በመንገድ ግንባታ የውጭ ኩባንያዎች ብልጫ እንደያዙ ነው
– በ14 ዓመታት ለመንገድ ግንባታ 80 ቢሊዮን ብር ወጪ ሆኗል
በኢትዮጵያ የመንገድ ልማት ፕሮጀክት ባለፉት 14 ዓመታት የተገነቡትና በመገንባት ላይ ላሉ መንገዶች ሥራ ወጪ ከተደረገው 80 ቢሊዮን ብር ውስጥ የውጭ ኮንትራክተሮች 37.7 ቢሊዮን ብር፣ የአገር ውስጥ ኮንትራክተሮች ደግሞ 30 ቢሊዮን ብር ወጪ የሚጠይቁ ግንባታዎችን ማካሄዳቸው ተገለጸ፡፡