ለረጅም ጊዜ በአገራችን ፖለቲካ ሰፊ ጥናት ያካሄዱት ጆን ማርካኪስ “ኢትዮጵያ፣ ዘ ላስት ቱ ፍሮንቲየርስ” የሚለውን አዲሱን መጽሀፋቸውን ለማስተዋወቅ በለንደን ቻትሀም ሀውስ በተገኙበት ወቅት ህወሃት መራሹ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ስልጣን በበቂና ተጨባጭ በሆነ መልኩ ወደ ክልሎችና ወደ ወረዳዎች ለማስተላለፍ ባለመቻሉ፣ የመፈረካከስ አደጋ ተጋርጦበታል ብለዋል። በዚህ ስነሥርዓት ላይ ተመሳሳይ ንግግር ያደረጉት ሌላው ታዋቂ ምሁር ፕሮፌሰር ክርስቶፈር ክላፋም […]

እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር ከትናንትና ወዲያ ማክሰኞ ኖቨምበር 29 ቀን በፍራንክፈርት ጀርመን የተቃውሞ ሰልፉን ያካሄዱት ኢትዮጵያዊያን፤ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ በአገራችን ውስጥ እየፈጸመ ያለው ገደብ የለሽ ግፍና ሰቆቃ እንዲቆም ለመጠየቅ መሆኑን የሰልፉ አስተባባሪዎች መናገራቸውን ዘጋቢያችን ከስፍራው በላከልን ዜና ገልጾአል። የተቃዋሚ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴ ለመግታት በፓርቲ መሪዎች፤ በአባላቶቻቸውና ነጻ ጋዘጤኞች ላይ እየተወሰደ ያለውን እስርና እንግልት አጥብቀን እንቃወመዋለን ያሉት ሰልፈኞች፤ […]

ባለፈው እሁድ ለ11ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በተካሄደው ታላቁ ሩጫ የተሳተፉ ዜጎች፤ ወያኔ መራሹ የመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ በአገራችን ውስጥ እያሰፈነ ያለውን ኢፍትሃዊነትና አፈና የሚያወግዝ መፈክሮችን ሲያሰሙ እንደዋሉ የግንቦት 7 ዜጋቢ ከአዲስ አበባ በላከልን ዜና አስታወቀ። በዚይ የህዝብ ብሶት ሲስተጋባበት በዋለው የሩጫ ውድድር የተሳተፉት፤ ከምዝገባው ጀምሮ በተቻለ መጠን ለወያኔ ፖለቲካ ወገንተኝነት ያላቸው እንዲሆኑ በአዘጋጆች […]

ግርማ ብሩ ይህንን ያስታወቀው በፈረንጆች አቆጣጠር ያለፈው ሳምንት ኖቨምበር 20 ቀን በአትላንታ ከተማ አፍቃሪ ወያኔዎችን የሚላኒዬም ግድብ ብሎ ለተሰየመው ማደናገሪያ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ እንዲሰጡና ዲያስፖራውን በጥቅማጥቅም ለመያዝ በተረቀቀው አዋጅ ላይ ለመነጋገር ጠርቶአቸው በነበረው ስብሰባ ላይ ነው። “መንግሥታችን የህዳሴ ግድብ ብሎ የሰየመውን ይህንን ታሪካዊ ግድብ ለመገደብ ሲነሳ፤ ከናንተ ከዲያስፖራው ህብረተሰብ ወይም አገር ቤት ካለው ህዝብ በሚሰበሰብ […]

የአትዮጵያ ሕዝብ ላለፉት አራት አስርት አመታት በላይ ከፍተኛ መስዋትነት የሚጠይቅ ትግል ቢያደርግም ዴሞክራሳዊ ስርዓት መፍጠር አልተቻለም፡፡ ደርግን የተካው ኢህአዴግ ትምህርት ወስዶ የተሻለ ስርዓት ይገነባል ተብሎ ቢጠበቅም፣ እሱም የለየለት አምባገነንና አፋኝ ስርዓት ለመሆን በቃ፡፡ ጭቆና እንዲወገድ፣ እኩልነት እንዲረጋገጥና እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲመሠረት በሚድረግ ጥረት ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ለሀገራቸው ልማትና ብልፅግና ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ ከመስራት ይልቅ ጥላቻና […]

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ «ለአፍሪቃውያን ግብረ-ሰዶማዊ ወንዶች የቆመ ድርጅት» የተባለው ቡድን፣ በአዲስ አበባ የሚያደርገውን ስብሰባ በመ

አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምትለግሰው በቢሊዮን ዶላር የተቆጠረ እርዳታ የህጻናትንና የኤድስ ህሙማንን ሞት ሲቀንስ የእናቶች ጤና ላይ ብዙ መስራት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ።

የበጎ አድራጎትና ማኅበራት ማደራጃ ኤጀንሲ የኮሙኒኬሽን የሥራ ሒደት ባለቤት
የበጎ አድራጎትና ማኅበራት ማደራጃ ኤጀንሲ ራሱን ችሎ በ2001 ዓ.ም. ተቋቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ኢ.ቲ.ቪ.) ለሳምንት ያህል አንድ ማስታወቂያ እየደጋገመ ማሰማት ጀመረ። ‘አኬልዳማ’ የተባለ ልዩ የፊልም ዝግጅት። በአኬልዳማ ማስታወቂያ ፊልሙን ከ13 አመት በታች ያሉ ህጻናት እንዳይመለከቱት ጥብቅ ማስጠንቀቅያም አለለበት። ማስታወቂያውን ከዚህ በፊት ከነበሩት ለየት የሚያደርገው ይህ የማስፈራርያ ማስተንቀቅያው ነው። በማስታወቂያው ውስጥ የአርቲስት ደበበ እሸቱ ምስልም ይታያል። በዚህ ‘ልዩ’ ዝግጅት አርቲስት ደበበ እሸቱ የሚተውንበት ከሆነ ከቀድሞዎቹ የፈጠራ ስራዎች […]