እንጄራም ተሰዳ! ልያ ፋነታ ከዋሽንግተን ዲሲ

ቪዛ ሳትጠይቅ፣ ከሰው ብላ ጠጋ
እጂጉን ተጣጥፋ በላስቲክ ታሽጋ
ባህሩን አቋርጣ እሷ እኛን ፍለጋ
በዶላር ከፍ ብላ ልታወጣ ዋጋ
እሷም እነጄራይቱ መጥታለች እኛው ጋ

የሀገሬ ዜጎች ድሆቹ ሳይጠግቡ
ከአፋቸው ላይ ነጥቀው እኛን ሊመግቡ
ሀብታሞች ጨክነው የእንጄራ ነግድ ገቡ።

እርም ነው ይህ ለእኔ በእንባ የተቦካ
እንኳነስ ልበላው በጣቴም አልነካ
መቼ እንጄራ አጣሁ ስኖር በአሜሪካ

እንጄራ አትሰደጂ ግቢ ወደ ሀገርሺ
ስደት ማንን ደልቶት አነችም እዚህ መጣሽ።

ልያ ፋነታ
ከዋሽንግተን ዲሲ