በኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮንቴይነር የተጫነ ሰው ስዊድን ተገኘ

ፖሊስ በሕገወጥ መንገድ ሰዎችን የሚያሸጋግሩ አሉ ብሎ ይጠረጥራል

Ethiopian Airlines 787 dreamliner የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን

Ethiopia Zare (ሰኞ የካቲት 28 ቀን 2008 ዓ.ም. Mar. 01, 2016)፡- ከአዲስ አበባ ሌሊት ተነስቶ ዛሬ ጠዋት በስዊድን መናገሻ ስቶክሆልም በሚገኘው የአርላንዳ አየር ማረፊያ ባረፈው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን የዕቃ ኮንቴይነር ውስጥ የተደበቀ የ27 ዓመት ዕድሜ ያለው አንድ ሰው መገኘቱን ፖሊስ ገለጸ። ይኸው ግለሰብ በስዊድን ጥገኝነት መጠየቁ ታውቋል። ፖሊስ በሕገወጥ መንገድ ሰዎች የሚያሸጋግሩ ወገኖች እንዳሉ ጥርጣሬ አለኝ፣ ጉዳዩን እያጣራኹ ነው አለ።

ሙሉውን አስነብበኝ …