ኦህዴድ ከፍተኛ አመራሮችን ከስልጣን ሊያነሳ እንደሆነ ተገለጸ

ኢሳት (ጥር 19 ፥ 2008) – የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ማዕከላዊ ኮሚቴ በስራ አስፈጻሚ ደረጃ አስቸኳይ ስብሰባ መቀመጡ ታወቀ። የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ሙክታር ከድር እየተገመገሙ እንደሆነና ስልጣናቸውን ሊለቁ እንደሚችሉ ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል። ከጨፌ ኦሮሚያ የውስጥ ምንጮች ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ኦህዴድ በመላው የኦሮሚያ አካባቢ የተቀጣጠለውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ቁልፍ አመራር እየገመገመ መሆኑ ታውቋል። የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴና ስራ አስፈጻሚው ግምገማውን በአቶ ሙክታር ላይ በማተኮር ግምገማ እያደረገ እንደሆነ ከስፍራው የደረሰው ዜና ያስረዳል። የግምገማው ውጤትም አቶ ሙክታር ከድርን ከፕሬዚደንትነት በማንሳት ሊጠናቀቅ እንደሚችል የውስጥ ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። በአቶ ሙክታር ከድር ምትክ የገቢዎችና ጉምሩክ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ በክር ሻሌ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት ይሆናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ለማወቅ ተችሏል።

ግምገማው ከአቶ ሙክታር ከድር በተጨማሪ የኦህዴድ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ ከስልጣናቸው ሊነሱ እንደሚችሉ የኢሳት የጨፌ ኦሮሚያ የውስጥ ምንጮች ግምታቸውን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ የኦህዴድ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የኦሮሞ ብሄረሰብ ተወላጅ የሆኑ ነጋዴዎችን ለይቶ ለማወያየት ውሳኔ ማሳለፉን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በክልል ደረጃ የኦሮሞ ባለሃብቶችን በመሰብሰብ በወቅታዊ የህዝብ ንቅናቄ ላይ ለማወያየት የታቀደው በየአካባቢው የተደረገው ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ውጤት አልባ መሆኑን ተከትሎ ነው። በቅርቡ በአቶ ዱላ ገመዳና በሌሎቹ የኦህዴድ አመራሮች ተጠርቶ በነበረው የኦሮሞ ባለሃብቶች ስብሰባ ላይ ባለሃብቶቹ ጥቁር ለብሰው በመምጣት የመንግስት የግድያ ዕርምጃ መቃወማቸው ይታወሳል።

8 Comments on “ኦህዴድ ከፍተኛ አመራሮችን ከስልጣን ሊያነሳ እንደሆነ ተገለጸ”

  1. Shifting a cooking pot from one top burner to another would not induce food to be more savour. OPDO is a used up and broken draft animal,a treacherous bunch of running dogs which has been spat out by the Oromo Nation.

    It has no bride of its own, no self respect, and has debased itself beyond repair. This organization does not represent the Oromo Nation, and has no mandate to do so.

    If Tigre thinks that it can reverse the Oromo struggle by simply moving the dominos around, then it should know very well the Qubbee Generation is too smart not to be fooled.

    The best solution is for the Tigre is ” GO Home!” Before it is too late!

  2. I think, one should not just go home without paying the price for killing innocent children and pregnant women.

  3. መሬታችሁን በወያኔ የተነጠቃችሁ የአማራ የኦሮሞ የቤንሻንጉል የሀድያ ክልሎች በቃ ነመፍጠኛ እንደሆናችሁና ማንነታችሁን የሚያረጋግጥ ከነባህላችሁ ለውጭ አልሚ እየተሰጠ በመሆኑ ዳግም ላትመለሡበት የማትችሉትን ይዞታችሁ በወያኔ እያጣችሁ መሆናቸውን ያወቁትን የትግል አቅጣጫ እንድትቀላቀሉ ወገናዊ ምክሬን እየለገሥኩ ሁሉም ህዝብ መንደር ማሰባሰብ መብራትና ውሀት ትምህርት እንድታገኙ እየተባለ መሸወድ ቀርቶ ይህን የጠነሰሰውን ወያኔ እንድትደፋት ያሥፈልጋል።

  4. ባሣለፍነው የሚኒሥትሮች ሥብሰባ ላይ እንዳይገኙ ተደርጓል የተገኙት የትግራይ የአማራ የደቡብ አሥተዳደር ብቻ ናቸው ምናልባት የህወሀት በቅሎዋ ወሮ አሥቴር ልትሾም ትችላለች የሚል ግምት አለ።

