«ኢኬያ» እና የእርዳታ ማሰባሰብ ርምጃው
«ኢኬያ» በመባል የሚታወቀው የስዊድናውያኑ የመኖሪያ ቤት እቃዎች መሸጫ መደብር ከጥር 26፣ እስከ መጋቢት 20፣ 2006 ዓም ድረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ እርዳታ የማሰባሰብ ተግባር በማካሄድ ላይ ይገኛል።
«ኢኬያ» በመባል የሚታወቀው የስዊድናውያኑ የመኖሪያ ቤት እቃዎች መሸጫ መደብር ከጥር 26፣ እስከ መጋቢት 20፣ 2006 ዓም ድረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ እርዳታ የማሰባሰብ ተግባር በማካሄድ ላይ ይገኛል።
የዓለም ዜና
የማዕከላዊት አፍሪቃ ሪፓብሊክ ሰሜናዊ ጎረቤት ፣ ቻድ፣ ከአካባቢው ሃገራት ፤ በጦር ኃይል ይበልጥ የደረጀች መሆኗ ይነገርላታል። በፕሬዚዳንት ኢድሪስ ደቢ የምትራው ቻድ፤ የማዕከላዊት አፍሪቃ ሪፓብሊክን ውዝግብ ለመፍታት ፤ ራሷ በምትፈለገው መልክ ውሳኔ
በየመን እስር ቤት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እስረኞች የፍትህ ያለህ እያሉ ነው። ከ 15 ዓመታት በላይ በየመን እስር ቤት ውስጥ እየተሰቃዩ እንደሚገኙ የገለጹት እነዚሁ ኢትዮጵያውያን እስረኞች ያለኣንዳች ማስረጃ ከ 25 ዓመት እስከ ይሙት በቃ ተፈርዶብናል ባይ ናቸው።
የአንድን ሀገር ወግ፤ ባህል፤ ታሪክ እና ሁለንተናዊ ጉዞን ለማወቅ፤ የህዝቦችዋን ባህላዊ የበዓል አከባበር፤ ስነ-ፅሁፎችዋን በተለይ ደግሞ ስነ- ግጥሞችዋን ተመልከት ሲሉ አንዳንድ ምሁራን ይገልፃሉ። በአሁኑ ወቅት በርካታ ገጣምያን በግጥም መድረኩ ሲሳተፉ ይታያል፤ በግጥም፤ እምቅ አድናቆትን በግጥም እምቅ ፍላጎትን፣
ካርቱሞች፥ የጠላቶቻቸዉን ቁርጥር መቀነስ፥ የደከመ ምጣኔ ሐብታቸዉን መጠገን ይሻሉ።አማፂያኑ፥ጁባዎች ዉጊያ ሲገጥሙ የዲፕሎማሲ፥ የገንዘብ፥ የመሳሪያ ምንጫቸዉ ካናቱ ተበጥብጧል።ሌፍ እንደሚሉት የደቡብ ሱዳን ጦርነት ለደቡብ ኮርዶፋን «ሳይደግስ አይጣላም» አይነት ነዉ-የሆነዉ።ቢያንስ ለጊዜዉ።
ታላላቆቹ መንግሥታት ፤ ዩናይትድ ስቴትስ፤ ሩሲያ፣ ቻይና ፣ ህንድና ሌሎችም ኅዋን በማሰስ ፤ ጨረቃንና ማርስን ዒላማ በማድረግ ፉክክራቸውን እንደቀጠሉ ናቸው። አዳዲስ የኅዋ ጣቢያዎችን የማቋቋም እቅድም አላቸው። የተጠቀሱት ሀገራት ብቻ ሳይሆኑ ፤
አሜሪካዊዉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር እንደሚሉት የደቡብ ሱዳን፣ የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ እና የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክን ጦርነት፣ግጭትና ፖለቲካዊ ቀዉስን ለማስቆም ለማስቆም በሚደረገዉ ጥረት መንግሥታቸዉ ጉሉሕ አስተዋፅኦ እያደረገ ነዉ
የዓለም ኣገሮች እንደየ ገቢያቸው በዓለም ባንክ ትንቢያ መሰረት የበለፀጉ መካከለኛ ገቢ ያላቸው እና ደኃ ኣገሮች ተብለው በሶስት ይከፈላሉ። በዚሁ መሰረት ዓመታዊ የኣገር ውስጥ ጥቅል ገቢያቸው ለህዝብ ቁጥር ተካፍሎ የእያንዳንዱ ዜጋ የነብስ ወከፍ ገቢ በዓመት ከ 12 000 የአሜሪካን ዶላር በላይ ከሆነ ከፍተኛ
ለደቡብ ሱዳን ነፃነት በጋራ የታገሉት የሐገሪቱ ፖለቲከኞች ካለፈዉ ታሕሳስ ጀምሮ የለየለት ዉጊያ ገጥመዋል።ጦርነቱን ለማስቆም የሚደረገዉ ሁለተኛ ዙር ድርድር ከታቀደለት ቀን ተሸጋሽጎ ቢጀመርም ተፋላሚ ወገኖች መካሰሳቸዉ መቀጠሉ ነዉ የተሰማዉ።
የዕለቱ ዜና
