የአሸባብ ዛቻና የሶማሊያ አሜሪካዉያን

በያዝነዉ ሳምንት መጀመሪያ ሶማሊያ ዉስጥ የሚንቀሳቀሰዉ ከአልቃይዳ ጋ ትስስር እንዳለዉ የሚነገርለት ፅንፈኛ እስላማዊ ታጣቂ ቡድን አሸባብ በዩናይትድ ስቴትስ፣ ካናዳ፤ ብሪታኒያ እንዲሁም በሌሎች የምዕራብ ሃገራት በሚገኙ የገበያ ማዕከላት ላይ ጥቃት እንደሚያደርስ መዛቱ ተሰምቷል።