የ‘አኬልዳማ’ ማስታወቂያ

ክንፉ አሰፋ

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ኢ.ቲ.ቪ.) ለሳምንት ያህል አንድ ማስታወቂያ እየደጋገመ ማሰማት ጀመረ። ‘አኬልዳማ’ የተባለ ልዩ የፊልም ዝግጅት። በአኬልዳማ ማስታወቂያ ፊልሙን ከ13 አመት በታች ያሉ ህጻናት እንዳይመለከቱት ጥብቅ ማስጠንቀቅያም አለለበት። ማስታወቂያውን ከዚህ በፊት ከነበሩት ለየት የሚያደርገው ይህ የማስፈራርያ ማስተንቀቅያው ነው። በማስታወቂያው ውስጥ የአርቲስት ደበበ እሸቱ ምስልም ይታያል።