የባላገሩ ምርጥ አሸናፊ ዳዊት ፅጌ ሆኗል። እንኳን ደስ ያለህ! 2. ኢሳያስ ታምራት 3. ሜላት መንገሻ የባላገሩ ምርጥ የመጨረሻው ውድድር ዳዊት ፅጌ በሁለተኝነት ያቀረበው ሙዚቃ [youtube http://www.youtube.com/watch?v=XNMwIpBtRvo] ባላገሩ ምርጥ በነጠላ ውዝዋዜ ዘርፍ አሸናፊ ያሬድ ኬኔ ሆኗል። ባላገሩ ምርጥ በቡድን ውዝዋዜ ዘርፍ …

ድምጻዊ ዳዊት ጽጌ የባላገሩ ምርጥ አሸናፊ ሲሆን ኢሳያስ እና ሜላት 2ኛና 3ኛ ወጥተዋል Read more »

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ይህን ሰሞን እያየን ያለነው ጉዳይ አጅግ የሚገርም እና የለውጥ ሃይል ነን የሚሉ ኣማሳኞች ሳይቀሩ አየተራወጡ ያሉበት የዘረኝነት መነባነብ በኣገሪቱ ስር አንዳይሰድ ትውልዱ እንዳይበከል የሚያስፈራ ጉዳይ መሆኑ ውሎ ኣድርዋል፥፥የሚደርሱኝ መረጃዎች አንደሚጠቁሙት ዘረኝነትን ለማስፋፋት የተለያዩ ኣካላት ገንዘብ …

ዘረኝነት መድሃኒቱ ያልተገኘለት ትልቁ በሽታ እና የበታችነት አባዜ (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

በማይጨው ከተማ ያሉት 11 ሉኳንዳ ቤቶች ለከተማዋ ኑዋሪ የሚያቀርቡት ስጋ ለማሳረድ ወደ ማይጨው ቄራ የተዘጋጁት ከብቶች ይዘው እንዲመለሱ ተደርገዋል። የመታገዱ ምክንያ በቄራው የከብቶች ምርመራ የሚያካሂድ ዶክተር “ለእርዱ የሚበቃ ውሃ ስለ ሌለ ከብቶቻቹ ይዛቹ ተመለሱ” የሚል ትእዛዝ መስጠቱን ተከትሎ መሆኑ ባለሉኳንዳዎች ገልፀዋል። በመስቀል በዓል የማጨው ህዝብ የሚቀመስ ስጋ ማግኘት ኣልቻለም። በውሃ እጥረት ምክንያት ማይጨው በኣለ መስቀሉ […]

1437ኛው የኢድ አል አድኻ ( አረፋ) በአል በአዲስ አበባ  ስታዲየም ሲከበር ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ  አስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት በሽብር ወንጀል ተከሰው ከተፈረደባቸው የሙስሊሙ ማህበረሰብ ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት መካከል  ስድስቱ በቅርቡ የተለቀቁት በእነርሱ ጥያቄና ጥረት አንደሆነ፤ ጥያቄአቸው ምላሽ በማግኘቱና ጥረታቸው በመሳካቱ መደሰታቸውን ገልጸው ለመንግሥት ምሥጋና ማቅረባቸውን የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ዘጋቢ ከስፍራው ባስተላላፈው […]

The post ይቅርታ- የወያኔ ካርታ (ይገረም አለሙ) appeared first on ሳተናው (Satenaw)-Latest Ethiopian News & Breaking News.

የመጽሐፉ ርእስ፣                     አብዮቱና ትዝታዬ ደራሲ፣                                   ፍሥሓ ደስታ (ኮ/ል) አሳታሚ፣                               ፀሐይ አሳታሚ ድርጅት የገጽ ብዛት፣                            598 ገጾች ዋጋ፣                                      $44.95 (ቅኝት ክንፉ አሰፋ) ፀሐይ አሳታሚ ድርጅት ከዚህ ቀደም ሁለት የአብዮቱ መጽሃፍቶችን አበርክቶልናል። የኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያም – “ትግላችን” እና ሻምበል ፍቅረ …

አብዮቱና ትዝታዬ (ኮ/ል ፍሥሓ ደስታ)-አዲስ መጽሃፍ – አዲስ ምስጢር (ቅኝት ክንፉ አሰፋ) Read more »

በኦሮሚያ ክልል በምትገኘው አዳማ ከተማ ማክሰኞ ነሃሴ 26/2007 በተጻፈው የግራፊቲ ፅሁፍ ተከትሎ የከተማዋ ደህንነት ሃይሎች እና የኦሮሚያ ፖሊሶች ሙስሊሞችን እያሰሩ እና እያንገላቱ መሆናቸው ታውቋል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከደህንነት ሃይሎች ጋር በመቀናጀት በአዳማ ከተማ አሰሳውን በማጠናከር ሙስሊሙን እያሸበሩ ሲሆን ይፈለጋሉ በተባሉት …

በአዳማ ከተማ ንፁሃን ሙስሊሞችን የማሰር ዘመቻው ተጠናክሮ ቀጥሏል:: Read more »

ፖፕ አቡነ ቴዎድሮስ፣ የደመራ በዓልን በመስቀል ዐደባባይ ያከብራሉ አክሱም ጽዮንን፣ ጎንደርን፣ ላሊበላንና የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ይጎበኛሉ የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሃይማኖት አባቶች፣ በሃይማኖታዊ ጉዳዮችና በማኅበራዊ ግንኙነቶች ዙሪያ በአዲስ አበባ …

የግብጽ እና የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ሲኖዶሶች በዝግ ይመክራሉ Read more »

ኦሮሚፋ በቢቢሲ ስርጭት አድማስ እንዲያገኝ የተጀመረው ዘመቻ የሁላችንም የጋራ ጉዳይ እንጂ ከዜጎቻችን መካከል ለአንዱ የኦሮሞ ማኀበረሰብ አሊያም ደጋፊ ብቻ ተብሎ የሚተው አይመስለኝም፤ መሆንም የለበትም፡፡ ምክንያቱም በዚህ አንዱ ብቻ ተጠቃሚ ሌላው ዝም ብሎ ለሌላው ሲል በወገናዊነት ድጋፍ ያደረገ ያስመስለዋል፡፡ ቢቢሲ በኦሮሚፋ …

BBC በኦሮሚፋም ስርጭት እንዲጀምር የሚደረገው ዘመቻ ሊደገፍና ሊበረታታ ይገባዋል:: Read more »

• ኢቢሲ፣ ይሄን ዘገባ ሰሞኑን ያሰራጨው የት ከርሞ ነው? 1. ወጪው ከ1 ቢ. ብር በታች ነው የተባለው ግንባታ፣ ከ5 ቢ. ብር በላይ ፈጅቶም አላለቀም። 2. ቢበዛ በ3 ዓመት ውስጥ ግንባታው ይጠናቀቃል የተባለው ግድብ፣ 10 ዓመት አልበቃውም። 3. ግድቡ እየተጓተተ ወጪው …

ዘረፋ እና ፕሮፓጋንዳ – “ለዓመታት የተጓተተ ዘገባ” – ‘የተንዳሆ ግድብ ለዓመታት ተጓተተ” የሚለው የኢቢሲ ዘገባ… Read more »

  click here for pdf
ክፍል አንድ

በዚህ ዘመን በተደጋጋሚ ከሚነሡ መንፈሳውያን ጥቄዎች መካከል አንዱ የጥምቀትና አጥማቂዎች ጉዳይ ነው፡፡ ጥምቀት(የክርስትና ጥምቀትን አይመለከትም) በብሉይና በሐዲስ ኪዳን ምእመናን ፈውሰ ሥጋ ፈውሰ ነፍስ እንዲያገኙባቸው ከእግዚአብሔር ከተሰጡ ጸጋዎች አንዱ ነው፡፡(2ኛ ነገሥት 5፤ ዮሐ. 5፣ዮሐ. 9)፡፡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክም ውስጥ በልዩ ልዩ ገድላተ ቅዱሳን ላይ እንደምናነበው በጠበል ሕዝቡን ሲፈውስ ኖሯል፡፡ ሕዝብ ፈውስ የሚያገኝባቸው እንደ ሰሊሆምና እንደ ቤተ ሳይዳ የታወቁ የቃል ኪዳን ቦታዎችም ነበሩ፡፡
አሁን በያዝነው ዘመን አያሌ ‹አጥማቂ> የሚባሉ ሰዎች ተነሥተዋል፡፡ ክብራቸውን የሚገልጥ ማስታወቂያ ያስነግራሉ፣ መቁጠሪያ ይሸጣሉ፣ ቅባት ይቀባሉ፣ አዳራሽ ከፍተው ወይም ሕዝብ በሜዳ ሰብስበው እንፈውሳለን ይላሉ፤ ሰይጣን ተናገረ የሚባለውን በካሴት ቀድተው ይሸጣሉ፡፡ ከዚህ ቀጥዬ በማቀርባቸው አሥር ምክንያቶች እነዚህን ሐሳውያን መቀበል የለብንም ብዬ አምናለሁ፡፡

