በአገራችን ላይ ክፉ ምክር ሲመከር እነሆ ሁለት አስርተ ዓመታት ተቆጠሩ። አንድ ህዝብ የሌላው ህዝብ ጠላት እንዲሆን ተሰብኳል። በህዝብ መካከል ቋሚ ጥላቻን የሚመሰክሩ ሃውልቶችም ቆመዋል። አገሪቷ የነበራት እሴቶች ሆን ተብለው በጥናት ተዘምቶባቸዋል። የአገሪቷ ህግ በአንድ ክፉ ጣኦት ስሜት ተተክቶ ፍትህ በመጥፋቱ ዜጎች ለእስራት፤ ለስደትና ለውርደት ተዳርገዋል። ውርደቱ ወደ ክፉ ሮሮ በመሸጋገሩ ዜጎች እያለቀሱ ነው። መጽሃፈ ምሳሌ […]

የዘረኛው መለስ ዜናዊ አገዛዝ እየፈጸመ ያለውን የአገር ሃብት ዘረፋና የስልጣን ብልግና በመቃወም የመንግሥት ለውጥ እንዲመጣ በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው በመንቀሳቀስ ላይ ያሉትን የፖለቲካ ድርጅቶች ለማጥፋት ሲባል በ3 ተከታታይ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ተቀነባብሮ የተላለፈው የፈጠራ ድራማ ህዝብን በሰፊው እያነጋገረ መሆኑን የግንቦት 7 ዘጋቢ ከአዲስ አበባ በላከው የህዝብ አስተያየት ገለጸ። አኬልዳማ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ድራማ በክፍል አንድና ሁለት ኦነግና […]

ለረጅም ጊዜ በአገራችን ፖለቲካ ሰፊ ጥናት ያካሄዱት ጆን ማርካኪስ “ኢትዮጵያ፣ ዘ ላስት ቱ ፍሮንቲየርስ” የሚለውን አዲሱን መጽሀፋቸውን ለማስተዋወቅ በለንደን ቻትሀም ሀውስ በተገኙበት ወቅት ህወሃት መራሹ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ስልጣን በበቂና ተጨባጭ በሆነ መልኩ ወደ ክልሎችና ወደ ወረዳዎች ለማስተላለፍ ባለመቻሉ፣ የመፈረካከስ አደጋ ተጋርጦበታል ብለዋል። በዚህ ስነሥርዓት ላይ ተመሳሳይ ንግግር ያደረጉት ሌላው ታዋቂ ምሁር ፕሮፌሰር ክርስቶፈር ክላፋም […]

እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር ከትናንትና ወዲያ ማክሰኞ ኖቨምበር 29 ቀን በፍራንክፈርት ጀርመን የተቃውሞ ሰልፉን ያካሄዱት ኢትዮጵያዊያን፤ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ በአገራችን ውስጥ እየፈጸመ ያለው ገደብ የለሽ ግፍና ሰቆቃ እንዲቆም ለመጠየቅ መሆኑን የሰልፉ አስተባባሪዎች መናገራቸውን ዘጋቢያችን ከስፍራው በላከልን ዜና ገልጾአል። የተቃዋሚ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴ ለመግታት በፓርቲ መሪዎች፤ በአባላቶቻቸውና ነጻ ጋዘጤኞች ላይ እየተወሰደ ያለውን እስርና እንግልት አጥብቀን እንቃወመዋለን ያሉት ሰልፈኞች፤ […]

ባለፈው እሁድ ለ11ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በተካሄደው ታላቁ ሩጫ የተሳተፉ ዜጎች፤ ወያኔ መራሹ የመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ በአገራችን ውስጥ እያሰፈነ ያለውን ኢፍትሃዊነትና አፈና የሚያወግዝ መፈክሮችን ሲያሰሙ እንደዋሉ የግንቦት 7 ዜጋቢ ከአዲስ አበባ በላከልን ዜና አስታወቀ። በዚይ የህዝብ ብሶት ሲስተጋባበት በዋለው የሩጫ ውድድር የተሳተፉት፤ ከምዝገባው ጀምሮ በተቻለ መጠን ለወያኔ ፖለቲካ ወገንተኝነት ያላቸው እንዲሆኑ በአዘጋጆች […]

ግርማ ብሩ ይህንን ያስታወቀው በፈረንጆች አቆጣጠር ያለፈው ሳምንት ኖቨምበር 20 ቀን በአትላንታ ከተማ አፍቃሪ ወያኔዎችን የሚላኒዬም ግድብ ብሎ ለተሰየመው ማደናገሪያ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ እንዲሰጡና ዲያስፖራውን በጥቅማጥቅም ለመያዝ በተረቀቀው አዋጅ ላይ ለመነጋገር ጠርቶአቸው በነበረው ስብሰባ ላይ ነው። “መንግሥታችን የህዳሴ ግድብ ብሎ የሰየመውን ይህንን ታሪካዊ ግድብ ለመገደብ ሲነሳ፤ ከናንተ ከዲያስፖራው ህብረተሰብ ወይም አገር ቤት ካለው ህዝብ በሚሰበሰብ […]

