ተስፋዬ ገብረአብ

በዓለማችን ላይ ወጣቶች በአንድ ልብ የተሳተፉበት ያልተሳካ የአብዮት ታሪክ አናውቅም። የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው። ይህችን እየፃፍኩ ሳለ የማያቋርጥ፣ የተቀናጀ የአመፅ ዜና ከኢትዮ-ኦሮሚያ እየሰማሁ ነበር። ዝምታው ማብቃቱ ግልፅ ነበር። የኦሮሚያ ወጣቶች የሥርዓቱን ታጣቂ ኃይል በጦርና በጠመንጃ ይፋለሙት ይዘዋል። ከሻሸመኔ ወደ አዲስ አበባ መንገድ ተዘግቶአል። ልማደኛዋ ኮፈሌ ጦር ሜዳ ሆናለች። ብረት ለበስ ጦር ኮፈሌና ሻሸመኔ ገብቷል። በጥቅሉ ወለጋና ሐረርጌ ፀጥታ የለም። ሱሉልታ ብሶበታል። ጭራሽ ገበሬዎቹ ያስለቀቁትን መሬት መከፋፈል ጀምረዋል። ደራ ነፃ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግርማ ካሳ

የምታዩት ፎቶ ምን ያህል በኦሮሚያ ያለው እንቅስቃሴ በአክራሪዎች፣ በኦነጋውያን እንደተጠለፈ የሚያሳይ ነው

ከ25 ዓመታት በፊት ህወሓት/ኢህአዴግ ከፋፍሎ ለመግዛት በሚል የዘረጋው የዘር ፖለቲካ ወይንም የነርሱን አባባል ልጠቀምና “የብሔር ብሔረሰቦች” ፖለቲካ፣ ብዙዎች ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ሊያጠፋ የሚችል ትልቅ አደጋ “time bomb” እንደሚሆን ሲያስጠነቅቁ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይገረም አለሙ

ወያኔ ብአዴንና ኦህዴድ የሚባሉ አገልጋዮቸን ፈጥሮ፣ ኢትዮጵያውያንን በጎሣ አከፋፍሎና ለአገዛዙ እንዲመቸው አድርጎ አደላድሎ ለ17 ዓመታት የተዋጋለትን ዓላማውን ተግባራዊ ከማድረግ አልፎ ሃያ አራት ዓመታት በሥልጣን መቆየት በመቻሉ ሊደነቅ ይገባል። ለዴሞክራሲ እንታገላለን የሚሉ እንደ ወፍ ዘራሽ በየቦታው በቅለው ሳይለያዩ ተለያይተው፣ ሳይነጋገሩ ተጣልተው፣ የቃላት እንጂ የተግባር ሰውነት ርቆአቸው ሃያ አምስት ዓመታት ስንዝር መራመድ ባልቻሉበት ወያኔ እኩይ ዓላማውን ለማሳካት አንድነቱን አጥብቆ፣ ገመናውን ደብቆ በሌሎችም ተጠቅሞ መዝለቅ መቻሉን ማድነቅ አለመቻል የራስን ድክመት ለመቀበል አለመፍቀድ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፖሊስ በሕገወጥ መንገድ ሰዎችን የሚያሸጋግሩ አሉ ብሎ ይጠረጥራል

Ethiopian Airlines 787 dreamliner የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን

Ethiopia Zare (ሰኞ የካቲት 28 ቀን 2008 ዓ.ም. Mar. 01, 2016)፡- ከአዲስ አበባ ሌሊት ተነስቶ ዛሬ ጠዋት በስዊድን መናገሻ ስቶክሆልም በሚገኘው የአርላንዳ አየር ማረፊያ ባረፈው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን የዕቃ ኮንቴይነር ውስጥ የተደበቀ የ27 ዓመት ዕድሜ ያለው አንድ ሰው መገኘቱን ፖሊስ ገለጸ። ይኸው ግለሰብ በስዊድን ጥገኝነት መጠየቁ ታውቋል። ፖሊስ በሕገወጥ መንገድ ሰዎች የሚያሸጋግሩ ወገኖች እንዳሉ ጥርጣሬ አለኝ፣ ጉዳዩን እያጣራኹ ነው አለ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አቶ ንጉስ ገብረመድህን የተባሉ ኢትዮጵያዊ የሰው ልጅና እንስሳትን የመጉዳት መርዛማ ይዘት የሌለው የትኋን መድኃኒት ቀምመው አዘጓጅተዋል። የመድኃኒት ቅመማ እና የሕብረተሰብ ጤና ሳይንስ ባለሞያ አቶ ንጉስ ከሦስት ንጥረ ነገሮች ቀምመው ያዘጋጁት ይህ መድኃኒት በአንድ የገጠር መንደር ውስጥ ተሞክሮ ውጤታማ መሆኑን ተረጋግጧል። …

የፀረ ትኋን መድኃኒት በኢትዮጵያ – VOA Read more »

በአፍሪካ አሜሪካውያን የሲቪል መብቶች ትግል ውስጥ እና በደቡብ አፍሪካ ነባር ጥቁሮች ከመጤ አፍሪካነሮች የተነጠቁትን የዕኩል ሰውነት መብት ለማስመለስ ሲታገሉ፣ ጥቂት የማይባሉ ነጮች (ወይም አፍሪካነሮች) የትግላቸው አጋር ሁነውላቸው ነበር። ሌሎች ጥቂቶች በደሎቹን ምክንያታዊና ተገቢ ለማድረግ (to justify) ተከራክረዋል። ብዙኃኑ ግን በገለልተኝነት እና በስጋት ተመልክተውታል። ከጥቁሮቹ ታጋዮች መካከልም ከፊሎቹ ለዕኩል የሰውነት ማዕረግ ታግለዋል። ከፊሎቹ ነጮቹን ለመበቀል ታግለዋል። ዞሮ፣ ዞሮ ግን ሁሉም ነባሩን ትርክት እና ተቀባይነት የነበረውን (mainstream) አስተሳሰብ ማፈራረስ ነበራቸው። በዚህ ግዜ ነጮቹ ቀድሞ የነበራቸውን የተለየ መብት ከጥቁሮች ጋር መጋራታቸው መብታቸውን እንደመነጠቅ ቆጥረውታል። ለምሳሌ ቅድሚያ ይሰጣቸው የነበረውን አገልግሎት ከጥቁሮች ዕኩል እንዳደራረሳቸው እየተሰለፉ እንዲያገኙ መገደዳቸውን እንደመብት ነጠቃ ይቆጥሩታል።

እነዚህ ተግዳሮቶች መገፋፋት ይፈጥሩ ነበር። በዚህ ሳቢያ ከነጮቹም፣ ከጥቁሮቹም ወገን አብረን መኖር አንችልም የሚል ሰውነትን የመጠራጠር ዝንባሌ ታይቷል። በአሜሪካ እነማልኮም ኤክስ ይመሩት የነበሩት እንቅስቃሴ የነጭ የሆነውን ሁሉ መጠየፍን እንደስትራቴጂ የቆጠረ ነው። የነሱ ተቃራኒ ዕኩያ የሚባለው ኬኬኬ የሚባሉት የነጮች ጥቁር ተጠያፊ ቡድን ነው። የማልኮሜክስ ‘ኔሽን ኦቭ ኢስላም’ እና ‘ኩ ክላክስ ክላን’ አንዴ ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር። ጥቁሮቹም ነጭ የማያዩበት የጥቁር ዓለም፣ ነጮቹም ጥቁር የማያዩበት የነጭ ዓለም ሊመሠርቱ። አንዱ ሌላኛውን ለማግለል እንደመስማማት።

በቀድሞዋ አሜሪካ ሰሜኖቹ “ነጻ አገሮች” ሲሆኑ ደቡቦቹ “ባሪያ አሳዳሪ” ነበሩ። ሶሻሊስቶቹ በወቅቱ በሰሜን የነበረውን የጭሰኝነት ሁኔታ እያዩ በሰሜን ያለው የጭቁን ሠራተኞች ሁኔታ እና በደቡብ ያለው የባሪያዎች ሁኔታ አንድ ነው እስከማለት የሚደፍሩ ነበሩ – በመደብ ጭቆና ትንተና። ነገር ግን በወቅቱ ከደቡብ ባርነት ኮብልለው ወደሰሜን ጭሰኝነት የሚፈልሱ እልፍ ሰዎች ቢኖሩም፣ ከሰሜን ጭሰኝነት ወደደቡብ ባርነት የኮበለሉ ሰዎች አልነበሩም።

ሌላኛው ፈታኝ ነገር ያንን ጥቁሮችን የሚያንኳስስ ስርዓት የሚደግፉ ጥቁሮች መኖራቸው ለነጭ አስተባባዮች ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ ነበር። ማልኮም ኤክስ በባርነት የነበሩ ጥቁሮችን በሁለት ይከፍላቸው ነበር። የቤት እና የመስክ ኔግሮዎች (house and field negroes) ብሎ። የቤት ኔግሮዎቹ ጥቁር ቢሆኑም ከጌታው የሚተርፈውን ከስር ከስር የመቋደስ ዕድሉ ነበራቸው (they were privileged)። ተመችቷቸዋል። ስለዚህ፣ አብዛኛውን ፍዳ እንደሚቀምሱት የመስክ ኔግሮዎች ስርዓቱን አይቃወሙትም፣ እንዲያውም በደሉን በሰበብ ያለባብሱለታል።

እንዲህ ዓይነቱ የታሪክ ትርክት መገፋፋት ኋላ ላይ የዕኩል ሰውነት ማዕረግ ለማግኘት ይታገሉ ለነበሩት ለነማርቲን ሉተር ኪንግ ፈታኝ ነበር። በግለታሪኩ ላይ ኪንግ የሲቪል መብቶች ትግሉ አንዱ ፈተና ይህ እንደነበር ገልጿል። መጨረሻ ላይ ስኬታማ የሆነው ግን፣ የአግላዮቹ ሳይሆን የአካታቾቹ ትግል ነው። ጥቁሮቹ ዕኩል መብቱን ሲያገኙ ቀድሞ ነጮቹ ይፈሩት እንደነበረው ዓይነት ጥፋት አልደረሰም።

በደቡብ አፍሪካ ኤኤንሲ ጥቁሮች ብቻ ሳይሆን ነጮችንም በአባልነት ይቀበል ነበር። የነማርቲን ሉተር ኪንግ እንቅስቃሴም በርካታ ነጭ አጋሮች ነበሩት። ማልኮም ኤክስ ከመገደሉ ጥቂት ቀደም ብሎ ስለሚፀፅተው ነገር ሲናገር አንዲት ታዳጊ ልጅ ጠቅሷል። ከዓመታት በፊት ማልኮም የአግላዩ ትግል ሊቀ ጳጳስ እይያለ አንዲት የ10 ዓመት ሕፃን ልጅ እቅፍ አበባ ይዛ ለጥቁሮች ትግል አጋርነቷን ለማሳየት ስትወጣ ‘ሂጅ ከዚህ፤ እኛ ከነጮች ጋር አጋርነት የለንም’ ብሎ አባሯት ነበር። ኋላ፣ እየበሰለ ሲመጣ ተፀፅቷል።

እኛ አገር በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የፆታን ጨምሮ፣ ከፊሉ በመደብ፣ ከፊሉ በማንነት፣ ከፊሉ በመደብ እና በማንነት ምክንያት በሚሉት መሠረት (መሠረቱን ባለሙያዎች በጥናት ሊበይኑልን ሲገባ እኛ ባላዋቂነት ጭቃ እየተለቃለቅንበት እንገኛለን፣ ለማንኛውም) ለዘመናት በገዢዎች እና በተገዢዎች መካከል (ወይም ዘመንና በሕል ባፈረጠማቸው እና ባንኳሰሳቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች /ምሳሌ ወንዶች እና ሴቶች/) ለደረሱት በደሎች እና በዘለቄታው ላስከተሉት በማንነት ላይ የተመሠረተ የተጠቃሚነት ጉዳትን ለማስተካከል (undoing sustained system of repression) አንዱ የሌላው አጋር በመሆን አካታች የመብት ትግል በማድረግ ፈንታ አግላይ ትግል እያደረግን ሁሉንም አሸናፊ የሚያደርግ አማራጭ እያለን፣ ሁሉንም ተሸናፊ የሚያደርገውን አማራጭ እየተከተልን እንገኛን።

ብዙ ጊዜ አጋርነትን አለመከተል ጦስ አለው። “ችግር የለም” በሚል በክህደት (denial) የተጀመረው፣ ወደፍረጃ ወይም መጥሌ (prejudice) ያድግና ውጤቱ የእርስበርስ እልቂት ይሆናል። ለዕኩል ዕድል እና መብት የሚታገሉት ቡድኖች በአግላይ ትርክት ጠላት የሚል ሥም የሚያወጡለት ቡድን ስለሚኖረው “ተቃራኒያችን” የሚሉትን ወገን ይገፋሉ። በሌላ በኩል ያንኛው ወገንም አንዳንድ ነባር ጥቅሞቼ ሊሸረሸሩብኝ ነው፣ ከሌሎች የዕኩል ባለመብቶች ጋር ልጋራው ነው በማለት የአፀፋ ግፊት ይገፋሉ።

