የሩስያ ወታደሮች በክሬሚያ ተኩስ ከፈቱ
ሩስያ ክሪሚያን ይፋ የግዛትዋ አካል አድርጋ ከተቀበለች በኋላ ሩስያ በዚያ በይፋ የጦሩ ቁጥጥሯን አጠናከረች። ከዩክሬይን በተገነጠለችው ክሪሚያ ውስጥ ባሉት 147 የዩክሬይን የጦር ሰፈሮች የሩስያ ባንዴራ መውለብለብ መጀመሩን የሩስያ መከላከያ ሚንስቴር አስታውቋል።
ሩስያ ክሪሚያን ይፋ የግዛትዋ አካል አድርጋ ከተቀበለች በኋላ ሩስያ በዚያ በይፋ የጦሩ ቁጥጥሯን አጠናከረች። ከዩክሬይን በተገነጠለችው ክሪሚያ ውስጥ ባሉት 147 የዩክሬይን የጦር ሰፈሮች የሩስያ ባንዴራ መውለብለብ መጀመሩን የሩስያ መከላከያ ሚንስቴር አስታውቋል።
የአወሮጳ ህብረት ከአፍሪቃ ጋ በብራስልስ ጉባዔ ሊያደርግ ጥቂት ጊዜ በቀረበት ባሁኑ ጊዜ የጀርመን መንግሥት ለአፍሪቃ ህብረት ተጨማሪ ፊናንስ ርዳታ ለመስጠት ቃል ገባ። እርግጥ ፡ አፍሪቃውያን ለችግሮቻቸው ራሳቸው መፍትሔ ለማፈላለግ ይሻሉ፡ ያም ቢሆን ግን፡ ጀርመን ከጎናቸው መቆሟን የሀገሪቱ የልማት ትብብር ሚንስትር ጌርድ
ዜና 22.03.2014
የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሩስያ ፣ በዩክሬን ስር የነበሩትን ክሪምያንና የሴቫስቶፖል ከተማን የፌደሬሽኗ አካል የምታደርግበትን ይፋ ሰነድ ዛሬ ፈርመዋል ።
ኮርፖሬሽኑ በከተማዋ በመገንባት ላይ ባሉት ሁለት መስመሮች ማለትም በሰሜን ደቡብ ና በምስራቅ ምዕራብ መስመሮች በቀን ወደ 250 ሺህ መንገደኞች ለማጓጓዝ አስቧል ።
በስምምነቱ ሰነድ ላይ እንደተገለፀው የበርሊን አስተዳደር ስደተኞቹ ያቀረቡለትን ጥያቄዎች ለመመለስ ቃል ገብቷል ።እርዳታ ሰጭዎች አስፈላጊውን እንክብካቤ እንዲያደርጉላቸውም ፈቃደኝነቱን ገልጿል ።
ያልተፈለገ እርግዝናን እና ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ኮንዶም በዋነኝነት የሚጠቀስ መከላከያ ነው። ለመሆኑ የኮንዶም ግብይት በሶማሊያ እና ኢትዮጵያ ምን ይመስላል?
