ዘረኝነትንና ያለመቻቻል ስሜትን ፣ ጀርመን መታገል እንደሚኖርባት የአውሮፓ ም/ቤት ፀረ ዘረኝነት ኮሚሽን አሳሰበ። ኮሚሽኑ ትናንት ይፋ ባደረገው ዘገባ፤ በተለይ ወንጀለኞችን በመያዝና ጥፋተኞችን ተከታትሎ ተገቢውን ቅጣት በመስጠት ረገድ ድክመት ይታያል

ባለፈው ቅዳሜ በነፃ የተለቀቁት የቀድሞዋ የዩክሬን ጠቅላይ ሚኒስትር ዩልያ ቲሞሼንኮ ለፕሬዝዳንትነት የመወዳደር እቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል ። ከእስር እንደተለቀቁ ወደ ክየቩ የነፃነት አደባባይ በመሄድ ደስታቸውን እዚያ ከተሰበበሰው ከ100 ሺህ ከሚበልጥ ህዝብ ጋር የተጋሩት ቲሞሼንኮ በውዝግቡ የተገደሉት ሰዎች ጉዳይ እንዲጣራም ጠይቀዋል ።

በርዋንዳ የጎሣ ጭፍጨፋ ወቅት የግድያ ትዕዛዝ ሰጥተዋል ተብለው የተጠረጠሩት የቀድሞው የወንጌላዊቷ ጴንጠቆስጤ ቤተ ክርስትያን ቄስ ዣን ቦስኮ ዊኪንዴ ችሎት ዛሬ በመዲናይቱ ኪጋሊ ተጀመረ።

በኦጋዴን አካባቢ የሚካሄደውን የነዳጅ ዘይት ቁፋሮ ኣጥብቆ እንደሚቃወም ኣማጺው የኦጋዴን ነጻ ኣውጪ ግንባር በምህጻሩ « ኦ ኤን ኤል ኤፍ » ኣስታወቀ። ኣንድ ኣንጋፋ የግንባሩ መሪ ለ« አይ ፒ ኤስ » የዜና አገልግሎት እንደገለጹት በኦጋዴን የሚገኘው የነዳጅ ዘይት ከለማ የኢትዮጵያን መንግስት ባለጸጋ ያደርገዋል።

በአንድ ወቅት ምድር ላይ ይኖሩ የነበሩ እንስሳት አሁን ዘራቸዉ በመጥፋቱ በምስል ብቻ ከበርካታ ሚሊዮን ዓመታት በፊት እንደነበሩ ከመግለጽ የዘለለ አሻራ አጥተዋል። ዛሬስ ቁጥራቸዉ እየተመናመነ የሄደዉ የዱር እንስሳት የወደፊት እጣ ምን ይሆን?

በኦጋዴን አካባቢ የሚካሄደውን የነዳጅ ዘይት ቁፋሮ ኣጥብቆ እንደሚቃወም ኣማጺው የኦጋዴን ነጻ ኣውጪ ግንባር በምህጻሩ « ኦ ኤን ኤል ኤፍ » ኣስታወቀ። ኣንድ ኣንጋፋ የግንባሩ መሪ ለ« አይ ፒ ኤስ » የዜና አገልግሎት እንደገለጹት በኦጋዴን የሚገኘው የነዳጅ ዘይት ከለማ የኢትዮጵያን መንግስት ባለጸጋ ያደርገዋል።

በዩጋንዳ ትናንት ጀምሮ ግብረ ሰዶማዊነት የሚቃወም ህግ ተደንግጓል ። የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የዩጋንዳ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ግብረ ሰዶማዊነትን በመቃወም ባለፈው ታህሳስ ያሳለፈውን ህግ ትናንት በፊርማቸው አፅደድቀዋል ። ህጉ የፀደቀው በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና ግብረሰዶማዊነትን በሚቃወሙ ወገኖች መካከል

አንድነት ለፍትህ እና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ መድረክ በመባል ከሚታወቀው የፓርቲዎች ስብስብ መታገዱ ተሰማ። አንድነት የታገደው፤ የመድረኩ አመራር አካላት እንደሚሉት፤ የግንባሩን ደንብና መመሪያ አክብሮ ለመንቀሳቀስ ባለመቻሉ ነው።