የአንዱ እምነት ተከታይ ይሄ በደል ነበረብኝ፣ አለብኝ፣ በዘዴ እንዲቀጥል እየተደረገብኝ ነው ሲል፤ አንዱ ብሔርተኛ በማንነቴ ምክንያት እንዲህ ዓይነት በደል ይደርስብኝ ነበር፣ አሁንም አለብኝ፣ በዚህ አካሔድ ወደፊትም በደሉ ይቀጥልብኛል ሲል፤ አንዷ ሴት በመሆኔ ብቻ ወንዶች በቀላሉ የሚያገኙትን መብትና ዕድል ተነፈግኩ ስትል፣ «እኔ አለሁልህ/ሽ» በማለት ሰው ሠራሽ የእምነት እና የማንነት ድንበሮችን መስበር ካልቻልን ለሰውነት ማዕረግ ብቁ ነን ማለት አይቻልም። ተበዳይም በአርቲፊሻል ሰበቦች ላይ ተመሥርቶ ‘አንተማ በድለኸኛል፣ ወግድልኝ’ ካለ ትግሉ የሚገባውን የሰውነት ማዕረግ ለማግኘት ሳይሆን በተራው የሌሎችን ለመግፈፍ ነው ማለት ነው። ዳር ላይ ቁሞ ችግሩን ለመፍታት የሚፍጨረጨሩትን ፀጉር እየሰነጠቁ በማብጠልጠልም ግድግዳው አይፈርስም። የሚከፋፍለን ግድግዳ ፈርሶ፥ የሚያቀራርበን ድልድይ የሚሠራው እያንዳንዳችን ሌሎች በሚያደርጉት ትግል ውስጥ አጋርነታችንን በተግባር መግለጽ ስንችል ነው።

መጤ ሃይማኖት፣ ከመጤ ሃይማኖት በመምረጥ፣ (ግን በመሠረቱ ለገዢዎቹ ዋናው ሃይማኖቱ ሳይሆን በሥመ ሥዩመ–ፈጣሪነት የገዢነት ዕድል እና ተገዢ የማግኘት ጥረት ነው።) በወንዜ ማንነት ላይ በመመሥረት አገር ሲገዙ የነበሩ ሰዎች በነበሩበት አገር ውስጥ ያንን የሚያስተባብሉ (justify-ers) መኖራቸው አይገርምም። ይልቁን ከዚያ የአስተሳሰብ እስራት ወጥቶ ሰው ሆኖ መገኘት ነው ቁም ነገሩ።

ከገዢዎች እስራት ነጻ ከመውጣት በፊት ከገዛ ኋላ ቀር አስተሳሰባችን ነጻ መውጣት ይኖርብናል። መሬት የረገጠ ለውጥ ሊያመጡ እውነተኛውን ሥራ እየሠሩ ላሉት አጋር መሆን ካቃተን፣ ቢያንስ አደናቃፊ ላለመሆን መጣር ነው።

·        በስደት በሚገኙ አባቶች ጉባኤ አድርገው መግለጫ አውጥተዋል፤

·        “የቤተ ከርስቲያን ችግር” ያሉት በርግጥ ችግር ነውን?

·         ከመካከላቸው ያሉትና በእምነታቸው ነቅ የሌለባቸው አባቶች ለምን ዝምታን መረጡ?

·        “በስደት ባለው ሲኖዶስ ሥር ላሉ አብያተ ክርስቲያናት አገልጋዮችና ምእመናን” ከፍ ያለ ታሪካዊ ጊዜ ነው፤

 (ደጀ ሰላም፤ ማርች 6/2016፤ የካቲት 27/2008 ዓ.ም )፦ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት እና በዋናው ጠቅላይ ቤተክህነት ስር የሚገኙ የተለያዩ ካህናት “ጊዜው ተመችቶናል” በሚል ጦርነት በከፈቱበት በዚህ ወቅት በስደት በሚገኙ አባቶች የሚመራው ቤተ ክህነት አባላት የሆኑ ካህናትም ሰሞኑን ጉባዔ ማድረጋቸውንና የአቋም መግለጫ ማውጣታቸውን አስታውቀዋል (መግለጫውን በመጨረሻ ያገኙታል):: እነዚሁ “ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ” በሚባለውና በ4ኛው ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ በሚመራው ክፍል ሥር የሚገኙ ካህናት ያደረጉት ጉባዔ ከየካቲት 21-25/2008 ዓ.ም (ከፌብሩዋሪ 29 እስከ ማርች 4/2016 መሆኑ ነው) ድረስ የተካሄደ መሆኑን “ቆሞስ አባ ጽጌ ድንግል ደገፋው፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ” በሚል ፊርማና ማኅተም የወጣው መግለጫ ያትታል። ታዲያ ስለምን ተነጋገሩ? ውሳኔያቸውስ ምን ይሆን?

በሦስት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትምህርት መሰጠቱን ከባለ 4 ገጹ መግለጫ ለማወቅ ተችሏል። “1ኛ. “ትምህርተ ኖሎት”፤ 2ኛ.  “የቤተ ክርስቲያን ፈተና ትላንት እና ዛሬ”፤ 3ኛ. “አምልኮተ እግዚአብሔር እና ሥርዓቱ” በሚሉ ርዕሶች። አስተማሩ የተባሉት እነማን መሆናቸውን መግለጫው ባይጠቅስም ያወጡትን የጋራ መግለጫው በስምንት ቁጥሮች ከፍሎ አቅርቧል። ቁጥር 1 የመግለጫው አካል “ራሱን ማኅበረ ቅዱሳን ብሎ የሚጠራው አካል” በስደት የሚገኙ አባቶች ላይ (በስም ጠቅሶ ደግሞ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ላይ) “በቅርቡ በጀመረው የስም ማጥፋት ዘመቻ፣ በማን አለብኝነት የመከፋፈል ሥራ እየሠራ ይገኛል” ሲል ይከሳል።

በሰሜን አሜሪካ በመካሄድ ላይ ያለውን “ጸረ ተሐድሶ የስልክ ጉባዔዎች” የማኅበረ ቅዱሳን ጉባዔ ነው በሚል በስሕተት ወይም ደግሞ ሆን ብለው “ጠላት መጣባችሁ” በሚል ምዕመናንን ለማስተባበር የተጠቀሙበት ሊሆን እንደሚችል መገመት ቢቻልም ማኅበረ ቅዱሳን “በቅርቡ የስም ማጥፋት ዘመቻ ያደረገው” የት እና በምን ሁኔታ ነው የሚለውን ምንም አላብራሩም።

በቁጥር ሁለት መግለጫቸውም ከላይ በቁጥር አንድ የጀመሩትን በማብራራት “በየአጥቢያችን የተሰገሰጉ የማኅበሩ አባላት ረብሻዎችን ሊያስነሱብን ነው” የሚል ሥጋታቸውንና ጭንቀታቸውን ገልጸዋል። ቁጥር ሦስትም የዚያው ተጨማሪ ሆኖ ማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያነጣጠረ ውንጀላቸው እስከ ቁጥር 6 ድረስ ይዘልቃል። በሐሳብ ደረጃ ስንመለከታቸው የመግለጫው ፍሬ ሐሳቦች በአዲስ አበባ ሀ/ስብከትና በጠቅላይ ቤተ ክህነት ውስጥ ባሉ ሙሰኛ እና የተሐድሶ አስተምህሮ አራማጆች ተደጋግመው የሚገለጹትን ውንጀላዎች የደገሙ ሆነው እናገኛቸዋለን።

ቁጥር ሰባት ላይ “የሐሰት ትምህርት የሚያስተምሩ፤ እኛ ክርስቲያን አይደለንም፣ ጠላት ያወጣልን ስም ነው፣” የሚሉ ያሏቸውን ሰዎች ተቃውመዋል። እንዲህ እያሉ የሚያስተምሩት እነማን እንደሆኑ፤ ማንነታቸውን እና ምንነታቸውን ምን እንደሆነ አስረግጠው ሳያስረዱ በደፈናው ይቃወማሉ። ምእመናንን ከእነርሱ ለመጠበቅ በሚል ማስጠንቀቂያ ለመስጠትም ይሞክራሉ። ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ብቻ መግለጫ ሰጡ እንዳይባሉ ያስገቡት ይመስልባቸዋል።

በመጨረሻ፣ እንዳይቀር እንዳይቀር በሚል ጉባኤው “ራሳቸውን ተሓድሶ ነን በሚል የፕሮቴስታንቶችን ትምህርት በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ስም የሚያስተምሩ መሆናቸውን በሚዲያ ከለቀቁት የስሕተት ትምህርት ጉባኤው ተረድቷል” ካሉ በኋላ ጉባኤው ስለተረዳው ነገር እና ስለ አቋሙ ገለጥ አድርጎ ሳያብራራ በደፈናው “ትምህርታዊ መልስ በመስጠት ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ ተግቶ ለመሥራት ጉባኤው ተስማምቷል” በሚል ቤተ ክርስቲያናችንን በማመስ ላይ ስለሚገኘው ተሐድሶ ለማንሣት ይሞክራሉ።

ጉባኤው ለየትኛው ጉዳይ ክብደት ሰጥቶ ተነጋገረ? ዋናው የጉባኤው ዓላማስ ምን ነበር የሚለውን ለመረዳት ከስምንት ነጥቦች (መግቢያውን ሳይጨምር) መላልሶ ያነሣውን ጉዳይ መረዳት በቂ ነው። ይህንንም በማያሻማ ሁኔታ “በዚህ ዘመን ቤተ ክርስቲያናችን የተጋረጠባት ትልቅ አደጋ ምንድነው” ብሎ ይጠይቅና “ራሱን ማኅበረ ቅዱሳን ብሎ የሚጠራው ቡድን ነው” ሲል ራሱ ይመልሳል። (ገጽ 2)

ይህ ማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያነጣጠረው ዘመቻ አስደናቂ የማይሆነው ከጉባዔው ተሳታፊዎች ቀንደኞቹ በተሐድሶ ትምህርታቸው የሚነቀፉት ሰዎች መሆናቸውን ልብ ሲሉ ነው። እነዚህ ግለሰቦች ኢትዮጵያ ከሚገኘውና በዋናው ቤተ ክህነት እግሩን አንሰራፍቶ ከተቀመጠው የተሐድሶ ክፍላቸው ጋር በመቀናጀት በአንድ ሰሞን፣ አንድ ዓይነት መግለጫ በማውጣትና ነገሮችን ከሥሩ አይመረምርም የሚሉትን ምእመን ለማደናገር ሞክረዋል።

ይሁን እንጂ እነርሱ እንዳሰቡት ሳይሆን በተለያየ የፖለቲካ አመለካከታቸው በሀገር ውስጥ ያለውን መንግሥት የሚቃወሙ፣ በፓትርያርክ አባ ማትያስ የሚመራውን ቤተ ክህነት እና ራሳቸውን ፓትርያርኩንም የማይቀበሉ እየመሰሉ ነገር ግን እጅና ጓንት ሆነው እንደሚሠሩ በትክክል አሳይተዋል። በቤተ ክርስቲያናችን የተፈጠረው የአባቶች ልዩነት እና ሁለት ሲኖዶስ የሚባል ችግር እንዳይቀረፍ በዚህም በዚያም ሆነው የሚያከላክሉ ሰዎችን በተሐድሶ ጉዳይ ላይ አብረው ሲሰሩ መመልከታችን “ግርግር ለሌባ ያመቻል” የሚለውን ተረት አስታውሶናል። በአባቶች መለያየት ያተረፈው አካል ማን መሆኑ ግልጽ እየወጣ ነው።

ሌላውን ትልቅ ቁምነገር “በርግጥ የቤተ ክርስቲያናችን ትልቁ ችግር በቃ ይኸው ነው? የገዳማት መበተን፣ የመምህራን መቸገር፣ የምእመናን ቁጥር ከጊዜ ጊዜ እየቆረቆዘ መምጣት፣ የአጽራረ ቤተ ክርስቲያን መጠንከር፣ የምእመናን በዘረኛ መንግስት ቁም ስቅላቸውን ማየት፣ ከቀዬያቸው መፈናቀል፣ መታሰር፣ መገረፍ እና መገደል፤ የቤተ ክህነት አስዳደርን የጨበጡ ብዙ ሙሰኛና ዘራፊ ሰዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን ሀብት በጠራራ ፀሐይ መዝረፋቸው ወዘተ እንደ ችግር እንዴት ሳይታያቸው ቀረ?

በዓላማ የተሐድሶን እምነት የሚያስፋፉትና በዚህ ጉባኤ ላይ መኖራቸውን በፎቶግራፎች ያየናቸው ሰዎች ዓላማቸው ነውና “ያስቸገረን ማኅበረ ቅዱሳን ነው” ቢሉ ብዙም አይደንቅም። ሌሎቹ አባቶች፣ በሃይማኖታቸው የማይጠረጠሩትና ወልድ ዋሕድ ብለው የሚያምኑት ግን አሁንም ዝምታን የመረጡትና አጃቢ ሆነው የቀረቡት በይሉኝታ ነው፣ ባለማወቅ ነው፣ ወይስ በርግጥም የቤተ ክርስቲያን ችግር ምንነቱን አያውቀቱትም ወይም ዘንግተውታል?

