መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ውስጥ በንግድ እንቅስቃሴያቸው ከሚታወቁት አካባቢዎች መካከል አንዱ በሆነው ካዛንችስ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙ የንግድ ቤቶች በብዛት የፈረሱ ሲሆን፣ መኖሪያ ቤቶችን ለማፍረስ እንቅስቃሴ በመጀመሩ ነዋሪዎች ስጋት ገብቷቸዋል። የመንግስት ቤቶችን ተከራይተው ይሰሩ የነበሩ የንግድ ድርጅቶች በከተማዋ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ቦታዎች እንዲሰማሩ ቢደረግም፣ የግል የንግድ ቤት የነበራቸው …

መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከያዝነው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል የተባለው ሁለተኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የወጭ ንግዱን ከ3 ወደ 12 ቢሊየን ዶላር ለማድረስ መታቀዱ አሁን ሀገሪቱ ባለችበት ተጨባጭ ሁኔታ እጅግ የተጋነነና ተግባራዊ ሊሆን የማይችል ነው ሲሉ ሰሞኑን በባህርዳር ከተማ በተካሄደ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ያተኮረ ስብሰባ ላይ የተሳተፉ አንድ የኢኮኖሚ ባለሙያ አስተያየታቸውን …

መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዋጋ ቁጥጥር ውሳኔው አንዳንድ ት/ቤቶች አደናግጦአቸዋል፡፡ መመሪያው ፍትሐዊነት ጎድሎታል ያለውን የግል ትምህርት ቤቶች የክፍያ ሁኔታ ሰርኣት የሚያሲዝ ነው ቢባልም ፣ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ቅሬታቸውን እየገለጹ ነው። አዲሱ መመሪያ ከስርኣተ ትምህርት ውጪ ልዩ ልዩ የትምህርት ኣይነቶችን ማስተማርና ለዚህም ክፍያ መጠየቅ ይከለክላል፡፡ ክፍያ ሲጠየቅ ለ10 ወራት ብቻ መሆኑን፣ …

መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ዓመት በኩዌት ሱላቢካት ከተማ ውስጥ የአሰሪዋን ልጅ የ19 ዓመቷን ወጣት ሲሃም ማህሙድ በስለት በመግደል ወንጀል ተከሳ የነበረችው የ22 ዓመቷ ኢትዮጵያዊት ወጣት ራቢያ ማህሙድ ላይ የተላለፈው የሞት ፍርድ ውሳኔ መፅናቱን የአገሪቱ ፍርድ ቤት አስታውቋል። ግድያውን ለመፈጸም ያበቃት ሟቿ መኝታ ክፍልዋ በተደጋጋሚ ጊዜ በመምጣት በር በመዝጋት ጥቃት …

መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኮንጎ ብራዛቪል አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው በመላው የአፍሪካዊያን ጫወታ ላይ ኢትዮጵያዊያን ሯጮች ድል እየቀናቸው ነው። በ5 ሺ ሜትር የወንዶች የሩጫ ውድድር ጌትነት ሞላ የወርቅ ሜዳሊያ ሲያገኝ፣ ርቀቱን በ 13 ደቂቃ 21 ሰከንድ 88 ማይክሮ ሰከንድ ጨርሷል። ልዑልሲ ገብረስላሴ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል። በ1 ሺ500 ሜትር …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ «ደሚህት»ተብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን መሪ አቶ ሞላ አስገዶም ከተዋጊዎቻቸዉ ጋር ከጥቂት ቀናት በፊት ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋአል።

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በጋራ ላለመስራት ማንገራገር እና አለመፈለግ እና በስሜት መነዳት የፖለቲካ ውጤቱ እና ጠቀሜታው ለጋራ ጠላታችን ለወያኔ ነው::የተቃዋሚ ሃይሎች ጥንካሬ እንዲጎለብት በየድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እንከኖች በማጥራት በጋራ እና በተመቻቸ የሃሳብ መግባባት ተቻችሉ እና ተግባብቶ የትግል ስትራቴጂን ግብ …

ልዩነትን በማቻቻል እና በመከባበር በጋራ መታገል ችላ የማይባል ሃገራዊ አጀንዳ ነው። Read more »

  የማለዳ ወግ …” ሳውዲና ኢትዮጵያ የሰራተኛ ውል አልተፈራረሙም!” ================================== * ” የሳውዲና የኢትዮጵያ የሰራተኛ ውል ተፈረመ! “ወገን ለወገን – በሳውዲ ” ፊስ ቡክ ገጽ * ትክክለኛ መረጃ ህይዎት ነው ፣ የተሳሳተ መረጃ ጎጅ ነው! * የተሳሳተ መረጃ እንዳይጎዳን የመንግስት …

ሳውዲና ኢትዮጵያ የሰራተኛ ውል አልተፈራረሙም! Read more »

መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መስከረም 16፣ 2008 ዓም በደቡብ ክልል በጌዲዮ ዞን ወናጎ ከተማ ከንግድ ቤት ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ውዝግብ አድጎ ወደ ብሄረሰቦች ግጭት በማምራቱ በርካታ ሰዎች ጉዳት ሲደርስባቸው፣ የተለያዩ የንግድ ቤቶችም ተዘርፈዋል። የከተማው ባለስልጣኖች ሆን ብለው ቀስቅሰውታል በተባለው በዚህ ግጭት፣ የአንድ ብሄረሰብ አባላት ነን የሚሉ ሰዎች፣ የሌላ አካባቢ ብሄረሰቦች …

መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ድርጅት፣ ሲፒጄ የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ የሆኑት ቶም ሮድስ፣ የዞን 9 ጸሃፊዎች የዚህን አመት የአለማቀፍ የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ማሸነፋቸውን ተከትሎ ለኢሳት እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ሽልማት የሚገባቸው በርካታ ጋዜጠኞች አሉ ሲሉ ጋዜጠኞች ለፕሬስ ነጻነት እየከፈሉ ያለውን መስዋትነት አወድሰዋል። የዞን ዘጠኝ ጸሃፊዎችን ለመሸለም የፈለግነው በኢትዮጵያ …

መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፊታችን መስከረም 24 ቀን በኢህአዴግ መቶ በመቶ የተያዘው ፓርላማ ስራ ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የአቶ ሃይለማርያም የጠ/ሚኒስትርነት ሹመት ካጸደቀ በሃላ በጠ/ሚኒስትሩ አቅራቢነት የሚካሄደው የካቢኔ ሹም ር አዲስ ነገር ይዞ አይመጣም ተብሎአል። ለግንባሩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ለአዲስአበባው ዘጋቢያችን እንደተናገሩት ግንባሩ በሙስናና በመልካም አስተዳደር ችግሮች በተጨማለቁ የካቢኔ አባላት …

መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ድርጅትን እንዲያስተዳደር ለሁለት አመታት 21 ሚሊዮን 700 ሺ ዶላር ወይም ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ የተከፈለው ፓወር ግሪድ ይህ ነው የሚባል ስራ ሳያከናውን ተሰናብቷል። በአገሪቱ ውስጥ የሚታየው የመብራት መጥፋት ሊሻሻል ካለመቻሉ ጋር ተያይዞ፣ ቀድሞውንም ይህን ያክል ገንዘብ ማውጣት ለምን አስፈለገ የሚል ጥያቄ አስነስቷል። ስራ …

  በሃገር ቤት የሚንቀሳቀስ ፓርቲዎች ናቸው የተባሉ አራቱ በሕዝብ ዘንድ የተጠሉ እና የተተፉ ታማኝ ተቃዋሚዎች የወያኔ የፕሮፓጋንዳ ማድነቂያ ሆነዋል::ይህ ሰሞ ከአዲስ አመት ይልቅ በአዲሱ የሞላ ፕሮፓጋንዳ እየጎዳደለ የሚገኘው ወያኔ ደልሎ ይሁን ገዝቶ አፍኖ ይሁን መንገድ አሳስቶ ያመጣውን ሞላን እንደ ትልቅ …

አደርባይ ታማኝ ተቃዋሚዎች ከሃዲዎችን ማንቆለጳጰሳቸው የተለመደ የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ነው::(ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

– በወያኔ የአዲስ አመት ግብዣ ላይ አንድ ወጣት ተደበደበ የደረሰበትም አልታወቀም – ወያኔ የውሻ ምዝገባ እጀምራለሁ አለ – በአዲስ አበባ የአዕምሮ በሽተኞች ሊታፈሱ ነው – የአይቮሪ ኮስት ፕሬዚዳንት እርቅ እንዲወርድ ጥሪ አደረጉ – አማጽያኑ ስምምነቱን ጥሰው ጥቃት ፈጽመዋል በሚል የደቡብ …

ወያኔ የውሻ ምዝገባ እጀምራለሁ አለ – በአዲስ አበባ የአዕምሮ በሽተኞች ሊታፈሱ ነው:: Finote Democracy News Read more »

Minilik Salsawi – ከተለያዩ የኢሕአዴግ ካድሬዎች በተለያዩ የማህበራዊ ድህረገጽ የተሰበሰበ መረጃ እንደሚያመለክተው ኢሕአዴግ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እየሰራ ያለው ፕሮፓጋንዳ ኪሳራ እንደሆነ ካድሬዎቹ እየተናገሩ ነው::ካድሬዎቹ ድርጅታቸው የሚሰራው ዶክመንተሪ ፊልም አሊያም ቃለመጠይቅ እንዲሁም ሃተታና መግለጫ በሕዝቡ በተቃራኒው እንደሚተረጎም እና ተቀባይነት እንዳሌለው በደንብ …

ኢሕአዴግ እየሰራ ያለው ፕሮፓጋንዳ ኪሳራ እንደሆነ ካድሬዎቹ እየተናገሩ ነው:: Read more »

የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምጽ የሳምንቱን ዜናዎች ትረካዎችን እንዲሁም ዝግጅታችንም በሙዚቃዎች ታጅቦ ቀርቧል [youtube http://www.youtube.com/watch?v=wslR2idxuIc]

Minilik Salsawi መልካም እና ጽኑ ታጋዮች እንደተጠበቁ ሆነው በስለናል የትግል ልምድ አለን ከሚሉ ፖለቲከኞች ጀምሮ እዚህ ግቡ የማይባሉ ገደል ማሚቱዎች ድረስ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ቦርቅቀው ለማተራመስ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም::ከኛ በላይ ላሳር የሚሉ እንጭጭ ፖለቲከኛ ነን ባዮች ጥቂቶች ሰፊዉን ሜዳ በተግባር ኣልባ …

ሊቆም የሚገባው ጥላቻ ምቀኝነት ቅናት ክፋት እና ግለኝነት የተጠናወተው ፖለቲካ ( ‎ምንሊክ ሳልሳዊ‬ ) Read more »

በመሀል አዲስ አበባ ለዘመናት ታጥረው በተቀመጡና ግንባታ ባልተካሄደባቸው ቦታዎች ላይ ጠበቅ ያለ ዕርምጃ እንደሚወስድ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡ 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሀል አዲስ አበባን በድጋሚ መገንባት ያስፈልጋል በማለት ነዋሪዎችን ማስነሳቱ ይታወሳል፡፡ አስተዳደሩ በርካታ ኪስ ቦታዎችን ለባለሀብቶች ቢሰጥም፣ ባለሀብቶቹ ግንባታ ከማካሄድ ይልቅ አጥረው የያዟቸው ቦታዎች በርካታ ናቸው፡፡ 

እነዚህ ሕግን ያልተከተሉ አሠራሮች በነዋሪዎች ላይ ቅሬታ እያሳደሩ መሆኑ በተገኙ መድረኮች እየተገለጸ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ የ2007 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ካካሄደ በኋላ፣ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ አሠራሩን ማጥበቅ እንደሚያስፈልገውና የወጡ ሕጐችን በብቃት ማስፈጸም እንደሚገባ መግባባት ላይ መድረሱን አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኃየሎም ጣውዬ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ለመልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች ተይዘው ወደ ግንባታ ያልተገባባቸው ቦታዎች ያለባቸውን ችግር በተቀናጀ መንገድ ለመፍታት በዓመቱ ወደ ሥራ ለመግባት ታቅዷል፡፡ በዚህ መስክ ያለውን ችግር አቶ ኃየሎም ሲያስረዱ፣ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ አስፈላጊውን ሥራ ቀደም ብሎ ማጠናቀቅ ቢችልም ለተወሰኑ ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤት የማቅረብ ችግር አጋጥሟል፡፡ ‹‹ከዚህ በተጨማሪም ሙሉ በሙሉ ቦታው እስኪፀዳም ግንባታ በመጀመር በኩል መጓተት አለ፡፡ ይህንን ችግር ለመፍታት ከመሠረተ ልማት ተቋማት ጋር በጋራ መሥራት ይኖርብናል፡፡ መንግሥታዊ ተቋማትም በተሰጣቸው ቦታ ላይ ተነሺዎችን በማይጐዳ ሁኔታ ግንባታ እንዲካሄዱ እናደርጋለን፤›› ብለዋል፡፡ 

በርካታ አልሚዎች የወሰዷቸውን ቦታዎች አጥረው ማስቀመጣቸውን በተመለከተም፣ ‹‹በዚህ በኩል ያሉ ችግሮችን በመለየት ውል እንዳይራዘም በማድረግ መሬቱን ወደ መሬት ባንክ የማስገባት ሥራ ይሠራል፤›› በማለት አቶ ኃየሎም ተናግረዋል፡፡ መሥሪያ ቤታቸው ከወትሮው በተለየ ዘንድሮ ጠንካራ ዕርምጃዎችን እንደሚወስድ አስገንዝበዋል፡፡ 

በመልሶ ማልማት ሥራ ከተያዙት አንዱ የሸራተን አዲስ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ይገኝበታል፡፡ ለዚህ ቦታ በ2002 ዓ.ም. ነዋሪውን የማንሳት ሥራ ቢጠናቀቅም በዚህ ቦታ ላይ የሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ጋራዥ ባለመነሳቱ ብቻ ወደ ግንባታ ሳይገባ ቆይቷል፡፡ የፌዴራል ፖሊስ ተለዋጭ ቦታ የተሰጠው የራሱን ግንባታ ሳያካሂድ ከዚህ ቦታ ላይ የመነሳት ፍላጐት አላሳየም ተብሏል፡፡ ነገር ግን የአካባቢው ነዋሪዎች ቦታውን ከለቀቁ ከአምስት ዓመት በላይ ተቆጥሯል፡፡  

ከዚህ በተጨማሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስፋፊያ፣ አሮጌው ቄራ ቁጥር አንድና ቁጥር ሁለት ማስፋፊያ፣ ተክለ ሃይማኖት መልሶ ማልማት፣ ሸበሌ ሆቴል ጀርባ መልሶ ማልማት ቦታዎች ይገኛሉ፡፡

እነዚህና ሌሎች በሒደት ላይ ካሉ የመልሶ ማልማት ቦታዎች ላይ ነዋሪዎች እንዲነሱ ቢደረግም፣ የተወሰኑ መኖሪያ ቤቶችንና መንግሥታዊ ተቋማትን ማንሳት ባለመቻሉ ቦታዎቹ ታጥረው ለዓመታት እንዲቀመጡ ምክንያት ሆኗል፡፡ ይህም የነዋሪዎችን ኑሮ አስቸጋሪ ከማድረጉም በላይ በተነሱበት ምክንያት ላይም ጥያቄ እያነሱ እንደሚገኝ እየተገለጸ ነው፡፡ አቶ ኃየሎም እንዳሉት በአሁኑ ወቅት ከመሠረተ ልማት ድርጅቶች ከኤሌክትሪክ፣ ከውኃ፣ ከቤቶች ልማት ጋር በተጠናከረ ሁኔታ በጋራ በመሥራት መሬቱን ነፃ በማድረግ ወደ ልማት ለማስገባት እየተሠራ ነው፡፡

