ምርጫ በኮንጎ

በዴሞክራሲያዊት ኮንጎ ሬፑብሊክ በዛሬው ዕለት ፣ እአአ ኅዳር 28፣ 2011ዓም አጠቃላይ ምርጫ እየተካሄደ ነው። ለፕሬዚደንታዊው ምርጫ አስራ አንድ ዕጩዎች፣ ካለፉት አስር ዓመታት ወዲህ ሀገሪቱን በመምራት ላይ ያሉት የአርባ ዓመቱ ፕሬዚደንት ጆሴፍ ካቢላ ጭምር ለውድድር ቀርበዋል።

ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ዕጩዎች መካከል ለካቢላ ጠንካራ ተፎካካሪ ይሆናሉ የሚባሉት የዴሞክራሲያዊ እና ማህበራዊ ዕድገት ህብረት መሪ ኤትየን ቺሴኬዲ ናቸው። በካቢላ አመራር ስር የሀገሪቱ ኤኮኖሚ ዕድገት ቢያሳይም፡ ሕዝቡ አሁንም ከድህነት አረንቛ አልተላቀቀም። በዚህም የተነሳ የአጠቃላዩ ምርጫ ዘመቻ የብዙውን ሕዝብ ቀልብ የሳበ ሆኖ መቆየቱን ታዛቢዎች ገልጸዋል። ያዳምጡ