ሊሰመርበት የሚገባው ሌላው ጉዳይ በአገር ቤት ከሕወሐት ወያኔ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ አገራችንን እና ቤተ ክርስቲያናችንን በማፍረስ ላይ ያለው የተሐድሶ ቡድን በውጪ አገር ደግሞ የተቃውሞው ኃይል አካል መስሎ ለመታየት የቻለበት ሁኔታ ነው። በዚህ ዘዴያቸው ከኢትዮጵያውያን ሬዲዮኖች እስከ ድረ ገጾች ድረስ “የነጻነት ኃይል” መስለው ለመታየት ከመቻላቸውም በላይ በፖለቲካ እያሳከሩ እምነታቸውን ለማስፋፋት በመጣር ላይ ይገኛሉ። ይህ ጽሑፍ በሚዘጋጅበት ወቅት እንኳን ይህ የቤተ ክርስቲያንን ችግር ምንነት በተንሸዋረረ መልኩ ለማሳየት እና ምእመናን የአቅማቸውን እንዳያደርጉ አቅጣጫ የሚያስቀይር መግለጫ በhttp://ecadforum.com/Amharic/archives/16224/ድረ ገጽ ላይ ወጥቷል። ሌሎቹም ይከተላሉ፤ ሬዲዮኖቹም ይህንን የተሳሳተ አስተሳሰብ ሲያንጸባርቁ ይገኛሉ።

ነገ ነጻነት በኢትዮጵያ ሲመለስና ሕዝብ የመረጠው አስተዳደር ሲተከል እንኳን ዛሬ “ተቃዋሚ መስለው” የቀረቡት እነዚህ ኃይሎች ቤተ ክህነቱን ለመቆጣጠርና የአገራችንንና የቤተ ክርስቲያናችንን መከራ ለማክበድ እነሆ ተዘጋጅተዋል። ነጻነት ናፋቂው ክፍል በዚህ ጸረ ተዋሕዶ ክፍል በመታለል እስከ መቼ የአፍራሽ ተግባራቸው አካል ይሆናል?

እነሆ አሁን “በስደት ባለው ሲኖዶስ ሥር ላሉ አብያተ ክርስቲያናት አገልጋዮችና ምእመናን” ከፍ ያለ ታሪካዊ ጥያቄ መቅረቡን ሊገነዘቡት ይገባል። ከወንዝ ልጅነት ባለፈ በመካከላቸው ያለውን ጸረ ተዋሕዶ ቡድን ሊመለከቱ ይገባቸዋል። በርግጥም አሁንም “ተሐድሶ የሚባል የለም፤ ማኅበረ ቅዱሳን ነው የፈጠረው” በሚለው ማባበያ የሚታለሉ አይመስለንም። በርግጥ ይህንን ማስጠንቀቂያ ችላ ብለው ካለፉ እጅግም ባልራቁ ዓመታት ተሐድሶ ምእመናኑን በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ፕሮቴስታንቶች አድርጎ ያገኙታል። ያን ጊዜ ለመመለስ እጅግ ያስቸግራል። ከሕንድ ታሪክ እንማር፤ እንንቃ።

ማስጠንቀቂያ፦ በዚህ ጉባኤ ላይ የተገኙትን አባቶች በጅምላ ተሐድሶ ናቸው አለማለታችን ግልጽ ቢሆንም ደግመን ለማሳሰብ እንወዳለን። ነገር በማመሳሰል ያልተባለውን ተባለ ለሚሉት መናፍቃን ዕድል አንሰጣቸውም።

መልካም ዐቢይ ጾም

ቸር ወሬ ያሰማን፤

አሜን      

        

Deje Selam is a venue of news, views and opinions about or related to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. [email protected]

·        ከካቶሊክ ጋር ያለን ልዩነት ጠባብ ነው(አባ ማቲያስ ሕዳር 2008)

·        ከቫቲካን ጋር የነበረንን የቀድሞ ፍቅር(?) እንመልሰዋለን(አባ ማቲያስ የካቲት 2008)

·         ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስትያንን የገዛ ቅኝ ገዥ ነው(አባ ማቲያስ ጥቅምት 2008)
·        ወራሪዋን ቫቲካንን ፍቅር : ልጆቻቸውን ቅኝ ገዥ— አባት ብሎ ዝም!!

(ዘአዲስ እንደፃፉት):- አባ ማቲያስ በዚህ ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ትግራይ ሄደው ጉብኝት ማድርጋቸው ይታወሳል:: አዲግራት ላይ የአዲግራቱ የካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ቦታ ላይከካቶሊክ ጋር ያለን ልዩነት ጠባብ ነውበማለት መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል:: http://www.addisadmassnews.com/images/Issue-826.pdf

ሀገራዊ ማህበራዊና ብሔራዊ በሆነ ጉዳይ ላይአንተ ኦርቶዶክስ : አንተ ካቶሊክመባባሉ ሳይኖር የሁሉም እምነት ተከታይ የሆነ ኢትዮጵያዊ በአንድነት መቆም እንዳለበት ግልጽ ነው:: “ኦርቶዶክስና ካቶሊክ መካከል ያለው ልዩነት ጠባብ ነውብሎ የማይመስል ነገር መናገሩ ( ያውም ከፓትርያርኩ አንደበት) ግን እጅግ የሚያስተዛዝብና ግምት ውስጥ የሚጥል ስህተት ነው:: የሆነው ሆኖ ይህን ባሉ በሶስተኛው ወር የካቶሊኳ ራስ ቫቲካን ደርሰው የበርካታ ኢትዮጵያውያንን አንጀት አቁስለው ተመልሰዋል::

 ፓትርያርኩ ቫቲካን መሄድ ነበረባቸውን?

በመሰረቱ: ቫቲካን ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ላይ እጅግ የመረረ ግፍ ፈጽማለች:: ፋሺስት ጣልያን ኢትዮጵያን ስትወር : የቫቲካን ጳጳሳት የመርዝ ጋዝ እየባረኩ ኢትዮጵያን ለመውረር የሚደረገው ጦርነት ቅዱስ ጦርነት እንደሆነ አውጀዋል:: የወርቅ መስቀላቸውን ሳይቀር ለጦርነቱ አዋጥተዋል:: የሙሶሎኒምና የግራዚያኒ ቀኝ እጅ የነበረው የቫቲካኑ ጳጳስ ባደባባይ ወረራውን ደግፎ መግለጫ ሰጥቷል::

(http://www.globalallianceforethiopia.org/italianinvasion.pdf)

ፋሺስት ጣልያን አንድ በዛ ጦርነት አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ገድላለች:: በሺዎች የሚቆጠሩ ካህናትን አቃጥላለች:: በውል የታወቁትን እንኳን ብንቆጥር ወደ 2 ቪህ አብያተ ክርስቲናትን አውድማለች:: ጣልያን ከመውረሯ በፊትም የጣልያን ሰላይ እየሆኑ ይሰሩ የነበሩት የቫቲካን መነኮሳት ነበሩ::

ቫቲካን ስለሰራችው ጥፋት ኢትዮጵያንን እና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያንን ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ስላልሆነች : ላለፉት አርባና ሃምሳ ዓመታት የቫቲካንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስትያናት ግንኙነት በጣም ቀዝቃዛ ነበር:: ቫቲካን ይቅርታ እስካልጠየቀች ድረስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን አባቶች ከቫቲካን ጋር አንድነት እንዳይኖር በመወሰናቸው የሁለቱ አብያተ ክርስትያናት ግንኙነት በጣም ቀዝቃዛ ነበር:: ( የአለቃ አያሌውመች ተለመደና ከተኩላ ዝምድናመጽሓፍን ይመልከቱ)

በተለይ አሁን በቅርቡ ለጨፍጫፊው ግራዚያኒ ጣልያን ውስጥ ሀውልት እንዲቆም ከተወሰነ በኋላና የቫቲካን ጳጳሳትም ይህን ጉዳይ የመደገፋቸው ዜና በመሰማቱ : በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ በማሰማታቸው የሃውልቱ ስራ ቆሟል:: እነዚሁ ኢትዮጵያውያን ቫቲካን ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያንን ይቅርታ እንድትጠይቅ ቢወተውቱም : ቫቲካን ካላት ንቀት የተነሳ ፈቃደኛ አልሆነችም:: የሙገርመው ግን ጀርመን ናዚዎች አይሁዶችን ሲጨፈጭፉ ዝም በማለቴ ( ባልሳተፍበትም) ይቅርታ ጠይቃለሁብላ አይሁዶችን ይቅርታ ጠይቃለች::

(https://www.gopetition.com/…/vatican-apology-for-ethiopian-…)

ራሷ የጨፈጨፈችውንና ያስጨፈጨፈችውን ኢትዮጵያውያንን ግን ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ባለመሆኗ : ቫቲካን ኢትዮጵያን ይቅርታ እስክትጠይቅ ድረስ ይፋዊ ግንኙነት እንዳይኖር በኢትዮጵያ በኩል ተወስኖ ነበር:: የአለቃ አያለውውን መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና ያነቧል::

አባ ማቲያስ ግን ያንን እግድ ጥሰው ቫቲካን ድረስ በመሄድእኛና ቫቲካን ድሮም ፍቅር ነን: የድሮውን ፍቅር እንመልሰዋለንበማለት የብዙ ኢትዮጵያውያንን ድካም መና አብልተውታል::

የአባ ማቲያስ ቫቲካን መሄድ እንግዳ ቢሆንም ብዙዎእዛው ሀገራቸው ላይ ሄደው ቫቲካን ለሰራችው በደል ይቅርታ ትጠይቅብለው ይናገራሉ ተብሎ ተጠብቆም ነበር:: በተገላቢጦሹ ግን አባ ማቲያስድሮም እኛና ቫቲካን ፍቅር ነበርን ወደፊትም ያንን ፍቅር እንመልሰዋለንብለው አረፉት::

የቀደመው የቫቲካንና የኦርቶዶክስ ፍቅር የቱ እንደሆነ አልገባኝም:: የዲዮስቆሮስ ይሆንን? ከጥንት ጀምሮ ቫቲካን የምትልካቸው ሚሺነሪዎች ሕዝብ ሲያጨፋጭፉ ነገር ሲተክሉ እንጂ ፍቅር መስርተው ሲሄዱ አይታወቅም:: እነ አልፎንሱ ሜንዴዝን መጥቀስ ይቻላል:: ቃል በቃልኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን ላይ ሁለት እሾክ ተክዬባት ሄድኩእስከማለት የደረሱ ናቸው:: ጸጋና ቅባትን ያስትውሷል:: ጂሴፔ ሳፔቶና አባ ማስያስም ኢትዮጵያን ለጋ ቅቤ ሲቀቡ አናቃቸውም:: በሁለቱም የጣልያን ጦርነት ወቅትም ቫቲካን የሰራችው ወንጀል እንጂ የፍቅር ስራ አይደለም:: (አቡነ ጎርጎርዮስ ////ታሪክ)

የኦርቶዶክስና የቫቲካን የቀደመ ፍቅር የቱ እንደሆን አይገባኝም:: ፓትርያርኩ እንደዛ ከሚሉቫቲካን አትፍታለችና ይቅርታ ትጠይቅ,ኢለውን ያባቶቻቸውን ቃል አጽንተው እሳቸውም ይሄን ቢያደርጉ ለነፍሳቸውም ለስጋቸውም ታሪክ ነበር:; ማኅበረ ቅዱሳንንቅኝ ገዥያለ አንደበት እውነተኛዋ ቅኝ ገዥን ምን ይላት ይሆን ብዬ ጠብቄም ነበር::

ምን ያደጋል ! አባታችን አገላበጡት

Deje Selam is a venue of news, views and opinions about or related to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. [email protected]

ወያኔ የኦሮሞ ጠላት ነው

አንተነህ መርዕድ

Abayi Tsehaye አባይ ፀሐዬ

መለስ ሲያጉረመርምበት ብርክ የሚይዘውና የሚሙለጨለጨው፣ ጓደኞቹን ደጋግሞ በፍርሃቱ የሸጠው አባይ ፀሃዬ ዞር ዞር ብሎ ሲመለከት ከሱ የተሻሉና የሚያስፈሩት ህወሃቶች የሌሉ መሆናቸውን በማረጋገጡ በየመድረኩ ብቅ እያለ መፎከርና መዘባረቅ የእለት ተእለት ሥራው ሆኗል። በተለይም በዋና ባለቤትነት የአዲስ አበባን መሬት ሸጦ ከጨረሰ በኋላ የአካባቢውን ገበሬዎች ከነመሬታቸው ሊቀራመት ያደባበት ተንኮል አልሠራ ሲል “ልክ እናስገባቸዋለን” ሲል ፎከረ። አሁን ደግሞ ፉከራው የለኮሰውን እሳት ማዳፈን ተስኖት “ወያኔ የኦሮሞ ጠላት አይደለም” የሚል የሽሽት ሽምጥ ሩጫ ይዟል። እሳቱ ግን እሱን ሳይለበልበው የሚመለስ አይደለም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግርማ ካሳ

በግምት ከሃያ አራት ዓመታት በፊት ይሆናል ቀኑ። በኢትዮጵያ እርቅና ሰላም እንዲኖር ብዙ ጊዜ የሚደክሙና የሚጸልዩ፣ ቄስ ቶሎሳ ጉዲና የሚባሉ አንድ መንፈሳዊ አባት፣ ምዕመናንን ሲያስተምሩ የተናገሩት፣ ሁልጊዜ የማስታወሰውና የማልረሳው አባባል ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጌታቸው ኃይሌ

Identity crisis ማነኝ?

