የሕወሓትን ጓዳ ከነጫጩቶቿ ያንቀጠቀጠው የፕሮፌሰር መስፍን አዳፍኔ ፍርሃትና መክሸፍ (ምንሊክ ሳልሳዊ)

የሕወሓትን ጓዳ ከነጫጩቶቿ ያንቀጠቀጠው የፕሮፌሰር መስፍን አዳፍኔ ፍርሃትና መክሸፍ  (ምንሊክ ሳልሳዊ)
አዳፍኔ ፍርሃትና መክሸፍ

ሰሞናኛ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ አሸብረው የተሸበሩ የዘረኛ ቡድን ካድሬ የሆኑ የሕወሓት ጫጩቶች የማህበራዊ ሚዲያ ጫጫታ ነው::ምሁር በሽታቸው የሆነ ሕወሓቶች ጫጫታቸው ያተኮረው በፕሮፌሰር መስፍን ላይ መሆኑ ምን ያህል በበታችነት ዛሬም እንደሚያላዝኑ ያሳየ ነው::ፕሮፌሰር መስፍን አዳፍኔ የተባለውን የእኩይ ፖለቲከኞችን ሴራ ፍንትው አድርገው ያሳዩበት መጽሃፍ ከወጣ ጀምሮ ተራሮችን አንቀጠቀጥኩ የሚሉት እነአግበስብሴ ከነጫጩቶቻቸው ዘራፋቸውን ከመጀመራቸውም ሌላ መጽሃፉን የመተቸት/የመገምገም አቅሙ ስላሌላቸው የግለሰብን ሰብእና እስከመንካት ዘልቀዋል::ይህ የሚያሳየው የፕሮፌሰሩ አዳፍኔ የሕወሓትን ጓዳ ምን ያህል እንዳንቀጠቀጠ ነው::

ኢትዮጵያዊው ምሁር ፕሮፌሰር መስፍን ሲጽፉን ሲናገሩም የመጀመሪያቸው አይደለም::ሌሎችን ኢትዮጵያውያን ምሁራን እና ፖለቲከኞች በዘረኞች እና በእኩይ ፖለቲከኞች ላይ መጽሃፍትን ጽፈዋል::የአዳፍኔ ግን በተለየ ሁኔታ የሕወሓትን ቤት አናግቶታል::ሕወሓቶች ከጫፍ እስከ ጫፍ ፕሮፌሰሩ ላይ አፋቸውን አሹለው መነሳታቸው ያለቸው የፖለቲካ እምነት በበታችነት እና በዘረኝነት ላይ ስለተመሰረተ ተዳፍኖ ሳይቀር ስለተጋለጠባቸው መቆምያ መቀመጫ ሲያጡ ታዝበናቸዋል::የሕወሓት ፖለቲካ ምን ያህል በጥቂቶች የዘረኛ አስተሳስብ ላይ እንደተመሰረተ እያየን ያለንበት ሁኔታ ላይ ነው ያለነው::ሕወሕቶች ከነጫጩቶቻቸው ምነው እንዲህ ተራወጡ? የሚጽፉት ሰዎች ደሞ አንድ ወጥ የሆኑ ለምን ሆኑ? ብአዴኖች ኦሕዴዶች የት ገቡ ? ማን የበታችነት ስሜት ውስጥ ዘረኝነትን እንደሚዘፍቅ አዳፍኔ በተግባር እያሳየን ነው:: እድሜ እና ጤና ለፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም::ኣቦ ተባረክ !!! Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

Minilik Salsawi's photo.

6 Comments on “የሕወሓትን ጓዳ ከነጫጩቶቿ ያንቀጠቀጠው የፕሮፌሰር መስፍን አዳፍኔ ፍርሃትና መክሸፍ (ምንሊክ ሳልሳዊ)”

  1. የአመቱ ታላቅ ሰው መባል የነበረባቸው አራት አይናው ምሁር አለቃ(prof) መስፍን ወ/ማርያም ናቸው!

  2. እሽ ለእሳቸው ያለኝ ከበሬታና ጽናት እንዳለ ሆኖ ይኽነን ስለሙሶሉኒና ግራዚያኒ ቅድስና እና ጀግንነት እንድሁም ታላቅነት ከቤቱ ሲማር ያደገና በተቃራኒው ስለ ኢትዮጵያና ስለአርበኞችዋ ተጋድሎ ተቃራኒውን እቤቱ ሲነገረው ያደገና ይኽንንም ቂሙንና የበታችነት ስሜቱን በተግባር ያዋለን እስከ መጨረሻው እስትንፋሱ”ኢትዮጵያ” ለማለት ተጠይፎ ይች አገር እያለ ይሞተን የባዕዳን ወኪል እንዴት ብሎ ነው ከአፄ ኃለሥላሴ እና ከኮሎኔል መንግስቱ ጎን ለጎን የሱ ፎቶ የሚቀመጠው ?
    ሲጀመር ኢዮጵያዊ ያልሆነን ስው? ፕሮፌሰሩን ለመተቸት ብቃትም ድፍረትም ባይኖረኝም ለኢትዮጵያ በጎ ምኞት የነበራቸው ግን በስልጣን ፍቅር ተቸንፈው የተሳሳቱ ከባንዳ ልጅ የብርሃንና የጨለማ ያህል ይለያሉ።የመጽሃፋቸው ይዘት ይኽንን ቁልጭ አድርጎ እንደሚያቀምጠው ባልጠራጠርም ፎቶው ከኢትዮጵያዊያን ጎን መቀመጡ . . . .
    ልብ በሉልኝ ፕሮፌሰሩን ለመተቸት ቀርቶ የጫማቸውን ማሰሪያ ለመፍታትም አልበቃም።

  3. the professor I think he put all the 3 head of states for comparison purposes, on the other side if you take the book by the title of “yemeles trufatoch” the whole cover it shows the devil meles picture. if you wanted to read that book either you have to tear the cover or you have to start from the end towards to the start so it is something that you have to compromise in order to read these books.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*