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በመምህር የኔሰው ገብሬ አስደንጋጭ መስዕዋትነት ምክንያት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ይገልፃል። የመምህር የኔሰው ገብሬ መሰዋት ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጆቹና ለዳውሮ ዞን ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ መሪር ሃዘን ነው። በደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት በዳውሮ ዞን የሚገኘው የዋካ ከተማና አካባቢው ህዝብ በአስተዳደር በደል፣ በኑሮ ውድነትና በወረዳ አከላለል መነሻነት ከወር በላይ የዘለቀ […]

ላለፉት 20 አመታት በአገራችንና በህዝባችን ላይ በፈጸመው ወንጀል ተረብሾ ህዝብ በማሸበር ላይ የሚገኘው የመለስ ዜናዊ አገዛዝ የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ በሆነው አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት ወንጀል የከሰሳቸው 24 የፖለቲካ ፓርቲ የአመራር አባላት፣ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ አክቲቪስቶች የክስ ቻርጅ በመለስ ዜናዊ ቀጭን ት ዕዛዝ በሚዘወረው የከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል […]

ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ በህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው ግፍና በደል ልኩን አልፎ ከሚሸከመው አቅም በላይ እየሆነ በመምጣቱ ራሱን በቤንዚን አርከፍክፎ ህይወቱን የሰዋውን መምህር የኔሰው ገብሬን የህይወት መስዋዕትነት ለማድበስበስ ወያኔ ሆን ብሎ የፈጠረው ”አይምሮው ጤናማ አልነበረም” የሚለው ሃሰተኛ ማስተባቢያ አገዛዝ ያለበትን የወረደ የዝቅጠት ደረጃ በግልጽ የሚያመላክት ነው በማለት አስተያየት ሰጪዎች ተናገሩ። በዳውሮና አካባቢው የሚገኙና ስማቸው ፍጹም […]

የኢትዮጵያ ጦር ወደሶማሊያ ግዛት ዘልቆ መግባቱን ተከትሎ በአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት የአፍሪካ ተጠሪ የሆኑት ጆኒ ካርሰን ኢትዮጵያ ሶማሊያን ዳግም መውረሯ ፍጹም ትክክል አይደለም ሲሉ ተናገሩ። ጆኒ ካርሰን ይህን የተናገሩት ማክላቺ ከተባለው ጋዜጣ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው። ካርሰን ኢትዮጵያ ከአራት አመት በፊት ሶማሊያን በመውረር ለሁለት አመታት ያክል በአገሪቱ ውስጥ ብትቆይም፣ በመጨረሻ አልሸባብን ከመፍጠር በስተቀር ያመጣቸው […]

ህወሃት ለሁለት በተከፈለበት ወቅት ከነ አቶ ተወልደ ቡድን ጋር በመወገኑ ከሥልጣን ተባሮ የነበረውና ቦኋላ ንሰሃ ገብቶ የመለስ ዜናዊን ቡድን በመቀላቀል ድህረ ምርጫ 97 የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ሆኖ ለመሾም የበቃው ኩማ ደመቅሳ በከተማው ውስጥ እየታየ ያለው የኑሮ ውድነት ከባድ ፈተና ሆኖብናል በማለት ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ ለተሰበሰበው የወያኔ ፓርላማ አስታወቀ። እንደ ኩማ ደመቅሳ አነጋገር ከተማውን ለከባድ […]

የአረመኔውን የወያኔ አገዛዝ ግፍና በደል በመቃወም ራሱን በቤንዚን አርከፍክፎ በማቃጠሉ ኢትዮጵያዊው ቡአዚ የሚል ቅጽል ስም እየተሰጠው ያለው አርበኛው መምህር የኔሰው ገብሬ በተለይም በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጭ ባሉት ኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ የመወያያ አጀንዳ ሆኖ ሲሰነብት በርካታ የሬዲዮ ፕሮግራሞችና የመረጃ ድረገጾች ሰፊ ሽፋን ሰጥተው ሲዘክሩት ሰንብተዋል። በሃገር ውስጥ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ በርካታ ወጣቶች የመምህር የኔሰው ገብሬ […]

የዘረኛውና አረመኔው የወያኔ አገዛዝ የሚያደርስባቸውን ግልጽና ስውር አፈና ተቋቁመው ህትመት ላይ ቀርተው ከነበሩ ጋዜጦች መካከል የአውራ አምባ ታየምስ ጋዜጣ ዋና መስራችና አዘጋጅ የነበረው ዳዊት ከበደ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጋዜጠኞች ላይ የተከፈተው አዲስ ዙር መንግሥታዊ ሽብርና ዛቻ ለህይወቱ አስግቶት አገር ጥሎ መኮብለሉን ኢሳት በትናትናው የዜና እወጃ ፕሮግራሙ ዘግቦአል። የጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ አገር ጥሎ መሰደድ ካለፈው ሳምንት […]

