የኑሮ ውድነት ፈታኝ የአዲስ አበባ ችግር መሆኑን አስተዳደሩ አስታወቀ

–  ‹‹ዛሬም ከኪራይ ሰብሳቢነት አረንቋ አልወጣንም›› ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ

በዓለም የኢኮኖሚ ቀውስና በንግድና ግብይት ሥርዓት ቅልጥፍና ማነስ ምክንያት በአዲስ አበባ የተከሰተው የኑሮ ውድነት ችግር፣ ፈታኝ ከሚባሉ የከተማዋ ችግሮች መካከል አንዱ መሆኑን ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ አስታወቁ፡፡