ፓትርያርክ ማትያስ:- ከፖፕ ፍራንሲስ ሊማሯቸው የሚችሏቸው ነገሮች
(ማርች 2/2016/ የካቲት 23/2008 ዓ.ም):- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ወደ ቫቲካን ጉዞ ማድረጋቸው እና ከሮማማው ፓፓ “ፖፕ ፍራንሲስ” ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው በመገናኛ ብዙኃን ተዘግቧል፡፡ ሲጨባበጡ፣ ትከሻ ለትከሻ ተሳስመው ሰላምታ ሲለዋወጡ፣ ፓትርያርካችን ለፖፕ ፍራንሲስ ማስታወሻ መስቀል እና መጽሐፍ ሲሰጡ ሁሉ አይተናል።
የሁለቱ መሪዎች ዋነኛ የመወያያ ርዕሰ ጉዳይ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው የክርስቲያኖች መከራ፣ ስደትና የቤተ ክርስቲያን ውድመት እንደሆነ ከፖፑ ንግግር መረዳት ይቻላል። “የክርስቲያኖች የሰማዕትነት ደም የክርስትና ዘር ነው” የሚለውን ታዋቂ ቃል አንስተው ፖፑ ማብራራታቸው ተዘግቧል። ዝርዝሩን መመልከት ለሚሻ ዜናው ወደተዘገበባቸው ሥፍራዎች ጎራ ማለት ይችላል።
ሁለቱም መሪዎች ከተሾሙ ብዙም አልቆዩም። ፓትርያርክ ማትያስ February 28/ 2013፤; ፖፕ ፍራንሲስ ደግሞ በቀናት ልዩነት March 13/ 2013 ነው የተሾሙት። ሁለቱም መሪዎች በአማኞቻቸው የሚታዩበትን ጠባይ በአጭር ጊዜ ለመቅረጽ የቻሉ ሆነዋል። ያሳዩት ጠባይ ግን ልክ እንደ ልብሳቸው እጅግ የተቃረነና የተለያየ ነው። ፓፓ ፍራንሲስ ልጆችን በማባለግ እና በሌሎችም አስነዋሪ ተግባራት ስሟ የጎደፈውን የካቶሊክን ቤተ ክርስቲያን በጥቂት ዓመታት ውስጥ ስሟን ለማደስና በዓለም ሕዝብ ዘንድ ያላትን ተቀባይነት እጅግ በላቀ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ችለዋል።
ፓፓው ከሠሯቸው ተግባራት መካከል አንዱ ለረዥም ዘመናት ተለያይተው የነበሩትን ኩባንና አሜሪካንን ለማስታረቅ ድልድዩን ያበጁትና ታሪክ የሠሩት እርሳቸው መሆናቸው ነው። ኮሚኒስቱን የኩባ አስተዳደር ከደመኛ “ኢምፔሪያሊስት ጠላቱ” ከአሜሪካን መንግሥት ጋር ለማግባባትና በሁለቱ ሕዝቦች መካከል የፈረሰውን የግማሽ ምዕት የግንኙነት መስመር ለመጠገን ችለዋል።
ከዚህም በላይ ፓፓው በዓለም አማኝም ኢ-አማኒም ሕዝብ ዘንድ ሞገስ ያሰጣቸው ለድሀውና ለዝቅተኛ ኑሮ ለሚኖረው ለመላው የዓለም ሕዝብ ያሳዩት ጥብቅና፤ ገንዘብ አምላኪውን የዘመናችንን ሉላዊ ሥርዓት በይፋ እየተቃወሙ ለአገሮች ኢኮኖሚያዊ ጤንነት ያሳዩት ወገንተኝነት ነው። ድህነትን እንደበሽታ ለሚጠየፉ ብዙ ቅንጡዎች እና ቅምጥሎች ትልቅ ትምህርት በሚሰጠው ተግባራቸው ከኦባማ ዋይት ሐውስ እና የአሜሪካ ኮንግረስ እስከ ደቡብ አሜሪካ የተለያዩ አገሮች ግድ የለሽ መንግሥታት ድረስ ምክራቸውን እና ተግሳጻቸውን አሰምተዋል።
የቅምጥል ኑሮን የሕይወታቸው መመሪያ በማድረግ ረገድ ከዓለማውያኑ የባሱት መንፈሳውያን የእምነት መሪዎች በሆኑበት በዚህ ዘመን ፖፕ ፍራንሲስ የቫቲካንን ወደር የለሽ የድሎት መኪናዎች ለመጠቀም አሻፈረኝ በማለት እና እዚህ ግቢ የማትባል የግል መኪናቸውን በመጠቀም በንግግራቸውም በግብራቸው ቅምጥልነትን አውግዘዋል።