በአገራችን የተዘረጋው የስልክና የኢንተርኔት አቅርቦት ወያኔ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ለመገደብና ዜጎች ስለአገራቸውና ስለሚያስተዳድራቸው መንግሥት በቂ መረጃ እንዳያገኙ ለመከላከል እንዲያስችል ተደርጎ የተዋቀረ በመሆኑ ፤ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሆኑ ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ የሆነ አለም አቀፍ ድርጅቶችና ዲፕሎማቲክ ሚሽኖች ጭምር እያስመረረ መምጣቱን ባለፈው ሳምንት ይፋ የሆነ ዜና አረጋገጠ። በወያኔ አገዛዝ ቁጥጥር ሥር የሆነው የኢትዮ ቴሌኮም ኮርፖሬሽን ከደንበኞቹ ጋር […]

የኢትዮጵያን ፍርድ ቤቶችን በቁጥጥራቸው ሥር ያደረጉት የመለስ ዜናዊ ካድሬዎች ሰሞኑን የተለመደ ድራማቸውን አጧጡፈዋል። የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በሆኑት በአቶ አንዱዓለም አራጌ መዝገብ ውስጥ ሃያ አራት ዜጎች በበርካታ የፈጠራ የሽብር ወንጀሎች ተከሰዋል።  ከተከሳሾቹ ስምንቱ ብቻ ናቸው በመለስ መዳፍ ውስጥ ያሉት። ሌሎቹ  የገቡት ለማዳመቂያና ለማስፈራሪያ ነው። አስራ ሰባት ገፆች ያሉት “የክስ ቻርድ” […]

የኢትዮጵያን ህዝብ ከተቀረዉ የአፍሪካ ህዝብ ከሚለዩት ዋና ዋና ባህሪዮች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ለአገሩ ዳር ድንበር፤ ለመሬቱና ለሐይማኖቱ የሚሰጠዉ ልዩ ቦታ ነዉ። ይህንን ልዪ ባህሪዩን ደግሞ እንኳን ወዳጆቹ ጠላቶቹም በዉል ተገንዝበዉለት ሳይወዱ በግድ በታሪክ መዝግበዉ ያስቀመጡትና ቢፍቁት ቢፍቁት የማይደበዝዝ ሃቅ ነዉ። የቀድሞዉ መሪዎቻችን ህዝቡ አገሩንና አንድነቱን ከወራሪ እንዲከላከል ጥሪ ሲያደርጉ አገርህን ሊቀማህ፤ መሬትህን ሊወርስና ሐይማኖትህን ሊያረክስ […]

አረመኔው የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው ግፍና በደል ህሊናው ሊሸከመው ከሚችለው በላይ መሆኑን በመግልጽ የኔሰው ገብሬ የተባለ የደቡብ ተወላጅ እራሱን በእሳት አጋይቶ መግደሉን የግንቦት7 ድምጽ ሬዲዮን ጨምሮ ሌሎች በርካታ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የኔሰው ገብሬ በመባል የሚታወቀው መምህር በዳውሮ ዞን በተርጫ ከተማ ለበርካታ አመታት ነዋሪ ሲሆን የወያኔው አገዛዝ ሆድ አደር የዞንና የወረዳ ምክር ቤት […]

የኔሰው ገብሬ ይባላል። ዕድሜው ወደ 29 አመት ነው። ሥራው መምህር ነበር። የተወለደው በጂማ ከተማ ዉስጥ ሲሆን የአንደኛም ሆነ የ2ኛ ደረጃ ትምህርቱን የተከታተለው እዚያው ጂማ ከተማ ነበር። ከዚያም ወደ ዋካ ከተማ በመምጣት ታላቅ እህቱ ዘንድ ኑሮዉን አደረገ። ከዚያም ወደ መምህራን ኮሌጅ በመግባት በመምህርነት ሰልጥኖ በዳዉሮ ዞን ዉስጥ በተለያዩ ወረዳዎች ዉስጥ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እየተዛወረ በመምህርነት አገልግሏል። […]

በአካባቢው ያለውን ጭቆና፣ የመልካም አስተዳዳርና የፍትህ መታጣት በመቃወም እራሱን በእሳት በማጋየት ተቃውሞን የገለጠው የመምህር የኔሰው ገብሬ አስደንጋጭ ዜና የህዝቡ የመነጋገሪያ አጀንዳ በሆነበት ማግስት፣ የአካባቢው  ባለስልጣናት፣ “ተቃውሞውን የሚያስተባብሩት በከተማው የሚገኘው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ካህን ናቸው”  በሚል ሰበብ፣ የቤተክርስቲያኑዋን አስተዳዳሪ የሆኑትን በኩረ ትጉሀን ይልማ መኮንንን ከሃላፊነታቸው ማባረራቸውን ኢሳት  ከትናንትና በስቲያ የዜና እወጃው ዘግቦአል። እንደ ኢሳት ዘገባ የእገዳውን  ደብዳቤ […]

የዋካ ነዋሪዎች እንደሚሉት መምህር የኔሰው ገብሬ እራሱን በእሳት አቃጥሎ ከገደለ በሁዋላ፣ በከተማው ውስጥ አመጽ ሊያስነሱ ይችላሉ የተባሉ ከ80 ያላነሱ ሰዎች ባለፉት ሁለት ቀናት መታሰራቸውን ኢሳት በትናትናው ዜና ዘገባው ገልጾአል። እንደ ኢሳት ዘገባ እስካሁን ድረስ በተጫ ከተማ ብቻ ተወስኖ የነበረው እስር ወደ ገጠር መውረዱን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ የአካባቢው ባለስልጣናት ህዝቡን ለማሸበር መሳሪያቸውን ታጥቀው በከተማው እየተዘዋወሩ እንደሚገኙና ለራሳቸውም […]

መሬት የመንግስት ነው በሚል ሽፋን በገጠሩ የሚገኘው የኢትዮጵያ ህዝብ  በአገዛዙ ላይ ምንም ተቃውሞ እንዳያነሳ ሌት ከቀን ሲሰራ የነበረው የዘራፊው ወያኔ አገዛዝ ፊቱን ወደከተማ ነዋሪዎች በማዞር ማንኛውንም የከተማ ቦታን በሊዝ እንዲቀየር አዲስ ህግ መደንገጉ የሚታወቀ ሲሆን የየካ ክፍለ ከተማ  ነዋሪዎች ድንጋጌው ፤ ንብረት አልባ አድርጎ የሚያስቀርና ለወያኔም ተገዥ እንድንሆን የማድረጊያ መሳሪያ ነው በማለት በጽኑ መቃወማቸውን ዘጋቢያችን […]

በሰሜን አመሪካ በሲያትል ከተማ ከአመት በፊት የተቋቋመው የሲያትል ህዝባዊ ፎረም ከትናንትና በስቲያ እሁድ ህዳር 3 ቀን በአገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ 3 የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲ ተጠሪዎችን ለማወያየት አዘጋጅቶት የነበረው ስብሰባ እጅግ በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን የግንቦት7 ዘጋቢ ከሥፍራው በላከልን ዜና ገለጸ። ፎረሙ በጠራው በዚህ የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ ውይይት ለማድረግ የተጋበዙት የግንቦት 7 ንቅናቄ ፤ የኦሮሞ ነጻነት ግንባርና […]

በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በትናንትናው ዕለት ህዳር 4 ቀን ጄኔቫ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ጽቤት ፊት ለፊት ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ በዘጎች ላይ እየፈጸመ ያለውን ሰቆቃና እንግልት በአስቸኳይ እንዲያቆም አለም አቀፍ ጫና እንዲፈጠርበት ጠይቀዋል። የታሰሩ ፖለቲካ እስረኞችን ፎቶግራፎችና የተለያዩ መፈክሮችን ይዞ የወጡት እነዚህ ኢትዮጵያዊያን ሰልፈኞች፤ ወያኔ በሽብርተኝነት እየፈረጀ ያሰራቸው የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፤ አባላትና ደጋፊዎች […]

ባለንበት የመረጃ ዘመን፤ ሳይበር (ለምሳሌ ኢንተርኔት) ለፍትህ፣ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ትግል ከሚደረግባቸው አውድማዎች አንዱ ሆኗል። ለሰሜን አፍሪቃና መካከለኛ ምሥራቅ ህዝባዊ አብዮቶች ኢንተርኔት ስለተጫወተው ሚና ብዙ የተባለ ስለሆነ እዚህ ላይ ደግሞ ማንሳት አያስፈልግም። መረሳት የሌለበት ሃቅ ግን አምባገነኖችም ይህንን ስለሚያውቁ እነሱም የሚዘጋጁበት መሆኑ ነው። የዘመናችን አምባገነን መንግሥታት የምድር፣ የባህርና የአየር ኃይሎቻቸውን ከማፈርጠም ጎን ለጎን “የሳይበር ኃይላቸውን” ማጎልበት […]

ወያኔ ብሶት የወለደው የህዝብ ልጅ ነበር። አሁን ያ የህዝብ ብሶት የወለደው ድርጅት ሙቶ በቀበሩ ላይም መለስ ዜናዊ የሚባል ጣኦት ቁሟል።ኢትዮጵያዊያንም ለዚህ ጣኦት መስዋእት ሁነው ቀርበውለታል። ጣኦቱም በፈለገው መንገድ የቀረበለትን መስዋእት እየበለተ ምሱን እየወሰደ ነው። ይህ ጣኦት ይሁን ያለው እየሆነ አይሁን ያለው ደግሞ ሳይሆን እየቀረ እነሆ ሁለት አስርተ ዓመታት ተቆጠረ። ይህ ክፉ ጣዖት አማራና ኤምፔሪያሊዝም የትግራይ […]

ወያኔ በትግራይ ህዝብ ሥም ባቋቋመውና ለጥቂት የህወሃት ባለሥልጣኖች እንደግል ንብረት እያገለገለ ያለው የ ኤፈርት ኩባንያ  ስራ አስኪያጅ አባዲ ዘሙ ከሥራ አስኪያጅነቱ ተነስቶ ድርጅቱ ሙሉ በሙሉ  በዘረኛው ቡድን ቁንጮ መለስ ዜናዊ ባለቤት  አዜብ መስፍን እጅ  መውደቁ ተዘገበ። አዲስ ቮይስ በመባል የሚታወቀው የመረጃ አውታር እንደዘገበው፤ በህወሓት ውስጥ ረጅም ዓመታት ቁልፍ ቦታዎችን ይዞ ሲያገለግል የቆየውና የአምባገነኑ መለስ ዜናዊ […]