ብዙዉን ጊዜ አደገኛ ከሚባሉት የጤና ችግሮች ልብና ከልብ ጋ የተገናኙት በዋነኝነት ይጠቀሳሉ። በዓለማችን በአብዛኛዉ ለሞት ከሚያደርሱ የጤና እክሎችም አንዱ በመሆኑም ይታወቃል።
የደ/ሱዳን ኣማጺያን ከድርድሩ እራሳቸውን እንደሚያጋሉ ያስጠነቀቁት፤ ትላንት ከአዲስ ኣበባ እንደተገለጸው በሁለት ምክኒያቶች ነው። አንደኛው ያልተፈቱት አባሎቻቸው በኣስቸኩዋይ ካልተለቀቁ እና ሁለተኛው ደግሞ በዚያች ሀገር የሚገኙ የኡጋንዳ ወታደሮች ሀገሪቱን ለቀው ካልወጡ በሚል ነበር በቀጣዩ ድርድር ላይ እንደማይካፈሉ ያስታወቁት።
አፍሪቃ ውስጥ ርሀብ፣ የርስ በርስ ጦርነት እና ሌሎች ክስተቶች ከሚስተዋሉባቸው ሃገራት ተርታ ሶማልያ በምሳሌነት ትጠቀሳለች።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለማርያም ደሳለኝ በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳዮች እና ሀገሪቷን ከጎረቤት ሀገራት ጋር በሚያስተሳስሯት ነጥቦች ላይ ትናንት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
ሁለተኛዉ ዙር የሶርያ መንግሥትና የመንግሥቱ ተቃዋሚዎች ህብረት ድርድር ዛሬ በጄኔቭ ስዊትዘርላንድ ተጀመረ። ሁለቱ ተፋላሚ ሃይላት ባለፈው ወር መጨረሻ ያደረጉት የመጀመርያዉ ዙር ድርድር ያለምንም ዉጤት ነበር የተጠናቀቀው። በሳምንቱ መጨረሻ የተመድ ለሶርያውያኑ የሆምስ ከተማ አስፈላጊውን የሰብዓዊ ርዳታ ማድረስ አልቻለም።
በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳጊ ኢትዮጵያዉያን እንደሚማሩበት የሚገለፀዉ በጅድ የኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፍ ትምህርት ቤት ከተመሠረተ ከ15ዓመታት በላይ እንደሆነዉ ይነገራል።
የኦሎምፒክ ውድድሮች ኣጀማመር፣ የታሪክ ድርሳናት እንደሚጠቁሙት፣ ከ2700 ዓመታት በፊት ነበር፣ ከክርስቶስ ልደት በፊት፣ 776 ዓ ዓለም ገደማ መሆኑ ነው፣ በጥንታዊቷ ግሪክ፣ ኦሎምፒያ በምትባል ከተማ።
የጀርመኑ የልማት ትብብር ሚኒስቴር ጌርድ ሙለር ባለፈዉ ዓርብ በአዲስ አበባ ከኢትዮጵያ መንግስትና ከአፍሪቃ ህብረት ባለስልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት አፍሪቃ በሀገራቸው የውጭ ፖሊሲ ላይ ትልቅ ትኩረት ማግኘቷን አስታወቁ። ሚንስትሩ እንዳስረዱት፣
የዕለቱ ዜና
በያዝነዉ ሳምንት ማክሰኞ ፊስቡክ የመገናኛ መረብ ከተመሰረተ 10ኛ ዓመቱን ደፈነ። በፊስ ቡክ ፤ህዝባዊ ቅስቀሳ፤ በፌስቡክ አብዮት፤ በፌስቡክ መማመር፤ በፊስ ብክ ትዉዉቅ፤ እንዲሁም በፌስቡክ ስድድብ ሌላም ሌላም ይታያል። በአሁኑ ግዜ የኢንተርኔት አገልግሎት የማግኘት እድሉ ያላቸዉ፤ የፊስ ቡክ መረብን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ ናቸዉ።
የዕለቱ ዜና
የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ከአንድ ዓመት ገደማ በፊት፤ ከምድቡ ማጣሪያ ውድድሮችን አሸንፎ በአፍሪቃ የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ፤ ከ 31 ዓመታት ጥረት በኋላ ለመሳተፍ መብቃቱ ፤
በደቡብ አፍሪቃ ባለፈው ዓመት የተቋቋመው የ«አኻንግ ኤስ ኤ» ፓርቲ ሊቀ መንበር የሆኑት ፀረ አፓርታይድ ታጋይ ዶክተር ማምፌሌ ራምፌሌ እአአ የፊታችን ግንቦት ሰባት በሚካሄደው ቀጣዩ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪ ሄለን ሲለ አስታወቁ።