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ማንነት ዋና የመወያያ ርዕስ ሆኖ ቈይቷል። የሥነ ልቡና ምሁራን identity crisis የሚሉት ነው እንዳልል ያተኰረው “እኔ ማነኝ” ከሚለው ላይ አይደለም። ያተኮረው “ማንነት ከመሬት ጋር ይያያዛል ወይስ አይያያዝም?” ከሚለው ጥያቄ ላይ ነው። ውይይቱን እንዳዳመጥኩትና እንደሰማሁት፣ እኔም አስተያየቴን እንድሰጥ ተጠይቄ እንደተቸሁት፣ ማንነትን ከመሬት ጋር የሚያያይዙ እምነታቸውን ከኃይማኖት እምነት ደረጃ አድርሰውታል። ስለዚህ እነሱን በማስረጃ ማሳመን ሃይማኖታችሁን ለውጡ እንደማለት ሆኗል። “እምነቱ ሀገር አጥፊ ነው፤ ተውት” ቢባሉም፣ ማንነታቸው ከያዙት መሬት ጋር ከተቆራኘ፣ ይህ አደገኛ አቋማቸው ለሚያስከትለው ሀገራዊ ችግር አንዳች ሥጋት አይታይባቸውም። ክልል ይዞ ኢትዮጵያዊ መሆን ይቻላል የሚሉም አይጠፉም። መሳሳታቸውን መስማት አይፈልጉም፤ ግን ማንነት የሚዘራበት መሬት የሚያስፈልገው ዳጉሳ አይደለም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይገረም አለሙ

የአበው ተረት ለልጅ የሳቁለት ለውሻ የሮጡለት ነው የሚለው። ለፖለቲከኛ ያጨበጨቡለት የሚል ቢጨመርበት ተስማሚ ይመስለኛል። ልጅ ከሳቁለት ሁሉ ቦታ እየገባ ነገር ያበላሻል፤ ውሻ ከሮጡለት ጥሎ ካላንደባለለ ወይ ካልቦጨቀ አይመለስም ፖለቲከኛም ካጨበጨቡለት አበው ልቤ አደገና ያለ ቁመቴ አላስገባ አለኝ የገዛ ቤቴ እንደሚሉት ይሆንና ከእኔ በላይ ለአሳር በሚል መታበይ ብዙ ጥፋት ያደርሳል ኋላም ራሱን ያዋርዳል። እኛም ጥሎብን ይሁን ባህል ሆኖብን ባይታወቅም እየኮተኮቱ ማሰደግ እየገሩ ለወግ ማዕረግ ከማብቃት ይልቅ እያሞካሹ ማበላሹትን እያጨበጨቡ ወደ ገድል መግፋቱን ተክነንበታል። በዚህ መንገድ ስንት ለሀገርና ለወገን ሊጠቅሙ ይችሉ የነበሩ ሰዎችን አጥተናል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

(ማርች 2/2016/ የካቲት 23/2008 ዓ.ም):- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ወደ ቫቲካን ጉዞ ማድረጋቸው እና ከሮማማው ፓፓ “ፖፕ ፍራንሲስ” ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው በመገናኛ ብዙኃን ተዘግቧል፡፡ ሲጨባበጡ፣ ትከሻ ለትከሻ ተሳስመው ሰላምታ ሲለዋወጡ፣ ፓትርያርካችን ለፖፕ ፍራንሲስ ማስታወሻ መስቀል እና መጽሐፍ ሲሰጡ ሁሉ አይተናል።
የሁለቱ መሪዎች ዋነኛ የመወያያ ርዕሰ ጉዳይ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው የክርስቲያኖች መከራ፣ ስደትና የቤተ ክርስቲያን ውድመት እንደሆነ ከፖፑ ንግግር መረዳት ይቻላል። “የክርስቲያኖች የሰማዕትነት ደም የክርስትና ዘር ነው” የሚለውን ታዋቂ ቃል አንስተው ፖፑ ማብራራታቸው ተዘግቧል። ዝርዝሩን መመልከት ለሚሻ ዜናው ወደተዘገበባቸው ሥፍራዎች ጎራ ማለት ይችላል።

ሁለቱም መሪዎች ከተሾሙ ብዙም አልቆዩም። ፓትርያርክ ማትያስ February 28/ 2013፤; ፖፕ ፍራንሲስ ደግሞ    በቀናት ልዩነት March 13/ 2013 ነው የተሾሙት። ሁለቱም መሪዎች በአማኞቻቸው የሚታዩበትን ጠባይ በአጭር ጊዜ ለመቅረጽ የቻሉ ሆነዋል። ያሳዩት ጠባይ ግን ልክ እንደ ልብሳቸው እጅግ የተቃረነና የተለያየ ነው። ፓፓ ፍራንሲስ ልጆችን በማባለግ እና በሌሎችም አስነዋሪ ተግባራት ስሟ የጎደፈውን የካቶሊክን ቤተ ክርስቲያን በጥቂት ዓመታት ውስጥ ስሟን ለማደስና በዓለም ሕዝብ ዘንድ ያላትን ተቀባይነት እጅግ በላቀ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ችለዋል።
ፓፓው ከሠሯቸው ተግባራት መካከል አንዱ ለረዥም ዘመናት ተለያይተው የነበሩትን ኩባንና አሜሪካንን ለማስታረቅ ድልድዩን ያበጁትና ታሪክ የሠሩት እርሳቸው መሆናቸው ነው። ኮሚኒስቱን የኩባ አስተዳደር ከደመኛ “ኢምፔሪያሊስት ጠላቱ” ከአሜሪካን መንግሥት ጋር ለማግባባትና በሁለቱ ሕዝቦች መካከል የፈረሰውን የግማሽ ምዕት የግንኙነት መስመር ለመጠገን ችለዋል።
ከዚህም በላይ ፓፓው በዓለም አማኝም ኢ-አማኒም ሕዝብ ዘንድ ሞገስ ያሰጣቸው ለድሀውና ለዝቅተኛ ኑሮ ለሚኖረው ለመላው የዓለም ሕዝብ ያሳዩት ጥብቅና፤ ገንዘብ አምላኪውን የዘመናችንን ሉላዊ ሥርዓት በይፋ እየተቃወሙ ለአገሮች ኢኮኖሚያዊ ጤንነት ያሳዩት ወገንተኝነት ነው። ድህነትን እንደበሽታ ለሚጠየፉ ብዙ ቅንጡዎች እና ቅምጥሎች ትልቅ ትምህርት በሚሰጠው ተግባራቸው ከኦባማ ዋይት ሐውስ እና የአሜሪካ ኮንግረስ እስከ ደቡብ አሜሪካ የተለያዩ  አገሮች ግድ የለሽ መንግሥታት ድረስ ምክራቸውን እና ተግሳጻቸውን አሰምተዋል።
የቅምጥል ኑሮን የሕይወታቸው መመሪያ በማድረግ ረገድ ከዓለማውያኑ የባሱት መንፈሳውያን የእምነት መሪዎች በሆኑበት በዚህ ዘመን ፖፕ ፍራንሲስ የቫቲካንን ወደር የለሽ የድሎት መኪናዎች ለመጠቀም አሻፈረኝ በማለት እና እዚህ ግቢ የማትባል የግል መኪናቸውን በመጠቀም በንግግራቸውም በግብራቸው ቅምጥልነትን አውግዘዋል።

ለጉብኝት በሑዱባቸው አገሮች በአጃቢ የተሸለሙ መኪኖቻቸወን በማቆም እና በመንገድ ላይ ከሚጠብቃቸው ሕዝብ ጋር በተለይም ከሕጻናት እና የተለያየ በሽታ ካለባቸው ሰዎች ጋር በመገናኘት፣ እንኳን ለመንካት ለማየት እጅግ የሚፈትን በሽታ ያለባቸውን ሰዎች ሳይጸየፉ በማቀፍና ርኅራኄ በማሳየት ብዙዎችን አስደምመዋል። ሌሎችንም የታዘብናቸውን ብዙ ተግባሮቻቸውን መጥቀስ ይቻላል። ለዚህ ፅሑፍ ሲባል በዚሁ እንግታውና የኛው ፓትርያርክ ሊሟሯቸው ስለሚችሏቸው ነገሮች እናንሣ።

መቸም አንድ የኦርቶዶክስን አባት ከካቶሊክ መሪ “ይህንን ተማር፣ ይህ መልካም የሆነ የኮቶሊኩ መሪ ተግባር ነው” ማለት ችግር ላይ ሊጥል የሚችል ነገር እንደሆነ ይታወቃል። “ካቶሊኮችን ያመሰግናሉ” የሚል የነገረ ሰሪ ጥላሸት ሊያስቀባም ይችላል። በቀድሞው ዘመን ቢሆንማ “ሰዎቹ ኮተሎኩ” ሊያሰኝም ይችል ነበር።
ይሁን እንጂ ቅ/ያሬድ ከዚያች ትል መውደቅንና መነሣትን ተምሮና ተገንዝቦ፣ ሕይወቱን አርቆ ለቤተ ክርስቲያናችን ዓይን እንደሆነ ሁሉ የሰው ልጅም በሥላሴ አርአያ ከተፈጠረ ከሌላው ሰው (አማኝም ሆነ የማያምን፤ ኦርቶዶክስም ሆነ ካቶሊክ) መማር መቻሉ ያስመሰግነዋል እንጂ አያስነቅፈውም። ከባዶ ግብዝነትም ያድነዋል።
ወደ ቀደመ ነገራችን ስንመለስ …. ከላይ እንዳየነው ፓትርያርክ ማትያስ ከፖፕ ፍራንሲስ በቀናት ልዩነት ነው የመሪነት መንበር የተቀበሉት። ነገር ግን በነዚህ 3 ዓመታት ምን ሠሩ ብለን ብንገመግም ከፀብና ከዓምባ ጓሮ፣ በአደባባይና በሚዲያ ከሚሰጡት አሸማቃቂ ንግግር ባለፈ እንዲሁም ከቅ/ሲኖዶስ አባላት በመራቅ ቤተ ክርስቲያንን ተደራጅተው ከሚዘርፉ ሰዎች ጋር ከመወዳጀት ሌላ መልካም ስም ያተረፉ አይመስለንም።
የካቶሊኩ ፓፓ ለድሆች ጠበቃ መሆናቸውን አይተናል። የኛዎቹም ለኢትዮጵያ ድሃ ሕዝብ ጠበቃ ሊሆኑ ይገባቸው ነበር። በኑሮ ውድነት፣ በአስተዳደር ብልሹነት፣ በስግብግበነት መሬቱን እና ቤቱን እየተዘረፈ ትዳሩ ለሚፈርሰው ወገናቸው ጠበቃ ሊሆኑ ይገባ ነበር። ጋሻ ጃግሬዎቻቸው እርስበእርስ በመሸላለምና የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ በገፍ በመዝረፍ በተጠመዱበት በዚህ ጊዜ “ኧረ ተዉ!!!” የሚል የአባት ተግሳጽ ሊያሰሙ ይገባ ነበር።
እንደ ካቶሊኩ ፓፓ አስታራቂ እና የተበተኑትን ሰብሳቢ መሆን ቢያቅታቸው የተሰበሰቡትን ለመበተን መትጋት ግን አይገባቸውም ነበር። በዚህ አንድ ዓመት በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የፈጸሙትና እየፈጸሙት ያለው ተግባር ብቻ ለታሪካቸው ትልቅ ጠባሳ እንደሚሆን ሊገነዘቡት በተገባ ነበር።
በመካከለኛው ምስራቅ ለሚገደሉ ክርስቲያኖች አዝነው ሮም ድረስ እንደሔዱት ሁሉ፣ በአገራቸው ለሚጠፋው ሕዝባቸው፤ በመንግሥት ወታደር ዕለት ከዕለት እየተገደለ በየጥሻው ለሚጣለው ወገናቸው፤ ማዕከላዊን ጨምሮ በየእስር ቤቱ በማሰቃያዎች ለሚንገላታው ወገናቸው ጠበቃ መሆን ይችሉ ነበር።
ድሃ አደጉንና ዕጓለ ማውታውን ለመሰብሰብ ከአበው ሌላ ማን ይመጣል። ቤተ ክህነቱ ከገባበት አስረሽ ምቺው ተላቆና የምንኩስና አሰረ ፍኖቱን ተከትሎ ከዚህ የመንደላቀቅና የመሽቀርቀር አዚም ሊገላገል፣ ለድሃውም ሊያዝን ይገባው ነበር። የካቶሊኩን ፓፓ ካነጋገሩ አይቀር ይህንን ይህንንም ከእርሳቸው ይማሩ። ፓትርያርካችን ሆይ! በእርስዎ ዘመን ቤተ ክርስቲያናችን ስሟና ታሪኳ ይገነባል ወይስ ይፈርሳል?  
   
