የንግድ መርከብ ማኔጂንግ ዳይሬክተር በአዲሱ ተቋም አልተመደቡም

የኢትዮጵያ የገቢና የወጪ ምርቶችን በብቸኝነት በማጓጓዝ የሚታወቀውን የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ አክሲዮን ማኅበርን በማኔጂንግ ዳይሬክተርነት ሲመሩ የቆዩት አቶ አምባቸው አብረሃ፣ አዲስ በተቋቋመው ግዙፍ መንግሥታዊ ድርጅት ማኔጅመንት ውስጥ እስካሁን አለመካተታቸው ተጠቆመ፡፡