የዚምባብዌ ፕሬዚደንት ሮበርት ሙጋቤ ትናንት ዘጠናኛ ዓመታቸውን አከበሩ። ምዕራቡ ዓለም ጨካኝ አምባገነን አድርጎ የሚመለከታቸው ሮበርት ሙጋቤ በአፍሪቃ ብዙ ደጋፊዎች አሉዋቸው። ይሁንና፡ ሙጋቤ አምባገነን ናቸወ የሚለውን አነጋገር በለንደን የሚታተመው ሳምንታዊ መጽሔት «ኒው አፍሪካ» ዋና አዘጋጅ ባፉር አንኮማ መሠረተ ቢስ ሲል አጣጥሎታል።

ዩክሬንን ለሶስት ወራት ግድም ያተራመሳት የተቃውሞ ሰልፍ በእዚህ ሳምንት ውስጥ ተባብሶ በመቀጥል ለበርካታ ሰዎች ህይወት መጥፋት ሰበብ ሆኖዋል። ተቃዋሚዎች የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት በአስቸኳይ ስልጣን እንዲለቁ ጠይቀዋል። ፕሬዚዳንቱ በበኩላቸው ተቃዋሚዎች በኃይል ስልጣን ሊይዙ ይጥራሉ ሲሉ ይኮንናሉ። እስካሁን ቢያንስ 77 ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል።

ሱዳን መዲና ካርቱም ውስጥ በ6 ጋጠወጦች የተደፈረችው ኢትዮጵያዊት ስደተኛ፣ ወጣት፣ ነፍሰጡር ለአንድ ወር እስር ቤት እንድትቆይ እና 950 ዶላር እንድትቀጣ ትናንት ተበየነባት። ወጣቷ ኢትዮጵያዊት ስትደፈር 7ኛው ወንጀለኛ ድርጊቱን በሞባይል ቀርፆ በማኅበራዊ መገናኛ ዘርፍ ማሰራጨቱም ተነግሯል። ወጣቷ በአሁኑ ወቅት እስር ቤት ነው የምትገኘው።

በደቤብ ኢትዮጵያ ዳውሮ ዞን የዲሳ እና ዙሪያው አካባቢ ኗሪዎች የወረዳ መስተዳድር እንዲመሰረትላቸው እየጠየቁ ነው።
የመንግስት ባለስልጣናት ግን አካባቢው ለወረዳ መስተዳድር መሰረታዊ መመዘኛዎችን ኣያሟላም እያሉ ነው። በዚሁ ምክኒያት ተቃውሞ ያሰሙ

የጀርመኑ ዓለም አቀፍ የፊልም መድረክ “በርሊናለ” ዘንድሮ ለ 64ኛ ግዜ የተካሄደ ሲሆን በዓለም ዙሪያ በተለያዩ አገሮች የተሠሩ ከ5000 በላይ ፊልሞች ቀርበዉ በመድረኩ ከ 400 በላይ ፊልሞች ታይተዉበታል። ለአስር ቀናት የዘለቀዉ የጀርመኑ ዓለም አቀፍ ፊልም ፊስቲቫል በኢትዮጵያዉያን የተሠራ ፊልምን፤ አቀርቦ ሸልሞአል።

የአውሮፓውሕብረት፣በዝብምባብዌላይጥሎትየነበረውንማዕቀብበአብዛኛውእንዲነሣአድርጓል።ከፕሬዚዳንት
ሮበርት ሙጋቤና ባልተቤታቸውበስተቀር ፰ የመንግሥትአባላትየሆኑፖለቲከኞችወደአውሮፓውሕብረትአባልሃገራት
መግባትይፈቀድላቸዋልተብሏል።የአውሮፓው ሕብረት በዝምባባዌ ላይ ማዕቀብ

የጀርመን የትምህርትና የምርምር ሚንስቴር ፣ እ ጎ አ ከ እንደ ጎርጎሪዮሳዊው ዘመን አቆጣጠር ከ 2000 ዓ ም አንስቶ፣ ዐበይት የሳይንስ አርእስት እየመረጠ፤ ሕብረተሰቡ በያመቱ በአንድ ርእሰ ጉዳይ ላይ እንዲወያይ ፤ እንዲከራከር፤ በቀጥታ በተግባር

ከማክሰኞ፥ የካቲት 11 ቀን 2006 ዓም አንስቶ የተባባሰዉ የዩክሬን የፀጥታ ሁኔታ ወደእርስ በርስ ጦርነት እንዳያመራ እየተሰጋ ነዉ። የሀገሪቱ የፀጥታ ኃይሎች የመንግስት በጎዳና ላይ በሚካሄደዉ ግጭት መሃል ተቃዋሚዎች ወደ1,500 ጠብመንጃ መዉሰዳቸዉን አመልክተዋል።

ከ 20 ዓመት በፊት ሩዋንዳ ውስጥ ሙቩምባ በተባለች ሰሜን ምሥራቃዊ ከተማ ከንቲባ የነበሩት ኦንስፎር ሩዋቡኮምብ የተባሉት የ 54 ዓመት ጎልማሳ ፣ ያኔ በአንድ ቤተ-ክርስቲያን የተጠለሉ ሩዋንዳውያን እንዲጨፈጨፉ በማድረጋቸው ፣ ፍራንክፈርት ጀርመን ውስጥ

ኢትዮጵያ እጅግ ደሀ ከሚባሉት ጥቂት የዓለማችን ኣገሮች መካከል ብትመደብም በሌላ ጎኗ ደግሞ በተፈጥሮ ኃብት የበለጸጉ ከሚባሉት አካባቢዎች መካከልም ያንኑ ያህል ትጠቀሳለች። ለዓብነት ያህልም ለግብርና ምቹ በሆነ ሰፊ መሬት የታደለችው ኢትዮጵያ በቡና ምርትም ቀዳሚ ከሚባሉት መካከል ስትሆን በእንስሳት ሀብቷም እንዲሁ ከዓለም 10ኛ ናት።

ኢትዮጵያ ዉስጥ የመሬትና ዉሃ ቅርምት ማኅበረሰቡን እየጎዳ እንደሚገኝ ዓለም ዓቀፉ የመብት ተሟጋች ሂዉማን ራይትስ ዎች አመለከተ። ድርጅቱ ይህን አመልክቶ ባወጣዉ ዘገባ በዚህ ምክንያትም ኢትዮጵያና ኬንያ ዉስጥ 500,000 አርብቶ አደሮች ለችግር መጋለጣቸዉን ገልጿል።

እየጠረቃ ከመጣዉ የአፍሪቃ ምጣኔ ሐብት ከብዙዎቹ ቀድማ የገባች ብዙ የተጠቀመችና የምትጠቀም አዲት ሐገር አለች። ቻይና።እንደ ጎሮጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር በሁለት ሺሕ አስራ-ሁለት ቻይና ከአፍሪቃ ጋር ያደረገችዉ የንግድ ልዉዉጥ ሁለት መቶ ቢሊዮን ዶላር ነዉ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተወልደ ገብረማርያም የአፍሪቃ የበረራ እህት ድርጅቶች በአህጉሩ ባለው የበረራ ገበያ ላይ ያላቸውን ድርሻ ከፍ ለማድረግ ተጠናክረውሊሰሩ እንደሚገባ አስታወቁ።

በናይጄሪያ የክርስትና እና የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ ብዙም ሰላም አይስተዋልም። ከሳምንቱ መጨረሻ ጀምሮ ዳግም በሰሜን ምስራቃዊ ናይጄሪያ ከ100 የሚበልጡ ሰዎች ተገድለዋል። ለዚህም የሚጠረጠረው የናይጄሪያው አክራሪ ቡድን ቦኩ ሀራም ነው።

ባለፈዉ መጋቢት ወር የሴሌካ አማፅያን ርዕሰ ከተማ ቦንጊን ከተቆጣጠሩወዲህ የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፑብሊክ የፀጥታ ይዞታ ከዕለት ወደዕለት እየከፋ ነዉ። ክርስቲያንና ሙስሊሞች አንዳቸዉ በሌላቸዉ ላይ ተነስተዋል። ሰዎች ጎዳና ላይ ጥቃት ይደርስባቸዋል፣ በቆንጨራ ወይ በጥይት ተመተዉ ይገደላሉ፤ አካላቸዉ ይጎድላል።

በበርሊኑ 64ኛ የፊልም ትርዒት፤ ባለፈው ሳምንት ከ 400 በላይ ፊልሞች ለተመልካቾች ቀርበው ታይተዋል። በዚያ ከቀረቡት የውጭ ፊልሞች መካከል፤ አንዱ በጠለፋና መደፈር ላይ ያተኮረው በአቶ ዘርእሰናይ ብርሃነ መሐሪ የተሰናዳው ኢትዮጵያዊ ፊልም ነው።

