ጀማ ሲሚንቶ በሱዳን ኩባንያ መጭበርበሩን ለብሔራዊ ባንክ አቤቱታ አቀረበ

ፓስፊክ ፔትሮሊየም የተሰኘው የሱዳን ኩባንያ በገባው ውል መሠረት በ45 ቀናት ውስጥ 14,000 ቶን ፔትሮሊየም ኮክ (ከነዳጅ ተረፈ ምርት የሚገኝ ከሰል መሰል ምርት) ሊያቀርብልኝ ሲገባ አላቀረበልኝም ሲል፣ ጀማ ሲሚንቶ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አቤቱታ አቀረበ፡፡