ለዘመናት ቀጣይነት ያለው የተሟላ ሰላምና መረጋጋትን ኣጣጥማ የማታውቀው ኣፍሪካ፤ ኣንዳንድ የኣህጉሪቱ ፖለቲከኞች እንደሚሉት አመጹም ሆነ ጦርነቱ በቅኝ ኣገዛዝ ዘመን ለነጻነት ነው የነበረው። ከዚያ ወዲህም ቢሆን ቅኝ ገዢዎችን ከተኩት አምባገነኖች ጋር እስከሆነ ድረስ ለዲሞክራሲ እና ለፍትህ በመሆኑ የሚጠበቅ እንጂ ኣስገራሚ ሊሆን ኣይገባም።

ለሁለት ቀናት የዘለቀዉና አርብ ምሽት የተጠቃለለዉ የአፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ፤ በአህጉሪቱ ዉስጥ በሚታዩት አንዳንድ የፀጥታ ችግሮች ላይ የበለጠ ትኩረት ይዞ ታይተዋል። 54 አባል መንግስታትን ያቀፈዉ የአፍሪቃ ህብረት አርብ የተጠናቀቀዉ 22ኛዉ የመሬዎች ጉባኤ፤ ከከዚህ ቀደሙ በምን ይለያል?

ትውልደ ኤርትራዊው የስዊድን ዜጋ፣ ጋዜጠኛ ዳዊት ኢስኃቅ ድንገት ተይዞ ወዳልታወቀ ስፍራ የተወረወረው የዛሬ 13 ዓመት ገደማ ነበር እጎኣ መስከረም 23 ቀን 2001 ዓ ም። ከሚኖርበት ስዊድን ወደ እናት ኣገሩ ኤርትራ ተመልሶ ኣሁንም እጎኣ በ 1997 ዓም መሆኑ ነው፣ ሰቲት የተባለ ነጻ የግል ጋዜጣ ማዘጋጀት የጀመረው ዳዊት ኢስኃቅ የተወነጀለው

ኢትዮጵያ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች ተግባብተዉና ተዋህደዉ በስርዓት የሚኖሩባት ሀገር ስትሆን በዓለማችን እየታየ ያለዉ ለዉጥ፤ ማህበረሰባችን ይዞት የቆየዉን እምነቱን እና ባህሉን እየተፈታተኑት ነዉ ተብሎአል።

የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል፤ ጀርመን በአዉሮጳ ብሎም በዓለም ሃላፊነቷን እንደምትወጣ ተናገሩ። ሜርክል ስለመንግስታቸዉ ዛሪ በሰጡት መግለጫ፤ ጀርመን ይህንንድርሻዋን ካልተወጣች ፤

ህፃናት በጉዲፈቻ ከሀገር ሲወጡ ቤተሰቦቻቸው በማያውቁበት ሁናቴ በሕገወጥ መልኩ የ20 ሺህ ዶላር ክፍያ ይፈፀምባቸዋል ሲል «ሠንደቅ » ጋዜጣ ባወጣው ዘገባ መከሰሱን ዋና አዘጋጁ ገለፀ።

ዓለም አቀፉ የስደተኞች መርጃ ድርጅት በምህፃሩ IOM ባወጣው ዘገባ ባሳለፍነው የጎርጎሪዮሳዊው 2013 ዓመት በርካታ የሶሪያ፣ የኤርትራና የሶማሊያ ስደተኞች በአደገኛ የባሕር ላይ ጉዞ አውሮጳ መድረሳቸውን አትቷል።

22 ተኛው የአፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ተጀመረ ። ዛሬ ጠዋት የተከፈተው የዚህ ጉባኤ ይፋ አጀንዳ ግብርናና የምግብ ዋስትና የነበረ ቢሆንም በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክና በደቡብ ሱዳን የተባባሰው ግጭት ያስከተለው ሰብዓዊ ቀውስ የጉባኤው ትኩረት በሁለቱ ሃገራት ላይ እንዲሆን አድርጓል።

የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት በምህፃሩ ዩኔስኮ የትምህርት ጥራት እየዘቀጠ መሄድ በዓለም ዙሪያ ከተጠበቀው በላይ መሃይምነት ይበልጥ እየተስፋፋ እንዲሄድ ማድረጉን አስታወቀ ።

የዓለም የዜና እና ጋዜጣ አሳታሚዎች ማኅበር የ2014 የነጻነት ወርቅ ብዕር ሽልማቱን ለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ መስጠቱን ስታወቀ። የማህበሩ የፕረስ ነፃነት ዳሬክተር እንደሚሉት፤ ማህበሩ ይህን ሽልማት ለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ለመስጠት በመወሰኑ፤ ለኢትዮጵያ መንግሥት ግልፅ የሆነ መልዕክት ያስተላልፋል፣ እውነታውንም አጉልቶ ያሳያል።

ኣገራዊም ሆነ ኣህጉራዊ ልማት ሲታለም ኣስቀድሞ መታሰብ ያለበት ነገር ቢኖር የመሰረተ ልማት ኣውታሮች ዝርጋታ መሆኑ ኣያጠያይቅም። ኣንዱና ዋናው ደግሞ መንገድ ነው ቢባል ማጋነን ኣይሆንም። በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሰፋፊ እና ከባህር በር ፈንጠር ብለው ለሚገኙ ኣገሮች የባቡር ሀዲድ ኣስፈላጊ ብቻም ሳይሆን ወሳኝነትም ኣለው ተብሎ ይታመናል።

የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት የአውሮፓ ህብረት ወታደሮች ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ እንዲዘምቱ የሚፈቅደውንና ደም አፋሳሽ ብጥብጥ እንዲካሄድ ያደረጉ የቡድን መሪዎች ላይ ማዕቀቦች እንደሚጣል የሚያስጠነቅቀውን ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ትናንት ማፅደቁን አሳውቋል ።

ሁለቱ የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ወገኖች፤ የገቡት የተኩስ አቁም ስምምነት ገቢራዊ መሆኑ አጠያያቂ እየሆነ ነዉ። የደቡብ ሱዳን መንግሥትና አማፅያን የተኩስ አቁም ስምምነቱን በመጣስ ርስ በርስ እየተወነጃጀሉ ሲሆን ፤ ጦርነቱን ፈርተዉ ወደ ጎረቤት ሃገራት የተሰደዱት የደቡብ ሱዳን ነዋሪዎች፤ በሃገራቸዉ ሰላም ይመጣል የሚል ተስፋ የላቸዉም።

የኬሚካል ባለሙያ የሆነው እና የኣጥፍቶ ማጥፋት ጥቃቶችን በባቀድ እና በማቀነባበር የሚታወቀው ኣህመድ መሓመድ ኣሜ እስኩ ዱቅ በሚል መጠሪያው ይበልጥ ይታወቃል። ካለፈው ኣንድ ዓመት ወዲህ በተለይ በሞቃዲሾ እና በተለያዩ አካባቢዎች ከተሰነዘሩ የኣጥፍቶ መጥፋት ጥቃቶች በስተጀርባ መኖሩ የሚነገርለት ኣሜ

የሩስያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ዛሬ ብራስልስ ላይ ከአውሮፓ ህብረት ኮምሽን ፕሬዝደንት ጆሴ ማኑኤል ባሮሶ እና ከአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ኸርማን ቫን ሮምፖይ ጋ ተገናኝተው ተወያይተዋል።

አጥንት ከሰዉነት ክፍል ጠንካራዉ አካል ነዉ። እንደ ጥንካሬዉ ግን በተለያዩ ምክንያቶች ለጉዳት በሚዳረግበት አጋጣሚ ወደቀድሞ ይዞታዉ ለመመለስ ቀላል አይሆንም። አጥንት ከአካል እድገትና ከእድሜ መጨመር ጋ እያደር እያደገና እየጠነረ ሄዶ በጉርምስና እድሜ ማብቂያ ላይ እድገቱን ያቆማል።