‹‹አስቸጋሪ ሁኔታ እንኳ ቢፈጠር ግንባታውን ከሥር ከሥር ለማካሄድ ዕቅድ ተይዟል፤›› በማለት አቶ ኃየሎም የዘንድሮን ዕቅድ አስረድተዋል፡፡

ከንቲባ ድሪባ ኩማ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ፣ 360 ሔክታር መሬት በመልሶ ማልማት ፕሮግራም ለማልማት ታቅዷል፡፡ ይህ ልማት የሚካሄደው እንደ አዲስ ሲሆን፣ ለቦታው ለቤቶች ልማት፣ ለቢዝነስና ለባለ ኮከብ ሆቴል የሚውል ነው፡፡  በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለ90 ባለሀብቶች የተሰጠ መሬት ግንባታ ያልተካሄደበት በመሆኑ መናጠቁን ገልጸዋል፡፡

ከንቲባው እንዳሉት፣ በተካሄደው ግምገማ በአዲስ አበባ ከተማ መሬት ወስደው ግንባታ ያላካሄዱ አልሚዎች ከፍተኛ አቅም ያላቸው ናቸው፡፡ እነዚህ አልሚዎች ለምን ግንባታ እንዳላካሄዱ በሚመረመርበት ወቅት የከተማው አስተዳደር ችግር አንዱ ምክንያት ሆኖ ተገኝቷል፡፡ 

በዚህ ምክንያት አስተዳደሩ ያለበትን ችግር በመቅረፍ በዚህ ዓመት ወደ ግንባታ እንዲገባ ግፊት እንደሚደረግ፣ አልሚዎቹ ወደ ግንባታ የማይገቡ ከሆነ ግን ዕርምጃ ይወስዳል በማለት ከንቲባው አስረድተዋል፡፡ 

 

መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ የቀድሞው የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( ትህዴን) ሊቀመንበር አቶ ሞላ አስጎደም ለ14 ዓመታት የነበሩበትን ድርጅት ከድተው ለኢህአዴግ ባለስልጣናት እጃውን መስጠታቸውን ተከትሎ ገዢው ፓርቲ እየሰራ ያለው የቅስቀሳ ስራ በህዝብ ዘንድ የተለያዩ አስተያየቶችን እያስተናገደ ነው። የመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ትህዴን የአርበኞች ግንቦት7 አንድ የጦር ክፍል እንደሆነ አድርገው ማቅረባቸው፣ …

መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ከሆኑት መካካል ኡስታዝ ያሲን ኑሩ፣ ሳቢር ይርጉ፣ አቡበከር ዓለሙ እና ገጣሚው ሙኒር ሁሴን ከእስር መለቀቃቸውን አስመልክቶ ድምፃችን ይሰማ ባወጣው መግለጫ፣ ሁሉም እስረኞች ካለምንም ቅድመ ሁኔታዎች እስካልተፈቱ ድረስ ትግላቸው እንደሚቀጥሉ በአጽንኦት ገልጿል። ድምፃችን ይሰማ ፣ ” ተፈቺዎቹም ይሁኑ ታሳሪዎቹ ጀግኖቻችን ሃይማኖታችን በተደፈረበት፣ …

መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በለቡ መዝናኛ ውስጥ ከሴት ጓደኛዋ ጋር በመዝናናት ላይ የነበረችው ሰሎሜ ጉልላት የተባለችው የ20 ዓመት ወጣት ”አንቺ ሰው የማታናግሪው ለምንድ ነው?” በሚል ተልካሻ ምክንያት መሳሪያ የታጠቀው የፌደራል ፓሊስ አባል ተኩሶ ገድሏታል። ታጣቂው በወቅቱ እራሱንም ለማጥፋት ጭንቅላቱ አካባቢ ላይ ያቆሰለ ሲሆን፣ ሳይሞት በሕይወት መትረፉንና በሕክምና ላይ እንዳለ ለማወቅ …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ኛ የወንጀል ምድብ ችሎት በብርሃኑ ተክለ ያሬድ መዝገብ በተከሰሱ አራት የሰማያዊ አመራር አባላት ላይ ብይን ለመስጠት ዛሬ ቢሰየምም ለውሳኔው ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ።

እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ለህዳር 21 ተቀጠሩ ‹‹የሽብር ተከሳሽ በመሆናችን ህክምና ተከልክለናል›› ተከሳሾቹ በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን አቋርጠው ኤርትራ የሚገኘውን ግንቦት ሰባት የተባለ በተወካዮች ም/ቤት ሽብርተኛ የተባለ ድርጅትን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ በድጋሜ ለብይን …

ድንበርን አቋርጠው ሽብርተኛ ድርጅትን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል የተከሰሱ ለህዳር 21 ተቀጠሩ:: Read more »