የከተማ ቦታን በሊዝ ለማስያዝ  በሚል ድንጋጌ የወያኔ ምክር ቤት በቅርቡ ያወጣው የከተማ ቦታ አዋጅ የዜጎችን ነባር ይዞታ ለመቀማት የታሰበና ባለንበርቶች ቤታቸውን ለልጅ ልጆቻቸው ለማውረስ ያላቸውን ህጋዊ መብት የሚያሳጣ እንደሆነ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የህግ ባለሙያዎች ገልጸዋል። ኢ-ፍትሃዊ የነበረውን የአገራችንን የመሬት ይዞታ ስርዓት በ1967ቱ ስርነቀል የመሬት ላራሹ አዋጅ የለወጠው ደርግ ፤ የከተማ ቦታን በምሪት የመጠቀም መብት ሰጥቶ […]

የጀርመን ፓርላማ ምክር ቤት አባላት በቅርቡ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት አስመልክቶ ከትናንት በስቲያ 09.11.2011 በሰጡት መግለጫ አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላት የረጂም ጊዜ ግንኙነት በአገሪቱ እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እያየን ዝም እንድንል የሚያደርገን አይደለም አሉ። በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ ጉብኝት ያደረጉት የሊበራል ፓርቲ ተወካዩዋ ወይዘሮ ማርቲና ሹስተር  በጉብኝታቸው ወቅት ያስተዋሉትን እውነታ ሲገልጹ “ህግ ይፈቅድልኛል እያሉ አንድን ሰው […]

ዕሁድ ጥቅምት 26 ቀን ተከብሮ የዋለውን የኢድ-አልፈጥርን በዓል በቤልጂዬም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች አንድ ላይ በመሰባሰብ በደማቅ ሁኔታ ማክበራቸውን የግንቦት 7 ዘጋቢ ከስፍራው በላከልን ሪፖርት ገለጸ። በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በየአመቱ በደማቅ ሁኔታ በሚከበረው በዚህ ታላቅ መንፈሳዊ ሥነሥርዓት ላይ የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች መካከል እልቂት ሊያስነሳ የሚችል ክፍፍል ሆን ብሎ እየፈጠረ መሆኑን በድምጽና በቪዲዮ ማስረጃ የተደገፈ […]

ኢትዮጵያዊያንን በሰበብ አስባቡ በመከፋፈልና በማበጣበጥ ራሱን ስልጣን ላይ የማቆየት አባዜ የተጠናወተው ከፋፋዩ የወያኔ አገዛዝ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን ማጋጨቱን እንደቀጠለ ሲሆን ግጭቱን ወደ ከፋ ደረጃ ለማድረስ “አህባሽ” ለተባለው ቡድን ወታደራዊ ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ከአገር ውስጥ አልፎ በውጪ አገር የሚኖሩትንም ሙስሊም ህብረተሰብ  እጅግ እያሳሰበና እያስቆጣ መሆኑ ተገለጸ። በተለያዩ የአውሮጳ፤ የሰሜን አመሪካና ኤዥያ ከሚኖሩ የሙስሊም ኮሚኒቲዎች ጋር የጋራ ህበረትና […]

ከሁለቱ ስዊድናዊያን ጋራ በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት በዋና ወንጀል አድራጊነት የተከሰሱት የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) አባላት የሆኑት አብዲወሊ መሐመድ እስማኤል እና ከሊፍ ዐሊ ዳሂር የ17 ዓመት ጽኑ እሥራት ሲፈረድባቸው የስዊድን ሃገር ጋዜጠኞች ክስ ግን በቂ መረጃ አልተገኘም በሚል የቀረበባቸው ክስ ውድቅ መሆኑ ታወቀ፡፡ በእለቱ የፍርድ ቤቱን ታዳሚዎች […]

የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴለቪዥን ከሪፖርተሮቹ የደረሰውን መረጃ ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው በውጪ ምንዛሪ በውድ ዋጋ ታትመው ወደ አገር ቤት የገቡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ መጻህፍት ለተማሪዎችና መምህራን ከተከፋፈሉ ቦኋላ ነበር ባለሥልጣናቱ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፉት። ይሁን እንጂ መጽሀፉ ባለፈው መስከረም ወር በሚታደልበት ጊዜ  ተማሪዎች መጽሀፉን ቀድደው ቢገኙ 100 ብር እንደሚቀጡ በመምህራን በኩል ተነግሮአቸው እንደነበር ታውቆአል። የአማራ ክልል ባለስልጣናት ተማሪዎችና መምህራን […]