ቸር ወሬ ያሰማን
አሜን
Deje Selam is a venue of news, views and opinions about or related to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. [email protected]

(http://eotcmk.org):- ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዐረፉ:: ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በምሥራቅ ትግራይ ክለተ አውላሎ አውራጃ አውዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አጥቢያ ከአባታቸው ከአቶ ገብረ ሕይወት ፀዓዱ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ወለተ ክርስቶስ ቢሻው በ1923 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ዲቁናን ከአቡነ ይስሐቅ፣ ቅስና፣ ቁምስና እና ምንኩስና ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ተቀብለዋል፡፡

ጥር 13 ቀን 1971 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የትግራይ ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስ ተብለው ተሹመዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከ30 ዓመታት በላይ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው በማገልገል ላይ ሳሉ የካቲት 21 ቀን 2008 ዓ.ም ዐርፈዋል፡፡
ሥርዓተ ቀብራቸው ሐሙስ የካቲት 24 ቀን 2008 ዓ.ም በሀገረ ስብከታቸው ራሳቸው በገደሙትና ከፍተኛ መንፈሳዊ አገልግሎት ሲሰጡበት በነበረው ደብር ቅዱስ ደብረ መዓዛ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ይፈጸማል፡፡
                                                                                                                  
 የአባታችንን ነፍስ ከደጋጎቹ አበው ጋር ያድርግልን
አሜን።
         
Deje Selam is a venue of news, views and opinions about or related to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. [email protected]

አዋሳኝ ድንበራቸዉም የጦር ሐይል ፍጥጫ፤ ጠብ እና ቁርቁስ ተለይቶት አያዉቅም።አሁን በሰዎች መታገት በተለይ የኢትዮጵያን የምጣኔ ሐብት እና የሰዉ ሐይል ዋና ዋና ማዕከል ኦሮሚያን በሚንጠዉ ተቃዉሞና አመፅ ሰበብ እንዳዲስ መቀጣጠሉ «የከፋ ይከተላል» የሚል ሥጋት ማጫሩ አልቀረም-እንደ ሮንግ።

የኦሮሞ ሕዝብ ያነሳውን ጥያቄ ተከትሎ በሕወሓት መንግስት የኦሮሞን ህዝብ እንዲያረጋጉ ተልከው በየሚዲያው እየወጡ ሲያስተባብሉ የከረሙት የኦህዴድ ማዕከላዊ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኦቦ ዳባ ደበሌ ከስልጣናቸው ተነስተው ወደ ኦሮሚያ የትምህርት ቢሮ ተዘዋውረዋል:: በርሳቸው ቦታ ላይም በሕወሓት መንግስት ተላላኪነታቸው “ኦቦ ገብረመድህን” የሚል ስም የተሰጠው አቶ በከር ሻሌ ይህን ቁልፍ ስልጣን መረከቡን  ምንጮች ገልጸዋል:: አቶ በከር ሻሌ ከዚህ ቀደም […]

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ “ተሐድሶ” (ሪፎርሜሽን) ለማካሔድና በእነርሱ እምነት “ተባላሽቷል” የሚሉትን በመቀየር ገሚስ ፕሮቴስታንት ገሚስ ኦርቶዶክስ መሰል እምነት የመፍጠር ዓላማ መኖሩ አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው እውነታ ሆኖ “አለ ወይስ የለም?” በሚል ለምን ግር ይለናል? በሃይማኖታቸው ኦርቶዶክሳዊነት የማይጠረጠሩ ብዙ ሰዎች በዚህ ጉዳይ ልባቸው ይከፈላል። ለማመንም ለመተውም ይቸግራቸዋል። በሌላ አቀራረብ የሚቃወሙትን ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ ትምህርት ለማስፋፋት የሚጥሩትን ተሐድሶዎቹን ሲረዷቸው ይገኛሉ። ይህ የመደናገርና ግርታ ላይ የመውደቅ አባዜ እጅግ ሥር ከመስደዱ የተነሣ በአገር ቤት ያለችውን ቤተ ክህነት እጅግ እግሯን አስሮ ሊቆጣጠራት ምንም አልቀረውም። ከአገር ቤቱ ተገንጥለን የራሳችን ሲኖዶስ አለን የሚሉትንም አባቶች እንዲሁ መጠቀሚያው አድርጓቸዋል። የቤተ ክርስቲያናችን ፈተና የሆነው ይህ “ሪፎርሜሽን/Reformation” የተባለ አፈንጋጭ አስተምህሮ ሊያመጣ የሚችለው ውጤት ለማይታያቸው ምናልባት የዚሁ ችግር ሰለባ የሆነችውን የሕንድ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በአጭሩ መጥቀስ አብነት ሊሆን ይችል ይሆን?

የሕንድ ኦርቶዶክሶች ከቅ/ቶማስ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት የሚመዘዝ ረዥም ሃይማኖታዊ ታሪክ አላቸው። ልክ እንደኛዋ ቤተ ክርስቲያን ሁሉ በ17ኛው መ/ክፍለ ዘመን ወደ አገራቸው የገቡት ፖርቹጋሎች ባመጡት “ኦርቶዶክሳውያንን ካቶሊክ የማድረግ ዘመቻ” ብዙ መከራ ተቀብለዋል። ግማሽ ሕዝባቸውንም አጥተዋል። በእነርሱ እግር የተተኩት አዲሶቹ የሕንድ ገዢዎች እንግሊዛውያን በበኩላቸው ኦርቶዶክሶችን “አንግሊካን” ለማድረግ በነበራቸው ፍላጎት በገንዘባቸው “የቲዮሎጂ ኮሌጅ በማቋቋምና ራሳቸው ረዳት መስለው በመግባት” ኦርቶዶክስ መምህራንን ሊያፈራ የተቋቋመን መንፈሳዊ ኮሌጅ ለራሳቸው ዓላማ በመቀልበስ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰውባቸዋል። በዚህም ሰበብ “ማላባር ኢንዲፔንደንት ቸርች፤ ማላንካራ ማር ቶማ ሴሪያን ቸርች እና ሴይንት ቶማስ ኢቫንጄሊካል ቸርች” የተባሉ ሦስት የፕሮቴስታንት እምነት ክፍሎች ሊፈጠሩ ችለዋል።

ከሕንድ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደምንረዳው “ተሐድሶው” የተጀመረው በአንግሊካን እንግሊዞች እርዳታ፣ ቄስ ያውም የቲዎሎጂ መምህር በነበረ ሰው አማካኝነት ነው። ይህ “አብርሃም ማፕላን” የተባለ ግለሰብ ዘመዱ የሆነን ዲያቆን መንበረ ፕትርክናው ወደሚገኘው ወደ ሶሪያ የሐሰት ደብዳቤ አስይዞ በመላክ እና ጵጵስና እንዲቀበል በማድረግ ሐሳቡን ከግብ ለማድረስ ችሏል። ጵጵስናውን ተሳስተው የሰጡት ፓትርያርክ ነገሩ ስሕተት መሆኑን ዘግይተው ቢገነዘቡም የደረሰውን ጥፋት እና ስብራት ለመጠገን ሳይቻላቸው ቀርቷል። ችግሩን ለመፍታት ሕንድ ድረስ ቢጓዙም “የፈሰሰ አይታፈስ” ሆኖባቸው አልፏል።

ዛሬ ተሐድሶዎች በቤተ ክርስቲያናችን በሁሉም ዘርፍ ተንሰራፍተው ተቀምጠዋል። በአገር ቤትም በውጪውም ሲኖዶሶች አይነኬ ከመሆን ደረጃ ደርሰዋል። የሚያራምዱት እምነት ተሐድሶ መሆኑ በሰፊው እየተነገረ ዲቁናም ቅስናም የሚሰጣቸው ጳጳስ አላጡም። ምንኩስናን እየተቃወሙ ለጊዜው የመነኩሴ ቆብ የደፉትም ጵጵስና ለመቀበል በአገር ውስጡም በውጪውም ተራ በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ።

እነዚህ ሰዎች እንደሚፈራው እስከ ጵጵስናው ማዕረግ ለመድረስ ከቻሉ በሕንድ የደረሰው በእኛም ላይ እንደማይደርስ ምንም ማስተማመኛ ማግኘት አይቻልም። የሕንዱ ተሐድሶ (“የማር ቶማ ቸርች”) በእምነት ከአንግሊካኖች ጋር አንድ መሆኑን አውጆ የራሱን ጎጆ እንደቀለሰው ሁሉ የኛዎቹም የራሳቸውን ጎጆ የማይቀልሱበት ምንም ምክንያት የለም። በሕንዶች ከ1880ዎቹ ጀምሮ የተከሰተውን ታሪክ ከ150 ዓመት በኋላ የተፈጠርን ሰዎች ተመልክተን ችግሩን መገንዘብ ለምን ያቅተናል?

የሶሪያው ፓትርያርክ ለተሐድሶዎቹ የመጀመሪያ ጳጳስ ማዕረጉን ተሳስተው እንደሰጡት ሁሉ ዛሬም አውቀውም ይሁን ሳያውቁ መናፍቃኑን ማዕረግ በማዕረግ አድርገው በመንጋው ላይ በእረኛ ፈንታ ተኩላ የሚልኩባቸው ሰዎች ከፍ ያለ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባቸው ነበር።

በዚህ ወቅት የተሐድሶዎች ክፍል በቤተ ክህነቱ የተፈጠረው የአባቶች መከፋፈል ሰርግና ምላሽ ሆኖት ከዚህ ሲሉት ከዚያ፣ ከዚያ ሲሉት ከዚህ እያጣቀሰ ስሩን እያስፋፋ ሲሆን የአባቶች መከፋፈል እውነት የመሰለው ኦርቶዶክሱ ክፍል በዚህም በዚያም ወገን እየተጎዳ ከሁለት ያጣች ጎመን ሆኖ ተዘልሎ ተቀምጧል። የተሐድሶው ክፍል አገር ቤት ሲገባ ኢሕዴግን፤ ውጪ ሲወጣ ተቃዋሚውን እየመሰለ ዋና ዓላማው የሆነውን የኑፋቄ ስራ በሰፊው ያስፋፋል። “ፓትርያርካችን አቡነ መርቆርዮስ ናቸው” ሲል ይቆይና አቡነ ማትያስ የደገፉት ሲመስለው ተቀልብሶ ሲያመሰግናቸው ያመሻል። “አቡነ ማትያስ ፓትርያርኬ” ሲል የቆየው አገር ቤት ያለው ክንፋቸው ሲመቸው ደግሞ ውጪ ያሉት አባቶች ጋር ራት ሲበላ ይገኛል። በዚህም በዚያም ግን ቤተ ክርስቲያን እየደማች ነው። ይህ አዚም የሚለቀን መቼ ነው? የምንደናገረውስ እስመቼ ነው?

በዚህ ረገድ ፓትርያርክ አባ ማትያስ ቀደምቶቻቸው አድርገውት በማያውቁት መጠን እና ስፋት ቤተ ክርስቲያኒቱን ጅብ እያስበሏት ነው። አውቀውትም ይሁን ሳያውቁት የተሐድሶዎችና የዚሁ ዓላማ መጋቢ የሆኑ ግብረ በላ ወዳጆቻቸው መጠቀሚያ ሆነዋል። በቤተ ክህነቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚያስብል ደረጃ ከቅ/ሲኖዶስ ተነጥለው፣ ሲኖዶሳዊቱን ቤተ ክርስቲያን ኢ-ሶኖዶሳዊ አስተዳደር ተክለውባታል። ብዙ ሚሊዮን ሕዝቧ በረሃብና በችጋር የዓለም መሳቂያ መሳለቂያ በሆነበት ዘመን፤ የኑሮ ምሬት ያንገሸገሸው ሕዝብ ከሰሜን እስከ ደቡብ ግዛቶች ምሬቱን በሚያሰማበትና በዚሁ ሰበብ የሚያልቀው ምእመን የቀብሩን ስፍራ ባጣበበት በዚህ ወቅት “አስረሽ ምቺው” የቅንጦትና የዘረፋ ሰደድ ቤተ ክህነቱን አቀጣጥሎታል። ይህ ሁሉ ሰርግና ምላሽ የሆነው ግን ለተሐድሶው ኑፋቄ ነው። ይህ ሁሉ ነገር እንዴት ያደናግረናል? ለምንስ አንነቃም?