ለጉብኝት በሑዱባቸው አገሮች በአጃቢ የተሸለሙ መኪኖቻቸወን በማቆም እና በመንገድ ላይ ከሚጠብቃቸው ሕዝብ ጋር በተለይም ከሕጻናት እና የተለያየ በሽታ ካለባቸው ሰዎች ጋር በመገናኘት፣ እንኳን ለመንካት ለማየት እጅግ የሚፈትን በሽታ ያለባቸውን ሰዎች ሳይጸየፉ በማቀፍና ርኅራኄ በማሳየት ብዙዎችን አስደምመዋል። ሌሎችንም የታዘብናቸውን ብዙ ተግባሮቻቸውን መጥቀስ ይቻላል። ለዚህ ፅሑፍ ሲባል በዚሁ እንግታውና የኛው ፓትርያርክ ሊሟሯቸው ስለሚችሏቸው ነገሮች እናንሣ።
መቸም አንድ የኦርቶዶክስን አባት ከካቶሊክ መሪ “ይህንን ተማር፣ ይህ መልካም የሆነ የኮቶሊኩ መሪ ተግባር ነው” ማለት ችግር ላይ ሊጥል የሚችል ነገር እንደሆነ ይታወቃል። “ካቶሊኮችን ያመሰግናሉ” የሚል የነገረ ሰሪ ጥላሸት ሊያስቀባም ይችላል። በቀድሞው ዘመን ቢሆንማ “ሰዎቹ ኮተሎኩ” ሊያሰኝም ይችል ነበር።
ይሁን እንጂ ቅ/ያሬድ ከዚያች ትል መውደቅንና መነሣትን ተምሮና ተገንዝቦ፣ ሕይወቱን አርቆ ለቤተ ክርስቲያናችን ዓይን እንደሆነ ሁሉ የሰው ልጅም በሥላሴ አርአያ ከተፈጠረ ከሌላው ሰው (አማኝም ሆነ የማያምን፤ ኦርቶዶክስም ሆነ ካቶሊክ) መማር መቻሉ ያስመሰግነዋል እንጂ አያስነቅፈውም። ከባዶ ግብዝነትም ያድነዋል።
ወደ ቀደመ ነገራችን ስንመለስ …. ከላይ እንዳየነው ፓትርያርክ ማትያስ ከፖፕ ፍራንሲስ በቀናት ልዩነት ነው የመሪነት መንበር የተቀበሉት። ነገር ግን በነዚህ 3 ዓመታት ምን ሠሩ ብለን ብንገመግም ከፀብና ከዓምባ ጓሮ፣ በአደባባይና በሚዲያ ከሚሰጡት አሸማቃቂ ንግግር ባለፈ እንዲሁም ከቅ/ሲኖዶስ አባላት በመራቅ ቤተ ክርስቲያንን ተደራጅተው ከሚዘርፉ ሰዎች ጋር ከመወዳጀት ሌላ መልካም ስም ያተረፉ አይመስለንም።
የካቶሊኩ ፓፓ ለድሆች ጠበቃ መሆናቸውን አይተናል። የኛዎቹም ለኢትዮጵያ ድሃ ሕዝብ ጠበቃ ሊሆኑ ይገባቸው ነበር። በኑሮ ውድነት፣ በአስተዳደር ብልሹነት፣ በስግብግበነት መሬቱን እና ቤቱን እየተዘረፈ ትዳሩ ለሚፈርሰው ወገናቸው ጠበቃ ሊሆኑ ይገባ ነበር። ጋሻ ጃግሬዎቻቸው እርስበእርስ በመሸላለምና የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ በገፍ በመዝረፍ በተጠመዱበት በዚህ ጊዜ “ኧረ ተዉ!!!” የሚል የአባት ተግሳጽ ሊያሰሙ ይገባ ነበር።
እንደ ካቶሊኩ ፓፓ አስታራቂ እና የተበተኑትን ሰብሳቢ መሆን ቢያቅታቸው የተሰበሰቡትን ለመበተን መትጋት ግን አይገባቸውም ነበር። በዚህ አንድ ዓመት በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የፈጸሙትና እየፈጸሙት ያለው ተግባር ብቻ ለታሪካቸው ትልቅ ጠባሳ እንደሚሆን ሊገነዘቡት በተገባ ነበር።
በመካከለኛው ምስራቅ ለሚገደሉ ክርስቲያኖች አዝነው ሮም ድረስ እንደሔዱት ሁሉ፣ በአገራቸው ለሚጠፋው ሕዝባቸው፤ በመንግሥት ወታደር ዕለት ከዕለት እየተገደለ በየጥሻው ለሚጣለው ወገናቸው፤ ማዕከላዊን ጨምሮ በየእስር ቤቱ በማሰቃያዎች ለሚንገላታው ወገናቸው ጠበቃ መሆን ይችሉ ነበር።
ድሃ አደጉንና ዕጓለ ማውታውን ለመሰብሰብ ከአበው ሌላ ማን ይመጣል። ቤተ ክህነቱ ከገባበት አስረሽ ምቺው ተላቆና የምንኩስና አሰረ ፍኖቱን ተከትሎ ከዚህ የመንደላቀቅና የመሽቀርቀር አዚም ሊገላገል፣ ለድሃውም ሊያዝን ይገባው ነበር። የካቶሊኩን ፓፓ ካነጋገሩ አይቀር ይህንን ይህንንም ከእርሳቸው ይማሩ። ፓትርያርካችን ሆይ! በእርስዎ ዘመን ቤተ ክርስቲያናችን ስሟና ታሪኳ ይገነባል ወይስ ይፈርሳል?