ጥቅምት ወር ሲመጣ … “በግንቦት 7 1997 የሰጠነው የምርጫ ድምፃችን ይቆጠርልን!” በማለታቸው በጥቅምት 1998 ዓ.ም. በአዲስ አበባና ሌሎችም ከተሞች ጎዳናዎች በአጋዚ ጥይት በግፍ  የተገደሉ፤ ለአካል ጉዳት የተዳረጉ፤ የተደበደቡ እና የተጋዙ ወገኖቻችንን በሃዘንና በቁጭት እናስታውሳለን። ዘንድሮ የጥቅምት 98 ሰማዕታትን በምንዘክርበት ወቅት ሶስት አዳዲስ ኩነቶች ተደራርበው መጥተዋል። እነዚህ ኩነቶች የተለያዩ ቢመስሉም በአንድነት ሲጤኑ እየሄድንበት ያለውን መንገድ የሚያሳዩ […]

የኢትዮጵያ ህዝብ ያለፉት ሀያ አመታት ታሪክ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ከወያኔና ወያኔ ተሸክሞ ካመጣቸዉ ኮተቶች ጋር የተያያዘ ነዉ። ይህ ደግሞ ወደንና ፈቅደን ያቀፍነዉ የታሪክ ምዕራፍ ሳይሆን እንደ ቀንበር በግድ የተጫነብን ዕዳ ነዉ። ለዚህም ይመስላል ወያኔ የተባለዉ ቃል በተነሳ ቁጥር የኢትዮጵያ ህዝብ “ተዉ ስማኝ አገሬ ሲከፋኝ ነዉ መኖሬ” እያለ አንጀቱ ዉስጥ የሚነደዉ እሳት የሚቀዘቅዝ እየመሰለዉ በአፉ […]

በያረጋል አይሸሹምና በህወሀት ባለስልጣናት መካከል በተነሳው የፖለቲካ ውዝግብ ምክንያት ቀደም ሲል ታማኝነቱንና ታዛዥነቱን ለማግኘት ሲባል በተከፈተለት የሙስና በር በራሱና በቤተሰብቹ ስም እስከዛሬ ያከማቸው ሃብትና ንብረት እንዳይንቀሳቀስ የወያኔ ፍርድ ቤት ማገዱን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ በላከልን ሪፖርት ገለጸ። ፍርድ ቤት ተብዬው የወያኔ የማጥቂያ መሳሪያ፤ በያረጋል አይሸሹም፤ በባለቤቱ በትግስት በቃልና፣ በልጆቹ ስም ተመዝግበው የሚገኙ ንብረቶችን ያገደው፤ በአሶሳ በ1200 […]

በከፋፍለህ ግዛ የቅኝ ገዥዎች ፖሊሲ የተለከፈው የመለስ ዜናዊ አገዛዝ በብሄር ብሄረሰቦች መካከል የፈጠረው ክፍፍል የታሰበውን ውጤት ስላላመጣለት ፊትን ወደ ሃይማኖት ተቋማት በመመለስ የሙስሊሙን ህብረተሰብ ለሁለት ጎራ የሚከፍል ተግባር እያራመደ መሆኑን በዚህም አብዛኛው የሙስሊም ሃይማኖት ተከታዮች ከፍተኛ የሆነ ቅሬታ እንዳደረባቸው የግንቦት 7 ዘጋቢ ገለጸ። እንደዘጋቢያችን ሪፖርት በአገራችን ሙስሊሞች ዘንድ ቀደም ሲል እውቅና ያልነበረው አህባሽ የሚባል የእምነት […]

ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ አንስቶ ሃገራቸውን ለቀው ለስደት የሚዳረጉት ኢትዮጵያዊያን ቁጥር እጂግ እያሻቀበ መምጣቱና በታሪክ ታይቶ ከማይታወቅ ደረጃ ላይ መድረሱ ታወቀ። ሃገሪቱን ለቀው ወደውጪ ሃገራት በሚሰደዱ ኢትዮጵያዊያን ዙሪያ ለሚጠናቀረው መረጃ ቅርብ የሆኑ የውስጥ ምንጮቻችን እንዳረጋገጡት በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያን በመልቀቅ ወደ የመንና ሱዳን የሚሰደዱት ኢትዮጵያዊያን ብዛት በእጅጉ አስደንጋጭ እየሆነ መጥቱአል። ዘጋቢያችን የውስጥ ምንጮቹን […]

ድህረ ምርጫ 97 የሰጠነው የምርጫ ድምፃችን ይከበርልን በማለታቸው ልክ የዛሬ 6 አመት ጥቅምት 22 ቀን 1998 . በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ጎዳናዎች ላይ በአረመኔው የወያኔ አገዛዝ አጋዚ ጥይት በግፍ የተጨፈጨፉ፤ አካሎቻቸውን ያጡ፤ የተደበደቡ እና የተጋዙት ሰማእታት ወገኖቻችን 6ኛ አመት በሚሊየኖች በሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ እየተዘከረ ነው። የመለስ ዜናዊ አገዛዝ በወርሃ ጥቅምት 1998 በንጹሃን ወገኖቻችን ላይ የፈጸመውን […]

በአገር ውስጥ ያጣውን ድጋፍ በኢኮኖሚ ችግር ከተሰደዱትና ከወያኔ በመጠጋት ሊገኝ በሚችለው የጥቅም ትርፍራፊ ሊደለሉ የሚችሉ ግለሰቦችን በማሰባብሰብ ሊያገኝ ደፋ ቀና እያለ ያለው የፋሽስቱ መለስ ዜናዊ አገዛዝ፤ ባለፈው ቅዳሜ ጥቅምት 18 በብራስልስ ከተማ ድል ያለ ድግስ አዘጋጅቶ ግብር ማብላቱን የግንቦት 7  ዘጋቢ ከሥፍራው ከላከልን ዜና ለማወቅ ተችሎአል። በካሱ ኢላላ የሚመራው የቤልጂዬም የወያኔ ኤምባሲ ቀደም ሲል ለተጋባዦቹ […]

አረመኔው የመለስ ወያኔ አገዛዝ የእስር ጥቃቱን ሊያካሄድ ዝግጅቱን ያጠናቀቀው በዋነኛነት በኦሮሞ፣ ኦጋዴንና አማራ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እነዲሁም ተወላጆች ላይ መሆኑ ታውቅዋል። ይህ እቅድ ወያኔ ከሀምሌ ወር 2011 ጀምሮ እየተገበራቸው ካሉት ግዙፍ እኩይ ድርጊቶች ኢምንቱ እነደሆነ የታወቀ ሲሆን ይህም ሀገር ውስጥ የሚገኙ የተቃዋሚ ሀይላትን ከሀገር ጠራርጎ የማውጠት አላማን የተንተራሰ  ዘዴ ነው። መለስ ዜናዊ በቅርቡ በፓርላማ […]

ሲ ኤን ኤን እንደዘገበው የሳይናይ በረሀን በማቋረጥ ወደ እስረኤል ለመጓዝ ሙከራ የሚያደርጉ ኢትዮጵያውያን፣ ሱዳንያውያንና ኤርትራዊያን አስፈላጊውን ክፍያ መፈጸም ካልቻሉ፣ የሆድ እቃቸው ተከፍቶ ኩላሊታቸው ና ጉበታቸው ከወጣ በሁዋላ፣ በዚያው እንዲሞቱ እንደሚደረጉ ዘግቧል። ዘ ኒው ጄኔሬሺን ፋውንዴሽን ፎር ሁማን ራይትስ እናዘ ኤቭሪዋን ግሩፕ የተሰኙትን ድርጅቶች በመጥቀስ ሲኤን ኤን እንደዘገበው፣ ስደተኞቹ የተጠየቁትን በብዙ ሺ የሚቆጠር ክፍያ ለመፈጸም ካልቻሉ […]

ሊቢያን ለአርባ ሁለት ዓመታት ቀጥቅጠው የገዙት ኮሎኔል ጋዳፊ በትውልድ መንደራቸው ስርት ውስጥ እጎርፍ ማስወገጃ ቱቦ ውስጥ ተገኙ። እንደተባለው ከሆነ ከወርቅ የተሠራ ሽጉጣቸውን የመጠጣት እድል እንኳን ሳያገኙ በአልባሌ ጥይት ቆሰሉ። “አይጦች፣ በረሮዎች፣ ሃሽሻሞች፣ ዱርየዎች” እያሉ በሰደቧቸው እና የመድፍ ናዳ ሲያወርዱባቸው በነበሩ ወጣት አብዮተኞች ጫማ ተረገጡ፣ ተጎሸሙ። በጥፊ ተመቱ፤ ተዋረዱ። በመኪናም ታስረው ተጎተቱ:: እየጮሁ በአሳዛኝና በአዋራጅ ሁኔታ […]

ከሰሞኑ የመለስ ካድሬዎች አንድ ሙግት ይዘዋል። እንደ መለስ ያለ ብሄራዊ ስሜት ያለው መሪ በኢትዮጵያ አልተነሳም የሚል። መለስ ለአሜሪካና ለአውሮፓ መንግስታት ከሚያጎበድዱ ሞታቸውን ይመርጣሉ ብለውም ያሞካሿቸዋል። ይሄንንም እውነት ነው ብለን እንድንቀበለው ይገፋፉናል። መለስ ዜናዊ ያን አሳፋሪ ተክለ ሰውነቱን እንዲገነቡለት አይጋ ፎረም የተባለውን ድህረ ገጽ አቋቁሞና ነውረኛ ግለሰቦችን ቀጥሮ ነጋሪት እያስጎሰመ ነው።የአይጋ ፎረምና የእድምተኞቹ ከንቱ ጩኽት የአገሪቷን […]

በአውሮፓ ከሚገኙ 11 አገሮች የተወጣጡ የግንቦት 7 የአህጉርና የአገራት ተወካዩች ባለፈው ቅዳሜና እሁድ እንደፈረንጆች አቆጣጠር ኦክቶበር 22 እና 23 ከአውሮጳ ዋና ከተማ ከብራስልስ 30 ኪሜትር ርቄት ላይ በሚትገኘው የሉቨን ከተማ ተሰባስበው ንቅናቄያቸው ስለሚያካሄደው ሁለገብ ትግል በሰፊው እንደተወያዩና የአቋም መግለጫም እንዳወጡ የንቅናቄው የህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታወቀ። ከስዊድን፤ ከኖርዌዬ፤ ከዴንማርክ፤ ከፊንላንድ፤ ከሲውዘርላንድ፤ ከኢስፔን፤ ከፈረንሳይ፤ ከጀርመን ከእንግሊዝ፤ ከኒዘርላንድስና […]

