ምላሽ ለተስፋዬ ገብረአብ፤ “የአባይ ፀሐዬ ጦርነት” በሚለው ላይ
ግርማ ካሳ

አቶ ተስፋዬ ገብረአብ በአንድ ወቅት የኢሕአዴግ ባለሥልጣን የነበሩ ሰው ናቸው። ጥሩ ፀሐፊ ናቸው። ከኦሮሞ ብሔረተኞች ጋር የቅርብ ግንኙነት አላቸው። አንድ ወቅት እንደውም የኦሮሞ ተማሪዎች ማኅህበር ላይ የክብር እንግዳ ሆኖ ቀርበው ነበር። በዚያን ወቅት “በሞጋሳ እኔም ኦሮሞ ነኝ” ብለው ነበር። ሞጋሳ አንድ ሰው “ኦሮሞ” ባይሆንም የኦሮሞን ባህልንና ቋንቋን ከተቀበለ፣ በኦሮሞ “ሽማግሌዎች” ፍቃድ “ኦሮሞ” የሚሆንብት ሥርዓት ነው (naturalized ኦሮሞነት)።