1.      በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ገዳማዊ ሕይወት፣ ክህነታዊ ሕይወት፣ የጸሎት ሕይወት ወይም ሌላ አንዳች ተጋድሎ ሳይኖረው ማጥመቅ ብቻ ሥራው የነበረ ክርስቲያን የለም፡፡ ሀብተ ፈውስ የተሰጣቸው አባቶችና እናቶች የሌላው መንፈሳዊ ሕይወታቸው ውጤት ወይም ነጸብራቅ ነበር እንጂ ሥራቸው እየዞሩ ማጥመቅ አልነበረም፡፡ የሐዋርያት ሥራን ብናነብ ሐዋርያት ለወንጌል አገልግሎት ሲሠማሩ በአንድ በኩል አሕዛብን ወደ ክርስቶስ ለመጥራት በሌላ በኩል የአንደበት ትምህርታቸውን በእጃቸው ተአምር ለማጽናት  ተአምራትን ያደርጉ ነበር እንጂ በአንድ ከተማ ውስጥ ሲያጠመቁ ውለው ያደሩበት፣ ወይም ከወንጌል አገልግሎት ተለይተው አጥማቂ ብቻ የሆኑበት፣ ወይም ደግሞ በዚህ ቦታ ፈውስ እንሰጣለንና ተሰብሰቡ ብለው ያስነገሩበት አንድም ማስረጃ የለም፡፡ በገድለ ቅዱሳንም ቅዱሳን ጸጋ እግዚአብሔር ሲያድርባቸው፣ ሥጋቸውንና ሰይጣንን ድል ሲነሡ፣ በክርስትናቸው ሲበስሉ ተአምራት ይከተሏቸዋል እንጂ እንዲሁ ማጥመቅና መፈወስ ብቻ ሕይወቱ የነበረ ቅዱስ የለም፡፡ ሰው ያለ ተጋድሎ እንዴት ጸጋ ያገኛል፡፡ በአሁኑ ዘመን ግን ከተራ ሰዎች የተለየ መንፈሳዊ ሕይወት የሌላቸው ሁሉ እየተነሡ አጥማቂ ሊሆኑ የቻሉበት አሳማኝ ምክንያት የለም፡፡
2.     በገድለ ቅዱሳን ውስጥ ቅዱሳን በገዳማዊ ሕይወት፣ በሰማዕትነት፣ በክህነታዊ አገልግሎት ሲሠማሩ እግዚአብሔር ምእመናንን ለመጥቀም ወይም ክብረ ቅዱሳንን ለመግለጥ በእነርሱ ላይ ተአምራትን ያደርጋል፡፡ እነርሱ ግን ይህ ክብር እንዳይገለጥባቸው ሲሸሹ፣ እኔ አላደረግኩም ሲሉ ወይም ስለራሳቸው ደካማነት ሲነገሩ እናያለን እንጂ ‹ኑ እንፈውሳችኋላን› ብለው ዐዋጅ ሲናገሩ አይተንም፣ አንብበንም አናውቅም፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከአባ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ወጥተው ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ  ገዳም የሄዱበት ዋናው ምክንያት በገዳሙ እያሉ በፈወሱት አንድ በሽተኛ ምክንያት ስማቸው ከፍ በማለቱ፣ ብዙ ሰዎችም በመሰብሰባቸው የተነሣ ነው፡፡ ታላቁ አባት መቃርዮስ ገዳሙን ትቶ ወደ አንዲት መንደር መጥቶ የኖረው በገዳሙ ክብሩ በመገለጡና ተአምራቱ በመታየታቸው ከከንቱ ውዳሴ ለማምለጥ ነበር፡፡ ስምዖን ጫማ ሰፊው አካባቢውን ትቶ የጠፋው ተአምር አድራጊነቱ በመታወቁ ምክንያት ነበር፡፡ አሁን ግን ከዚህ በተቃራኒው ሰዎች እናጠምቃለን፣እንፈውሳለን ብለው ማስታወቂያ የሚያስነግሩበት፣ ካሴት የሚሸጡበት፣ ፖስተር የሚሰቅሉበት ዘመን ነው፡፡
3.      ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስ ማን እንደሆነ፣ ድንግል ማርያም ማን እንደሆነች፣ ቅዱሳን መላእክት ማን እንደሆኑ ሌሎቹም ቅዱሳን ማን እንደሆኑ ጠንቅቃ ታውቃለች፡፡ የእግዚአብሔርን ክብር ለሰዎች ሰጥታ አታውቅም፡፡ ቅዱሳንን ከፈጣሪ አስበልጣ አታወቅም፡፡ የቅዱሳን መገኛና መሠረት በባሕርዩ ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር መሆኑን ታምናለች፣ታስተምርማለች፡፡ ለእግዚአብሔር የማይቻል ለቅዱሳን ይቻላል፣ በእግዚአብሔር የማይሠራ በቅዱሳን ይሠራል ብላ አታምንም፣ አታስተምርም፡፡ በዘመኑ አጥማቂዎች ዘንድ የምናየው ግን ከዚህ በተቃራኒው ነው፡፡ በክርስቶስ ስም የማይወጣው ሰይጣን የቅዱስ ሚካኤልን ስም ሲጠሩበት ይወጣል፡፡ በክርስቶስ ስም የሚያሾፍ ሰይጣን የድንግል ማርያምን ስም ሲጠሩበት ተቃጠልኩ ይላል፡፡  ይኼ ፈጽሞ ክህደት ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያንም ትምህርት አይደለም፡፡ ‹‹በስመ ሥላሴ እቀጠቅጥ ከይሴ›› ብላ ያስተማረች ቤተ ክርስቲያን ላይ ‹‹በክርስቶስ ስም አንወጣም፣ በማርያም ስም ግን እንወጣለን›› እያለ አጋንንት ወጣ የሚል ትምህርት ማስፋፋት ክህደት ነው፡፡
4.     መቁጠሪያ በቤተ ክርስቲያናችን ለጸሎት መቀስቀሻና ማስታኮቻ የሚውል ነው፡፡ ምእመናን እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ፣ በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ፣ ኪርኤ አላይሶን የተባሉትን የምሕላ ጸሎቶች በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የተመደበላቸውን ቁጥር ሳይስቱ እንዲጸልዩ የተሠራ ሥርዓት ነው፡፡ በጸሎት ጊዜ ዝንጋኤ እንዳይገጥማቸው ኅሊናቸውን ለመሰብሰብም ይረዳል፡፡ አንድ ቅዱስ ለብዙ ዘመን የጸለየበት መቁጠሪያ፣ የተደገፈበት መቋሚያ፣ የቆመበት ምድር፣ የለበሰው ልብስ፣ የተጠቀመበት መጽሐፍ ተአምራት ቢያደርግ አይገርምም፡፡ ቅዱሳን የነፍሳቸው ቅድስና ለሥጋቸው፣ የሥጋቸውም ለልብሳቸው፣ የልብሳቸው ለጥላቸው ተርፎ አይተን እናውቃለንና(የሐዋ. 5፣12-17፤ 19፣ 11-12)ከዚህ ውጭ ግን የሚሸጥ መቁጠሪያ ሰይጣን የሚያስወጣበት፣ ሰው ራሱን በመቁጠሪያ ስለደበደበ ከዲያብሎስ እሥራት የሚፈታበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ሰይጣን በጾምና በጸሎት እንጂ በመቁጠሪያ ድብደባ አይለቅም(ማቴ.17፣21)፡፡ ያ መቁጠሪያ ተአምር የሚሠራ ቢሆን እንኳን አንድ ቅዱስ የተጋደለበት፣ ከዚያ ቅዱስም በረከት ያተረፈ መሆን አለበት፡፡ ልክ የቅዱስ ጳውሎስ የጨርቁ እራፊ ይፈውስ እንደነበረው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክም የትኛውም አባት መቁጠሪያ ሲያድልና በመቁጠሪያ ሰይጣን ታወጣላችሁ ብሎ ሲያስተምር አልታየም፡፡
5.      ጌታችን በሺዎች የሚቆጠር ሕዝብ አስተምሯል፡፡ በጌንሳሬጥ ምድር አምስት ሺ(ማቴ 1413-21)፣ በገሊላ ባሕር አጠገብ አራት ሺ(ማቴ 15፣32-39)፣ ይህ ሁሉ ሕዝብ የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት አይቶ ይኼድ ነበር እንጂ ሰይጣን አድሮበት በአንድ ጊዜ የጅምላ ጩኸት ሲጮህ ታይቶ አይታወቅም፡፡ የተወሰኑ ሰዎች ግን እየቀረቡ ፈውሰ ሥጋ ፈውሰ ነፍስ አግኝተዋል፡፡ በዚህ ጊዜም ቢሆን መድኃኒት ያደረገብሽ፣ ድግምት ያስደገመብህ፣ መተት ያስመተተብህ እገሌ ነው የሚል ሰይጣን አልተሰማም፡፡ ዛሬ ግን በአንድ ቦታ ለጥምቀት የሚሰበሰቡ ሰዎች አብዛኞቹ ይጮኻሉ፡፡ ሁሉም በሰይጣን ተይዘዋል ይባላሉ፣ ሁሉም ድግምት፣ መተት፣ መድኃኒት፣ ጥንቆላ እንደተደረገባቸው ይነገራቸዋል፡፡ ሰይጣንን አምነው ከባሎቻቸው፣ ከሚስቶቻቸው፣ ከእኅት ወንድሞቻቸው፣ ከጎረቤቶቻች፣ ከሥራ ባልደረቦቻቸው ይጣላሉ፡፡ ከባቴ አበሳነትን ፈጽሞ የረሳ፣ ከፍቅር ይልቅ ጠላትነትን ለማስፈን የመጣ፣ ሰዎች እግዚአብሔርን አምነው ከመፋቀር ይልቅ ሰይጣንን አምነው እንዲጣሉ የሚያደርግ የሰይጣን አሠራር ነው፡፡ ለመሆኑ ይህንን ሁሉ ሕዝብ ሰይጣን ሲቆጣጠረው ክርስቶስ የለምን? የተጠመቅነው የልጅነት ጥምቀት፣ የቆረብነውስ ቁርባን አይሠራምን? ገና ወደ ክርስትና ያልመጡ የገሊላ ክርስቲያኖች እንኳን በጩኸት አልተደበላለቁም እንኳን እኛ በክርስቶስ ክርስቲያን በወልድ ውሉድ የተባልነው፡፡ ይህ አሠራር የክርስቶስን ነገረ ድኅነት የሚፃረርና ከማዳን ሥራውም የወጣ ነው፡፡ ከክርስቶስ ክብርና ኃይል ይልቅ የሰይጣንን ኃይል ለማሳየት የሚሠራም ነው፡፡  
6.     ለመሆኑ ስመ እግዚአብሔርን የሚጠራ ሁሉ ትክክለኛ ነውን? አንዳንድ ምእመናን እንዲህ ይላሉ ‹እግዚአብሔርን ይጠራሉ፣ እመቤታችንንም ያከብራሉ››፡፡ ልክ ነው ሰይጣን ለአመሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅሳል ይባላል፡፡ ሰይጣን ምንም እንኳ የሐሰት አባቷ ቢሆንም (ዮሐ. 8፣44) ሙሉ ውሸት ግን አይናገርም፡፡ በከፊል እንጂ፡፡ ሔዋንን ‹ንግሥተ ሰማይ ወምድር› ሲላት ከፍሎ ነው የዋሻት፡፡ ንግሥተ ምድር ናት፤ ንግሥተ ሰማይ ግን አልነበረቺም፡፡ በወንጌል ውስጥ አጋንንት ስመ እግዚአብሔርን ጠርተው ያውቃሉ፡፡ ሰይጣን ጌታን ሲፈትነው ከቅዱሳት መጻሕፍት ጠቅሶ ነው(ማቴ 4)፤ ጌታችን በጌርጌሴኖን ያገኛቸው አጋንንት ያደሩባቸው ሰዎች ‹የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ› ብለው ነበር የተናገሩት፡፡ ንግግራቸው ልክ ነው፡፡ እነርሱ ግን አጋንንት ናቸው፡፡ ጌታም አስወጣቸው እንጂ ማን ድግምት እንዳደረገባቸው አላናዘዛቸውም፡፡ በሌላ ቦታም በምኩራብ ሲያስተምር አንድ ሰይጣን ያደረበትን ሰው አመጡለት፡፡ ሰይጣኑም ‹‹የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ‹ ብሎ ነበር የጠራው፡፡ ጌታ ግን ‹ዝም ብለህ ወጣ› አለው እንጂ መድኃኒት ማን እንዳደረገ ተናገር አላለውም(ማር. 1፣21-28)፡፡ የናዝሬቱ ኢየሱስ ስላለውም ሰይጣንነቱን አልቀየረውም፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ሲያስተምር ፊልጵስዩስ የተባለ ከተማ ደረሰ፡፡ በዚያም አንዲት በርኩስ መንፈስ የተያዘች ሴት እየተከተለቺው ‹‹የመዳንን መንገድ የሚነግሯችሁ እነዚህ ሰዎች የልዑል አምላክ ባሪያዎች ናቸው›› አለች፡፡ ሴትዮዋ የተናገረቺው ምንም ስሕተት የለውም፡፡ እነ ቅዱስ ጳውሎስ የመዳንን መንገድ ያስተምራሉ፡፡ የልዑል አምላክ ባሪያዎችም ናቸው፡፡ ይህ ትክክል ስለሆነ ግን ቅዱስ ጳውሎስ ዝም አላለም፡፡ መንፈሱን አስወጣው እንጂ(የሐዋ.16፣16-18)፡፡ እነዚህ ሁሉ የሚነግሩን አንድ ሰው ስመ እግዚአብሔርን ወይም ስመ ቅዱሳንን ስለጠራ ብቻ ትክክል መሆኑን እንደማያሳይ ነው፡፡ እርስ በርሱ የማይጣረስ ርቱዕ የሆነ እምነትም ያስፈልገዋል፡፡ ርቱዕ የሆነ ሕይወትም ያሻዋል፡፡ በክርስትና አንድ ሰው መንገዱ ትክክል ሳይሆን ውጤቱ ትክክል ሊሆን አይችልም፡፡ ያለ ትክክለኛ እምነት፣ ያለ ትክክለኛም መንፈሳዊ ሕይወት ትክክለኛ ተአምራት ሊኖረው አይችልም፡፡ በሲኦል በኩል ወደ ገነት ሊገባ አይችልምና፡፡  