የዓለም ዜና
ኢትዮጵያ፣ 152 ሃገራትን ያቀፈው የዓለም የንግድ ድርጅት (WTO)አባል ለመሆን አዲስ አበባ ውስጥ በ 4ኛውና በመጨረሻው ዙር ድርድር ላይ እንደምትገኝ ተገለጠ። ስለዚህ ድርድር ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
አፍሪቃ ውስጥ ከውዝግብ ካልተላቀቁት አካባቢዎች አንዲዱ የሱዳን ምዕራባዊ ክፍለ ሀገር ፣ ዳርፉር መሆኑ አይታበልም። የዳርፉር ኑዋሪዎች፤ እ ጎ አ ከ 2003 ዓ ም አንስቶ ፤ ከሽብር ሁከት ግድያና ስደትገና አልተገላገሉም፤ በመኻሉ በቆዩ ችግሮች ላይ አዳዲስ ታክለዋል።
የአውሮፓ ሕብረትና ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ፤ በምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) የሚመራውን የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር በሚያደናቅፉት ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠነቀቁ። የሕብረቱና የአሜሪካ ተወካዮች፤ አምባሳደር ዶናልድ
በዓለም ላይ ያሉ በርካታ ሃገራት ቱሪዝምን ዋና የኤኮኖሚ ምንጭ በማድረግ በየዓመቱ በሚሊያርድ የሚቆጠር ገንዘብ በማግኘት፤ ቱሪዝምን ጠቃሚ የኤኮኖሚ ዘርፍ ማድረጋቸዉ ይታወቃል። ቱሪዝም ከገቢ ማስገኛነቱ ባሻገር ባህልና ሃገርን በማስተዋወቁ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለዉ ይታወቃል።
ጽሕፈት ቤቱ ኦስሎ ኖርዌይ የሚገኘዉ የሃገራት የተፈጥሮ ሃብት አስተዳደር ይዞታ ግልፅነት ሊኖረዉ ይገባል የሚለዉ በእንግሊዝኛ ምህፃሩ EITI የተሰኘዉ ስብስብ ኢትዮጵያ ለአባልነት ያቀረበችዉን ማመልከቻ ተቀበለ። በአንፃሩ መንግስት የሲቪል ማኅበራትን እንቅስቃሴ ማረጋገጥ እንደሚኖርበት የEITI ቦርድ በአፅናኦት አሳስቧል።
ይሁንና የማማከሩ ምግባር መሳካቱን የጀርመን መከላከያ ሚኒስቴር ባለሥልጣናት ይጠራጠራሉ።ምክንያታቸዉ የሶማሊያ ጦር ግልፅ አደረጃጃት የለዉም የሚል ነዉ።ማቲያስ ቬበር እንደሚሉት የሶማሊያ ጦር አደረጃጃትን ቅጥ ካሳጡት ዋናዉ በጎሳ ልይ የተመሠረተ መሆኑ ነዉ።
የዕለቱ ዜና
በጀርመን የሕዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት፤ የቀድሞው የውጭ ፖለቲካ ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሩፕሬሽት ፖሌንዝ ፣ ሩሲያ፣ የክሪሚያን ልሳነ-ምድር በኃይል መያዟ ፤ በኃላፊነት፤ የአውሮፓውን ሕብረት አይመለከትም አሉ። እንደርሳቸው ትዝብት፤ ትናንት፤
ለሰወስት ወር በሚቆየዉ ጉባኤ ከአምስት መቶ የሚበልጡ የመንግሥት፤ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፤ የሐይማኖት ተቋማት፤ የኩባንያና የንግድ ድርጅት ተጠሪዎች፤የሰራትኞች፤ የሙያና የፆታ ማሕበራት ተወካዮች፤ የሥነ-ጥበብ ባለሙያዎችና ታዋቂ ግለሰቦች ተካፍለዋል
ሎሪያል ተቋምና የተመ የትምህርት ሳይንስና ባህል ድርጅት ማለትም UNESCO በጋራ ያዘጋጁት 16ኛዉ የሳይንስ እና ሴቶች ልማት መርሃግብር ኢትዮጵያዊቷን ሳይንቲስት ዶክተር ሰገነት ቀለሙን ከዓመቱ ተሸላሚዎች አንዷ አድርጎ መረጠ።
