አባ ማቲያስ:- ከመሳሳም ይቅርታ ይቅደም!

·        ከካቶሊክ ጋር ያለን ልዩነት ጠባብ ነው(አባ ማቲያስ ሕዳር 2008)

·        ከቫቲካን ጋር የነበረንን የቀድሞ ፍቅር(?) እንመልሰዋለን(አባ ማቲያስ የካቲት 2008)

·         ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስትያንን የገዛ ቅኝ ገዥ ነው(አባ ማቲያስ ጥቅምት 2008)
·        ወራሪዋን ቫቲካንን ፍቅር : ልጆቻቸውን ቅኝ ገዥ— አባት ብሎ ዝም!!

(ዘአዲስ እንደፃፉት):- አባ ማቲያስ በዚህ ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ትግራይ ሄደው ጉብኝት ማድርጋቸው ይታወሳል:: አዲግራት ላይ የአዲግራቱ የካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ቦታ ላይከካቶሊክ ጋር ያለን ልዩነት ጠባብ ነውበማለት መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል:: http://www.addisadmassnews.com/images/Issue-826.pdf

ሀገራዊ ማህበራዊና ብሔራዊ በሆነ ጉዳይ ላይአንተ ኦርቶዶክስ : አንተ ካቶሊክመባባሉ ሳይኖር የሁሉም እምነት ተከታይ የሆነ ኢትዮጵያዊ በአንድነት መቆም እንዳለበት ግልጽ ነው:: “ኦርቶዶክስና ካቶሊክ መካከል ያለው ልዩነት ጠባብ ነውብሎ የማይመስል ነገር መናገሩ ( ያውም ከፓትርያርኩ አንደበት) ግን እጅግ የሚያስተዛዝብና ግምት ውስጥ የሚጥል ስህተት ነው:: የሆነው ሆኖ ይህን ባሉ በሶስተኛው ወር የካቶሊኳ ራስ ቫቲካን ደርሰው የበርካታ ኢትዮጵያውያንን አንጀት አቁስለው ተመልሰዋል::

 ፓትርያርኩ ቫቲካን መሄድ ነበረባቸውን?

በመሰረቱ: ቫቲካን ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ላይ እጅግ የመረረ ግፍ ፈጽማለች:: ፋሺስት ጣልያን ኢትዮጵያን ስትወር : የቫቲካን ጳጳሳት የመርዝ ጋዝ እየባረኩ ኢትዮጵያን ለመውረር የሚደረገው ጦርነት ቅዱስ ጦርነት እንደሆነ አውጀዋል:: የወርቅ መስቀላቸውን ሳይቀር ለጦርነቱ አዋጥተዋል:: የሙሶሎኒምና የግራዚያኒ ቀኝ እጅ የነበረው የቫቲካኑ ጳጳስ ባደባባይ ወረራውን ደግፎ መግለጫ ሰጥቷል::

(http://www.globalallianceforethiopia.org/italianinvasion.pdf)

ፋሺስት ጣልያን አንድ በዛ ጦርነት አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ገድላለች:: በሺዎች የሚቆጠሩ ካህናትን አቃጥላለች:: በውል የታወቁትን እንኳን ብንቆጥር ወደ 2 ቪህ አብያተ ክርስቲናትን አውድማለች:: ጣልያን ከመውረሯ በፊትም የጣልያን ሰላይ እየሆኑ ይሰሩ የነበሩት የቫቲካን መነኮሳት ነበሩ::

ቫቲካን ስለሰራችው ጥፋት ኢትዮጵያንን እና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያንን ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ስላልሆነች : ላለፉት አርባና ሃምሳ ዓመታት የቫቲካንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስትያናት ግንኙነት በጣም ቀዝቃዛ ነበር:: ቫቲካን ይቅርታ እስካልጠየቀች ድረስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን አባቶች ከቫቲካን ጋር አንድነት እንዳይኖር በመወሰናቸው የሁለቱ አብያተ ክርስትያናት ግንኙነት በጣም ቀዝቃዛ ነበር:: ( የአለቃ አያሌውመች ተለመደና ከተኩላ ዝምድናመጽሓፍን ይመልከቱ)