የዓለም ዜና
ዛሬ ማምሻዉን በተከፈተዉ በዓለም ዓቀፉ የክረምት ኦሎምፒክ ከ87 ሃገራት የተዉጣጡ ከሁለት ሺህ ስምንት መቶ በላይ አትሌቶች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የዓለም አዕምሯዊ ንብረት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ፍራንሲስ ጌሪ፤ በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገለጻ አደረጉ።
እንደ ጁዶ እና ሌሎች ተመሳሳይ የራስ መከላከል ስፖርታዊ ጥበቦች ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙም የተለመዱ አይደሉም። ሆኖም ጀርመን ነዋሪ የሆኑት ዶክተር ፀጋዬ ደግነህ ወደ ኢትዮጲያ ሄደው በዚህ ስፖርት ወጣቶችን ማሰልጠን ከጀመሩ አንስቶ አንዳንድ በአለም ዓቀፍ ደረጃ ሳይቀር ተሰልፈው የሚወዳደሩ ወጣት ኢትዮጵያውያንን ማፍራት እንደተቻለ ገልፀውልናል።
የዓለም ዜና
በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ም/ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ የእስር ጊዜያቸውን ቢጨርሱም ኣመክሮ መከልከላቸው ተሰማ። ህክምናም እያገኙ ኣይደለም ተብሏል። የኮንግረሱ ዋ/ጸኃፊ ለዶቸቬሌ እንደ ነገሩት ከሆነ አቶ በቀለ ገርባ የ 3 ዓመት ከ 7 ወር የእስር ጊዜያቸውን ኣጠናቀው መለቀቅ የነበረባቸው ባለፈው ጥር 11 ቀን ነበር
በያዝነዉ ሳምንት ማክሰኞ ፊስቡክ የመገናኛ መረብ ከተመሰረተ 10ኛ ዓመቱን ደፈነ። በፊስ ቡክ ፤ህዝባዊ ቅስቀሳ፤ በፊስ ቡክ አብዮት፤ በፊስ ቡክ መማመር፤ በፊስ ብክ ትዉዉቅ፤ እንዲሁም በፊስ ቡክ ስድድብ ሌላም ሌላም ይታያል። በአሁኑ ግዜ የኢንተርኔት አገልግሎት የማግኘት እድሉ ያላቸዉ፤ የፊስ ቡክ መረብን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ ናቸዉ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ከ31 ዓመት በኃላ ለአፍሪቃ ዋንጫ ተሳትፎ ያበቁ አሰልጣኝ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል። አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው። ይሁንና ትናንት የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻውን ከነበራቸው ኃላፊነት ማንሳቱን አሳውቋል።
የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር አዲስ ፕሬዝደንት መረጠ።
በመንግስት መግለጫዎች መሰረት ካለፉት 10 ዓመታት ወዲህ ኢትዮጵያ በየዓመቱ በሁለት ዓኃዝ ወይንም በእንግሊዝኛው ኣገላለጽ «ዳብል ዲጂት» የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ ላይ ትገኛለች። ይህ ማለት ባለስልጣናቱ እንደሚሉት ኢትዮጵያ በእነዚህ ዓመታት 11 ከመቶ እና ከዚያም በላይ እያደገች ነው።
የሰው ብቻ ሳይሆን የሥልጣኔውም ጭምር መገኛ የሆነው ግዙፉ የአፍሪቃው ክፍለ ዓለም ለብዙ ምዕተ ዓመታት ተዳክሞና በሌሎችም ተጽእኖ ሥር ከቆየ በኋላ ተመልሶ በዘመናዊ ሥልጣኔ ለማገገምና ርምጃ ለማሳየት የውጭ የሥነ ቴክሊክ ዝውውር ፣ አንዱ መንገድ ቢሆንም
የአዉሮጳ ኅብረት በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነዉን የሙስና ዘገባ ሰሞኑን ብራስልስ ላይ ይፋ አድርጓል።
