ብሄራዊ ባንክ 5 የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ከፍተኛ አመራሮችን አነሳ

ኢሳት ዜና (መስከረም 12 ፣ 2008)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አምስት ከፍተኛ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ አመራሮችን ከውጭ ምንዛሪ ጋር በተገናኘ ዛሬ ረቡዕ ከሃላፊነታቸው አነሳ።

የቀድሞ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታና የባንኩ የቦርድ ሊቀመንበር ዶ/ር አበራ ደሬሳ፣ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ወንድማገኘሁ ነገራ፣ እንዲሁም ሁለት ምክትል ፕሬዚዳንቶች አቶ ቶሎሳ በየነና፣ አቶ አበበ ጥላሁን ከባንኩ አመራርነት መነሳታቸው ታውቋል።

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ማህበር ባንክ የአለም አቀፍ ማንኪንግ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ባንታየሁ ከበደም ለአመታት ካገለገሉበት ሃላፊነት መሰናበታቸውን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል።

የብሄራዊ ባንክ እርምጃው ከውጭ ምንዛሪ ጋር በተገናኘ እንደሆነ ቢገልፅም፣ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአንድ ጊዜ አምስት ከፍተኛ የባንክ አመራሮችን ከሃላፊነት ሲያሰናብት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን ድርጊቱ በኦሮሚያ ህብረት ባንክ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል ተብሎ ተሰግቷል።

በኢትዮጵያ የተከሰተውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ተከትሎ የብሄራዊ ባንክ በግል ባንኮች ላይ ከፍተኛ ቁጥጥሩን እንደሚያደርግ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አካላት ይገልጻሉ።

ከሁለት አመት በፊት የብሄራዊ ባንክ ከውጭ ምንዛሪ አያያዝና አጠቃቀም ጋር በተገኛኘ የተወሰኑ የባንኩ ሃላፊዎች ከሃላፊነት ማንሳቱ የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ረቡዕ የተወሰደው እርምጃም በግል ባንኮች ዘንድ ድንጋጤን መፍጠሩ ታውቋል።

ሃገሪቱ ያጋጠማትን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለመቅረፍ መንግስት ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ዘንድ በሁለተኛ ዙር ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለመበደር በዝግጅት ላይ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።

በተጠናቀቀው 2007 አም ያጋጠመውን የውጭ ንግድ ማሽቆልቆልና የአንደኛውን ዙር ትራንስፎርሜሽንና የእድገት እቅድ አለመሳካት ተከትሎ የአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ክምችት በጣም ዝቅተኛ መሆኑን የመንግስት ባለስልጣናት ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።

በአሁኑ ሰአትም ለተወሰኑ ተቋማት ብቻ የውጭ ምንዛሪ እየተሰጠ እንደሚገኝ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አካላት አስረድተዋል።

 

4 Comments on “ብሄራዊ ባንክ 5 የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ከፍተኛ አመራሮችን አነሳ”

  1. ከትግራይ የተማረ የለም እንጂ ከየት አምጥቶ እንደሚተኩ ግራ ተጋብቷል ባንኩ የግል ባንኮች በምንዛሬ አቅርቦት ሣብያ ውድ ደንበኛዎችን ማጣት አይፈልጉም ወያኔ ደግሞ ኢፍትሀዊ ቁጥጥር በማድረጉ ግንባር አይቶ የማደል ሥራውን እሡ ፈላጭ ቆራጭ በመሆን የንግድ ማህበረሠቡን ላልተፈለገ ሙሥናና ኪሣራ ዳርገውታል ይህ የአንባገነን የባንክ ሥርአት ንግዱን ውድድር ሞኖፖላፕዝ ሆኖ በተወሠኑ የወያኔን ሥርአት ደጋፊዎች ብቻ እየዋለ መሆኑን ያሣያል።

  2. ለሆድ አደር በሬ ወለደ ጉጅሌ EliaAss Kifle
    You are a major violator. We can not let you get away with that. Either you will stop posting fabricated news and poisonous articles or feel the brunt of our response to your website.No ban can stop us. Actually the silent outrage many of us have on you will turn in to protest in the near future. Like your brother Negussie Woldemariam today, you will be confronted and kicked away. You can bet on that. It is coming soon. .

    Berhanu Nega ill from food poisoning
    Post a reply
    Postby elias » 04 Aug 2015, 21:27

    Our sources in Eritrea have informed us that AG7 chairman Dr Berhanu Nega is currently recovering from food poisoning. If his condition doesn’t improve he will travel to Europe for treatment, the sources added. Coalition talks between AG7 and TPDM continue but agreement may be delayed. Also stay tuned for U.S. Government’s official statement pertaining to Dr Berhanu’s move to Eritrea and related issues. Yosef Haimanot, a young Ethiopian-British national who went to Eritrea to visit the Ethiopian opposition group, EPPF, is still missing and presumed to be in jail or killed. His friends in London have informed ER that the London police is processing a report for investigation by the Interpol.

    [Caption: Dr Berhanu Nega at the AG7 office in Asmara]
    Reported by ጉጅሌ EliAss kifle
    ከጉንጭ አልፋ ፍሬከርስኪ አውርቶ አደሮች መንደር
    ከወሬ አርበኞች መንደር

  3. yes ወያኔ ኢትዬጵያን አይወክልም!!!

    ከጫካ የመጣችሁት ትግራይን ነፃ ለማውጣት ነው
    ትግራይ የራሷ የባህር በር መሥመር መዘርጋት
    EFort የንግድ አዙርሪት ኢኮኖሚውን ማቀጨጭና ሞኖፖላይዝ ማረግ
    የመጨረሻው ግብ ሟቹ መለሥ ያላችሁ ካቃታችሁ ኢንተርሀርምዌይ እንደ ሩዋንዳ በጎሣ መበታተን…ያሉትን
    ባህል ሀይማኖትን ተንተርሦ የፖለቲካ ምህዳሩን በአንድ ጎሣ የበላይነት ሥርአቱን ማሥቀጠል የበቀሉትን ማጥፋት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*