በተለይ አሁን በቅርቡ ለጨፍጫፊው ግራዚያኒ ጣልያን ውስጥ ሀውልት እንዲቆም ከተወሰነ በኋላና የቫቲካን ጳጳሳትም ይህን ጉዳይ የመደገፋቸው ዜና በመሰማቱ : በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ በማሰማታቸው የሃውልቱ ስራ ቆሟል:: እነዚሁ ኢትዮጵያውያን ቫቲካን ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያንን ይቅርታ እንድትጠይቅ ቢወተውቱም : ቫቲካን ካላት ንቀት የተነሳ ፈቃደኛ አልሆነችም:: የሙገርመው ግን ጀርመን ናዚዎች አይሁዶችን ሲጨፈጭፉ ዝም በማለቴ ( ባልሳተፍበትም) ይቅርታ ጠይቃለሁብላ አይሁዶችን ይቅርታ ጠይቃለች::

(https://www.gopetition.com/…/vatican-apology-for-ethiopian-…)

ራሷ የጨፈጨፈችውንና ያስጨፈጨፈችውን ኢትዮጵያውያንን ግን ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ባለመሆኗ : ቫቲካን ኢትዮጵያን ይቅርታ እስክትጠይቅ ድረስ ይፋዊ ግንኙነት እንዳይኖር በኢትዮጵያ በኩል ተወስኖ ነበር:: የአለቃ አያለውውን መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና ያነቧል::

አባ ማቲያስ ግን ያንን እግድ ጥሰው ቫቲካን ድረስ በመሄድእኛና ቫቲካን ድሮም ፍቅር ነን: የድሮውን ፍቅር እንመልሰዋለንበማለት የብዙ ኢትዮጵያውያንን ድካም መና አብልተውታል::

የአባ ማቲያስ ቫቲካን መሄድ እንግዳ ቢሆንም ብዙዎእዛው ሀገራቸው ላይ ሄደው ቫቲካን ለሰራችው በደል ይቅርታ ትጠይቅብለው ይናገራሉ ተብሎ ተጠብቆም ነበር:: በተገላቢጦሹ ግን አባ ማቲያስድሮም እኛና ቫቲካን ፍቅር ነበርን ወደፊትም ያንን ፍቅር እንመልሰዋለንብለው አረፉት::

የቀደመው የቫቲካንና የኦርቶዶክስ ፍቅር የቱ እንደሆነ አልገባኝም:: የዲዮስቆሮስ ይሆንን? ከጥንት ጀምሮ ቫቲካን የምትልካቸው ሚሺነሪዎች ሕዝብ ሲያጨፋጭፉ ነገር ሲተክሉ እንጂ ፍቅር መስርተው ሲሄዱ አይታወቅም:: እነ አልፎንሱ ሜንዴዝን መጥቀስ ይቻላል:: ቃል በቃልኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን ላይ ሁለት እሾክ ተክዬባት ሄድኩእስከማለት የደረሱ ናቸው:: ጸጋና ቅባትን ያስትውሷል:: ጂሴፔ ሳፔቶና አባ ማስያስም ኢትዮጵያን ለጋ ቅቤ ሲቀቡ አናቃቸውም:: በሁለቱም የጣልያን ጦርነት ወቅትም ቫቲካን የሰራችው ወንጀል እንጂ የፍቅር ስራ አይደለም:: (አቡነ ጎርጎርዮስ ////ታሪክ)

የኦርቶዶክስና የቫቲካን የቀደመ ፍቅር የቱ እንደሆን አይገባኝም:: ፓትርያርኩ እንደዛ ከሚሉቫቲካን አትፍታለችና ይቅርታ ትጠይቅ,ኢለውን ያባቶቻቸውን ቃል አጽንተው እሳቸውም ይሄን ቢያደርጉ ለነፍሳቸውም ለስጋቸውም ታሪክ ነበር:; ማኅበረ ቅዱሳንንቅኝ ገዥያለ አንደበት እውነተኛዋ ቅኝ ገዥን ምን ይላት ይሆን ብዬ ጠብቄም ነበር::

ምን ያደጋል ! አባታችን አገላበጡት