴን ጦር በመሪው ሞላ አስገዶም እየተመራ ወደ ኢትዮጵያ ገባ:: ወያኔ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። Read more »

ዘረኝነትና ጥላቻ በመንግሥት ደረጃ በሚሰበክበት አገር፣ ድንቁርና እጅግ በተጫናቸው የወያኔ ቱባ ባለሥልጣናት ሕዝብ በሚዘለፍበት፣ ታሪክ ተጣሞ የአንድ ቋንቋ ተናጋሪን የሕብረተሰብ ክፍል በሌላው ላይ ለማነሳሳት ሌት ተቀን የሚደክሙና ጉርጓድ የሚምሱ ቡድኖችና ግለሰቦች ባሉበት አገር፣ ፍርሃትና ጥርጣሬ በነገሱበትና አፈና በበረታበት እንደ ኢትዮጵያ ባለ አገር እንደ ቴውድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ‹ ያሉ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በማሕበረሰቡ ውስጥ ያላቸው ሚና በዘፈን […]

የገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ አጋር የሆነው የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ሥራ አስፈጻሚ አባላት መካከል አለመግባባት መፈጠሩ ተሰማ፡፡ በዚህ ምክንያት የክልሉን ቋሚ መስተዳድር መመሥረት እንዳልተቻለ ምንጮች ገልጸዋል፡፡አለመግባባቱ የተፈጠረው አብዴፓንና የአፋር ክልልን ላለፉት 20 ዓመታት ሲመሩ በቆዩት የቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ እስማኤል ዓሊ …

በአፋሩ አብዴፓ አመራሮች መካከል የሥልጣን አለመግባባት መፈጠሩ ተሰማ Read more »