                                               

ቸር ወሬ ያሰማን፤

አሜን። 

Deje Selam is a venue of news, views and opinions about or related to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. [email protected]

በበፍቃዱ ኃይሉ

ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እያለሁ ፖለቲከኛ ከሆነውም ካልሆነውም ጋር በፖቲካ ጉዳዮች እንከራከር ነበር። ከክርክሮች በአንዱ ከተወሰኑ ሰዎች ጋር እኔ እንደሃይማኖት የማከርረውን “ሠላማዊ ትግል አልተሞከረም” እያልኩ እንደወትሮዬ ስሟገት የደረሰልኝ ብቸኛ ሰው ፍቅረማርያም አስማማው ነበር። ፍቅረ በሙግት ሲያጣድፉኝ የነበሩትን፣ እያንዳንዳቸውን “አንተ ሰልፍ ወጥተህ ታቃለህ? ፓርቲ ተቀላቅለህ ታቃለህ?…” እያለ ቀድመው አፋችን ላይ የሚመጡልንን የሠላማዊ ትግል እንቅስቃሴ የሚባሉትን ሁሉ ሲጠይቃቸው “አይ…” በማለት ይመልሳሉ። ከዚያ ፍቅረ “ብዙ ጊዜ ሠላማዊ ትግል አያዋጣም እያሉ የሚከራከሩት ምኑንም ያልሞከሩት  ናቸው” አለና ክርክሩን ቋጨልኝ።

ከዚያ ከፍቅረ ጋር ብቻችንን ስንሆን፣ “የምር የምታምንበትን  ነው የተናገርከው?” አልኩት። ግንቦት 7ን ለመቀላቀል ከብርሃኑ ተ/ያሬድ እና ከእየሩሳሌም ተስፋው ጋር ሲሄድ መያዙ ይታወቃልና።

እጅግ ሲበዛ የሚያስደንቀኝ  ትሕትና ያለው ፍቅረ፣ በተለመደ ትሕትናው ሊያስረዳኝ ሞከረ። “ለሠላማዊ ትግል ክብር አለኝ” ብሎ ነበር የጀመረው። “ቢሆንም…” በማለት ብዙ አስረድቶኛል። በተለይ መደራጀት በማይቻልበት ጥቂቶች ሠላማዊ ትግልን የመረጡ በግልጽ እየታዩ ለመኮርኮም ይመቻቻሉ አለኝ። ተለቅቄ እስክወጣ ክርክሯችን አልበረደም ነበር። ከዚያ በኋላ ግን አማራጩን ከሕይወት መርሔ ጋር የሚጋጭ በመሆኑ ባልቀበለውም፣ ቢያንስ “የእነርሱን መረዳት አለብኝ?” በሚል ብዙ አስቤበታለሁ።

ምዕራፍ ፩ – ሦስቱ ወጣቶች በሠላማዊ መንገድ ላይ…

ለመጀመሪያ ግዜ እየሩስን በአካል የተዋወቅኳት እስር ቤት ውስጥ ነው። ‘ግራዚያኒ በትውልድ ሀገሩ የመታሰቢያ ኀውልት ሊሠራለት የማይገባ ነፍሰ–በላ ሰው ነው’ ብለው የተቃውሞ ሰልፍ ሲያደርጉ እኔ በዚያ’ጋ በአጋጣሚ ሳልፍ ፖሊስ እየደበደበ ሲያፍሳቸው አየሁ። ይቺንማ ፎቶ ማንሳት አለብኝ ብዬ ሦስት ፎቶ እንዳነሳሁ እኔም አብሬ ታሰርኩ። የሰማያዊ ፓርቲ እና የባለራዕይ ወጣቶች ነበሩ ሰልፈኞቹ። ፖሊሶቹ «እንፍታቸው፣ አንፍታቸው?»፤ «የት እናሳድራቸው?» ሲባባሉ ሦስት ጣቢያ እያዞሩን አስመሹን። እኔ በወቅቱ በፍርሐት ስርድ እነሱ ሌሎቹ በጀግንነት ይዘፍኑ ነበር። ማታ ላይ ብርዱ ይሁን ፍርሐቱ ሲያንቀጠቅጠኝ እየሩስ የመጣላትን ጋቢ አለበሰችኝ።…

በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ እያንዳንዳቸው ከ10 ጊዜ በላይ ታስረው ተፈትተዋል። ሁሉንም እስሮቻቸውን ጥፋተኛ ተብለውት አያወቁም። የሚታሰሩት አንዳንዴ “ወረቀት በተናችሁ”፣ አንዳንዴ ደግሞ “ዕውቅና ያልተሰጠው ሰልፍ ወጣችሁ” በሚሉና በሌሎችም ተልካሻ ሰበቦች ነው።

ታስረን እያለን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እየመጡ ይጠይቁን ነበር። ፍቅረ እና ብሬ አንድ ቀን ያለወትሯቸው ፊታቸው ላይ ተስፋ መቁረጥ በግልፅ በሚነበብበት ሁኔታ ሊጠይቁን መጡ። ሁለቱም ከከተማ ውጪ እንደነበሩ፣ እና ለምርጫ ዕጩ እየመለመሉ አንደከረሙ ነገሩን።

«እንዴት ነው ታዲያ?» በጉጉት ጠየቅናቸው።

«ተስፋ አስቆራጭ ነው» አሉ። «‘እኔን ዕጩ አድርጉኝ’ ብሎ ወጥሮ የያዘን ሁሉ አዲሳባ ስንደርስ ‘ይቅርብኝ፣ ይቅርብኝ’ ብሎ ይደውልልናል።»

«ምንድን ነው ችግሩ?»

«ችግሩማ ኢሕአዴግ ነው። ዕጩዎቻችንን እያስፈራሩ ራሳቸውን እንዲያገሉ እያደረጓቸው ነው። እምቢ ያሏቸውንም በየሰበብ አስባቡ እየሰረዙ ከግማሽ በላይ የሆኑትን አባሎቻችንን ሰረዙብን።»

ብርሃኑ «ከዚህ በኋላ በዚህ በኩል መጥተን የምንጠይቃችሁ አይመስለንም። ወይ በውስጥ እንገናኛለን፤» እንደሚታሰሩ ገምተዋል ብዬ ደመደምኩ። ወቅቱ ቅድመ ምርጫ እንደመሆኑ እስር ብርቅ አልነበረም።

ብርሃኑ ፖለቲካ ሲያወራ አንጀቴን ያርሰዋል። ቀረብ ብለው ሲያዋሩት የተቃዋሚውንም የኢሕአዴግንም ድክመት ያለስስት መተቸት ያውቅበታል።
ከዚያ በኋላ አልመጡም። ቆይተን መታሰራቸውን ሰማን። መጀመሪያ እንደወትሮው ዓይነት እስር መስሎን ነበር። ጉዳዩ ሌላ መሆኑ የገባን ዝርዝሩን ስንሰማ ነው። በአካል መልሰን የተገናኘነው ከማዕከላዊ ወደ ቂሊንጦ ሲዛወሩ ነው።

እኔ፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ አብርሃ ደስታ፣ ዘላለም ወርቅአገኘሁ እና ሌሎችም የነበርንበት ዞን 2 የተመደበው ፍቅረማርያም ነበር። ፍቅረማርያም የግለሰብ አጀንዳ የሌለው ሲበዛ ትሁት ወጣት ነው። የሱን ትህትና የሚፎካከር ያገኘሁት አብርሃ ደስታን ብቻ ነው። ፍቅረ የሚታገለው በሚንቀለቀል ነገር ግን ለውለታው ምላሽ በማይፈልግ የወጣትነት ስሜት ነው።

ምዕራፍ ፪ – ሦስቱ ወጣቶች በፍርድ ቤት ክርክር…
(ያልተሞከረውን ሙከራ)

ልጆቹ ትግል ላይ በቂ ልምድ ስላላቸው ሲያዙ ሌሎች እንደሚያደርጉት ወደ ክህደት አልሄዱም። «ሠላማዊ ትግል ላይ ያለን እምነት ስለተቀየረ፣ የቀድሞ ፓርቲያችንን ሰማያዊን ለቀን፣ የግንቦት ሰባትን የትጥቅ ትግል ለመቀላቀል እየሄድን ነበር» አሉ። ይኸው ክስ ሆኖ ተመሰረተባቸው።

መዝገባቸው አራት ሰዎች ይዟል።
1ኛ፣ ብርሃኑ ተ/ያሬድ
2ኛ፣ እየሩሳሌም ተስፋው
3ኛ፣ ፍቅረማርያም አስማማው
4ኛ፣ ደሴ ካህሳይ

ደሴ ካህሳይ ወደኤርትራ ሊያሻግራቸው የነበረው ሰው ነው። እነብርሃኑ ፍርድ ቤት «ድርጊቱን ፈፅማችኋል ወይስ አልፈፀማችሁም?» ሲላቸው የሰጡትን መልስ ነው ‘ያልተሞከረውን ሙከራ’ የምለው።

«ድርጊቱን ፈፅመናል፤ ግን ጥፋተኞች አይደለንም» አሉ።

ከዚህ በፊት በግንቦት ሰባት ተጠርጥረው ያመኑ እና በዚያው የተቀጡ እስረኞች ገጥመውኛል። ሆኖም «ድርጊቱን ፈፅመናል። ጥፋተኞች ነን» ነበር የሚሉት።

«ምን አስባችሁ ነው?» አልኩት ፍቅረን።

«ግንቦት ሰባት በእኛ እምነት አሸባሪ ቡድን አይደለም። ነፃ አውጪ ቡድን ነው። ልክ የፀረ–ሽብር አዋጁ ሠላማዊ ትግልን እያደናቀፈ ነው ይሰረዝ እንደምንለው ሁሉ፣ የግንቦት ሰባት ‘አሸባሪ ነው’ የሚለውም እንዲሰረዝ ፍ/ቤቱን በሕጋዊ አካሄድ መሞገት እንፈልጋለን» አለኝ።

«እና በዚህ መንገድ ተከራክራችሁ እና ረትታችሁ ነፃ እንወጣለን የሚል እምነት አላችሁ?» የኔ ጥያቄ ነበር።

«ጉዳዩ በዚህ ክርክር ነፃ መውጣት አለመውጣት አይደለም። እኛ የምናደርገው ክርክር አንደኛ መንግሥት ሠላማዊ ትግሉን ሆነ ብሎ ሠላማዊ ወዳልሆነው ሜዳ እየገፋው እንደሆነና ለዚህ መከሰስም ካለበት ራሱ መንግሥት መከሰስ እንዳለበት፤ ሁለተኛ ግንቦት ሰባት የገዢው ፓርቲ እንጂ የሕዝብ ጠላት አለመሆኑን ለማሳየት መሞከር ነው ዓላማችን» አለኝ። ይህንን ስናወራ የነበረው እዚያው ቂሊንጦ እያለሁ ነበር። አሁን ተከላክለው ነፃ እንዲወጡ በ14ኛው የፌ/ወ/ችሎት ተበይኖባቸው የመከላከያ ምስክሮችን ለማስደመጥ ለመጋቢት 22, 2008 ተቀጥረዋል።

«እህ ምን አሰባችሁ?» በማለት የእስር ጓዶቼን ልጠይቃቸው ቂሊንጦ የሄድኩ ጊዜ ፍቅረን ጠየቅኩት።

ፍቅረ «ማንኛውንም በሠላማዊ ትግል የተሰማራ ሰው በሙሉ ከቻልክ ለኛ እንዲመሰክርልን ጥሪ እንድታደርግልን እንፈልጋለን» አለኝ። «እንዴ?» አልኩኝ ድንግጥ ብዬ። «ይሄማ እንዴት ሊሆን ይችላል። በሠላማዊ ትግል ውስጥ ያለ ሰው እኮ የናንተ ተቃዋሚ ነው። የተሳሳተ መንገድ ነው የሚከተሉት እያለ እንዴት ምስክር ይሁኑን ትላለህ?» አልኩት።

የሰጠኝ መልስ ባጭሩ እንዲህ የሚል ነው።

«እኛ የምንፈልገው ሠላማዊ ታጋዮች በሠላማዊ ትግል ውስጥ የገጠማቸውን ፈተና ለፍርድ ቤቱ እንዲያስረዱልን ብቻ ነው። ይህ መንግሥት ሠላማዊ ትግል እንዲያበቃለት መንግሥት ራሱ መንስኤ እየሆነ እንደሆነ ያሳይልናል። ቀሪውን ማስረዳት የኛ ድርሻ ነው።»

ፍቅረ በተጨማሪም ስርዓቱ ራሱ ለነሱ ውሳኔ እያደረገ ያለውን ኢ–ሕገመንግሥታዊ ዘመቻ አንድ ባንድ የሚሞግቱበት ስትራቴጂ እንዳላቸው ነገረኝ። ነገርዬው ፈረንጆቹ ‘ጁዲሻል አክቲቪዝም’ የሚሉት ሕግን መሠረት ያደረገ አክቲቪዝም ዓይነት መሆኑ ነው። እኔ በግሌ ወጣቶቹ የትግል ስትራቴጂ መቀየራቸውን አልወደድኩላቸውም ነበር። እስር ክፉ አጋጣሚ ቢሆንም፣ አጋጣሚውን ወደዕድል በመቀየር፣ ውጤቱ እንደጠበቁት ቢሆንም ባይሆንም  በሠላማዊ የትግል ስትራቴጂ (በጁዲሻል አክቲቪዝም) ራሳቸውን ለማስፈታት (ወይም አጭር ፍርድ ለመቀበል) ሳይሆን መንግሥትን ለሞገት በመወሰናቸው ደስ ብሎኛል።

በእኔ እምነት ከሠላማዊ ትግሉ ወጥቶ የኃይሉን መቀላቀል ለኢሕአዴግ እጅ መስጠት ነው። እስከዛሬ ደክመው እጅ የሰጡትን ሁሉ እየጠቀሰ የሚያሳጣው ኢሕአዴግ ነበር። አሁን ግን በነብርሃኑ ተ/ያሬድ መዝገብ የተከሰሱት ወጣቶች ‘ለዚህ ያበቃኸን አንተው ነህ’ እያሉ ኢሕአዴግን ይከሳሉ።