የካቲት 29 ቀን 2006 ዓ ም፤ (08 03 2014) ከደቡብ ምሥራቅ እስያዊቷ ሀገር ማሌሺያ 239 መንገደኞችን አሣፍሮ ወደ ቤይጂንግ ጉዞ የጀመረ አኤሮፕላን፣ አቅጣጫውን ድንገት ለውጦ ከተመለሰ በኋላ እስካሁን እምን እንደገባ በይፋ ያልታወቀበት ሁኔታ
በጋምቤላ የሚኖሩ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች የዓለም ዓቀፋ ኅብረተሰብ አስፈላጊዉ ድጋፍ ካላደረገላቸዉ በቀር በረሃብና በሽታ ምክንያት ለአደጋ ሊጋለጡ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አስተዳደር አስጠነቀቀ።
ጀርመን ከአፍሪቃ ጋር በትብብር በምትሠራባቸው ጥናትና ምርምሮች ላይ አትኩሮ ትናንት በርሊን ውስጥ በተካሄደ ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ ላይ የተገኙት የናምቢያ የግብርን ምክትል ሚኒስትር አና ሽዌዳ በመስኩ በሚከናወኑት የትብብር ሥራዎች ሁለቱም ወገኖች ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል ።
የዩክሬይን ግዛት የሆነችው ክሪምያ ባለፈው እሁድ ከሩስያ ፌዴሬሽን ጋ ዳግም ለመዋሃድ የሚያስችላትን አወዛጋቢውን ህዝበ ውሳኔ ካካሄደች በኋላ የአዉሮጳ ኅብረት አባል ሃገራት በሩስያ ላይ የመጀመርያዉን ማዕቀብ ጥለዋል። በተጣለዉ ማዕቀብ መሠረት፣ 21 ሩሲያውያን እና የክሪሚያ ባለሥልጣናት በምዕራቡ ዓለም፤
አምባሳደሯ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ከአቶ ሐይለማርያም ደሳለኝና ከተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይም ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ያደረጉት ዉይይት የኢትዮጵያን የፓለቲካ የሠብአዊ መብትና የዴሞክራሲ ይዞታን፤ የእስረኞች ሁኔታን የሚመለከት እንደነበር የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች ዘግበዋል
የእሥልምና ሥነ-ፅሁፍ ምሥራቅ አፍሪቃ ዉስጥ በሚነገሩ በተለያ ቋንቋዎች ለረጅም ጊዜ የተለያዩ አገልግሎቶች ሲስጥ እንደነበር አጥኚቹ ተናግረዋል።በተለይ ሐረር ከተማ የገኙ መዛግብትና መፃሐፍት የምሥራቅ አፍሪቃዉ ጥንታዊዉ የሙስሊሞች ሥልጣኔ ከዝነኛዋ የቲምቡክቱ (ማሊ) ሥልጣኔ ጋር ታሪካዊ ትስስር እንዳለዉ ተመራማሪዎቹ አስታዉቀዋል
ለሰወስት ወር በሚቆየዉ ጉባኤ ከአምስት መቶ የሚበልጡ የመንግሥት፤ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፤ የሐይማኖት ተቋማት፤ የኩባንያና የንግድ ድርጅት ተጠሪዎች፤የሰራትኞች፤ የሙያና የፆታ ማሕበራት ተወካዮች፤ የሥነ-ጥበብ ባለሙያዎችና ታዋቂ ግለሰቦች ተካፍለዋል
ኢትዮጵያ ዉስጥ በየአካባቢዉ እንደሚነገረዉ ቋንቋ የየግል መጠሪያ ቢኖረዉም በአብዛኛዉ ግን ሬት በሚለዉ ስሙ ይታወቃል። ብዙዎችም ዛሬም ቢሆን ለጡት አስጣይነት ይጠቀሙበታል። ለመብቀል ብዙ ክብካቤና ዉሃ አይፈልግም፤ በዉስጡ ግን በርከት ያለ ዉሃ የማጠራቀም ባህሪ አለዉ።
የዓለም ዜና