ሕጋዊ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ የሌላቸዉና የሳዉዲ መንግስት እንዲወጡ የሚላቸዉ ወገኖች ሁኔታ ላለፉት ጊዜያት በተከታታይ ሲነገር ቆይቷል።
አዲስ አበባ ላይ ጠዋትና ማታ ወዳሰቡበት ለመድረስ ረዥም የታክሲ ወረፋ መጠበቁ ብቻ ሳይሆን የክፍያዉ ሁኔታም ተገልጋዮችን እያማረረ እንደሚገኝ ዮሐንስ ገብረ-እግዚአብሔር የላከዉ ዘገባ ያመለክታል።
ዶቼ ቬለ በየዓመቱ የሚያዘጋጀዉ «ምርጥ የድረ-ገፅ አምድ» በመባል የሚታወቀዉ ሽልማት በዓለማችን ጥሩ እንቅስቃሴን በማድረጉ የሚታወቅን ድረ-ገፅ በማወዳደር ሽልማት ያበረክታል። በዓለም ዙርያ በድረ-ገጽ ላይ ስለላ እጅግ እየተጣነከረ በመምጣቱ በርካታ ተጠቃሚዎች የግል ምስጢር ሰነዳችን በሌሎች እጅ ይወድቃል የሚል ስጋት ላይ ወድቀዋል።
ሁለት የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር፣ የ«ኦብነግ» ባለሥልጣናትን አግተዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሁለት የኬንያ ፖሊሶች በፍርድ ቤት ክስ እንደተመሠረተባቸዉ የመዲናይቱን ናይሮቢ ወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ክፍልን ጠቅሶ አዣንስ ፍራን ፕሪስ ዘግቦአል።
የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ሊቀ መንበር፣ እንዲሁም፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ሊቀ መንበር ዶክተር መረራ ጉዲና ደጋፊዎቻቸውን ለመጪው ምርጫ ለመቀስቀስ በወቅቱ በአውሮጳ
የዓለም ዜና
ዶቼ ቬለ በየዓመቱ የሚያዘጋጀዉ «ምርጥ የድረ-ገፅ አምድ» በመባል የሚታወቀዉ ሽልማት በዓለማችን ጥሩ እንቅስቃሴን በማድረጉ የሚታወቅን ድረ-ገፅ በማወዳደር ሽልማት ያበረክታል። በዓለም ዙርያ በድረ-ገጽ ላይ ስለላ እጅግ እየተጣነከረ በመምጣቱ በርካታ ተጠቃሚዎች የግል ምስጢር ሰነዳችን በሌሎች እጅ ይወድቃል የሚል ስጋት ላይ ወድቀዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን ከጥር ከነገ አንስቶ እስከፊታችን ዓርብ፤ በ 126ኛው ዓለም አቀፍ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ስብሰባ ፣ በክብር እንግድነት በመገኘት እንደሚሳተፉ ተነገረ። ስብሰባው የሚካሄድባት ከተማ ፣ የክረምት ኦሊምፒክ እስፖርት ውድድር የምታዘገጀው የሩሲያ ከተማ ሶቺ ናት።
የአፍሪቃ ኅብረት አባል ሃገራት የመሪዎች ጉባኤን ተከትሎ ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፑብሊክ ዉስጥ ያለዉን ችግር ለማስቆም የድጋፍ ማሰባሰቢያ ጉባኤ አዲስ አበባ ላይ ተካሂዷል።
ምንም እንኩዋን የገዢው ፓርቲ ወከባ ቢፈታተነንም ትላንት እሁድ በጎንደር ከተማ የጠራነው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ስኬታማ ነበር ሲል ስማያዊ ፓርቲ ኣስታወቀ።
የፓርቲው ም/ሊቀመንበር ዛሬ ለዶቸቬሌ እንደነገሩት መንግስት ከህዝብ እውቅና ውጪ የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን ኣሳልፎ ለመስጠት የያዘውን ስውር ደባ በመቃወም ነበር ስማያዊ ፓርቲ
ብዙዎች በተለያዩ ምክንያቶች ከሀገር ይወጣሉ፤ ይሰደዳሉ። እንዳወጣጣቸዉ ሰንቀዉ የሚነሱት ዓላማና ህልም እንደመለያየቱ፤ ያለሙትን የጨበጡ፤ የተመኙትን ያገኙም ብዙ አይሆኑም።