7.     ተአምራት ማድረግ ብቻውን የቅድስና ማሳያ አይደለም፡፡ ተአምራት ከመንፈሳዊ ሕይወት ብቃት ሲመነጩ እንጂ፡፡ ተአምር ከመንፈሳዊ ሕይወት ብቃት የመጣ ሲሆን ‹ስም በመንግሥተ ሰማያት በመጻፉ እንጂ በድንቅ ነገር ማንም ደስ አይለውም››(ሉቃ. 10፣ 17-20)፡፡ ተአምራትን ሲከተሉ መኖርም የአሕዛብነት ምልክት እንጂ የክርስትና ምልክት አይደለም(ማቴ. 12፣ 39)፡፡ የክርስትና ዋና መሠረቱ ክርስቲያናዊ ትምህርት፣ ክርስቲያናዊ እምነትና ክርስቲያናዊ ሕይወት ናቸው፡፡ አንዳንዶች በማርቆስ ወንጌል መጨረሻ ላይ(ማር 16) ‹‹ያመኑት እነዚህ ምልክቶች ይከተሏቸዋል›› የሚለውን ይጠቅሳሉ፡፡ እዚህ ላይ ያመኑት የተባሉት ‹የበቁት› ማለት ነው፡፡ ያማ ባይሆን ኖሮ ሁላችንም ተአምር ስናደርግ መኖራችን ነበር፡፡ አምነናልና፡፡ ደግሞም ያመኑት የሚለው ለሁላችንም ይሠራል ካልን እስኪ መርዝ ጠጥተን ምንም ሳንሆን ፣እባብም ጨብጠን ስንተርፍ እንየው፡፡ ይህ ሁሉ ግን በእመነት ለበሰሉ የሚቻል ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራም በሐዋርያት እጅ ያመኑት ሁሉ ተአምር ሲሠሩ አናይም፡፡ በሐዋርያት ሥራ ድንቅ ሲሠሩ የምናያቸው ክርስቲያኖችም በጸሎት የተጉ፣ በሐዋርያነት አገልግሎት ሰማዕትነት የከፈሉ፣ በገድል የተቀጠቀጡ ናቸው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ራሱ ሕይወቱ በተአምራት ከመገለጡ በፊት በሱባኤ የተወሰነ ነበረ(የሐዋ. 13፣ 1-3) የዛሬ አጥማቂዎች ግን ማጥመቅ ፕሮፌሽናቸው እንጂ የመንፈሳዊ ሕይወታቸው መገለጫ አይደለም፡፡ እንዲህ ባለው ገዳም በገድል የኖሩ፣ እንዲህ ያለ መሥዋዕትነት ለክርስትና የከፈሉ ወይም ለምእመናን አርአያ የሚሆን እንዲህ ያለ መንፈሳዊ ሕይወት የነበራቸው ናቸው ተብሎ የማይመሰከርላቸው ራሳቸውን በራሳቸው የሾሙ ናቸው፡፡
8.     የሰይጣን ምትሐትም አለ፡፡ የሙሴ ጸጋና ሕይወት ድል እንዲሆኑ ባያደርጋቸው ኖሮ የፈርዖን ጠንቋዮች ብዙ አስደናቂ ነገር ሠርተው ነበር(ዘጸ. 7፣8- 13)፡፡ በዘመነ ሳዖል የነበረቺው ሟርተኛም የሙታንን መንፈሶች ትጠራ ነበር(1ኛ ነገሥት. 28፣ 8-24)፡፡ አይሁድም አጋንንትን ያወጡ ነበር(የሐዋ. 19፣13)፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም የሐሳዊ መሲሕን አመጣጥ ሲያስተምረን ‹‹የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች፣ በሐሰተኞች ድንቆችም በዓመጽም ማታለል ሁሉ እንደ ሰይጣን አሠራር ነው›› ይላል (1ኛ ተሰ. 2፣9)፡፡ ይህም  ከመንፈሳዊ ብቃት የማይመጣ ተአምር፣ ድንቅና ምልክት ምንጩ ከሰይጣን እንደሆነ ይጠቁመናል፡፡ ዛሬ በእነዚህ ይህንን ያህል የምንታለል ከሆነ ነገ ሐሳዊ መሲሕ ከዚህ የሚበልጡ አስደናቂ ተአምራትን ሲያደርግ ጨልጠን ገርኝተን መከተላችን የማይቀር ነው፡፡ ‹‹የተመረጡትን እንኳን እስኪያስት ድረስ›› ተብሏልና፡፡
9.      ምሥጢረ ቀንዲል መሠረቱን መጽሐፍ ቅዱስ ያደረገ(ያዕቆብ. 5፣13) ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ ነው፡፡ የሚፈጸመው በካህናት ሲሆን የራሱ የሆነ የጸሎትና የመቀባት ሥርዓት አለው፡፡ ለዚህም መጽሐፈ ምሥጢረ ቀንዲልን ማንበብ ይጠቅማል፡፡ አሁን የምናየው ግን በጀሪካል ቅባት ይዞ ማከፋፈል፣ ምእመናን ከአጥማቂዎች ‹ቅብዐ ቅዱስ› ወስደው እንዲጠጡና እንዲቀቡ ማድረግ፣ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያልነበረ፣ በምሥጢረ ቀንዲል ያልተፈቀደና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንም ውስጥ የሌለ ነው፡፡ አንዳንድ አጥማቂዎችም ‹‹ከኢየሩሳሌም የመጣ ነው›› ይላሉ፡፡ ከኢየሩሳሌም የሚመጣ የተለየ ቅባት የለም፡፡ አንድን ቅባት ቅዱስ የሚያደርገው ጸሎቱና ሥርዓቱ አንጂ የተሠራበት ከተማ አይደለም፡፡ ኢየሩሳሌም ውስጥ ግሪክ ኦርቶዶክሶች፣ ካቶሊኮች፣ የይሖዋ ምስክሮች፣ ፕሮቴስታንቶች፣ ሌሎችም አሉ፡፡ ከኢየሩሳሌም የመጣ ማለት ከየት የመጣ ነው? ምእመናን ለኢየሩሳሌም በጎ ኅሊና ስላላቸው ‹‹ከኢየሩሳሌም ተባርኮ የመጣ ›› ይባላል፡፡ ማን ባረከው? ብሎ የሚጠይቅ የለም፡፡
10.    ከአክባሪው ይልቅ ከባሪው፣ከሰጭው ይልቅ ተቀባዩ፣ከጌታው ይልቅ አገልጋዩ የሚከብርበት ሥራ የእግዚአብሔር አይደለም፡፡ መንፈሳዊ አገልግሎት ዓላማው እግዚአብሔርን ማክበር፣ አሕዛብም እግዚአብሔርን እንዲያውቁ ማድረግ፣ ከመንገድ ጠራጊውም ይልቅ መንገዱን እንዲያገኙት ማስቻል ነው፡፡ አሁን የምናያቸው ‹አጥማቂዎች› እና ‹ተአምራት› አድራጊዎች ግን ራሳቸውን የሚያከብሩ፣ እግዚአብሔርን የሚሸፍኑ፣ ሕዝቡ ቅዳሴና ትምህርት እየተወ እነርሱን በየሜዳው እንዲከተል የሚደርጉ፣ ሕዝቡ ንስሐ መግባት፣ ሥጋወ ደሙ ከመቀበል ይልቅ የእነርሱ አድናቂና ካዳሚ እንዲሆን የሚስቡ ናቸው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ስለ ራሱ ሲናገር ‹እኔ ዝቅ ዝቅ ልል፣ እርሱም ከፍ ከፍ ሊል ይገባል›. ነበር ያለው (ዮሐ. 3፣29)፡፡ ለእነ ቅዱስ ጳውሎስም በልስጥራ እግሩ የሰለለውን ሰው በፈወሰው ጊዜ ሕዝቡ ተደንቆ  እንደ አምላክ ሊሠዉላቸው ወድደው ነበር፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ግን ‹እንደ እናንተ ሰዎች ነን›. እያለ ለምኖ አስተዋቸው፡፡ ሕዝቡንም ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መለሳቸው፤ የእግዚአብሔርም ስም እንዲከብር አደረገ(የሐዋ 14፣8-18)፡፡
በእነዚህና ቤሎችም ምክንያቶች በዘመናችን የተነሡትን ‹አጥማቂ ነን ብለው ማስታወቂያ የሚያስነግሩትን፣ መቁጠሪያና ቅብዐ ቅዱስ የሚያከፋፍሉትን፣ በየሜዳው ሕዝብ ሰብስበው ምትሐት የሚሠሩትን ሰዎች መቀበል አለብን ብዬ አላምንም፡፡ ቤተ ክርስቲያን የጸጋው ግምጃ ቤት ናት፡፡ በጸሎት የሚተጉ፣በእምነት ሕይወት ያሉ ክርስቲያኖች በየምሕረት አደባባዮች ምሕረትን ያገኛሉ፡፡ በቤተ ሳይዳ መልአኩ ውኃውን ይባርከው እንደነበር ሁሉ የጠበል ቦታዎችን ራሱ እግዚአብሔር በቃል ኪዳኑ ባርኳቸዋል፡፡ የተለየ አጥማቂ አያስፈልገቸውም፡፡ የክህነት አገልግሎት የሚሰጥ ሰው እንጂ፡፡ ደግሞም ሁሉም ሕመም መዳን የለበትም፡፡ ደዌ ዘእሴት(ለበጎ የሚሰጥ ሕመም) አለ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ የብዙዎችን ሰይጣን እያስወጣ እርሱን ግን የሚጎስመው ሰይጣን ነበረው፡፡ ጌታን ሲለምንም ‹‹ተወው›› ነው የተባለው(2ኛቆሮ. 12፣ 7)፡፡ የዛሬ አጥማቂ ነን ባዮች ግን ሁሉም ሕመም ይድናል ይላሉ፡፡ ለቅዱስ ጳውሎስ ያልተቻለ ተቻላቸውን? ከሐዋርያት አንዱ የነገረው ያዕቆብ እግረ በሽተኛ ነበር(ዜና ሐዋርያት፣ በእንተ ያዕቆብ ሐዋርያ)፤ እርሱ ግን ብዙዎችን ይፈውስ ነበር፡፡ ከእግዚአብሔር ምሕረት አገኘን የምንለውም ስንፈወስ ብቻ መሆን የለበትም፤ የምንታገሥበት ዐቅም ስናገኝም ጭምር እንጂ፡፡ ልመናችንም ለፈውስ ብቻ ሳይሆን ለመታገሥ ዐቅም እንዲሰጠን መሆንም አለበት፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን ለመፈውስ የሚችል ቢሆንም ሁሉንም ግን አይፈውስም፡፡ ለበረከት፣ ለተግሣጽ፣ ከከንቱ ውዳሴና ከትዕቢት ለመከላከል የሚፈቅደው ደዌም አለ፡፡ ያዕቆብ ወልደ ይስሐቅ ይህ ተሰጥቶት ነበር(ዘፍ. 32፣31)፡፡ ክርስትና በመንፈሳዊ ሕይወት በመኖር፣ በንስሐ መንገድ በመመላለስ፣ በምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን በመሳተፍ እንጂ በድንቅና በተአምራት የሚኖር አይደለም፡፡
አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ‹‹ገንዘብ ይሰበስባሉ፣ ገቢ ያስገኛሉ›› ብለው እነዚህን ሐሳውያን እንደሚደግፉ ይታወቃል፡፡ ምእመናንም ‹‹ታድያ አቡነ እገሌ ለምን ፈቀዱ›› ይላሉ፡፡ እኛ ግን መሠረት ማድረግ ያለብን የቅዱሳት መጻሕፍትን ትምህርት፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን፣ታሪከ ቤተ ክርስቲያንን፣ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ነው፡፡ ማንም ከዚህ የወጣ ቢኖር ትምህርቱን ለመቀበል አንገደድም፡፡ ታላቅነት በእምነት እንጂ በሥልጣን አይገኝምና፡፡ ታላቁ አባት ዲዮስቆሮስ በ451 ዓም የኬልቄዶን ጉባኤ የልዮንን የሁለት ባሕርይ ትምህርት አልቀበል ሲል የሮም ባለ ሥልጣናት ‹‹እርሱኮ በቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የተቀመጠ የሮም ፖፕ ነውና አለቃህ ነው›› ባሉት ጊዜ ‹‹ሰይጣንም ለቅዱስ ሚካኤል አለቃው ነበረ›› ብሎ ነው የመለሰላቸው፡፡
ሳንድያጎ፣ ካሊፎርንያ