Minilik Salsawi – መጀመሪያ ማወቅ ያለብን የማያቋርጠው ትግላችን ፍሬ እያፈራ መሆኑን እና ጥንካሬን እያላበሰን መሆኑን አንዘንጋ::በአዲስ አመት 2008 መምጫ ላይ የወያኔው ጉጅሌ መንግስት በሰጠው መግለጫ (በምሕረት?)ፈታሄቸው ያላቸው ኢትዮጵያውያን እስረኞች የተፈተቱት ሕዝቦች ግፍን ላለመቀበል በጋራ ባደረጉት ትግል ጫና እንጂ በወያኔ አምባገነናዊ …

የተፈቱ እስረኞች በማያቋርጥ የትግል ውጤት ሂደት እንጂ በወያኔ የዋህነት አይደለም:: Read more »

‹‹በትጥቅ ትግል የሚያምኑ ሰዎች ስኬት የራቃቸው በሰላማዊ ትግል ምክንያት አድርገው ካሰቡ ስህተት ነው፡፡ በሰላማዊ ትግል የምናምን ሰዎችም በትጥቅ ትግል ምክንያት ሊሳካልን እንዳልቻለ ካሰብን ስህተት ነው፡፡›› አንዱዓለም አራጌ (የሀገር ፍቅር ዕዳ) ይችን ርዕስ በአንድ ወቅት እጅግ የማከብረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተጠቅሞባት …

ኑ! እንወቃቀስ! (ጌታቸው ሺፈራው) Read more »

ሰሎሜ ጉልላት የተባለችው የ20 ዓመት ወጣት ከጓደኛዋ ጋር በመሆን በለቡ ኮንዶሚኒየም ቤቶች አካባቢ በሚገኝ የጓደኛቸው መዝናኛ ውስጥ በመዝናናት ላይ እያሉ ነው ከተጠርጣሪው ገዳይ ጋር የተገናኙት፡፡ ለጊዜው ስሟን መናገር ካልፈለገችው ጓደኛዋ መረዳት እንደተቻለው፣ የፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሰው ግለሰብ ከዚህ ቀደም ሰሎሜን …

ወጣት ሶሎሜን የገደላት ፖሊስ ጭንቅላቱን በጥይት መትቶ ራሱን ለማጥፋት ሞክሮ ተርፏል:: Read more »

በፍኖተ-ዴሞክራሲ ሬዲዮ ለቀረበው ውንጀላ የተሰጠ አጸፋዊ መልስ ሠሞኑን የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ንብረት የሆነው «ፍኖተ-ዴሞክራሲ» በመባል የሚታወቀው የሳተላይት ሬዲዮ ጣቢያ በዐማራው ነገድ ተወላጆች ላይ የጅምላ ክስ አቅርቧል። ክሱ «በአማራ ሕዝብ ስም ሌሎችን መዝለፍ የሚወገዝ ነው» በሚል ርዕስ ያዘጋጀውንመግለጫ ነሐሴ ፳፪ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም. በሬዲዮ አስተላልፏል[1]፤ በጽሑፍ ደግሞ በተባባሪ ድረ-ገፆች «አሲምባ[2]» እና «ደብተራው[3]»አሠራጭቷል። ከሁሉም የሚያሣዝነው […]

ኢትዮጵያ ውስጥ እያደገ የመጣው የሰብዓዊ ዕርዳታ ፍላጎት ከሚሰጠው ምላሽ ጋር ሊጣጣም እንዳልቻለ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ – ኦቻ የአዲስ አበባ ፅሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

(ሪፖርተር፤ ነአምን አሸናፊ፤ መስከረም ፪ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.) የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፖፕ እና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ካልዕ፣ በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ላይ ለመታደም እና የአራት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ፣ መስከረም ፲፭ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. ከቤተ ክርስቲያኒቱ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋር በመኾን አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡ ፓትርያርክ አቡነ ቴዎድሮስ አራት ቀናት …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

“በምህረት” እንዲፈቱ ከተወሰነላቸው ኡስታዞቻችን እና ወንድሞቻችን መካከል አራቱ ተፈቱ! አቡ ዳውድ ኡማን በሃሰት በሽብር ወንጀል የተፈረደባቸው በኡስታዝ አቡበከር አህመድ መዝገብ ከሚገኙት ኮሚቴዎቻችን እና ወንድሞቻችን መካከል ስድስት የሚሆኑትን አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ በይቅርታ መንግስት እንደፈቱ መወሰኑን መዘገቡ የሚታወስ ሲሆን እስከዛሬ ድረስ …

“በምህረት” እንዲፈቱ ከተወሰነላቸው በኡስታዝ አቡበከር አህመድ መዝገብ በሃሰት የተፈረደባቸው መካከል አራቱ ተፈቱ! Read more »

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌዴራል የሥነምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን የባለስልጣናትን ሐብት ምዝገባ ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ እንደተሳነው የኮምሽኑ ምንጮች አጋለጡ፡፡ ለጠ/ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆኑትን የኮምሽኑ ኮምሽነር ዓሊ ሱሌይማን ትዕዛዝ ተቀብለው ብቻ የሚያስሩና የሚፈቱ በመሆናቸው በአዋጁ መሰረት ለህዝብ ይፋ መደረግ የነበረበት የባለለስጣናት የሐብት ምዝገባ በወቅቱ ለማከናወን ድፍረት ማጣታቸው ታውቆአል፡፡ የሐብት ምዝገባ ሥራን በኢንፎርሜሽን …

