የ1436ኛው የኢድ አድሃ በአል በኢትዮጵያ በድምቀት የተከበረ ሲሆን ፖሊሶች ለመተናኮስ ሲሞክሩ ታይተዋል:: (ምንሊክ ሳልሳዊ)

የ1436ኛው የኢድ አድሃ በአል በኢትዮጵያ በድምቀት የተከበረ ሲሆን ፖሊሶች ለመተናኮስ ሲሞክሩ ታይተዋል:: (ምንሊክ ሳልሳዊ)

 

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የክልል ከተሞን(በመላው ኢትዮጵያ) የኢድ አል አድሃ በአል በደመቀ ሁኔታ የተከበረ ሲሆን ህዝበ ሙስሊሙ በተለመደው መልኩ በሰላም በፍቅር እና በትእግስት የስላቱን ፕሮግራም አጠናቆ ወደ ቤቱ ሲመለስ በአንዳንድ አከባቢዎች ፖሊሶች ለመተናኮል ቢያስቡም እጅግ የሰላም እና የፍቅር ባለቤት የሆነው ሙስሊሙ በሰላም ወደየቤቱ የገባ ሲሆን ፊዳከ የሚል ቲሸርት ለብሰው ወደ አዲስ አበባ ስታዲዬም ለኢድ ሰላት ለመስገድ ሲሄዱ የነበሩ ወጣቶች መታሰራቸው ታውቋል::ፖሊሶች እንደለመዱት መንገድ እየዘጉ ሰው ታክሲ እና መኪና ሲፈትሹ ተስተውለዋል፡፡

ከፍትህ ራዲዮ የተገኘ ዘገባ እንደሚያመለክተው የ1436ኛውም የኢድ አል አድሃ ሰላትን በአዲስ አበባ ስታዲዬም ለመስገድ ወደ ስታዲየሙ ፊዳከ የሚል ቲሸርት በመልሰበት የተጓዙ ወጣት ሙስሊሞች በፖሊሶች መያዛቸውን የአይን እማኞች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡ተመሳሳይ ቲሸርት የለበሱ ሙስሊሞችን ፖሊሶች ከየመሃሉ በማሶጣት እየመለሱ እና እያሰሩ እንደነበር ተዘግቧል፡፤በሌሎች እምነት በአላት ላይ ሁሉም በየአካባቢው ሃይማኖታዊ ጥቅስ ያረፈባቸውን ቲሸርቶች በነጻነት እንደሚለብሱ የሚታወቅ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፊዳከ የሚል ቲሸርት የሚለብሱ ሙስሊሞች እየታሰሩ እንደሚገኝ ታውቋል፡፤ከዚህ ቀደም በሻሸመኔም በተመሳሳይ ፊዳከ የሚል ቲሸርት የለበሱ ሙስሊሞች መታሰራቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡መንግስት በኢድ አል አድሃ በአልም ሙስሊሙን ሰላም ወጥቶ በኣሉን እንዳያካብር የተለመደ ትንኮሳውን አካሂዷል፡፡

Minilik Salsawi's photo.
Minilik Salsawi's photo.
Minilik Salsawi's photo.
Minilik Salsawi's photo.
Minilik Salsawi's photo.