በተጠረጠሩበት የነፍስ ግድያ መርማሪዎችና ዓቃቤ ሕግ መመሳጠራቸው ተጠቆመ

የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለሥልጣን አቶ ወንድሙ ቢራቱን በተጠረጠሩበት ከባድ የሙስና ወንጀል በቁጥጥር ሥር አውሎ እየመረመራቸው የሚገኘው የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን፣ ሰሞኑን ባካሄደው

ምርመራ ተጠርጣሪው ከግለሰቦች 10.5 ሚሊዮን ብር ጉቦ የተቀበሉበትን ሰነድ መሰብሰቡን ገለጸ፡፡

መርማሪ ቡድኑ ከግለሰቦች ጉቦ ለመቀበላቸው የምስክሮችን ቃል መውሰዱን አክሏል፡፡ ተጠርጣሪው በሕገወጥ መንገድ ከቀረጥ ነፃ ተሽከርካሪዎችን በሌሎች ግለሰቦች ስም ማስገባታቸውን የጠቆመው መርማሪ ቡድኑ፣ ተሽከርካሪዎቹን ማሳገዱን አስረድቷል፡፡

የኮሚሽኑ መርማሪ በድን ባለፉት ሳምንታት ባካሄደው ምርመራ፣ ተጠርጣሪው በተጠረጠሩበት የነፍስ ግድያ ወንጀል በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖችና በአዲስ አበባ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን መሰብሰቡን ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ አቶ ወንድሙ በነፍስ ግድያ ተጠርጥረው እያለ፣ መርማሪዎችና ዓቃቤ ሕግ ተመሳጥረው ወደ ምስክርነት እንዲዛወሩ ማድረጋቸውንም የሚያስገነዝብ ማስረጃ መሰብሰቡን ገልጿል፡፡

ቀደም ብሎ እንደሚያከናውናቸው ከገለጻቸው የምርመራ ሥራዎች ውስጥ በተጠርጣሪው ላይ በጉምሩክ ተጀምሮ የነበረውንና በመመሳጠር ተቋርጦ የነበረውን ጅምር የምርመራ መዝገብ ከጉምሩክ መቀበሉንም ገልጿል፡፡ ሐሰተኛ ሰነድ እያሳተሙ በተለያዩ ከተሞች ሲፈጽሙ የነበረውን ግብር የመሰብሰብ ድርጊት የሚያስረዱ ምስክሮችን እያፈላለገ እንደሚገኝ መርማሪ ቡድኑ ገልጿል፡፡

የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን ጨምሮ እንደገለጸው፣ ለተጠርጣሪው ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግሥት ግብርን እንዲሰበስቡ ደረሰኝ አትሞ ከሰጣቸው ግለሰብ የምስክርነት ቃል መቀበል ይቀረዋል፡፡ ሌሎች ለመንግሥት መግባት የነበረባቸውን የተጨማሪ እሴት ታክስና ግብር ለማስቀረት ጉቦ የተቀበሉበትን የባንክ ሰነድ መሰብሰብና ተጨማሪ የሰው ማስረጃ መሰብሰብ ይቀረዋል፡፡ 

ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የሰው ማስረጃ ቃል መቀበሉን፣ ተጨማሪ የሰነድ ማስረጃ መሰብሰብ እንደሚቀረውና ሎሎች ተፈላጊ ተጠርጣሪዎችን አድኖ መያዝ እንዳለበት ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ ጉቦ ሲቀበሉና ሲያቀብሉ የነበሩበት የባንክና ሌሎች ሰነዶችን ከመጠቀም በተጨማሪ፣ በሥልጣን ዘመናቸው ሲያጠራቅሙ የነበረውን ተጨማሪ የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ሀብት ማፈላለግ እንደሚቀረው ለፍርድ ቤቱ ገልጾ፣ ይኼንን ለሚያከናውንበት ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲፈቀዱለት ጠይቋል፡፡

የተጠርጣሪው ጠበቃ መርማሪ ቡድኑ ያቀረበውን ተጨማሪ ጊዜ በመቃወም፣ እስካሁን ያደረገው ምርመራ በቂ መሆኑንና ተጨማሪ ምርመራ እንደማያስፈልግ በማስረዳት፣ የደንበኛቸው የዋስትና መብት እንዲጠበቅላቸውና ከእስር እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡

መርማሪ ቡድኑ ግን ቀሪ ምርመራ እንደሚቀረው ማስረዳቱን በማስታወስ ዋስትናውን ተቃውሟል፡፡

ተረኛ ችሎቱ የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኋላ፣ የተጠርጣሪውን ጠበቃ አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ለመርማሪ ቡድኑ የሰባት ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ፈቅዷል፡፡ 

 

ምኒሊክ ሳልሳዊ = በሕወሓት ተመልምለው ከውጪው አለም የሚኖሩ ዲያስፖራ የሕወሓት ደጋፊዎች የደህንነት እና ስለላ ስራዎችን ስልጠና በጦላይ ከጨረሱ በኋላ ወደየመጡበት አህጉር መመለሳቸው ምንጮች ጠቁመዋል::ከሰሜን አሜሪካ አውሮፓ እና መካከለኛ ምስራቅ እንዲሁም ከአፍሪካ ተመልምለው የመጡ እና በስራ ፈትነት በዲያስፖራው መሃል ሲኖሩ የነበሩ …

በጦላይ የሰለጠኑ የሕወሓት ደህንነቶች ወደየመጡበት አህጉር ተላኩ:: Read more »

ድምፃችን ይሰማ . ሁላችንም ለስኬታማነቱ በብር ላይ በመፃፍ እንረባረብ! . ባለፉት ጥቂት የትግል አመታት ከህዝብ ወደ ህዝብ በሚሰነዘሩ የተለያዩ ሐሳቦች በመገፋት የቀጠለው ሰላማዊ ትግላችን በሂደት ጥቂት የማይባሉ የሰላማዊ ትግል ስልቶችን ተጠቅሞ ድምጹን ለማሰማትና የሚፈጸሙ ሕገ ወጥ ድርጊቶችም እንዲቆሙ ለማስደረግ ሲጥር …

የድምጻችን ይሰማ ‹‹የወረቀት ብር ግራፊቲ›› (Money Grafitti)ተግባራዊ ስራ ተጀመረ:: Read more »

በሳዑዲው አሰቃቂ አደጋ የአገሪቱ ባለሥልጣናት እየተወዛገቡ ነው

131 ዜጎቿን ያጣችው ኢራን፤ ሳኡዲ አረቢያን ተጠያቂ አድርጋለች
እስካሁን በአደጋው 717 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል

በሳዑዲ አረቢያ በሀጂ ስነስርዓት ላይ ከትናንት በስቲያ 717 ሰዎች በሞቱበት አደጋ የአገሪቱ ባለስልጣናት እየተወዛገቡ ሲሆን፤ የኢራን መንግስት 131 ዜጐቹ መሞታቸውን በመግለጽ የሳዑዲን መንግስት ተጠያቂ አድርጓል፡፡
ከመካ በ5 ኪ.ሜትር ርቀት በሚገኘው ሚና የሚባል አካባቢ፣ በሰይጣን ላይ ድንጋይ የመወርወር ሃይማኖታዊ ስነ ስርአት ላይ በተፈጠረ ግርግር ነው አደጋው የተከሰተው ተብሏል፡፡ የብዙዎችን ህይወት በቀጠፈው አደጋ፤ 863 ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
ለሃጂ ስነስርዓት በሄዱ ኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰ አደጋ ስለመኖሩ የታወቀ ነገር የለም፡፡
የኢራን መንግስት መሪ አያቶላ ሆሚኒ፤ አደጋው የተፈጠረው በሳዑዲ መንግስት ዝርክርክ አሰራር ነው፤ ለአደጋው ሙሉ ኃላፊነቱን መውሰድ አለበት ብለዋል፡፡
የሳኡዲ የጤና ሚኒስትር ካሊድ አል-ፍሌህ በዚህ አይስማሙም፡፡ አደጋው የተከሰተው በምዕመናን ጥፋት ነው ብለዋል፡፡ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መንሱር አልቱርኪ፤ ተመሳሳይ ሃሳብ ሰንዝረዋል፡፡ ብዙ ምዕመናን፤ በተመሳሳይ ሰአት በጠባብ መተላለፊያ ላይ የፈጠሩት ግርግር የአደጋው መንስኤ ነው ብለዋል – ቃል አቀባዩ፡፡
የሀጂ ኮሚቴ ሊቀመንበር ልዑል መሃመድ ቢን ናይፍ በበኩላቸው፤ የአደጋው መንስኤ በአስቸኳይ ተጣርቶ እንዲቀርብላቸው ትዕዛዝ የሰጡ ሲሆን፣ የሀገሪቱ ንጉስ ሰልማን ግን የሀጂ ጉዳይ ድርጅቱ እንደገና እንዲዋቀር አዘዋል፡፡
በአደጋው ከሞቱት መካከል፣ 131 የኢራን፣ 14 የህንድ፣ 18 የቱርክ፣ 7 የፓኪስታን፤ 3 የአልጄሪያ እና 3 የኢንዶኔዢያ ዜጎችን ጨምሮ፣ ቁጥራቸው ያልተጠቀሰ የናይጄሪያ፣ ኒጀር፣ ቻድ፣ እና ሴኔጋል ዜጎች የአደጋው ሰለባ ሆነዋል ተብሏል፡፡
በሳኡዲ የብዙዎችን ህይወት የቀጠፈ አደጋ በአንድ ወር ውስጥ ሲያጋጥም ያሁኑ ሁለተኛው ነው፡፡ ከቀናት በፊት በመካ ታላቁ መስጊድ ላይ፤ የግንባታ ክሬን ወድቆ፣ 109 ሰዎች መሞታቸው ይታወቃል፡፡
ከትናንት በስቲያ ያጋጠመው አደጋ ከተሰማ በኋላ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ ባንኪሙን እና የካቶሊክ ፓፓስ ፍራንሲስ የሀዘን መልዕክታቸው ካስተላለፉት ቀዳሚዎቹ ሆነዋል፡፡
እ.ኤ.አ በ1990 ካጋጠመውና 1426 ሰዎችን ለህልፈት ከዳረገው ተመሳሳይ አደጋ ቀጥሎ የሰሞኑ የበርካታ ምዕመን ህይወት የተቀጠፈበት አደጋ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

፻፲፰ኛው የእስክንድርያ ፖፕ እና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ዳግማዊ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ባደረጉላቸው ወዳጃዊ ጥሪ መሠረት ባለፈው ፳፻፯ ዓ.ም.፣ ከጥር ፩ – ፯ ቀን ድረስ በግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የስድስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ …

ኢሳት ዜና (መስከረም 14 ፣ 2008) በማላዊ እስር ቤቶችን የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኙ 36 ህጻናትን ጨምሮ 387 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደሃገራቸው ለመመለስ ከአሜሪካ መንግስት በኩል ድጋፍ መገኘቱን የአለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት (IOM) ዛሬ አርብ ገለጠ። ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ወደ ማላዊ በህገወጥ መንገድ ገብታችኋል ተብለው የተላለፈባቸውን የዘጠኝ ወራት የእስር ቅጣት ቢያጠናቅቁም ወደኢትዮጵያ የሚመልሳቸው አካል በመጥፋቱ በእስር …

ኢሳት ዜና (መስከረም 14 ፣ 2008) የግብፅ መንግስት በመገንባት ላይ ያለውን የአባይ ግድብን በልዩ የሳታላይት ቴክኖሎጂ እየተከታተለ እንደሆነ ዛሬ አርብ ይፋ አደረገ። ሰሞኑን በግብፅ መገናኛ ብዙሃን በግድቡ የውሃ መሙላት ሂደት በግብፅ ላይ የውኋ እጥረት ተፈጥሯል ሲሉ ላቀረቡት ዘገባ ምላሽን የሰጡት የሃገሪቱ ባለስልጣናት፣ በሳተላይት ቴክኖሎጂ በደተረገ ክትትል ግድቡን በውሃ የመሙላት ስራ እንዳልተጀመረ ሊረጋገጥ መቻሉን ገልጸዋል። በግብፅ …

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከድርጅቱ በተገኘው መረጃ መሰረት በቀን ውስጥ ወደ ንቅናቄው ከሚደውሉ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ስልኮች መካከል 80 በመቶው ፣ ንቅናቄውን ለመቀላቀል መረጃ የሚፈልጉ ሰዎች ናቸው። በሁለተኛ ደረጃ የሚመጣው ደግሞ የማበረታቻ ሃሳቦችን ለመስጠት የሚፈልጉ ሰዎች ሲሆኑ፣ 2 በመቶ የሚሆነው ደግሞ መረጃ ለመስጠት የሚፈልገው ነው። የድርጅቱ የስልክ መረጃ አያያዝ እንደሚያመለክተው ካለፈው …

