መለስ ዜናዊ ብሄራዊ ስሜት የለውም!!!

ከሰሞኑ የመለስ ካድሬዎች አንድ ሙግት ይዘዋል። እንደ መለስ ያለ ብሄራዊ ስሜት ያለው መሪ በኢትዮጵያ አልተነሳም የሚል። መለስ ለአሜሪካና ለአውሮፓ መንግስታት ከሚያጎበድዱ ሞታቸውን ይመርጣሉ ብለውም ያሞካሿቸዋል። ይሄንንም እውነት ነው ብለን እንድንቀበለው ይገፋፉናል።

መለስ ዜናዊ ያን አሳፋሪ ተክለ ሰውነቱን እንዲገነቡለት አይጋ ፎረም የተባለውን ድህረ ገጽ አቋቁሞና ነውረኛ ግለሰቦችን ቀጥሮ ነጋሪት እያስጎሰመ ነው።የአይጋ ፎረምና የእድምተኞቹ ከንቱ ጩኽት የአገሪቷን ገንዘብ ከማባከን በስተቀር ለኢትዮጵያችን ያተረፈው በጎ ነገር የለም።

መለስ ዜናዊ ብሄራዊ ስሜት የለውም። ብሄራዊ ስሜት ያለው ሰው ቢሆን ኖሮ ብሄራዊ ማንነቱን ከክልላዊ ማንነቱ አግዝፎ የአገርን አንድነት የሚሸረሽር ተግባራትን ባልፈጸመ ነበር። “ወርቅ ከሆነው ዘር በመወለዴ ኩራት ይሰማኛል” በማለት ሌሎቻችንን ከመዳብ ወይም ከከሰል ከየትኛው እንደመደበን እርሱ ብቻ ያውቃል ባልተመጻደቀ ነበር።

መለስ ዜናዊ ብሄራዊ ስሜት ቢኖረው በዜጎች መካከል ያለውን ልዩነት ህዝቡን ለመከፋፈልና ለማዳከም አይጠቀምበትም ነበር። መለስ ዜናዊ ብሄራዊ ስሜት ስለሌለው ዜጎችን በጎሳቸው ይከፋፍላል። አንዱም ጎሳ የአንዱ ጠላት እንደሆነ አድርጎ ይሰብካል። በህወሃት ማንፌስቶ ላይ የትግራይ ህዝብ ቀንደኛ ጠላቶች “አማራና ኤምፔሪያልዝም” ናቸው  ተብሎ የተጻፈው የመለስን ብሄራዊ ስሜት ማጣት አመላካች ነው። ይህ ግለሰብ በኦሮሞዎችና በአማሮች መካከል ሊፈጥር የሞከረው እልቂትም የሚረሳ አይደለም።

መለስ ዜናዊ ብሄራዊ ስሜት ቢኖረው ዜጎች ዘመኑ የደረሰበትን ሁኔታ ለማወቅ የሚያስችላቸውን የመገናኛ ብዙሃን እንዳያገኙ ሬዲዮኖችን፤ቴሌቭዥኖችን፤ ልዩ ልዩ ድህረ ገጾችንና፤ ጋዜጦችን ማፈን ባላስፈለገው ነበር። መለስ ዜናዊ ብሄራዊ ስሜት ስሌለው በአገሪቷ ውስጥ ነጻ አስተሳሰብ እንዳይሰፍን ዜጎችን አስሮ ይዟል። ዜጎች ከመረጃ ርቀው በጨለማ ውስጥ እንዲኖሩ ለማድረግ ብዙ ገንዘብ ከአገሪቷ ካዝና እያወጣ ለቻይናና ለሌሎች ይበትናል። እንዲህ ያለ ግለሰብ ብሄራዊ ስሜት አለው ለማለት አይቻልም።

