ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደኦልትራፎርድ ዳግም ሊመለስ ነው

image

ክርስቲያኖ ሮናልዶ እንግሊዝ እና ፖርቱጋል ለዩሮ 2016 ለሚያደርገት የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ወደኦልትራፎርድ ሊመለስ ይችላል። የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር ሁለቱ ሃገራት ስለሚያደርጉት የወዳጅነት ጨዋታ ከፖርቱጋል አቻው ጋር ንግግር እያደረገም ይገኛል። በአሁኑ ጊዜ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዝውውር ወደእንግሊዝ እንደሚመጣ ማረፊያውም ኤልራፎርድ ሊሆን እንደሚችል በሰፊው እየተወራ ይገኛል። የፖርቱጋል እግር ኳስ ማህበር ምንጭ በሁለቱ ሃገራት መካከል ለወዳጅነት ጨዋታ ድርድር እየተደረገ እንደሚገኝ ሹክ ያለ ሲሆን፣ ድርድሩ የሚሳካ ከሆነም ከእንግሊዝ ሶስት የወዳጅነት ጨዋታዎች መካከል አንዱ በሆነው በዚህ ጨዋታ የቀድሞው የማንችሥተር ዩናይትድ ኮከቡ ሮናልዶ ወደእንግሊዝ መምጣት ለእግር ኳስ ማህበሩ የትኬት ሽያጭ ገቢ ከፍ ማለት ዓይነተኛ ምክኒያት ሊሆን ይችላል። በተያያዘም የሮይ ሆዲሰኑ ቡድን በሌሎች የወዳጅነት ጨዋታዎች የሌላኛውን የዓለም ኮከብና የባላንዶር አሸናፊ የሊዮኔል ሜሲውን አርጄንቲናን በዌምብሌይ የሚገጥምበት ሰፊ ዕድል አለ።

ምንጭ፦ ሚረር