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኤምባሲው የ2015 የዲቪ ሎተሪ የመጨረሻ ቀን ረቡዕ መስከረም 19 ቀን 2008 ዓ.ም. መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን የቴክኒክና ሙያ የትምህርት ማስረጃን እንደሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ማስረጃነት ከዚህ ቀደም ሲቀበል መቆየቱን በማስታወስ ከአሁን በኃላ የማይቀበል መሆኑን አስታውቆአል፡፡ ኤምባሲው ይህን ለምን እንዳደረገ በመግለጫው የጠቀሰው ነገር ባይኖርም የኤምባሲው ምንጮች እንደጠቆሙት የአሜሪካ መንግስት …

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በሀዲያ ዞን “አባ ሰንጋ” የተሰኘው የከብቶች በሽታ ተከስቶ በርካታ ሰዎችና ከብቶች ለሞት እየተዳረጉ መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በስፍራው የሚገኘው ዘጋቢያችን እንዳጠናቀረው መረጃ እስካሁን በበሽታው አስራ ስድስት ሰዎች ሞተዋል። በበሽታው እጅግ በርካታ ከብቶች እያለቁ በመኾናቸውም የ አካባቢው ህዝብ መጪውን የመስቀል በዓል ከስጋ ተዋጽኦ ውጪ …

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ከተማ በየካቲት ወር 2008 ጀምሮ ይከናወናል ተብሎ የታቀደው የፈጣን አውቶቡስ መስመር ግንባታ ፕሮጀክት ከአዋጪነት አንጻር በሚገባ በጥናት ያልታየና በአሁኑ ሰዓት የተገነቡ መሠረተ ልማቶችን የሚያሳጣ ነው በሚል ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ነዋሪዎች እንደጠቆሙት ፕሮጀክቱ ከዊንጌት፣ በጎፋ ገብርኤል አድርጎ ወደ ጀሞ የሚዘልቅ ለከተማ አውቶቡስ ብቻ …

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኬንያ ኢዞሎ ግዛት ውስጥ ድንበር አቋርጠው ለመሻገር ሲሞክሩ የተያዙት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በተጨናነቀ እስር ቤት ውስጥ በስቃይ ላይ እንደሚገኙ ኦል አፍሪካን ዘግቧል። በኬንያ ኢዞሎ ጂኬ እስር ቤት ውስጥ ከሚገኙት 450 እስረኞች መካከል 300 ዎቹ ኢትዮጵያዊያን ናቸው። እስር ቤቱ ከ 150 የበለጡ እስረኞችን መያዝ እንደማይችል የኢዞሎ ግዛት ምክትል …

በአውሮፓ የተሻለ ህይወት ለመምራት ያሰቡ በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪቃውያን ስደተኞች በሜዲትራንያን ባህር ሰምጠው ሞተዋል። ከነዚህም ውስጥ አብዛኞቹ ወጣቶች ናቸው። የስደተኞቹ ጩኸት እና የድረሱልን ጥሪያቸው በሀገሮቻቸው ሰሚ አላገኘም።

የዲላ ዩኒቨርስቲ ሰራተኞች በፕሬዝዳንታቸው “ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ ኮሬ” ላይ ዓመፅ በማስነሳት ወደ ትምህርት ምኒስቴር ጥያቄያቸው ልከዋል። ፕሬዝዳንቱ “ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ ኮሬ” ላይ 16 ክሶች ቀርቦላቸዋል። ከክሰቹ መሃል ፩) ከ229 በላይ ሰራተኞች ከህግና ድንብ ውጪ በራሳቸው ስልጣን እንዲቀጠሩ ኣድርገዋል፣ ፪)ሰራተኞች ዩኒቨርስቲው …

የዲላ ዩኒቨርስቲ ሰራተኞች በዩንቨርስቲው ፕሬዚዳንት ላይ ኣመፅ ኣስነሱ። ዝርዝር ደብዳቤውን ይዘናል:: Read more »

ኢሳት ዜና (መስከረም 13, 2008) በኢትዮጵያ በተከሰተው የድርቅ አደጋ ለምግብ እርዳታ የሚጋለጡ ሰዎች ቁጥርና የእርዳታ መጠን በቀጣዮቹ አራት ወራቶች በከፍተኛ መጠን ሊጨምር እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጀት አስታወቀ። የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር 4.5 ሚሊዮን አካባቢ እንደነበር ያወሳው ድርጀቱ፣ የተረጂዎችን ቁጥር ከታህሳስ ወር መጨረሻ ጀመሮ ጭማሪን እንደሚያሳይ ገልጿል። በፈረንጆቹ አዲስ አመት ባሉ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራቶች …

አስፋ ጫቦ Corpus Christi, Texas USA መስከረም ሲጠባ ፤አደይ ሲፈንዳ፤ እንኳን ሰው ዘመዱን ፤ ይፈልጋል ባዳ ማለት እውነት ነው!ለኔ፣የኔ እወነት ነው! ዳዊት “..ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ …፤ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ምድርም ሐሴት ታደርግ“  ያለው መሆኑ ነው።ዘፈን ዘፈን !ዝፈን ዝፈን! ብሎኛል እንደማለት ።ዳዊት የተናገረው በምናቡ ኢትዮጵያን እያየ መሆን አለበት። እንጅማ የሱ አገር በአበባ ሠምሮ፥ደምቆ፥ ሰውም፤ምድሪቱም የሚዘፍኑበት አይመስለኝም:: የሰሐራ በረሀ […]

The post ዮ ..ሀ.. ማስቃላ!! ….አደይ ሲፈንዳ!! (አስፋ ጫቦ ) appeared first on ሳተናው (Satenaw)-Latest Ethiopian News & Breaking News.

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

መስከረም ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየአመቱ በድምቀት የሚከበረው የኢድ አል አድሃ በአል ለ1 ሺ 436ኛ ጊዜ በኢትዮጵያና በመላው አለም ተከብሯል። በሳውድ አረቢያ መካ በአሉን ለማክበር በስፍራው ከተገኙ ከ2 ሚሊዮን በላይ የሃይማኖቱ ተከታዮች መካከል ከ700 ያላነሱ ሰዎች ተረጋገጥተው ህይወታቸው አልፎአል። ከ900 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ክፉኛ መቁሰላቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። በሰንአ በአንድ መስኪድ ላይ …

መስከረም ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ማዬት የተሳናቸው ተማሪዎች መስከረም 11 ቀን 2008 ዓም ፣ ከመብት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን በማንሳታቸው በፖሊሶች ክፉና የተደበደቡ ሲሆን፣ የተማሪዎችን ተወካዮች ጨምሮ 17 ማዬት የተሳናቸው ተማሪዎች ተይዘው ታስረዋል። ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ተማሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ፣ ተማሪዎች የማደሪያ ክፍል በአንድ ግቢ ውስጥ ለሚገኘው ኮሌጅ በመሰጠቱ ፣ ተማሪዎች እንዲመለስላቸው …

መስከረም ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ኢህአዴግ በመቀሌ ላይ ባደረገው ጉባኤ ግንባሩን ጥለው የሚወጡ ሰዎች ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ መጨመሩን የገለጸ ቢሆንም፣ አሁንም ድርጅቱን ጥለው የሚወጡ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ፣ ግንባሩ የመልቀቂያ ጥያቄን እንደማያስተናግድ አስታውቋል። ድርጅቱን ለመልቀቅ ጥያቄ ያቀረቡ አባላት አርፈው እንዲቀመጡ ተነግሯቸዋል። ለኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የመልቀቂያ ጥያቄ የሚያቀርቡ …

መስከረም ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዶ/ር ሽመልስ ከሌሎች ታዋቂ ምሁራንና ፖለቲከኞች ጋር በመሆን ቀስተደመናን ፓርቲ፣ ከዚያም ቅንጅት እንዲመሰረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል። የቅንጅት መሪዎች በታሰሩበት ወቅትም ዶ/ር ሽመልስ፣ ትግሉ እንዳይቀዛቀዝ ከፍተኛ ስራ ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን፣ አንድነት ፓርቲ በተመሰረተበት ወቅትም ፓርቲውን በአመራር አባልነት አገልግለዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ነጻ የሬዲዮና ቴሌቪዥን ስርጭት ለመጀመር የተቋቋመውና …

የቀድሞው የቅንጅት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የነበሩት እና የታዋቂው የታሪክ ተመራማሪ እና ጸሃፊ የአቶ ተክለጻዲቅ መኩሪያ ልጅ የሆኑት ዶክተር ሽመልስ ተክለጻዲቅ መኩሪያ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል::ዶክተር ሽመልስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነት እና መብት በመታገል ያበረከቱት አስታውጾ ታሪክ አይረሳውም::በዶክተር ሽመልስ ሞት የተሰማኝን ጥልቅ …

ዶክተር ሽመልስ ተክለጻዲቅ መኩሪያ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ:: Read more »

  በዛሬው እለት በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የክልል ከተሞን(በመላው ኢትዮጵያ) የኢድ አል አድሃ በአል በደመቀ ሁኔታ የተከበረ ሲሆን ህዝበ ሙስሊሙ በተለመደው መልኩ በሰላም በፍቅር እና በትእግስት የስላቱን ፕሮግራም አጠናቆ ወደ ቤቱ ሲመለስ በአንዳንድ አከባቢዎች ፖሊሶች ለመተናኮል ቢያስቡም እጅግ የሰላም እና …

የ1436ኛው የኢድ አድሃ በአል በኢትዮጵያ በድምቀት የተከበረ ሲሆን ፖሊሶች ለመተናኮስ ሲሞክሩ ታይተዋል:: (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