  5. ሌተናንት ጄነራል ጃገማ ኬሎ(የበጋዉ መብረቅ) ከተወለዱ ዛሬ 95
    አመት ይሞላቸዋል ፤

    ================

    የ ሌተናንት ጄኔራል ጃገማ ኬሎ 95ኛ አመት የልደት በአል በዛሬው
    እለት ጥር 20 2008 ፤ ጦር ሀይሎች በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው
    ይከበራል፤፤ በዚሁ እለት ልጆቻቸው ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ፤፤
    በትናትናው እለት በስልክ ያነጋገርኩዋት የጄነራል ጃገማ ኬሎ
    የመጨረሻ ልጅ ምህረት ጃገማ የልደት በአሉ እርሳቸው ባሉበት
    ሞቅ ደመቅ ያለ ሊሆን እንደሚችል አጫውታኛለች፤፤ የ ሌተናት
    ጄኔራል ጃገማ ልጆች እንደ እድሜያቸው ቅደም ተከተል ይህን
    ይመስላል ፤፤ አቶ ሰለሞን ጃገማ ፤ ጸዳለ ጃገማ ፤ የትምወርቅ
    ጃገማ ፤ ሸዋዪ ጃገማ ፤ ብሩክታዊት ጃገማ ፤ እና ምህረት ጃገማ
    ናቸው ፤፤
    ሌ/ጀ/ጃገማ ኬሎ የተወለዱት በጥር 20 ቀን 1913 ዓ.ም ነው::
    ለቤተሰባቸው የመጨረሻ ልጅ ቢሆኑም ከሁሉም ጎበዝ ብርቱ ነበሩና
    አባታቸው የቤተሰቡ አለቃ አደረጓቸው:: አባታቸው ጃገማ ገና
    ሳይወለዱ ለወላጅ እናታቸው ‹‹ልጃችንን ስሙን ጃጋማ ብየዋለሁ››
    በማለት ነበር ጃገማ ብለው የጠሯቸው::
    “ጃገማ” የአባታቸው የፈረስ ስም ሲሆን በኦሮምኛ ሀይለኛ ማለት
    ነው:: ሌ/ጀ/ ጃገማ እስኪወለዱ ድረስ የፈረሳቸውን ስም
    የሚሰጡት ሁነኛ ልጅ አላገኙም ነበር::
    የኢጣሊያ ጦር የአድዋ ላይ ሽንፈቱን ሊወጣ ጦሩን እጅግ አግዝፎ
    ከ40 ዓመት ዝግጅት በኋላ በ1928 በድጋሚ ሀገራችንን ወርሮ
    ህዝብ ሲፈጅ ሀገሩን ሊታደግ ሁሉም በየፊናው ሲራወጥ በ15
    ዓመት ዕድሜ የአባታቸውን ጀብድ ሊደግሙ በዱር ዘምተው ጠላትን
    አርበድብደዋል። በዚህም “የበጋ መብረቅ” ተብለው ተሰይመዋል።
    ሌ/ጀ/ ጀገማ ፤ ከኢጣሊያ ጋር 5 ዓመት ሲዋጉ አንድም ቀን ድል
    ሆነው አያውቁም:: ጥይት ሲያልቅባቸው ብቻ ቦታውን ለቅቀው
    ይሄዳሉ:: ጥይት መልሶ ለማግኘት እንዴት ያደርጉ እንደነበር እንዲህ
    ብለዋል፡፡ “<>
    ሁለተኛ የዓለም ጦርነት ጊዜ እንግሊዝ ኢጣሊያን ከአፍሪካ
    እንድታስወጣ ተወሰነ:: ስለዚህ ወቅት ጃገማ ኬሎ እንዲህ
    ብለዋል…<>
    ሌ/ጀኔራል ጃገማ ኬሎ በአጼ ኃይለስላሴ ዘመን ከነበሩት ሌ/
    ጀኔራሎች መካከል በህይወት የሚገኙት ብቸኛው ጀኔራል ሲሆኑ አንድ
    ወንድና አምስት ሴት ልጆች፣ አምስት የልጅ ልጆችና አራት የልጅ
    ልጅ ልጆችን አፍርተዋል፡፡

  6. What do you mean opdo are trying to overthrow its elite its not right to say OPDO has the power to elect its regions leaders since when as we know Woyane elite`s work who gave this job for OPDO we know well about it . your information always important thanks .

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*