የመቀሌና ፤ በበልጂግ የሎይቨን ካቶሊካዊ ዩንቨርስቲ መካከል ባለፉት ዓመታት የተደረጉ የሥራ ትብብሮችና ውጤቶችን የገመገመ፤ የወደፊቱን አቅጣጫም ያመላከተ ስብሰባ ባለፈው ሰሞን በሎይቨን ዩንቨርስቲ ዋና ቤተ መጻሕፍት አዳራሽ መካኼዱን ገበያው ንጉሤ የላከልን

ዛሬ ጠዋት ጄኔቫ – ዚውዘርላንድ ላይ ለማረፍ የተገደደው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጠላፊ ራሱ የአይሮፕላኑ ረዳት አብራሪው መሆኑ ተረጋግጧል። በርካታ መንገደኞችን አሳፍሮ ከአዲስ አበባ ወደ ሮም ይበር የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አይሮፕላን ጄኔቫ አየር ማረፊያ ሲራርፍ በመንገደኞቹ ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

ያዩ እንደሚሉት በርግጥም ዘግናኝ ነዉ።የሰዉ አንገት በገጀራ ይቀነጠሳል።እጅ፥ እግር፥ በጎራዴ ይቆረጣል።ሌላ አካል በጩቤ ይጨቀጨቃል። መንገዶች በደም አበላ ጨቅይተዋል-እየጨቀዩም ነዉ።አስከሬን በየጉርጓዱ ይከመራል።ከተንቀሳቃሽ ሥልክ እስከ ምግብ፥ ከሐብል እስከ ብስክሌት ያሉ ቁሳቁሶች ይመዘበራሉ። ቤቶች፥ መደብሮች፥ ቁሳቁሶች፥ መሳጂዶች ይነዳሉ።

በትላልቅ የኢትዮጵያ ከተሞች፣ በተለይ በአዲስ አበባ የመኖሪያ ቤቶች ችግር እንዳለ ብዙ ሲነገር ይሰማል። የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ከሕዝቡ ፍላጎት ጋ ያልተጣጣመበት ምክንያቱ እና መፍትሔው ምን ሊሆን ይችላል? ስለጉዳዩ የሚከታተሉ ሰዎችን አወያይተናል።

በሊቢያ እአአ የፊታችን የካቲት 20፣ 2014 ዓም አዲስ ምክር ቤት ይመረጣል። ከያካባቢው 20 አባላት፣ ባጠቃላይ 60 አባላት የሚጠቃለሉበት ይኸው ምክር ቤት በሚቀጥሉት ወራት ለሀገሪቱ አዲስ ሕገ መንግሥት የማርቀቅ ስራ ይጠብቀዋል። ይህ ስራው ቀላል እንደማይሆን እና የምርጫው ሂደትም በተረጋጋ ሁኔታ መከናወኑ እንደሚያጠራጥር ታዛቢዎች ገምተዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታየውን ሕገወጥየዱርእንስሳትአደንናንግድንበተመለከተ ከመላ ዓለም የተውጣጡ የመንግሥት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች እና ጠበብት በዚህ ሳምንት ለንደን ብሪታንያ ስብሰባ አካሄዱ። ለተፈጥሮ ጥበቃ እና ለዱር አራዊት ህልውና የሚሟገቱት ጠበብት እንዳመለከቱት፣

በፍርድ ቤቱ ዉሳኔ መሠረት አቶ አስራት አምስት ወራት እስራት ተቀጥተዉ፥ በሁለት ዓመት ገደብ ተለቀዋል።የአቶ አስራት ጠበቃና ፓርቲያቸዉ ብይኑን ተቃዉመዉ ይግባኝ እንደሚጠይቁ አስታዉቀዋል

እጎአ የካቲት 14 ቀን ማለትም ዛሬ በተለይ በምዕራብ ሀገራት የፍቅረኛሞች ቀን ይከበራል። በአዲስ አበባ እና አካባቢዋም ከአመት ዓመት ቀኑን የሚያከብሩት ፍቅረኛሞች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። ወጣቶቹ የት እና እንዴት ያከብሩታል? አከባበሩ ምን ይመስላል?

የተመድ መቅዲሹ አዉሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የደረሰ ፍንዳታ ህይወት አጥፍቶ ጉዳት ቢያደርስም የሶማሊያ መንግስት እንዲህ ያለ ጥቃትን ለማስቆም የሚያደርገዉን ጥረት መደገፉን እንደሚቀጥል አስታወቀ። ዋና ፀሐፊ ባን ጊሙን በጥቃቱ ህወታቸዉን ላጡት ቤተሰቦችና ለተጎዱት ሃዘናቸዉን ገልጸዋል።