***
ብርሃኑ፣ እየሩስ፣ ፍቅረ እና ደሴ ከታሰሩ እነሆ ልክ አንድ ዓመታቸው ዛሬ።

ሰሞኑን ሻለቃ ኃይሌ ገ/ሥላሴ ለአንድ የውጪ ጋዜጠኛ “ዲሞክራሲ (መስፍነ ሕዝብ) ለአፍሪካ አያስፈልጋትም! ለአፍሪካ የሚያስፈልጋት መልካም አሥተዳደር ነው!” ብሎ መናገሩን ሰምተናል፡፡ እንደሰማንም በእጅጉ አፍረናል ተሸማቀናልም፡፡ እኔ በበኩሌ “እንዲያው ይሄ ሰውየ እያሰበና ነገሮችን በቅጡ ተረድቶ ተገንዝቦ ገብቶት መናገር የማይችል ከሆነ ምናለ ዝም ቢል ባይናገርስ!” ብያለሁ፡፡ ይሄንን ንግግሩን “አይ እሱ ለማለት የፈለገው…” ብለን ልንለው የምንችለው ምንም ሌላ ነገር […]


የቀድሞው የእሥራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሁድ ኦልመርት (Ehud Olmert) ለአንድ ዓመት ከሰባት ወር የተፈረደባቸውን እሥር በዛሬው እለት ጀምረዋል። ሮበርት በርገር ለአሜሪካ ድምጽ ከእየሩሳሌም አጭር ዘገባ ልኳል። ሰሎሞን ክፍሌ አቅርቦታል – ያድምጡ → listen

ግርማ ካሳ

አቶ ብርሃነመስቀል አበበ፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ መብት ዙሪያ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ጽሁፎችን ይጽፋሉ። ቢቢሲ በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ስርጭት እንዲኖረው ፔቲሽኖችን በማስፍረም አንድ ዘመቻ እንደነበረ የምናስታወሰው ነው። ይሄንን ዘመቻ ይመሩ ከነበሩት መካከል አቶ ብርሃነመስቀል አንዱ ነበሩ። እኔም ሆንኩም በርካታ ኢትዮጵያዊያን ፔቲሽኑ ላይ ፊርማችንን በማስፈር፣ ፔቲሽኑ ያልፈረሙ እንዲፈረሙ በማበረታታት እንደነ አቶ ብርሃነመስቀል ባይሆንም፣ የድርሻችንን አበርክተናል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Gambella, western Ethiopia zones
ከአንድ ሺህ አራት መቶ በላይ ናቸው የሚባሉት የልዩ ኃይሉ አባላት በክልልሉ ዋና ዋና በሚባሉት አኝዋክና ኝዌር ጎሣቸው ተከፋፍለው መጋጨታቸው የተገለፀ ሲሆን ፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሠራዊት አባላት ገብተው ሁኔታውን መቆጣጠራቸውን እነዚሁ የአካባቢው ሰዎች ተናግረዋል፡፡

Anon+

Ethiopia Zare (ሰኞ ጥር 30 ቀን 2008 ዓ.ም. Feb. 08, 2016)፡- በኢህአዴግ መንግሥት ሙሉ ቁጥጥር ስር ያለውና ጋዜጦችንና መጽሔቶችን የሚያሳመው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ድረገጽ “አኖን ፕላስ” (AnonPlus) በተሰኙ ያልታወቁ ወገኖች ከቅዳሜ ጥር 28 ቀን ጀምሮ ተጠለፈ (ሐክ ተደረገ)። ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ ድረገጹ እንደማይሠራ ለመገንዘብ ችለናል።

ሙሉውን አስነብበኝ …


የአርበኞች ግንቦት 7 የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀ መንበር ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ባሁኑ ወቅት እዚህ በዩናይትድ ስቴትስ ይገኛሉ። በቅርቡ በወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ለአውሮፓ ፓርላማ አባላት ማብራሪያ ለመስጠት ብራሰልስ እንደነበሩም ተዘግቧል። ዶክተር ብርሃኑን ወደ ዋሺንግተን ያመጣቸው ጉዳይ ምንድነው?በኢትዮጵያ መንግሥት ባሸባሪነት መፈረጃቸው በጉዞዎቻቸው ላይ ችግር ፈጥሮ ይሆን? ድርጅታቸው የአርበኞች ግንቦት 7 የወቅቱን በኦሮሚያ እየተካሄደ ያለውን ተቃውሞ እንዴት ያየዋል? ሰሎሞን ክፍሌ ከዶክተር ብርሃኑ ጋር ባደረገው አጭር ቆይታ ካነሳቸው ጥያቄዎች አንዳንዶቹ ናቸው። የውይይቱን ክፍል 1 ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ። ያዳምጡ → listen

የላላው ጭቃአንዱዓለም ተፈራ

አሁንም ቀኑን እንቆጥራለን። ሌሊቱንም እንዲሁ። አሁንም የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባርን ተግባር እንዘረዝራለን። አሁንም ሰዎች በገዛ ሀገራቸው እንዳውሬ እየታደኑ፣ እየተያዙ፣ ይታሰራሉ፣ ከሀገር ይሰደዳሉ፣ ይገደላሉ፣ … እንላለን። አሁንም በየቤተክርስትያኑና በየመስጂዱ እግዚዖ እንላለን። አሁንም የሀገራችን ለም መሬት ከባለቤቱ ኢትዮጵያዊ እየተነጠቀ፤ ለሹማምንትና ለውጪ ሀገር ባለሀብቶች ተሠጠ እያልን እናላዝናለን። አሁንም ሹማምንት ጀኔራሎችና ዘመዶቻቸው፤ ከተማዎችን ፎቅ በፎቅ አድርገው፤ ድሃን ማደሪያ አሣጡት እንላለን። ምን የማንለው አለ! ብቻ በገባንበት አረንቋ አሁንም እንረግጣለን።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግርማ ካሳ

Dr Berhanu Nega. ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ

አንዳንንድ ወገኖች በግንቦት ሰባቶች ላይ የግል ችግር ያለብኝ ይመስላቸዋል። አይደለም። ከነርሱ ጋር የዓላማ ልዩነት የለኝም። ልዩነቴ የስትራቴጂ ነው። ግንቦት ሰባት ውስጥ ያሉ ወገኖች ዳይናሚክ የሆኑ ትልቅ ፖቴንሻል ያላቸው እንደሆነ አውቃለሁ። ሊቀመንበሩ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ በቅንጅት ጊዜ ቁልፍ ሚና የተጫወቱ መሪ ናቸው። ብዙዎቻችንን ኢንስፓየር ያደረጉ። ሆኖም በግንቦት ሰባት አመራርነት የወሰዱት ስትራቴጂ ግን ያላቸውን ፖቴንሻል እንዲጠቀሙበት የረዳቸው አይመስለኝም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተስፋዬ ገብረአብ

Andargachew Tsege. አንዳርጋቸው ፅጌ

እነሆ! ቅዳሜ ዞሮ መጣ። በዚህች የቅዳሜ ምሽት ስለ አንዳርጋቸው ጥቂት አወጋ ዘንድ መንፈሴ መራኝ። አዲስ ነገር አትጠብቁ። ከቀንዱም ከሸኾናውም ዝም ብዬ አወጋለሁ። የምትሠሩት ሌላ አስቸኳይ ጉዳይ ካላችሁ ይህን ጽሑፍ ለማንበብ ጊዜአችሁን አታቃጥሉ። እንደው ዘና ብላችሁ ከሆነ ግን ብታነቡት ምንም አይላችሁም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይገረም አለሙ

Goonder before and after 1991

ወቅቱ 1994 ክረምት ነው። በየዓመቱ ትምህርት ቤቶች ሲዘጉ መምህራንን አንድም በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ለማጥመቅ ሁለትም ሥራ ፈተው ከዋሉ የሚሠሩት ስለማይታወቅ ጠርንፎ ለማቆየት የሚዘጋጀው ስብሰባ ጎጃም ደብረ ማርቆስ በሦስት አዳራሾች እየተካሄደ ነው። ቤተ መንግሥት አዳራሽ፣ ሲኒማ ቤትና መንገድ ትራንስፖርት አዳራሽ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ኦሮምያ ክልል ውስጥ የተወሰደው የኃይል እርምጃ “ስህተት መሆኑን የኢትዮጰያ መንግሥት ባለሥልጣናት አምነዋል” ሲሉ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ አስታውቀዋል፡፡

ዐፄ ቴዎድሮስ በበጌምድር ማንም ለሞተ ዘመዱ እንዳያለቅስ የሚል ዐዋጅ ዐውጀው ‹ሰው ሁሉ ዕንባውን ያጠጣ ነበር፡፡› በዚህ መካከል ደጃች ውቤ ሞቱና ለእቴጌ ጥሩ ወርቅ ወደ መቅደላ መርዶ ተላከ፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስም ሕዝቡን ‹ለደጃች ውቤ አልቅሱልኝ› ብለው አዘዙ፡፡ ሰውም ሁሉ ዘመዱ ሲሞት የቀረበት …

የደጃች ውቤ ልቅሶ – ዳንኤል ክብረት Read more »

“የጥጥ ግብይት ቆሟል፤ አምራቹ ከጥጥ ስራ ሊወጣ ነው”

  የኢትዮጵያ ጥጥ አምራቾች ማህበር፤ ያመረትነውን ጥጥ የሚገዛን አጥተናል ሲል ያማረረ ሲሆን መንግስት አምራቾቹን ለመርዳት በኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት በኩል ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል ተብሏል።
የጥጥ አምራቾች ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሐዱሽ ግርማይ፤ የመንግስት ጥረት ያልተሳካው ድርጅቱ ለግዥ ያቀረበው ዋጋ እጅግ አነስተኛ በመሆኑ ነው ይላሉ፡፡ የኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት፤ የራሱን ትርፍ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ለአምራቹ እንደየጥጡ ደረጃ በኪሎ ከ30-33 ብር የግዥ ዋጋ መተመኑን ምክትል ፕሬዚዳንቱ ገልፀው፣ ይሄን የዋጋ ተመን ግን አምራቹ አያዋጣኝም ብሎ አልተቀበለውም፡፡
የሌሎች አገራት አምራቾች መንግስታቸው ይደግፋቸዋል፤ በእኛ ሀገር የጥጥ ሴክተሩ በተገቢው ሁኔታ እየተደገፈ አይደለም የሚሉት አቶ ሐዱሽ፤ “አለም በሄክታር ከ50 እስከ 60 ኩንታል ሲያመርት፤ እኛ ግን በሄክታር እያመረትን ያለነው ከ10 እስከ 15 ኩንታል ብቻ ነው” ብለዋል፡፡
አምራቹ የተለያዩ ችግሮች እንዳሉበት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ይናገራሉ፡፡ “ኬሚካልና የተለያዩ ማሽኖችን ከውጪ እያመጣ ነው የሚሰራው፤ በዚያ ላይ የምርጥ ዘር ችግሮች አሉበት፤ የምርምር ስራው በጣም የተዳከመ በመሆኑም የምንጠቀመው ዝርያ ከዛሬ 25 አመት በፊት እንጠቀምበት የነበረውን ነው” – ብለዋል፤ አቶ ሃዱሽ። ይህም የዘርፉን ጥራትና ምርታማነት እንደጐዳው ይገልፃሉ፡፡ “በአሁኑ ወቅት የጥጥ ግብይት ቆሟል፤ አምራቹ እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድረስ እንሄዳለን፤ ሰላማዊ ሰልፍም እንወጣለን፣ መንግስት መልስ መስጠት ይኖርበታል” እስከማለት ደርሰዋል ያሉት አቶ ሃዱሽ፤ ይህ ሁሉ ችግር ቢያልፍ እንኳን በሚቀጥለው ዓመት አምራቹ ከጥጥ ምርት ለመውጣት ወስኗል ብለዋል። እኛም እንደ ማህበር ድልድይ ሆነን ከመንግስት ጋር ያለውን አለመግባባት ለመፍታት ሞክረን ነበር፤ ግን አልቻልንም ይላሉ – ምክትል ፕሬዚዳንቱ፡፡
የኢንዱስትሪ ግብአት አቅርቦት ድርጅት (የቀድሞው ጅንአድ) በበኩሉ፤ የጥጥ ዋጋው የወጣው በገለልተኛ አካል መሆኑንና አምራቹን ለማበረታታት በኪሎ 2 ብር ድረስ ጭማሪ መደረጉን ገልጿል፡፡ የድርጅቱ የግዥና አቅርቦት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይ ከበደ ስለሁኔታው ሲያስረዱ፤ “እኛ ገዝተን የምንሸጠው ለጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪው ነው፤ ኢንዱስትሪው ምርቱን አምርቶ በአገር ውስጥ ገበያ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ገበያም ተወዳዳሪ መሆን አለበት። ዋጋው የተሰላውም የዓለም አቀፍ ገበያውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡ ከዚህ በላይ ዋጋው ቢጨምር ገዥ አይኖርም፡፡ ድርጅታችን የተቋቋመው በዋናነት አምራቹንና ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ እንጂ ለትርፍ አይደለም” ብለዋል፡፡   
አምራቹ በተባለው ዋጋ አያዋጣኝም ካለ፣ እናንተም በዚህ ዋጋ ካልሆነ አንገዛም ካላችሁ የመጨረሻ መፍትሔው ምንድነው ያልናቸው አቶ አባይ፤ “አልሸጥም ያለ አካል የራሱን አማራጭ ይወስዳል” ሲሉ መልሰዋል፡፡