ኢሳት ዜና (መስከረም 12 ፣ 2008) በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኙ 4ሺ በላይ የመንግስት ሰራተኞች ላይ እርምጃ የወሰደው የከተማዋ አስተዳደር በአስር ክፍለ ከተሞች ሹምሽር አካሄዷል። ከቀናት በፊት በተጀመረው በዚሁ ሹም ሽር በ116 ወረዳዎች የሚገኙ ከ100 በላይ አመራሮች የተነሱ ሲሆን የከተማዋ አስተዳደር ድርጊቱ ከትምህርት ብቃት ጋር የተገናኘ እንደሆነ መግለፁን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። …

ኢሳት ዜና (መስከረም 12 ፣ 2008) ኢትዮጵያን ጨምሮ በድሃ ሃገራት ከሚኖሩ ህዝቦች መካከል 90% የሚሆኑት የኢንተርኔት ተጠቃሚ አለመሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። ከአፍሪካ ዝቅተኛ የኢንተርኔት ሽፋን ያላት ኢትዮጵያም በአለም በአገልግሎቱ አሳሳቢ ተብለው ከተፈረጁ አስር አገራት መካከል አንዷ መሆኗን ድርጅቱ በአመታዊ ረፖርቱ ገልጿል። ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ቡሩንዲ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ረፐብሊክ፣ ጊኒ፣ ላይቤሪያ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ማላዊ፣ ሞዛምቢክና፣ …

ኢሳት ዜና (መስከረም 12 ፣ 2008) ከኢትዮጵያ የሚደረገውን ከፍተኛ የወጣቶች ስደት ተከትሎ የአውሮፓ ህበረት ልዩ የሉዑካን ቡድን በጉዳዩ ዙሪያ ለመምከር ወደአዲስ አበባ መጓዙን ህብረቱ ዛሬ ረቡዕ ገለጠ። በሃገሪቱ የሶስት ቀን ቆይታ የሚኖረው ይኸው የልዑካን ቡድን ከኢትዮጵያ እየጨመረ በመጣው የወጣቶች ስደት እና ችግሩ በሚቀንስበት ዙሪያ ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ሰፊ ምክክር ያካሂዳል ተብሎ ይጠበቃል። የአለም አቀፉ የስደተኞች …

ኢሳት ዜና (መስከረም 12 ፣ 2008) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አምስት ከፍተኛ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ አመራሮችን ከውጭ ምንዛሪ ጋር በተገናኘ ዛሬ ረቡዕ ከሃላፊነታቸው አነሳ። የቀድሞ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታና የባንኩ የቦርድ ሊቀመንበር ዶ/ር አበራ ደሬሳ፣ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ወንድማገኘሁ ነገራ፣ እንዲሁም ሁለት ምክትል ፕሬዚዳንቶች አቶ ቶሎሳ በየነና፣ አቶ አበበ ጥላሁን ከባንኩ አመራርነት መነሳታቸው ታውቋል። የኦሮሚያ ህብረት …

የዒድ አል አድሐ በዓልን አስመልክቶ በእስር ከሚገኙ መሪዎቻችን የተሰጠ መግለጫ ረቡእ መስከረም 12/2008 የመግለጫው ፒዲኤፍ ቅጂ ሊንክ፡- http://goo.gl/XfMlRP የመግለጫው ሙሉ ቃል በጽሁፍ፡- ******************************* ******************************* በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ፣ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው! ጥያቄዎቻችን እስኪመለሱ እና ብሄራዊ የሃይማኖት ጭቆናው እስከሚያከትም …

የተከበራችሁ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሆይ! – የዒድ አል አድሐ በዓልን አስመልክቶ በእስር ከሚገኙ መሪዎቻችን የተሰጠ መግለጫ Read more »

‎- የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለእደለኞቹ አይታደሉም ተባለ ‎- በዘንድሮ የትምህርት ዘመን የመጽሐፍት እጥረት መኖሩ ታወቀ – የቡርኪና ፋሲ የመከላከያ ሰራዊት መፈንቅለ መንግስት ላካሄዱት ክፍሎች የጊዜ ገደብ ያለው ማስጠንቀቂያ ሰጠ. ‎- የግብጽ መንግስት በግብጽና በጋዛ ወሰን የሚገኙ ከሶስት ሺ በላይ ቤቶችን አፍረሰ፣ …

– የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለእደለኞቹ አይታደሉም ተባለ ‎- በዘንድሮ የትምህርት ዘመን የመጽሐፍት እጥረት መኖሩ ታወቀ:: Read more »

በመጪው እሁድ መስከረም 16 ቀን 2008 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ህዝቡ በመንግስት ላይ ጠንከር ያለ ተቃወሞ ሊያስተጋባ እና ለያሰማ ይችላል በሚል ስጋት ውስጥ የወደቀው የህወሃት ኢህአዴግ መንግስት የፀጥታ ሀይሎች የሚላቸው አካላት በተጠንቀቅ እንዲቆሙ መመሪያ መተላለፉን ውስጥ …

በደመራ በአል ወቅት ረብሻ ሊነሳ ይችላል በሚል ስጋት የፀጥታ ሀይሎች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ መመሪያ ተላለፈ:: Read more »

Minilik Salsawi – አምባገነን መንግስታት ወንጀላቸው እየበዛ መውጪያ ቀዳዳ እያጡ ሲሄዱ በሕዝብ ጫንቃ ላይ ተቀምጠው የሕዝብ ጥያቄ መመለስ ሲያቅታቸው በከፍተኛ ደረጃ ዘረፋ ውስጥ ሲዘፈቁ ሕዝብን በሃሰት ፕሮፓጋንዳ ለመሸንገል የሚያደርጉት መፍጨርጨር ሕዝቡ ከነሱ ቀድሞ እንደሚያውቅ ይዘነጋሉ አሊያም እንደለመዱት በሃይል ለመቀጠል ደፋ …

በፕሮፓጋንዳ ቀውስ የሚዋዥቀው የወያኔው ጉጅሌ አገዛዝ (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

ቪዛ ሳትጠይቅ፣ ከሰው ብላ ጠጋ እጂጉን ተጣጥፋ በላስቲክ ታሽጋ ባህሩን አቋርጣ እሷ እኛን ፍለጋ በዶላር ከፍ ብላ ልታወጣ ዋጋ እሷም እነጄራይቱ መጥታለች እኛው ጋ የሀገሬ ዜጎች ድሆቹ ሳይጠግቡ ከአፋቸው ላይ ነጥቀው እኛን ሊመግቡ ሀብታሞች ጨክነው የእንጄራ ነግድ ገቡ። እርም ነው …

እንጄራም ተሰዳ! ልያ ፋነታ ከዋሽንግተን ዲሲ Read more »

በዚህ ቭድዮ በአይሲስ የተጠቁ ግፍ የተፈጸመባቸው ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ::የሰሃራን በረሃ አቋርጠው ወደ አውሮፓ ለተሻለ ኑሮ ሲሄዱ በዚህ 2015 ከ2000በላይ ስደተኞች ሞተዋል:: [youtube http://www.youtube.com/watch?v=QsdYXjzB9Yw]   https://news.vice.com/video/witness-to-islamic-state-atrocities-extra-scene-from-libyas-migrant-trade

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5፣ በተለምዶ ውቤ በረሃ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን (አራዳ ጊዮርጊስ) አዲሱ የባቡር ተርሚናል እስከ አፍንጮ በር የሚገኙ ነጋዴዎች፣ ምትክ

የንግድ ቦታ ሳይሰጣቸው የንግድ ቤቶቻቸውን በግዳጅ ለማፍረስ ወረው እያሸገ መሆኑን ገለጹ፡፡

ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር እኩል ሊባል የሚችል ዕድሜ ያስቆጠሩ ንግድ ቤቶች በአንድ ሳምንት ማስጠንቀቂያ ማፍረስ ተገቢ አለመሆኑን የሚናገሩት ነጋዴዎቹ፣ አስተዳደሩ የገባላቸውን ቃል በማጠፍ፣ ‹‹ተለዋጭ ቦታ የምሰጣችሁ አሁን ያላችሁበትን የንግድ ቦታ አፅድቼ ስጨርስ ነው›› ማለቱ፣ ከሕግም ሆነ ከመንግሥት ፖሊሲ አንፃር የዜጐችን መብት የማያስከብር በመሆኑ አግባብነት የለውም ብለዋል፡፡ 

የከተማ አስተዳደሩ ነጋዴዎቹን ከዓመት በፊት ሰብስቦ በአክሲዮን እንዲደራጁና እያንዳንዳቸው 25,000 ብር በማዋጣት በባንክ እንዲያስቀምጡ፣ እንዲሁም በየወሩ ከ2000 ብር በላይ ገቢ እንዲያደርጉ ያቀረበውን ሐሳብ መቀበላቸውንና ተግባራዊ ማድረጋቸውን የሚናገሩት ነጋዴዎቹ፣ በንግድ ቦታቸው ላይ ግንባታ ተካሂዶ እያንዳንዳቸው 25 ካሬ ሜትር ቦታ እንደሚሰጣቸው የተነገራቸው ሁሉ ታጥፎ፣ በቀናት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ መወሰኑ እንዳስደነገጣቸው ተናግረዋል፡፡ 

መንግሥት ከወሰነ በኋላ የገባውን ቃል ተላልፎ በአስቸኳይ እንዲለቁ የሚያደርግ ከሆነ፣ ለሌሎች የልማት ተነሺ ነጋዴዎች የተሰጠው ዕድል ለእነሱም መነፈግ ስለሌለበት፣ ተለዋጭ የኮንዶሚኒየም የንግድ ቦታዎች እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