የኢትዮጵያ፤ የሱዳንና የግብፅ የጋራ ኮሚቴ ባለፈዉ መጋቢት ጥናቱን እንዲያደርጉ የመረጣቸዉ ሁለቱ ኩባንዮች የጥናት ዉጤታቸዉን ባለፈዉ ነሐሴ ማብቂያ ለኮሚቴዉ ማቅረብ ነበረባቸዉ

”ከሚያዚያ ወር ጀምሮ የ7ዓመት ግምገማ እያደረግን ቆይተናል። በዚህም ሞላ በፖለቲካ አመራር ድርጅቱን አዳክሞታል የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰናል። ሰራዊቱ የአመራር ለውጥ በሚፈልግበት ጊዜ ላይ በተካሄደው በዚሁ ግምገማ ሞላ ከፍተኛ ተቀውሞ ከድርጅቱ አመራሮችና አባላት ደርሶበታል። ” ”ይዞ የወጣው ታጋይ ቁጥሩ ተጋኗል። ያም ቢሆን ለስራ ተብለው(የኪነት ቡድኑ ለበዓል) የተታለለ ነው። በተቻለን መጠን አብዛኛውን መልሰናል። የተዋጋው ከእኛው ጋር ነው። […]

መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፋይናንሻል ታይምስ እንደዘገበው ባለፈው ታህሳስ ወር 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዳላር ከግል ባንኮች የተበደረው መንግስት፣ ተጨማሪ በድር ለመውሰድ እንቅስቃሴ ጀምሯል። በሚቀጥለው ሳምንት የመንግስት ባለስልጣኖች ከአበዳሪ ተቋማት መሪዎች ጋር ለንደን ውስጥ ይገናኛሉ። ላዛርድ የተባለ የመንግስት የገንዘብ አማካሪ ድርጅት ባለስልጣኖቹን ከጀርመኑ ዶች ባንክና ከአሜሪካው ጄፒ ሞርጋን ሃላፊዎች ጋር እንደሚያገናኛው የዘገበው …

መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቀድሞው የህወሃት አባልና በሁዋላም የአፋር ፓርቲ መስርተው የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆነው ለ20 አመታት በስልጣን ላይ የነበሩት አቶ እስማኤል አሊ ሴሮ ከስልጣናቸው ከተነሱ በሁዋላ፣ የአብዴፓ ሊቀመንበር ሆነው በተመረጡት በአቶ ጠሃ ሙሃመድ ቡድንና በአቶ አሊ ሴሮ ቡድን መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል። የውዝግቡ መነሻ አቶ ጠፋ የክልሉ ፕሬዚዳንት ሊሆኑ …

መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በንግድ ስራ የምትደዳረዋ ካሚል ሙሃመድ ታውኒ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አላት በሚል በኬንያ ልዩ ፖሊስ ተይዛ ለሶማሊና ለኢትዮጵያ መንግስታት ተላልፋ መሰጠቷን ተከትሎ ሰቆቃ እንደተፈጸመባት ተናግራለች። ቃሏን ለፍርድ ቤት ስታሰማ እንባዋ ያቋርጣት እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል። ወ/ት ትዌኒ የህክምናዋን ወጪ ለመሸፈን የኬንያ መንግስት የገንዘብ ካሳ እንዲሰጣት ፍርድ ቤትን ጠይቃለች። ፍርድ …

በእናት ሃገራችን ኢትዮጵያ ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘው የሕወሓት አምባገነን ቡድናዊ አገዛዝ በሕዝብ ላይ የሚፈጽመው የፖለቲካና የኢኮኖሚ በደል ገደቡት አልፎ ዜጎች በገዛ አገራቸው መኖር እንዳይችለ ሆነዋል:: በሃገራችን ተከስትው ይሚገኙ የፖለቲካ ጫናዎች የኑሮ ውድነት የድርቅ እና የተለያዩ ችግሮች አገዛዙ በሚፈጽመው በደል ላይ ተደራርበው …

የህዝብን ዝምታ ሰብሮ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የለውጥ ሃይሎች በጋራና በጽናት እንጓዝ:: (ምንሊክ ሳልሳዊ‬ ) Read more »

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በማዕከላዊ ሶማሊያ ሂራን ግዛት ራሶ መንደር አቅራቢያ የ20 ና የ25 ዓመት ወጣት የሆኑት ወንድማማቾች ሶማልያዊያንና አንድ ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ በአልሸባብ ታጣቂዎች በግፍ ተገለው ተገኝተዋል። ሁለቱ ወንድማማቾች ባለፈው ሳምንት ነበር በቡቃበል ከተማ ውስጥ በድንገት የኢትዮጵያ ወታደሮችና የሶማሊያ መንግስት ሰራዊቶች አካባቢውን ለቀው ሲወጡ በአልሸባብ ሚሊሻዎች ታግተው የተያዙት። የአካባቢው …