የ45 ዓመቱ ጎልማሳ ስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በቀጣይ የውድድር ዓመት የእንግሊዙን ማንቸስተር ሲቲ ለማሰልጠን የሶስት ዓመት ተኩል የውል ስምምነት ፊርማውን ማኖሩ ታወቀ። የማንቸስተር ሲቲ አሰልጣኝ የሆኑት ቺሊያዊው የ64 ዓመቱ አዛውንት ማኑኤል ፔልግሪኒ የጋርዲዮላን ወደ ሲቲ መምጣት በበጎ ጎኑ ተቀብለውታል። ፔልግሪኒ በማንቸስተር … Continue reading

ግርማ ካሳ

Tesfaye Gebreab, ተስፋዬ ገብረአብ

አቶ ተስፋዬ ገብረአብ በአንድ ወቅት የኢሕአዴግ ባለሥልጣን የነበሩ ሰው ናቸው። ጥሩ ፀሐፊ ናቸው። ከኦሮሞ ብሔረተኞች ጋር የቅርብ ግንኙነት አላቸው። አንድ ወቅት እንደውም የኦሮሞ ተማሪዎች ማኅህበር ላይ የክብር እንግዳ ሆኖ ቀርበው ነበር። በዚያን ወቅት “በሞጋሳ እኔም ኦሮሞ ነኝ” ብለው ነበር። ሞጋሳ አንድ ሰው “ኦሮሞ” ባይሆንም የኦሮሞን ባህልንና ቋንቋን ከተቀበለ፣ በኦሮሞ “ሽማግሌዎች” ፍቃድ “ኦሮሞ” የሚሆንብት ሥርዓት ነው (naturalized ኦሮሞነት)።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጥር 7፣ 2008 ዓ.ም | በወንድወሰን ጥበቡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እንግሊዝ እና ፖርቱጋል ለዩሮ 2016 ለሚያደርገት የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ወደኦልትራፎርድ ሊመለስ ይችላል። የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር ሁለቱ ሃገራት ስለሚያደርጉት የወዳጅነት ጨዋታ ከፖርቱጋል አቻው ጋር ንግግር እያደረገም ይገኛል። በአሁኑ ጊዜ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዝውውር ወደእንግሊዝ እንደሚመጣ ማረፊያውም ኤልራፎርድ ሊሆን እንደሚችል በሰፊው እየተወራ ይገኛል። የፖርቱጋል እግር ኳስ ማህበር ምንጭ … Continue reading “ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደኦልትራፎርድ ዳግም ሊመለስ ነው”

ወያኔና ሌሎች የጥፋት ኃይሎች አማራን የማጥፋት የቆረጠ የጥፋት ዓላማና ድርጊት ይዘው መምጣታቸውና ሀገሪቱን ከመቆጣጠራቸው የወሰዱት የተቀናጀ ዘግናኝ የዘር ማጥፋት ጥቃት መፈጸማቸው የአማራ ልኂቃንን አስጨንቆ ሕዝቡን ከወያኔና መሰሎቹ የዘር ማጥፋት ጥቃት የታደጉ፣ የሠወሩ፣ ያዳኑ፣ የከለሉ፣ የተከላከሉ መስሏቸው ሁለት የተለያዩ አቋሞችን ለማራመድ ሲያስገድድ ከአማራው ሕዝብም ቀላል ቁጥር ያልያዘውን ምናልባትም አሁን የአማራ ሕዝብ ተብሎ ከሚገለጸው የሚበዛውን በተለይ በወያኔ […]

ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል ዳይሬክተር አቶ ኒካው ኦቻላ ለኢሳት እንደገለጹት የንዌር ተወላጆች የጋምቤላ እስር ቤትን ሰብረው በመግባት 7 የአኝዋክ ተወላጆችን ሲገድሉ፣ 7ቱን ደግሞ አቁስለዋል። 4 የሌሎች ብሄረሰቦች አባላት መቁሰላቸውምን ዳይሬክትሩ ገልጸዋል። በሁለቱ ብሄረሰቦች መካካል እንዲህ አይነት ደም የሚያፋሰስ የመረረ ግጭት ተቀስቅሶ እንደማያውቅ የገለጹት አቶ ኒካው፣ ለአሁኑ ግጭት መባባስ …

ተስፋዬ ገብረአብ (Gadaa)

Abay Tsehaye. አባይ ፀሐዬ

ከኦሮሚያ አመጽ ጋር በተያያዘ አባይ ፀሐዬ ስሙ በተደጋጋሚ ይነሳል። አንዳንድ ደንፊ ንግግሮች መናገሩንም ስናነብ ሰነባብተናል። ምን እንደነካው እንጃ እንጂ ጠባዩ እንኳ እንዲያ አልነበረም። አባይ በጠባዩ ድመት መሆኑ ነበር የሚታወቀው። ሊያጠቃ ሲፈልግ እንደ ፈረስ ጋማህን እያሻሸ እንጂ እንደ ቋረኛው ካሳ ጎራዴ አያወዛውዝም። ከታላቁ የኦሮሚያ አመጽ ጋር በተያያዘ “በሚናገራቸው ንግግሮች” ግን ስሜቱን መቆጣጠር የተቸገረ ይመስላል። ዞረም ቀረ አባይ ፀሐዬ እና ጓደኞቹ የገጠማቸውን ጦርነት በአሸናፊነት ለመወጣት መጣራቸውን ቀጥለዋል። ይሳካላቸው ይሆን?

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሃዋሳ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ለአስራ አምስት ቀናት ትምህርት መቋረጡን የዩንቨርሲቲው አስተዳደር መግለጹን ተከትሎ ግቢውን ለቀው ወጥተዋል። በአንድ ተሽከርካሪ ላይ ተጭነው ከግቢው በመውጣት ወደ ወላጆቻቸው በመሄድ ላይ ከነበሩት ተማሪዎች ውስጥ ወደ በመቂ እና ሞጆ ከተሞች መዳረሻ አካባቢ የመኪና አደጋ ደርሶባቸዋል። የአደጋው መንስኤ የሚጓዙበት ተሽከርካሪ ከአዲስ አበባ ወደ ሀዋሳ …

ኢሳት (ጥር 19 ፥ 2008) የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ማዕከላዊ ኮሚቴ በስራ አስፈጻሚ ደረጃ አስቸኳይ ስብሰባ መቀመጡ ታወቀ። የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ሙክታር ከድር እየተገመገሙ እንደሆነና ስልጣናቸውን ሊለቁ እንደሚችሉ ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል። ከጨፌ ኦሮሚያ የውስጥ ምንጮች ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ኦህዴድ በመላው የኦሮሚያ አካባቢ የተቀጣጠለውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ቁልፍ አመራር እየገመገመ መሆኑ ታውቋል። የድርጅቱ …

By Eyob Dadi |ጥር 19 ፣ 2008 ዓ. ም ስዋሬዝ እንግሊዝ ደርሷል።የህክምና ምርመራውን ዛሬ ሀሙስ አመሻሹ ላይ እንደሚያደርግ ተረጋግጧል። የፊዮረንቲና አማካይ የሆነው ስፔናዊው ማሪዮ ስዋሬዝ ከስፔኑ አትሌቲኮ ማድሪድ ከተዛወረ በኋላ በጣሊያን ሴሪ ኣ ተጽእኖ መፍጠር አቅቶታል። ተጨዋቹ በፊዮረንቲና 5 ጨዋታ ብቻ የተጫወተ ሲሆን ወደ እንግሊዙ ዋትፎርድ ለመዘዋወር ዛሬ ሀሙስ በምሳ ሰአት ላይ እንግሊዝ እንደደረሰ ታውቋል። … Continue reading “ስዋሬዝ ወደ እንግሊዝ ፕሪምየርሊግ ሊዛወር ነው።የህክምና ምርመራ ለማድረግ እንግሊዝ ደርሷል”

በዓለም ዙሪያ የሚሰማው የምጣኔ ኃብት ድቀት እና የማኅበራዊ ነውጥ ፍራቻ አምባገነን መንግሥታት በአውሮፓ አቆጣጠር ባለፈው 2015 ዓ.ም ይበልጥ አፋኝና ጨቋኝ እንዲሆኑ ሰበብ ሳይሰጣቸው እንዳልቀረ ዛሬ የወጣ የዓለም የነፃነት ሁኔታ ሪፖርት አስታውቋል፡፡

By Eyob Dadi የቀድሞ ኮከብ ሮናልዲንሆ ጎቾ የሴይንት ናግጄ የእግርኳስ ውድድር ለመክፈት በህንድ ይገኛል። ሮናልዲንሆ በህንድ ቆይታው ከሞት መትረፉን ነው ጎል ስፓርት የዘገበው። ሮናልዲንሆ በአድናቂዎቹ ፉጨት እና ጩኸት ታግዞ በሚጓዝበት ወቅት ግዙፍ የሆነ የዛገ የትራፊክ መብራት ፓል ከመኪናው በቅርብ ርቀት ላይ ከፊትለፊቱ ተሰብሮ ወድቆ መኪናውን ሳያገኘው ቀርቷል። ፓሉ ሲወድቅ አድናቂዎቹ በድንጋጤ ጸጥ እንዳሉ ሲታወቅ ወዲያው … Continue reading “ሮናልዲንሆ ከሞት ተረፈ”

የአዲስ አበባንና የፊንፊኔ ዙሪያ ዞኖችን የከተሞች ማስፊፊያ እቅድ ተንተርሶከተቀሰቀሰውና በኦሮምያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ትምሕርት ቤቶችተማሪዎች ሲያካሂዱ የቆዩት የተቃውሞ እንቅስቃሴ የክልሉ መንግስት እቅዱንመተዉን ካስታወቀም በኋላ በአንዳንድ አካባቢዎች አሁንም መቀጠሉ እየተዘገበ ነው።

ሰሞኑን በምዕራብ ወለጋ ጊዳ ወረዳ፤ ጉደቱ አርጆ ከተማ በተከናወነ የሰርግ ሥነ ሥርዓትላይ በጭፈራው መሃል የተቃውሞ ድምጽ …

በሬክተር የምድር ንዝር መለኪያ 4.3 ያስቆጠረ የመሬት ነዉጥ ባለፈዉ እሁድ ምሽትና ሰኞ ጥዋት በሃዋሳ ከተማ መሰማቱ ተዘገበ።

የምድር ነዉጡ በሰዉ ሆነ በንብረት ላይ ጉዳት አላደረሰም ተብሏል። ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮሮሬሽን ትንታኔ የሰጡ የአድስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከርሰ-ምድር ጥናት ምሁርን መግለጫ ተንተርሶ እስክንድር ፍሬዉ ዘግቧል።

የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያድምጡ።

 

ይገረም አለሙ

Dr. Merera Gudan and Girma Seifu. ዶ/ር መረራ ጉዲና (በግራ) እና አቶ ግርማ ሰይፉ (በቀኝ)

ለዚህች ጽሑፍ መነሻ ምክንያት የሆነኝ አቶ ግርማ ሰይፉ “የዶ/ር መረራ የቡዳ ፖለቲካ እና መቀበል ያቃተው መራራ እውነት”በሚል ርዕስ ያስነበቡን ጽሑፍ ሲሆን፤ ርሳቸው ለጽሑፋቸው ምክንያት የሆናቸው ደግሞ “የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ሕልሞች” የሚለው የዶ/ር መረራ መጽሐፍ እንደሆነ ገልጸዋል። የቡዳ ፖለቲካ የሚለው ቃልም ከዚሁ መጽሐፍ የተገኘ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጥር ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምእራብ ጎጃም ዞን የየስማላ ከተማ ነዋሪዎች መብራት ከተቋረጠባቸው 5 አመታትን ማሳለፋቸውን፣ በሰሜን ጎንደር ሃሙሲት ከተማ ደግሞ የከተማው ነዋሪዎች የቧንቧ ውሃ ከተቋረጠባቸው 5 አመታትን ማሳለፋቸውን ዘጋቢያችን ነዋሪዎችን አነጋግሮ የላከው ዘገባ ያሳያል። ነዋሪዎቹ ችግሮቻቸው እንዲፈቱላቸው በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም ሰሚ አካል አላገኙም። በሞጣ ከተማ ደግሞ መብራት ከተቋረጠ 2 ወር …

Ethiopia Oromo students protest addis ababa plan. የኦሮሞ ተማሪዎች በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ላይ ያሰሙት ተቃውሞይገረም አለሙ

በሀገር ውስጥም በውጪም ቁጥራው እጅግ የበዛ ተግባራቸው ግን ብዙም የማይታይ ፓርቲዎች አሉ። እነዚህ የሚችሉት ተዋህደው አንድ በመሆን፤ የማይችሉት ተባብረው ትብብርም ይሁን ግንባር በመፍጠር የነጻነት ቀናችንን ለማፋጠን የሚያስችል ትግል ያደርጉ ዘንድ ስንመኝ፣ ስንጠይቅ፣ ስንማጸን፣ ይህን ባለማድረጋቸውም ስንኮንን ወዘተ ዓመታት ተቆጥረዋል። እነርሱ ግን መተባበሩ ቀርቶ መከባበሩ አልሆን ብሎአቸው፣ ተደጋግፎ መቆሙ ቢቀር አንዱ ለአንዱ እንቅፋት ከመሆን መቆጠብ ተስኖአቸው ወያኔ ያሻውን እንዳሻውና ባሰኘው መንገድና ግዜ እየፈጸመ ከዚህ እንዲደርስ አድርገውታል።

ሙሉውን አስነብበኝ …