በደመራ በአል ወቅት ረብሻ ሊነሳ ይችላል በሚል ስጋት የፀጥታ ሀይሎች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ መመሪያ ተላለፈ::

በመጪው እሁድ መስከረም 16 ቀን 2008 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ህዝቡ በመንግስት ላይ ጠንከር ያለ ተቃወሞ ሊያስተጋባ እና ለያሰማ ይችላል በሚል ስጋት ውስጥ የወደቀው የህወሃት ኢህአዴግ መንግስት የፀጥታ ሀይሎች የሚላቸው አካላት በተጠንቀቅ እንዲቆሙ መመሪያ መተላለፉን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልፀዋል፡፡

መንግስት ተቃውሞ ይገጥመኛል ብሎ ስጋት ውስጥ ሊወድቅ የቻለው በሊቢያ የተሰውት ሰማዕታትን ለማሰብ በሚል ራሱ መንግስት የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ህዝቡ ያሳየውን ቁጣ ተከትሎ መንግስት በወሰደው የሀይል እርምጃ ብዙዎችን ለጉዳት እና ለእስር በመዳረጉ ምክንያት በዓሉ በሚከበርበት እለት በሊቢያ የተሰው ሰማዕታት ፎቶዎችን በመያዝ ተቃውሞው አይሎ ሊሰማና ለፈጠር ይችላል የሚል ድምዳሜ ላይ መደረሱን ምንጮቻችን አያይዘው ገልፀዋል፡፡