አንድ ጆሮና ጊዜ የገጠሙለት ሰው ነበር አሉ፡፡ ሰውዬው የተማረው ትምህርት የለውም፡፡ ሁለት ችሎታ ግን ነበረው፡፡ ሲባል የሰማው እውነትም ይሁን ስሕተት ልቅም አድርጎ ይይዝና ሌላ ቦታ ሄዶ የተማረው ያህል ያንደቀድቀዋል፡፡ ሁለተኛው ችሎታው ደግሞ አፈ ጮሌ ስለሆነ ነገር በምላሱ ይቆላል፡፡ ያንንም ይኼንንም እያቆላመጠ ከተማሩትና ከተመራመሩት በላይ ከብሮና ታፍሮ ይኖራል፡፡ አንድ ቀን የማያውቀውን ቀለም ሲያዜም የሰሙት ሊቅ አፍረው አቀረቀሩ፡፡ እርሱ ግን ከዕውቀት የደነገለ ነበርና አልገባውም፡፡ በኋላ ቀረብ ብሎ ‹ደኅና ነዎት የኔታ› አላቸው፡፡ እርሳቸውም ‹ደኅና ነህ›› ብለው ዝም አሉት፡፡ እርሱም ያላወቁት ስለመሰለው ‹አላወቁኝም መሰል መሪጌታ እኮ ነኝ› አላቸው፡፡ሊቁም ‹ዐዉቄሃለሁ› አሉት፡፡ እንዳቀረቀሩ፡፡ ‹ታድያ ምነው ካወቁኝ ከነ ማዕረጌ ሳይጠሩኝ ቀሩሳ› አላቸው፡፡ ‹አንተን አከብራለሁ ብዬ ሞያውን እንዳልሰድበው ፈርቼ ነው›› አሉት ይባላል፡፡
 
እኔም ‹እርቲስቶቻችን› የሚለው ቃል በትእምርተ ጥቅስ ያደረግኩት ሊቁ የፈሩትን ፈርቼ ነው፡፡ እንዳልተውባቸው ደግሞ ምን ብዬ እንደምጠራቸው ግራ ገብቶኝ፡፡ የአዲስ ዓመት ዋዜማውን መርሐ ግብር በዕለቱ ለማየት ስላልቻልኩ ቪዲዮውን ነው የተመለከትኩት፡፡ ሊነግሩን የፈለጉት ስለ እድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ፣ ስለ ሀገራችን ዕድገት፣ ስላለፈው ስኬታችን ቢሆንም እንኳን የቀረበው ዝግጅት ግን አደገች የምትባለውን ኢትዮጵያን የማይመጥን፣ ጥበብ ዞር ብላ ያላየቺው፣ ከንግግር ከፍ፣ ከፉከራ ዝቅ ያለ፤ ከፕሮፓጋንዳ ወረድ፣ ከዲስኩር ራቅ፣ ከድንፋታ ጠጋ ያለ ወለፈንዲ ሆኖ ነው የታየኝ፡፡ 
 
በሀገራችንኮ የልቅሶ ሥነ ሥርዓት እንኳን ወግ አለው፤ ጥበብ አለው፤ ትርዒት አለው፤ ፍሰት አለው፤ ድባብ አለው፤ ፈጠራ አለው፤ ርቀት አለው፣ ምጥቀት አለው፤ ደረጃ አለው፡፡ ይኼኮ ወግ የለው፣ ጥበብ የለው፣ ትርዒት የለው፣ ፍሰት የለው፣ ፈጠራ የለው፣ ደረጃ የለው፡፡ ድፍረት ብቻ፡፡ መሪዎቻችን ግን ለምንድን ነው የጥበብ አማካሪ የማይኖራቸው? ለምንድን ነው ጥበብን ከሚሰድቡ ሰዎች ጋር አብረው የሚቆሙት? ለምን ‹አርቲስቶቹን› እናከብራለን ብለው ሞያውን ይሰድቡታል? ይህቺ ሀገርኮ ሰማየ ሰማያት ደርሰው የመጡ፣ ድንጋዩን አቅልጠው ጥበብ የሚያፈልቁ፣ አራት ጸሐፊ አስቀምጠው አንድ አንድ ምዕራፍ እየነገሩ መጽሐፍ የሚያስጽፉ፤ መሰንቆ እንደ ሰው፣ ክራር እንደ ወፍ፣ በገና እንደ መልአክ የሚያናግሩ፤ ስንትና ስንት ጠቢባን ነበሩባት፡፡ ከሐይቅ ዳር የሸንበቆ ውዝዋዜ ተነሥተው ኅሊና የሚመስጥ አቋቋም የቀመሩ፣ እያዜሙ ሲሄዱ እንኳን ገበሬውን በሬዎቹን የሚያስደምሙ ጠቢባን ነበሩባት፡፡ እንዴት በጥበብ ሀገር በኢትዮጵያ ጠቢብ ነኝ የሚል ሰው ‹ከዕውቀት ርቆ፣ ንጽሕ ጠብቆ› በድፍረት ይኖራል? ይኼኮ ሀገርን መድፈር ነው?  
አገሪቱ አድግበታልሁ፣ እመነደግበታለሁ፣ እለወጥበታለሁ፣ አሰላለፌን አስተካክልበታለሁ ብላ የደከመችበት የአምስት ዓመት ዕቅድ እንዴት በስሕተትና በድፍረት በተሞላ መድረክ እንዲታወጅ ይፈቀዳል? ይህንን ዕቅድ ባስታወስን ቁጥር ያንን ትልቅ ስሕተት እንድናስታውስ ለምን ተፈረደብን? ጥበብ ሳይሆን ድፍረት ትዝ እንዲለን ለምን ተገደድን? 
 