መለስ ዜናዊ ብሄራዊ ስሜት ቢኖረው በብዙዎች ደምና አጥንት የቆመችን ባንዲራ የጨው መጠቅለያ ጨርቅ ነው ብሎ ባልተሳደበ ነበር።ኢትዮጵያዊያኖች “ወድቃ በተነሳችሁ ባንዲራ” ሲባሉ ከቆሙበት ሳይንቀሳቀሱ ለባንዲራቸው ያላቸውን ክብር ሲያሳዩ ኑረዋል። ዜጎች የሚኮሩበትንና የሚመኩበትን ደግ ነገር ሁሉ ማንቋሸሽና ማዋረድ መለስ ዜናዊ ተልእኮው ነውና ባንዲራን ጨርቅ ቢል ብዙም አንደነቅም። እንዲህ ያለ ግለሰብ  ብሄራዊ ስሜት አለው ተብሎ ሲሰበክለት ግን ያሳፍራል።

በዓለማችን ላይ አሉ የሚባሉ ድሃ አገሮች ልጆቻችንን ለአረቦች አሳልፈን አንሰጥም ሲሉ መለስ ዜናዊ ግን ኢትዮጵያዊያን ወጣት ሴት ልጆችን ለአረቦች አሳልፎ በመሸጥ ጉድ ያሰኘ ተግባር ፈጽሟል።ወጣት ሴቶችን በራሱ ሰዎች አማካኝነት ባቋቋመው ድርጅት አማካኝነት እየሸጠ ብዙ ገቢ ማግኛ መንገድ አድርጎት ቆይቷል። ዜጐቻቸውን ወክለው በዓረቡ ዓለም የተቋቋሙ ኤምባሲዎችና ቆንሲላዎች የሴቶቻችንን መከራና ስቃይ ለመታደግ ምንም ዓይነት ጥረት አለማድረጋቸው የመለስ ዜናዊን ብሄራዊ ስሜት ማጣት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ድርጊት ነው።

ብሄራዊ ስሜት ያለው መሪ ከአገሩ ዜጎቹ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ለዕለት ጉርሱ ከፈረንጅ አገር በሚመጸወት የእርዳታ ስንዴ ላይ እየተማመነ ከ8 ነጥብ 6 በላይ የአሜሪካን ዶላር ገንዘብ ሰርቆ በባዕድ አገር ባንኮች አያከማችም። መለስ ዜናዊ ግን ኢትዮጵያ ለምትባል አገር በጎ ስሜት ስለሌለው የዝርፊያው ቀንደኛ መሪ በመሆን አገሪቷን የዘራፊዎችና የወሮበላዎች መናኸሪይ በማድረግ ለኢትዮጵያችን ያለውን ክፍ ስሜት አሳይቶናል።

ብሄራዊ ስሜት ያለው መሪ የገዛ አገሩን ድሃ ገበሬዎች አፈናቅሎና መሬት አልባ አድርጎ ለኢትዮጵያ በጎ አመለካከት ለሌላቸው ቡድኖች ለምና ድንግል መሬቶችን በመሸጥ ዜጎችን የባእዳን ጥገኛ አያደርግም ነበር። መለስ ግን መሬቱን ለተቀራማቾች በማከፋፈል ኢትዮጵያዊያንን ያሳዘነ ተግባር ፈጽሞ ብሄራዊ ስሜት የሚባል ነገር እንደሌለው ያስመሰከረ የኢትዮጵያችን ጠላት የሆነ ግለሰብ ነው እንጂ ብሄራዊ ስሜት አለው ተብሎ መወድስ ሊቀርብለት የሚገባ ግለሰብ አይደለም።

እኛ ኢትዮጵያዊያን መለስ ዜናዊን የምናውቀው በአገር ከዳተኝነቱ ነው እንጂ በብሄራዊ ስሜቱ አይደለም። እርሱን የምናውቀው ባየነው ተግባሩ ነው እንጂ በነውረኛ ቡድኖች ሊገነባለት የሚሞከረውን ተክለሰውነት አይደለም። ይህን አገር ከዳተኛና ዘረኛ ግለሰብ ከጫንቃችን ላይ አሽቀንጥረን ወዲያ መጣል የኢትዮጵያዊነት ግዴታችን ነው። መለስና ዘራፊ ቡድኑን ከተቆናጠጡበት ስልጣን ላይ አውርደን ለመጣል ሳናቅማማ የሚፈነቀሉ ድንጋዮችን ሁሉ እንፈነቅላለን።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!