ቸር ወሬ ያሰማን
አሜን


We have a ferenji or western puppet regime in power in Ethiopia, and this “Patriarch” was imposed on Ethiopians by the western puppet regime TPLF, he is not the real one, the real Patriarch, His Holiness Patriarch Abune Merkorios, lives now in exile.
EOTC and Vatican are no friends, the latter is rather a criminal organization given all its crimes from child abuse to money laundering.
Millions of African catholics are therefore not happy about their church, and are converting either to traditional African religions or other religions.
The duty of a Patriarch of the EOTC would have been to be an alternative to the millions disappointed African catholics and to organize mass conversions in stadiums and other places, and in doing so lay the foundation for an African empire. That would have been the job of a real EOTC Patriarch at this point in time.
The EOTC and others were supposed to think and act in terms of Empire building.
http://cache4.asset-cache.net/gc/74094624-haile-selassie-i-emperor-of-ethiopia-attends-gettyimages.jpg?v=1&c=IWSAsset&k=2&d=GkZZ8bf5zL1ZiijUmxa7QSl7%2bLTY4UX4YP77%2fxALcrCsQwpSfiBCqx0BLt8D9TXiNx0EIHqarPna81b2ouAQhA%3d%3d
Picture above shows Haile Selassie at the foundation stone laying ceremony for an Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in Trinidad in 1966 G.C..
Matias “Patriarch” is not a real patriarch he is a cadre serving as a revolutionary democracy for the facist woyane regime inorder to destroy the Orthodox relgion and others.
PATRIARCH ALEN ENDE ?
KKKKKKKKKKK
Yehie ye Asterye weyim ye Amare asteyayet demo maan lakebn
Yabedu wushoch .