ተቃዋሚዎቻቸውን አንዴ ሽብርተኞች ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ በሃሺሺ የደነዘዙ አይጦች በማለት ሲያጣጥሉ የነበሩትን የሙአመር ጋዳፊ የውርደት አሟሟት የተመለከቱ በርካታ ኢዮጵያዊያን የመለስ ዜናዊ የመጨረሻ እጣ ፋንታ ተመሳሳይ ሊሆን እንደሚችል በስፋት እየተነበዩ መሆኑን በአዲስ አበባና አጎራባች ከተሞች የሚኖሩትን የህዝብ አስተያየት ያሰባሰቡ የግንቦት 7 ዘጋቢዎች ለዝግጅት ክፍላችን በላኩት ዜና ገለጹ። ሙአመር ጋዳፊ በዙሪያቸው ያደራጁትን የመከላኪያ ሠራዊት ብዛትና ጥንካሬ […]

ሰሞኑን አምባገነኑ መለስ ለአሻንጉሊቱ የኢትዮጵያ ፓርላማ ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ ፤ ከወትሮው በተለየ መልኩ በዘረኛው መለስ አስተያዬት ዙሪያ ሀሳባቸውን ለመስጠት እንዳልተፈቀደላቸው መጥቀሳቸውን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት ዘገበ። “ይህ ነገር መታረም ካልቻለ  ምናልባትም ለምክር ቤቱ ጥያቄዎቻችንን አስገብተን መለስ መልስ እንዲሰጥና እኛም ሂደቱን በቴሌቪዥን ብንከታተል የሚሻል ይመስለኛል” ያሉት አቶ ግርማ፤ “የምክር […]

ኢትዮጵያን በዘርና አሃይማኖት ከፋፍሉ የመግዛት አባዜ የተጠናወተው የወያኔ አገዛዝ የከፋፋይነት መርዙን በሃገሪቱ ከረጨ ወዲህ በበርካታ የኢትዮጵያ ክልሎች ግጭቶች እየተከሰቱ ሲሆን ላለፉት 13 ዓመታት “እኛ ሃላባዎች እንጂ ሃድያዎች አይደለንም፤” በሚል የማንነት ጥያቄ ሲያነሱ የቆዩ ናቸው የተባሉ በሃዲያ ዞን ውስጥ የሚገኙ ሦስት ወረዳዎች፣ ጥያቄያቸው ምላሽ በማጣቱ ወደ ግጭት በማምራት ላይ መሆናቸው ታወቀ። ቁጥራቸው አሥር የሚደርሱ በሃዲያ ዞን […]

ኢትዮጵያዊያንን በጠመንጃ ሃይል ረግጦና በስልጣን ወምበር ላይ ተፈናጥጦ ለዘመናት መቆየት የሚፈልገው ዘረኛ የወያኔ አገዛዝ እድሜየን ያሳጥራሉ ብሎ የፈራቸውን የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራር አካላት፣ አባላት፣ አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች  ሽብርተኞች ናችሁ የሚል ታፔላ እየለጠፈ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት በግፍ ሲያጉር እንደቆየ የሚታወቅ ሲሆን ይህኑ ተግባሩን በማስፋፋት፣  በመድረክ አባላት ላይ የሚያደርገውን ማሳደድ አጠናክሮ መቀጠሉ ተዘገበ። የኢትትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት […]

በብሪታኒያ ጥልቅ የፖለቲካ የምክክር መድረክ የሆነዉ ቻታም ሃዉስ የአፍሪቃ ፕሮግራም አማካሪና ተመራማሪ ሮጀር ሚድልተን ኢትዮጵያ ሶማሊያን በመዉረር አልሼባብን አጠናክራለች ሲሉ  ገለጹ።  ተመራማሪው ይህንን የገለፁት ባለፉት አምስት ቀናት ዉስጥ የኬንያ ወታደሮች በሶማሊያ ዉስጥ ጣልቃ መግባታቸዉን በማስመልከት በሰነዘሩት አስተያየት  ነዉ። ሮጀር ሚድልተን ይህን መሰል ያልታሰበበትና አሉታዊ የሆነ ጣልቃ ገብነት የሚያስከትለዉን ዉጤት ካለፈዉ የኢትዮጵያ ወረራ ያለመማር ስህተት እንደሆን […]

የእኛኑ ገሀነብ ማን እንዲያፈርስልን? እፉኝ ነኝ እንዴ ወፍ ዘራሽ መደዴ በንፋስ አቅጣጫ  ሚወሰን መንገዴ። ብናኝ አቧራ ነኝ? ከጠጠር የከሳ እፍ ባሉት ቁጥር በኖ የሚነሳ ። ቆሻሻ ነኝ እንዴ? የምድር ላይ ጥራጊ ከግም ከብስብሱ አንድ ላይ ታሻጊ። አረም ነኝ ወይ እንዴ? ተመዝዤ እምጣል የማበብ መብት ያጣሁ ከፍጥረታት መሃከል። እንዴት ልገልጸው ነው ሰውነት የኔን የክብር አቅል አጥቶ  […]