አዲሱ የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዛሬ አዲስ መንግሥት መሰረቱ ። በሳምንቱ መጨረሻ ላይ የተሰየሙት ጠቅላይ ሚኒስትር አንድሬ ዛባያኬ ባቋቋሙት በአዲሱ ካቢኔ ሰባት ሴቶች ይገኙበታል ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከ2 ቀናት በፊት ሲሾሙ ፕሬዝዳንት ካትሪን ሳምባ ፓንዛ ደግሞ ባለፈው ሀሙስ ነው ቃለ መሃላ የፈፀሙት ። ፕሬዝዳንት ሳምባ ፓንዛ

ቀድሞ የግብጹ መሓመድ ዓሊ ንጉሳዊ ግዛት አካል የነበረው የሱዳን ምድር እጎኣ በ1956 ዓም ነጻ መንግስት መሆኑን ተከትሎ በኣገሪቱ በተቀሰቀሰው የመጀመሪያው የሱዳኖች የእርስ በርስ ጦርነት ምክኒያት ደቡብ ሱዳን ያኔ የራስገዝ ኣስተዳደር ለመሆን በቅታ ነበር። በ 1972 ዓም።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት በመባል የሚጠራው ቡድን ፤ ስለ ኢትዮጵያ የሽግግር ወቅት የቀረበዉን ረቂቅ ህገ-መንግስትን በተመለከተ ዋሽንግተን ዲሲ ይዩናትድ ስቴትስ ውስጥ ህዝባዊ ዉይይት አደረገ።

ሜንሽን ፎር ሜንሽን፤ ሰዎች ለሰዎች የተሰኘዉ ምግባረ ሰናይ ድርጅት፤ በ13 ዓመታት ዉስጥ በሰሜን ሸዋ በተለይ በመረሃቤቴ አና በሚዳ ወሪሞ አካባቢዎች ያከናወናቸዉን በርካታ የገጠር ልማት ሥራዎች ለተጠቃሚዉ ህብረተሰብ አስረከበ ።

የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ወገኖች፤ በፕሬዚደንት ሳልቫኪር የሚመራው የጁባው መንግስት እና የቀድሞው የኣገሪቱ ምክትል ፕሬዚደንት ሪክ ማቻር የሚመሩት ኣማጺ ቡድን ተወካዮች ትናንት ማታ የተኩስ ኣቁም ስምምነት ተፈራርመዋል። አዲስ አበባ ዉስጥ የተፈረመዉ ሥምምነት ገቢራዊ የሚሆንበት መንገድ ግን እንዳጠያየቀ ነዉ።

በኮምፒውተር ቴክኖሎጂ ላይ የሚዘግበው «ሴቴ» የተሰኘው ታዋቂ የጀርመን መፅሄት ሰሞኑን አንድ ፁሁፍ ለአንባቢዎቹ አቅርቧል። ይህም ጥናታዊ ፁሁፎች በቀላሉ ለኢትዮጵያ የትምህርት ተቋማት እንደማይደርሱ ያመላክታል። ለዚህ ምክንያቱ ምንድን ነው? ምንስ መፍትሄ ሊሆን ይችላል?

የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ወገኖች፤ በፕሬዚደንት ሳልቫኪር የሚመራው የጁባው መንግስት እና የቀድሞው የኣገሪቱ ምክትል ፕሬዚደንት ሪክ ማቻር የሚመሩት ኣማጺ ቡድን ተወካዮች ትናንት ማታ የተኩስ ኣቁም ስምምነት ተፈራርመዋል። አዲስ አበባ ዉስጥ የተፈረመዉ ሥምምነት ገቢራዊ የሚሆንበት መንገድ ግን እንዳጠያየቀ ነዉ።

ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት ICC በሰብዓዊነት ላይ በተፈፀመ ወንጀል የተከሰሱት የኬንያዉ ፕሬዝዳት ኡሁሩ ኬንያታን ለመመልከት የያዘዉን ቀጠሮ አራዘመ። ፍርድ ቤቱ ቀጠሮዉን ያዘወረዉ፤ አቃቤ ሕግ የፍርድ ሂደቱ በሌላ ቀን እንዲጀመር በመጠየቁ ነበር።