ሐረር ከተማ ዉስጥ በሳምንት ልዩነት ባለፈዉ ቅዳሜ ማታም የእሳት አደጋ መድረሱን ኗሪዎቿ ይናገራሉ።
ጊዚያዊ ጥቅላይ ሚንስትሩ እንዳሉት የሩሲያ ጦር በሳቸዉ አገላለጥ ለክሪሚያ «ገንጣይና ከፋፋዮች» ከለላ መስጠቱ እዉነት ነዉ።የዚያኑ ያክል ያዜንዩክና ጓዶቻቸዉ በዩናይትድ ስቴስና በተባባሪዎችዋ እቅፍ ዉስጥ መሆናቸዉም ሐቅ።
ከዓለም የጦር መሣሪያ በመግዛት ብዛት ቻይና ፣ህንድ እና ፓኪስታን የመጀመሪያውን ስፍራ ይዘዋል ይላል የዓለም አቀፍ የጦር መሣሪያ ንግድን የሚመረምረው «የሰላም ጥናት ተቋም» በምህፃሩ «ሲፕሪ» ዛሬ ያወጣው ዘገባው።
የምዕራብ ሀገራት ያወገዙት በዩክሬን ክሪምያ ልሳነ ምድር ህዝበ ውሳኔ ተጠናቀቀ። ለሞስኮ መንግስት የሚያደላዉ የክርምያ አስተዳደር ባለስልጣናት የህዝበ ዉሳኔዉ ዉጤት ከሩስያ ጋር ለመቀላቀል ማረጋገጫ የሰጠ መሆኑን በመግለፅ ላይ ይገኛሉ። ከክሪሚያ አስተዳደር በወጣዉ መግለጫ መሰረት 93 በመቶ መራጭ፤
የምዕራብ ሀገራት ያወገዙት ህዝበ ውሳኔ በዩክሬንክሪምያልሳነምድርተጠናቀቀ። ለሞስኮ መንግስት የሚያደላዉ የክርምያ አስተዳደር ባለስልጣናት ከሩስያ ህዝበ ዉሳኔዉ ዉጤት ከሩስያ ጋር ለመቀላቀል ማረጋገጫ የሰጠ መሆኑን በመግለፅ 93 በመቶ መራጭ የክሪምያ ልሳነ ምድር ከዩክሪይን እንዲገነጠል መወሰኑን እየገለፀ ነዉ።
የሰውን ፣ ሰብአዊ መብት ለማክበር ፣ በኤኮኖሚ፤ በልማት መደርጀት ቅድመ ግዴታ አይሆንም። የትምህርት መሥፋፋት፣ እርግጥ እገዛ ሊያደርግ ይችላል። ሙሉ ወሳኝነት አለው ተብሎ ግን አይታሰብም።
ወደ የማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ የተጓዙት የጀርመን የልማት ትብብር ሚንስትር ጌርድ ሚውለር ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የርስበርስ ጦርነት ያመሰቃቀላንት የማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ ሲቭል ሕዝብ ስቃይ የማብቃትበቸልት ማለፍ እንደማይገባው አሳስቡ።
በርካታ ናይጀሪያውያን ቦኮሃራም የሚያደርሰውን ጥቃት በመሸሽ እየተሰደዱ ነው ። አብዛኛዎቹ የሚፈናቀሉት በተለይ ባለፈው ዓመት በግንቦት ወር መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገባቸው ከሰሜን ምሥራቅ ናይጀሪያ ግዛቶች ነው ። በዚህ ሰበብ የሃገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ መሄድ በተለይ በትላልቅ ከተሞች አሉታዊ ተፅእኖ አሳድሯል ።
ባለፈዉ የዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን ዕለት በተደረገዉ ታላቅ ሩጫ ሁከትና ብጥብጥ ፈጥራችኋል በሚል የተከሰሱ ሰባት ሴቶች እና ሶስት ወንዶች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ።
ፈጣን ፣ደፋር እና ወጣት አትሌት ናት። ገንዘቤ ዲባባ። የ23 ዓመቷ ወጣት ወደ ሩጫው ዓለም ከገባች 8 ዓመታት ተቆጠሩ።
የጀርመን ፍርድ ቤት ዛሬ ተገቢዉን ግብር ሳይከፍሉ በማጭበርበር በተከሰሱት የባየር ሙኒክ የእግር ኳስ ቡድን ሥራ አስኪያጅ ዑሊ ሆነስ ላይ የ3 ዓመት ተመንፈቅ እስራት በየነ።
በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ያተኮረ ውይይት ጄኔቭ ስዊትዘርላንድ ውስጥ ዛሬ ተካሂዷል ። የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ባዘጋጁት በዚሁ ውይይት ላይ በኢትዮጵያ ይፈፀማሉ የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በዝርዝር ቀርበዋል።
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ባለቀለም ፊልም በሆነው «ጉማ» በተሰኘው የሚሸል ፓፓታኪስ ፊልም ስም የተሰየመው የፊልም ስራ ሽልማት ለመጀመሪያ ጊዜ በብሄራዊ ቴአትር ባለፈው ሰምወን እለት ምሽት በድምቀት ተከናውኗል።
የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የዩክሬይንን የሽግግር መንግሥት ጠቅላይ ሚንስትር አርሴኒ ያዜንዩክ ትናንት በዋይት ሀውስ ቤተ መንግሥት ተቀብለው አነጋገሩ። ግዛቷ ክሪሚያ በሩስያ የተያዘባትን ዩክሬይን ዩኤስ አሜሪካ እንደምትደግፍ ኦባማ ለያዜንዩክ አረጋገጠዋል።
የዓለም ዜና
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ የትምህርት ክፍል በተማሪዎች ብዙም የማይመረጥበት ሁኔታ የትምህርት ዘርፉን ሕልዉና ሳይፈታተን እንደሚይቀር እየተገነገረ ነዉ።
ባለፈው ዓመት ፣ የዩናይትድ ስቴትስና የብሪታንያ የስለላ ድርጅቶች ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ የድርጅቶችን ፣ የግለሰቦችን የታወቁ የሀገር መሪዎችን የግል ተንቀሳቃሽ ስልኮች የድምጽ፤ የጽሑፍና ስዕል አገልግሎት ጭምር ይጠልፉ ነበር ተብሎ፣ ዜናው በዓለም
ፕሬዝዳንት ኪር ባለፈዉ ታሕሳስ በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሐላፊዎችን ከመንግሥት እኩል ሐገር ለመምራት ይሞክራሉ በማለት ወንጅለዋቸዉ ነበር።በቀደም ጁባ ዉስጥ ለተሰለፉት ወጣቶች ንግግር ያደረጉት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄምስ ዋኒ ኢጋ የአለቃቸዉን አባባል ደገሙት
የአፍጋኒስታን ምርጫ ከመካሄዱ አንድ ወር በፊት ታዛቢዎች በዚህ አጋጣሚ ለፉክክር የሚቀርቡ 11 እጩዎች ሶስቱ የሕዝቡን ቀልብ እንደያዙ ያመለክታሉ። የፕሬዝደንት ሃሚድ ኻርዛይ ወንድም ቃዩም ኻርዛይ ከፉክክሩ ራሳቸዉን አግልለዉ የቀድሞ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩትን ዛልማይ ራሶልን እንደሚደግፉ ገልጸዋል።
በማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ በቀድሞ የሴሌካ ሙሥሊም ዓማፅያን አንፃር የሚንቀሳቀሱት ራሱን ፀረ ባላካ ብሎ የሚጠራ የወጣት ክርስትያን ሚሊሺያ ቡድን አባላት ሽብራቸውን አስፋፉ። ሚሊሺያዎቹ ሙሥሊሞቹን ዜጎች መግደል ብቻ ሳይሆን
በጀርመናዊቷ የሀኖፈር ከተማ ባለፈው እሁድ የተከፈተው እና አምስት ቀናት የሚቆየው ትልቁ የኮምፒውተር ትርዒት የመረጃ ቴክኖሎጂን አጠባበቅ እንዴት አስተማማኝ ማድረግ ይቻላል ለሚለው ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶዋል።