በቤልጂዬም የሚገኘው የወያኔ ኤምባሲ ለአፍቃሪ ወያኔ ስደተኞችና ሆድ አደሮች ግብር ማብላቱ ተዘገበ
በአገር ውስጥ ያጣውን ድጋፍ በኢኮኖሚ ችግር ከተሰደዱትና ከወያኔ በመጠጋት ሊገኝ በሚችለው የጥቅም ትርፍራፊ ሊደለሉ የሚችሉ ግለሰቦችን በማሰባብሰብ ሊያገኝ ደፋ ቀና እያለ ያለው የፋሽስቱ መለስ ዜናዊ አገዛዝ፤ ባለፈው ቅዳሜ ጥቅምት 18 በብራስልስ ከተማ ድል ያለ ድግስ አዘጋጅቶ ግብር ማብላቱን የግንቦት 7 ዘጋቢ ከሥፍራው ከላከልን ዜና ለማወቅ ተችሎአል።
በካሱ ኢላላ የሚመራው የቤልጂዬም የወያኔ ኤምባሲ ቀደም ሲል ለተጋባዦቹ ባሰራጨው የግብዣ ጥሪ ወረቀት፤ የኢትዮጵያን አድስ አመት ለማክበርና የሂዳሴ ግድብ ቦንድ ሺያጭ በኤምባሲው መጀመሩን ለማብሰር የርሰፕሽን ግብዣ በኤምባሲው ስለተዘጋጀ እስከነቤተሰብዎ ተጋብዘዋል የሚል መልዕክት መተላለፉ ታውቆአል።
አገር ውስጥ በመኖር የአገሪቱን የድህነት ዕጣ እየተጋፈጡ ያሉ የመንግሥት ሠራተኞች፤ መምህራን፤ የፋብሪካ ሠራተኖችኛና በተለያዩ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ተቀጥረው የሚያገለግሉ ዜጎች በየጊዜው እየናረ በሄደው የኑሮ ውድነት እራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን መመገብ እንደማይችሉ እየታወቀ፤ ያለውዴታቸው በግዴታ ቦንድ እንዲገዙ ተጽ ዕኖ የሚያደርግባቸው መንግሥት ፤ ከባህር ማዶ በንጽፅር የተቀማጠለ ኑሮ የሚኖሩትን ስደተኞች ለማባበል ከዚያ ደሃ ህዝብ በሚሰበሰብ ገንዘብ ድል ያለ ድግስ ደግሶ ማብላት አገዛዙ የደረሰበትን የፖለቲካ ኪሳራ አመልካች ነው ተብሎአል።
በዘር ሃረግና በጥቅም ትስሥር ምክንያት የህወሃት ቁንጮ የሆነው መለስ ዜናዊና ግብረአበሮቹ በአገራችንና በህዝባችን ላይ እየፈጸሙ ያሉት ክህደትና ሰቆቃ ለማየት የተሳናቸው እነዚህ ሆድ አደሮች፤ እንኳን ከሰው ልጅ ከቤት እንስሳ የሚተርፍ ትኩስ ምግብ በቆሻሻ መጣያ ገንዳ ውስጥ በሚጣልበት አገር ውስጥ ቁጭ ብለው፤ ለሆዳቸው ሲሉ የገዛ ወገኖቻቸውን የስቃይ ጣር የሚያራዝም የፖለቲካና የገንዘብ ድጋፍ ለማበርከት ኤምባሲው ባዘጋጀው ድግስ ላይ መገኘታቸው በአገሪቱ የሚኖሩትን የህዝብ ወገኖች ሁሉ አሳዝኖአል።
ወያኔ ባዘጋጀው በዚህ ግብር የማብላት ሥነሥርዓት ላይ ከተገኙት አብዛኛዎቹ ወያኔ በሚያራምደው የዘር መድልዎ ተጠቃሚ በመሆን ለትምህረት ወደ ቤልጂዬምና ሆላንድ የተላኩ የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ በወያኔ የዘር ፖለቲካ ወገኖቻቸው ግንባር ቀደም የጥላቻ ሰለባ የሆኑና በወያኔ የአባይ ግድብ ግንባታ ፕሮፖጋንዳ የእርቅ ፊቱን የመለሰላቸው የመሰላቸው አንዳንድ ድኩማን መሆናቸው ታውቆአል።
በድግስ ሥነሥርዓቱ ላይ ተገኝቶ ዜናውን ያጠናከረው ዘጋቢያችን እንደገለጸው ጥሪ ከተደረገላቸው የኦሮሞና፤ የአፋር ኮሚኒት አንድም በድግሱ ላይ እንዳልተገኘ የታወቀ ሲሆን እስከ 500 ሰዎች ሊመጡ ይችላሉ ተብሎ በቻርተር አውሮጵላን ከአገር ቤት ተጭኖ የመጣው ብዛት ያለው ባህላዊ ምግብና ቅዱስ ግዩርጊስ ቢራ በመትረፉ፤ በግብዣው ላይ ከተገኙት አብዛኛዎቹ የተረፈውን ምግብ በፈስታል ተከፋፈለው ወደየቤታቸው መሄዳቸው ተዘግቦአል።
በግብዛው ላይ አጭር ንግግር ያደረገው ካሱ ኢላላ ወያኔ የዋሆችን ለማደኛ ስለፈጠረው የሂዳሰ ፕሮጄክት አጭር ድስኩር ካሰማ ቦኋላ “ዕለቱ በመብላትና በመጠጣት በጋራ የምንደሰትበት ቀን ስለሆነ ንግግር አላበዛባችሁም” በማለት በወያኔ ቤተመንግሥት ተዘጋጅቶ ለግብር የተላከው እንጀራና ወጥ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ጋር በአሽቃባጭ አሳላፊዎች ተስተናግዶአል።
በልጅዬም ከ300 አይነት ቢራዎች በላይ በማምረት የምትታወቅ አገር ሲትሆን በአለም በታላቅነቱ ከመጀመሪያዎቹ ተርታ የሆነው ስቴላ የተባለ ቢራ ፋብሪካ የሚገኘው ድግሱ ከተካሄደበት 30 ኪሎሜትር ረቀት ላይ ነው። ሆኖም ደካማ ዜጎችን በሆድ መደለልና ምርኮኛ ማድረግ የተዋጣላቸው የወያኔ መሪዎች የአንድ ቢራ ዋጋ ከሊትር ውሃ በታች በሆነበት አገር ለምን በአውሮጵላን ቢራ ጭኖ መላክ እንዳስፈለጋቸው ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም።