ስፖርት

በትላንት ዕሁዱ ታላቁ የኢትዮጵያ ሩጫ የአሥር ሺህ የጎዳና ውድድር ሙስነት ገረመውና አበበች አፈወርቅ አሸንፈዋል። ከቀደሙት ውድድሮች ሁሉ በበለጠ 36 ሺህ ሯጮች ተሣትፈውበታል።

ከሀገር ውጭም ቀዳሚ ሥፍራዎችን አላስቀመሱም፣

በኢጣልያ – ፍሎረንስ ማራቶን ብርሃኑ በቀለ በርጋና አሻ ጊጊ፥ በሕንድ – ኒው ዴልሂ ግማሽ ማራቶን ሌሊሳ ዴዲሳ፥ በቤይሩት በሁለቱም ፆታዎች፥ የኮርሱን ሬከርድ በማሻሻል ጭምር ታሪኩ ጂፋርና ሰዓዳ ከድር አሸንፈዋል።

ሌሎች የእግር ኳስ ስፖርት ዜናዎችን ደግሞ ያድምጡ።

አዘጋጅና አቅራቢው ሰሎሞን ክፍሌ ነው።