ሁለቱ የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ወገኖች፤ በፕሬዚደንት ሳልቫኪር የሚመራው የጁባው መንግስት እና የቀድሞው የኣገሪቱ ምክትል ፕሬዚደንት ሪክ ማቻር የሚመሩት ኣማጺ ቡድን አዲስ ኣበባ ላይ ማምሻውን የተኩስ ኣቁም ስምምነት ተፈራርመዋል።

በኢትዮጵያ ጅብ ተከብሮ ስጋ ጎርሶ፤ ገንፎ ተገንፍቶ ቀርቦለት የሚኖረዉ ሐረር ከተማ ላይ ነዉ። ከጥር ስምንት እስከ 10 የሐረሬ ጅቦችና የከተማዋ ነዋሪዎች አንድ ላይ የሚያከብሩት የአሹራ በዓል ይሰኛል። ሐረሪዎች የሚያከብሩት ሶስት በዓላቶች መካከል ለጅብ ገንፎ የማብላት ስነ-ስርዐት አንዱ ነዉ።

በዓለማችን ላይ በተለያዩ አካባቢዎች የሚካሄድ በርካታ ህዝባዊ አመፅች መታየቱ እየተበራከተ መትዋል። በሰሜናዊ አፍሪቃ፤ በዩክሪይን፤ በታይላንድ በየቀኑ አመፅ የቀላቀለ ህዝባዊ ተቃዉሞ የእዕለት ዕለት ክስተት ሆንዋል።

22ኛዉ የአፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ መርህ የአህጉሪቱ የእርሻና የምግብ ዋስትና ነዉ። ፕሪቶርያ ደቡብ አፍሪቃ የሚገኘዉ ዓለማቀፍ የፀጥታ ጉዳዮች ጥናት ተቋም ዋና ኃላፊ ያኪ ሲሊዪ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ጉባኤዉ የአህጉሪቱን ድህነትና እና ረሃብ መቅረፍ በሚቻልበት መንገድ ላይ ለመነጋመገር አጀንዳ ይዞአል።

የእስራኤል ባለሥልጣናት አፍሪቃውያን ስደተኞች በሃገሪቱ በረሃማ ደቡባዊ ክፍል ወደ ሚገኘው የሆሎት የስደተኞች ማቆያ እንዲገቡ አዟል ። ባለሥልጣናት እንደሚሉት ወደ ዚህ መጠለያ ለገቡት ስደተኞቹ በቋሚነት የሚኖሩበት ቦታ እየተፈለገላቸው ነው ።

ከኣንድ ወር በላይ ለዘለቀውና ከ 10 ሺህ በላይ ሰዎች ለሞቱበት የደቡብ ሱዳን የእርስ በርስ ውጊያ መፍትሄ ለመሻት ነገ ሐሙስ እዚያው ደቡብ ሱዳን ር/ከተማ ጁባ ውስጥ ሊካሄድ ታስቦ የነበረው የምስራቅ ኣፍሪካ የልማት ቤይነ መንግስታት ባለስልጣን ኢጋድ አባል ሓገራት መሪዎች ጉባዔ ቢሰረዝም የሰላም ጥረቱ ግን ተጠናክሮ መቀጠሉ ተሰማ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት አሁን ጦሩ በአሚሶም ዕዝ ሥር የተጠቃለለዉ በጋራ መንቀሳቀሱ የጦሩን ተዕልኮ ከግብ ለማድረስ ጠቃሚ በመሆኑ ነዉ።የወጪ ጉዳይም ከግምት የሚገባ ነዉ።አሚሶምን የተቀየጠዉ የኢትዮጵያ ጦር አራት ሺሕ ወታደሮች አሉት።

የሱዳኑ ፕሬዚደንት ኦማር ሀሰን ኣልበሺር በኤርትራ ያደረጉት ጉብኝት የሁለቱን ኣጎራባች ኣገሮች ግንኙነት ከማጎልበት ጎንለጎን በአካባቢያዊ እና ዓለም ዓቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገለጸ።

ኣልበሺር ከኤርትራው አቻቸው ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ባደረጉት የሶስት ቀናት ቆይታ የደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታን ጨምሮ