የኔሰው ገብሬ: ነፃነትን በእሳት የተቀዳጀ ሰማዕት!!!
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በመምህር የኔሰው ገብሬ አስደንጋጭ መስዕዋትነት ምክንያት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ይገልፃል። የመምህር የኔሰው ገብሬ መሰዋት ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጆቹና ለዳውሮ ዞን ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ መሪር ሃዘን ነው። በደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት በዳውሮ ዞን የሚገኘው የዋካ ከተማና አካባቢው ህዝብ በአስተዳደር በደል፣ በኑሮ ውድነትና በወረዳ አከላለል መነሻነት ከወር በላይ የዘለቀ […]