ጥበብ ምንም ዓይነት ይዘት ይኑረው የጥበብን ደረጃ ማሟላት ግን አለበት፡፡ ልማታዊም ሆነ አብዮታዊ፣ ዲሞክራሲያዊም ሆነ አምባገነናዊ፣ ይዘቱ ይለያይ እንጂ የጥበብ ደረጃው ግን አንድ ነው፡፡ ጥበብም የሚያሰኘው የጥበቡ ደረጃ እንጂ የያዘው ይዘት አይደለም፡፡ እንዴት ምግብ ቤቶቻችን ለምግብ አሠራርና አቀራረብ የሚጨነቁትን ያህል ለሀገራዊ መድረክ የሚጨነቅ ይጥፋ? እንዴት የበያይነቱ ምግብ ያህል ጥበብ በሀገራዊ መድረክ ላይ እንጣ?
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹ሀገራችን የራስዋ የሆነ ልዩ የዘመን አቆጣጠር አላት› ብለው ነገሩን፡፡ እውነት ነው ጠቅላይ ሚኒስትራችን የሀገር ባህል ልብስ ለብሰው በነገሩን የሀገራችን ልዩ የዘመን ቆጠራ እንስማማለን፡፡ ‹አርቲስቶቹ›› ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሳስተዋል፤ ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ የዘመን አቆጣጠር የላትም›› አሉን፡፡ ‹‹አዲስ ዘመንም የሚብተው እንደ አውሮፓውያን በእኩለ ሌሊት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችን የዘመን አቆጣጠራችን የተለየ ነው ያሉት ተሳስተው ነው›› አሉን፡፡ ኧረ እባክዎን ይጠይቁልን? ለምን ‹‹አርቲስቶቹ›› ጠቅላይ ሚኒስትሩን መቃወም ከፈለጉ የፖለቲካ ድርጅት መሥርተው በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው ተቃዋሚ ፓርቲ አያቋቁሙም? ደግሞስ ለሌሎች ያልተፈቀደ እንዴት ለእነርሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የቀጥታ የዓመት በዓል ሥርጭት እንዲቃወሙ ተፈቀደላቸው? እንደ አሜሪካ የምርጫ ክርክር በቀጥታ ሥርጭት ተቃዋሚና መንግሥት በአንድ መድረክ የሚቀርቡ ከሆነማ እውነትም ሀገሬ ተለውጣለች?
 
የዛሬ ዓምስት ዓመት እንዲሁ ያለ ስሕተት ‹አርቲስቶቹ› ሲሠሩ ዐውቀው በድፍረት ሳይሆን ሳያውቁ በስሕተት ነው ተብሎ ታለፈ፡፡ ዘንድሮ እንዳይደገምም ብዙዎች በሚችሉት ሁሉ አስቀድመው አሳሰቡ፡፡ ሰሚም መስሚያም ጠፋና ስሕተቱ በባሰ ሁኔታ ተደገመ፡፡ ሰውና ሰይጣን የተለያዩትኮ ከስሕተት በመታረምና ባለመታረም ነው፡፡ ወደ ሥልጣኔው መሄድ ሲገባን ወደ ስ…   
ጠቅላይ ሚኒስትር ሆይ፤ አሁን ማንን እንመን? እርስዎን እንመን ወይስ ‹አርቲስቶቻችንን››?
  

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “ስለሚያገባን እንጦምራለን” በሚል መሪ ቃል ከዛሬ አራት ዓመት በፊት የተቋቋመው የዞን ፱ ዐምደ መረብ ጸሃፍት የሕገመንግስቱ የመጻፍ ነጻነት በሚፃረረው መልኩ እንደ ሌሎቹ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በአሸባሪነት ተከሰው ካለ ፍትሕ በእስር ቤት የሚገኙት ጦማሪያኑና የቡድኑ አባላት ለፕሬስ ነፃነት ላደረጉት አስተዋፆ ዓለማቀፉን የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ተሸላሚ አድርጓቸዋል። የጋዜጠኞች መብት …

“አንድነት በምናስብበት ወቅት ምንግዜም ሁለት እኩል ባለመብት ሰወችን እያሰብን መሆን አለበት፥፥ ልዮነት ራሱ የተፈጥሮ ባህሪ ነው፥፥ ላይ ላዩን ለሚመለከት አንድነት እና ልዩነት ተቃራኒ ብቻ ናቸው፥፥ ጠለቅ ብሎ ለሚመለከት ግን ልዩነት የ አንድነት መሰረት ስለሆነ አንድነት ትርጉም እና ሃይል ሊኖረው የሚችለው …

አንድነት እና ልዩነት በፕሮፌሰር መስፈን ወልደማሪያም Read more »

CPJ Zone 9 Bloggers Ethiopia - CPJ will honor Zone 9 bloggers with 2015 International Press Freedom Awards.

የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የሲፒጂ አለማቀፍ የፕሬስ ነጻነት የ2015 ሽልማት ተሸላሚ ሊሆኑ ነው:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪- CPJ will honor Zone 9 bloggers with 2015 International Press Freedom Awards. Minilik Salsawi – “ስለሚያገባን እንጦምራለን!” በማለት ለሕዝብ የዲሞክራሲን እና የሕግ ጽንሰ ሃሳብን በዳበረ መልኩ …

የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የሲፒጂ አለማቀፍ የፕሬስ ነጻነት የ2015 ሽልማት ተሸላሚ ሊሆኑ ነው:: Read more »