ኤርትራ ‹‹የኢትዮጲያ አይነ ውሃ አላማረኝም ›› ማለቷ ተሰማ! (አሌክስ አብርሃም)

 

ኤርትራ ‹‹የኢትዮጲ ያ አይነ ውሃ አላማረኝም ›› ማለቷ ተሰማ! (አሌክስ አብርሃም)

የኤርትራ የኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ትናንት መግለጫ አውጥቶ ነበር ….እናም በመግለጫው ኤርትራ ‹‹በኢትዮጲያ እየተደረገባት ያለው ዛቻና ወታደራዊ ትንኮሳ እየጨመረ ነው …ማስፈራሪያውም በርክቷል ›› መባሉን ዘ ገልፍ ቱዴይ ዘግቦታል ፡፡ የኤርትራው መግለጫ ጨምሮ እንደገለፀው ‹‹ኢትዮጲያ አይነውሃዋ አላማረንም ወረራ ማሰቧንና ለዚሁ መዘጋጀቷን የሚያመላክቱ መረጃዎች አሉ ….ለዚህም የልብ ልብ የሚሰጧት እንደአሜሪካ አይነት የኢትዮጲያ አጋሮች ናቸው›› ሲል ክሱን አስፍቶታል !

Alex Abreham's photo.

በኢትዮጲያ በኩል እስካሁን ለዚህ ክስ የተሰጠ ምላሽ ባይኖርም ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ለኢትዮጲያ ፓርላማ ኤርትራ እጇን ካልሰበሰበች እና እያሰረገች የምታስገባቸውን ‹ሽብርተኞች› ሃይ ካላለች ‹‹ህዝባችንን አስፈቅደን›› እርምጃ ልንወስድባት እንጅላለን ›› ማለታቸው የሚታወስ ነው …አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በወቅቱ ‹‹ህዝብ ለግድቡ ሳንቲም ከማዋጣት ጎን ለጎን እንዲህ ለጦርነት ሃሳብ እና ፈቃድ ማዋጣት መጀመሩ የአገራችንን ባለሁለት አሃዝ እድገት የሚያመላክት ነው ›› ማለታቸው ይታወሳል፡) ….በነገራችንላይ ሁለቱም አገራት አንዱ አንዱን ‹‹ውስጥ ችግራቸውን በፍታት ሲያቅታቸው የህዝቡን ትኩረት ወደውጭ ለመመለስ ነው ጦርነት ሽብር የሚያስቡት›› እየተባባሉ ይወነጃጀላሉ እነፕሬዝደንት ኦባማም ዝምታን መርጠዋል ምናልባት ዘና ብለው ተቀምጠው ‹‹አስተናጋጅ ቡጥቡጡ ከመጀመሩ በፊት አንድ ቢራ›› እያሉ ይሆናል !….

ለማንኛውም አገራችን በዚህ ወቅት እንደገና ወደጦርነት ባትገባብን ምርጫችን ነው !! ‹‹አይ ሳንዋጋ አስር አመት አለፈንኮ እጃችንን እናፍታታ …ወንድነታችንም ትንሽ ይፈተሸ እንጅ ›› ከተባለ . . .፡)ማነሽ አልጣሽ ምንሽሬን አቀብይኝ…ወደሰማይም ቢሆን እተኩሳለሁ …እግዜርን በምንሽር ካልቀሰቀስነው ፆለታችንን አልሰማ ብሏል፡)፡)እናተ ልጆች ዝሆኖች እንደገና ሊጣሉ ነው ሳሩን ወደጥግ ወደጥግ አድርጉት እስቲ !

Alex Abreham's photo.

3 Comments on “ኤርትራ ‹‹የኢትዮጲያ አይነ ውሃ አላማረኝም ›› ማለቷ ተሰማ! (አሌክስ አብርሃም)”

  1. our country ETHIOPIA needs no war this time or any time the only war she needs is to get rid off these stupid juntas (the so called) weyanes that one is to be done.
    The ERITRIANS now learned their lessons they wanted to be with ETHIOPIA. we are going to build our relations on dead bodies of weynes.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*