ቤተሰቦቻቸውንና ቀደምት ነጋዴዎችን በመተካት ሥራቸውን በንግድ ላይ በማድረግ ልጆቻቸውን የሚያስተምሩት፣ የሚመግቡትና ራሳቸውንም እያኖሩ የሚገኙት በያዙት ንግድ ቤት እየነገዱ በሚያገኙት ገቢ መሆኑን የሚናገሩት ነጋዴዎቹ፣ በሕገወጥ መንገድ በ‹‹አፍራሽ ግብረ ኃይል›› አማካይነት ወደ ጎዳና ተገፍተው ከመጣላቸው በፊት መንግሥት ሊደርስላቸው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ 

ዕድሜ ጠገብ የንግድ ቤቶች ከሆኑት መካከል የታዋቂው ክራር ተጫዋች ከተማ መኰንን ቤት የነበረው አሁን ብሔራዊ ሆቴል በቅጽል ስሟ ‹‹ጭራ ቀረሽ›› በሚል መጠሪያ የምትታወቀው የዘነበች ታደሰ የነበረውና አሁን ግሪን ባርና ሬስቶራንት፣ መዲና በመባል የሚታወቀው አሁን ያሲን ሱፐር ማርኬት፣ ድምፃዊት አበበች ደራራ የነበረችበት አሁን ሰላም ልኳንዳ፣ ዘመናት ያስቆጠረው አባ ገዳ ማተሚያ ቤት፣ አርቲስት አሰለፈች አላምረው ትሠራበት የነበረው ሆቴል፣ ኤፍሬም ግሮሰሪና ሌሎችም ታዋቂ የንግድ ቤቶች የሚፈርሱ መሆናቸውንም ነጋዴዎቹ ገልጸዋል፡፡

መንግሥት ለልማት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን እነሱም የሚደግፉት ተግባር እንደሆነ የገለጹት ነጋዴዎቹ፣ ከሁሉም በፊት የዜጐች መብትና ክብር መቅደም ስላለበት፣ እንዲሁም መንግሥት ዜጐቹን የመንከባከብና እንደየሥራ ዘርፋቸው ማሰማራት የሚጠበቅበት በመሆኑ ምትክ ቦታ ሰጥቶ እንዲታደጋቸው ጠይቀዋል፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ የቀድሞ ቀበሌ 03/09 (ወረዳ 5) አስተዳደር፣ በደል ሊፈጽምባቸው መሆኑን እየገለጹ ስለሚገኙት የውቤ በረሃ ነጋዴዎች ጉዳይ ለማነጋገር ሪፖርተር ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

በተመሳሳይ ከአራዳ ክፍለ ከተማ መሬት አስተዳደርና ከተማ ማደስ ጽሕፈት ቤቶችም በተመሳሳይ ምላሽ ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡   

 

የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት አብዛኛዎቹን የክፍላተ ከተሞችና የወረዳ አመራሮች በማንሳት፣ በአዳዲስ አመራሮች እየተካ መሆኑ ታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካት

ወረዳዎችና ክፍላተ ከተሞች መመራት ያለባቸው ዲፕሎማና ከዚያ በላይ የትምህርት ደረጃ ባላቸው መሆን አለበት የሚል አዲስ አቋም መያዙ፣ ለሹም ሽሩ ምክንያት መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በዚህ መሠረት በአሥሩም ክፍላተ ከተሞችና በሥራቸው በሚገኙ 116 ወረዳዎች የሚገኙ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አመራሮች ተነስተዋል፡፡ በተጨማሪም ሹም ሽሩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰፈነውን የመልካም አስተዳደርና የሙሰኝነት ችግር ለመቅረፍ መንግሥት ከያዘው ዕቅድ ጋር የሚያያዝ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

ይህን ችግር ለመቅረፍ በቅድሚያ ይህ ችግር ያለባቸው አመራሮች ተገምግመው እንዲነሱ መደረጉም ተገልጿል፡፡ ለማሳያ ያህል በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ 12 ወረዳዎች ከዲፕሎማ በታች ያላቸው አመራሮች 70 የሚጠጉ ሲሆን፣ እነዚህ ሁሉ እንደተነሱ ተገልጿል፡፡ በሙስናና በተለያዩ ግድፈቶች ደግሞ 30 አመራሮች እንዲነሱ መደረጉም ተመልክቷል፡፡ 

በሌሎች ክፍላተ ከተሞችና በሥራቸው በሚገኙ ቀበሌዎችም በተመሳሳይ ከ100 ያላነሱ አመራሮች በእነዚህ ሁለት ምክንያቶች መነሳታቸው ተገልጿል፡፡ ይሁንና ከዲፕሎማ በታች የትምህርት ደረጃ ኖሯቸው አመራር ሲሰጡ የቆዩ አባላት ቅሬታ አቅርበዋል፡፡ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉት እነዚህ አመራሮች ትምህርት ለመማር ጥያቄ  በሚያቀርቡበት ወቅት መንግሥት ቅድሚያ ሥራችሁን ሥሩ የሚል ምላሽ የሰጣቸው በመሆኑ ትምህርት መማር እንዳልቻሉ አስታውሰው፣ ውሳኔው ፍትሐዊ እንዳልሆነ ጠቁመዋል፡፡ 

በአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ይህንን አለመግባባት ለማስቀረት የውይይት መድረኮች ፈጥሮ እንደነበርም ታውቋል፡፡ በዚህም ያላቸው የትምህርት ደረጃ ዝቅተኛ በመሆኑ የተነሱ አመራሮች የሦስት ወራት ደመወዝ፣ በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው ሥራዎችን እንዲሠሩ ወይም ዕድሜያቸው ለጡረታ የደረሰው ደግሞ በጡረታ እንዲገለሉ ሐሳብ ቀርቦ፣ ከሞላ ጎደል መግባባት ላይ መደረሱ ተመልክቷል፡፡

ዋነኛው የአዲስ አበባ ከተማ ችግር የመልካም አስተዳደር እጦትና ኪራይ ሰብሳቢነት [ሙስና] እንደሆነ ነዋሪዎች ባገኙት አጋጣሚ ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡ ይህ ችግር የ2007 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸም በሚገመገምበት ወቅት በሰፊው ተነስቷል፡፡ በተለይ በመሬት፣ በንግድና በአገልግሎት መስጫ ዘርፎች ላይ ኅብረተሰቡ ከፍተኛ እሮሮ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡

በእነዚህ ዘርፎች ለተገልጋዮች ተገቢውን አገልግሎት አለመስጠት፣ ተገልጋዮችን ለማስተናገድ ዝግጁ አለመሆን፣ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ውሳኔ አለመስጠት፣ ‹‹ጉዳዩ አልታየም›› በማለት ተገልጋዮችን ማጉላላትና ጉቦ መጠየቅ ከሚቀርቡት ቅሬታዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በንግድ በኩል የንግድ ፈቃድ ዕድሳት፣ የንግድ ስያሜ አሰጣጥ፣ የንግድ አድራሻ ማረጋገጫ አሰጣጥ፣ ሕገወጥ ንግድ በሰፊው የሚታዩ ችግሮች ከመሆናቸውም በተጨማሪ፣ በአጠቃላይ የንግድ ሥርዓቱ የተተረማመሰ እንደሆነ ቅሬታ ይቀርባል፡፡

በእነዚህ ሁሉ ችግሮች ሙስና ዋነኛ መገለጫ መሆኑ ከኅብረተሰቡ በሰፊው የሚነሳ ጉዳይ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይህንን የኅብረተሰብ ሮሮ በመቀበል፣ የራሱን ግምገማ አካሂዶ ችግሩ እንዳለ አምኗል፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ ከሕዝብ ጋር ተወያይቶ ወደ ተግባር እንደሚገባ ገልጾ ነበር፡፡ 

ይህንን ችግር ለመፍታት በተካሄዱ ተከታታይ ግምገማዎች ግድፈት እንዳለባቸው የተለዩ አመራሮችን ከክፍላተ ከተሞችም ሆነ ከወረዳዎች ማንሳት ዋነኛ ዕርምጃ ሆኗል፡፡

በዚህ መሠረት ቢያንስ ችግሩ ጎልቶ በሚታይባቸው ክፍላተ ከተሞች ከ30 በላይ አመራሮች፣ በወረዳ ደረጃም በተመሳሳይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አመራሮች እንደተነሱ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ 

ይሁንና በአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ባለቤትነት የሚካሄደው ይህ ሹም ሽር ባለፈው ሳምንት መገባደዱን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተወልደ ገብረ ፃድቃን ሥራው እየተካሄደ መሆኑን ለሪፖርተር አረጋግጠው፣ ሥራው ባለመጠናቀቁ መረጃ ለመስጠት እንደማይችሉ ገልጸዋል፡፡ 

ከዚህ በመቀጠል የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት በማዕከል ደረጃ የሚገኙ ቢሮዎችንና ኤጀንሲዎችን የሚመሩ አመራሮች ላይ ሹም ሽሩን እንደሚቀጥልም ተገልጿል፡፡ ሹም ሽሩ በርካታ አመራሮችን ከካቢኔ የሚያስወጣና በምትካቸው አዳዲስ የካቢኔ አባላትን እንደሚሾም ምንጮች ተናግረዋል፡፡

የካቢኔ አባላቱ ሹም ሽር በቅርቡ ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ቀርቦ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡  

 

በ1920ዎቹ ማብቂያ ኢትዮጵያን የወረረው የፋሽስት ኢጣሊያ ጦር በወቅቱ በዓለም ዙሪያ የተከለከሉ የጦር መሳሪይዎችን በመጠቀም ሰላማዊ ሰዎችን ጭምር ሳይቀር መግደሉን ያትታሉ አቶ ኪዳኔ፤ የፋሽስት ጦር ከቫቲካን ድጋፍ እንደነበረው ይናገራሉ።